የቧልት ብልት!

የቧልት ብልት!
„እውቀትን ለማን ያስተምረዋል? ወይስ ወሬ ማስተዋልን ለማን ይሰጣል?
              ወተትን ለተው ወይስ ጡት ለጣሉ ነውን?“
ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፰ ቁጥር ፱
ከሥርጉተ©ሥላሴ 17.08.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።




መፈራረጃ እንደ በር፤


ይግርሙኛል የሰሞኗቱ ጉዳዮቹ ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ለውጡ እንዳይቅለበስ ምንትሶ ቅብጥርሶ ይሉናል … የተፎካካሪ ፓርቲዎች ደግሞ ለውጡን ስለማስቀጠል ይነግሩናል፤ የለውጡ መሪ መንፈሱ የት አለና ለውጡ የሚቀጥለውስ የሚቀድመውስ? 

ቁልጭ ያለው ዕውነት እኮ አንጃው እና ወያኔ ሃርነት ትግራይ ቀልብሶ በምስል እየተፍነሸነሸ ነው። ለወያኔ ቧልት ደግሞ እጅ ነሺዎች ሆናናል። ደጅ ጠኚዎችም።

አሁን እውነት ጠፍቷቸው ነው ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ለውጡ እንዳይቀለበስ ምንትሱ ቅብጥሮሶ የሚለኑ? እንዴት ነው ማተብ የሚባል፤ ኪዳን የሚባል የለምን?

ቅደስት ተዋህዶም ቤተክርስትያኔ ስቃይ ውስጥ ናት እና የህግ ጥበቃ አልተደረገለኝም እያለች ነው። ያው ያተራመሰው ወያኔው ስለሆነ ለወያኔ ሃርነት ትግራይ አቤቱታው ወደ መቀሌ ቢላክ መልካም ነው። ወይ ደግሞ ለእነ ሳጅን በርከት ስምዖን ጁንታዎች፤ እዛው ቤተ መንግሥት አዲስ ሴራ ላይ ለተጠመዱት ለእነሱ ቢሆን ይሻላል። አባ ቅንዬማ ካቴና ውስጥ ናቸው፤ 

ወዱቼ አዱኛዎቼ ጥቂት በምልስት እና በቅኝት አብረን እንሁን እላለሁኝ ... 

ቧልቱን በብልት በብልቱ ለማየት እነዚህ ሊንኮች በሚመለከት የቤት ሥራ ልስጣችሁ እና እዩዋቸው - ጥያቄ ግን በትሁት መንፈስ ነው። ነፃነት የተቀማው አንበሳ በሁለት ሳምንት ውስጥ ስንት ተግባራትን መከውን ሲችል አስረው ይዘው ፍዳውን ያስከፍሉታል። 

እሱን ለምስል ልክ እንደ ሮቦት ወዲህ እና ወዲያ እያወዛወዙ ይቀልዳደሉ እና አቤቶ በረከት ስምዖን። ግን ግን ንጉሥ ጃዋር እና አጃቢዎቹ የት ገቡ? ዙፋኑ ተደፋ ወይስን ተከነበረለ? እንዴት ነው ቅብ ተደረገለት ወይስ እንዳልኩት የሳሙና አረፋት ሆኖ በቅጽበት ለቅጽበት ሰገደን? ቄሱም ዝም መጸሐፉም ዝም ሆነ እኮ።

የኔዎቹ ቅኖቹ፤ --- ብልት በዬፈርጁ። ካሳኛችሁ ፈረሰኛም፤ አጭር ረጅም እግርም መላላጫም እያደረጋችሁ ከቪዲዮው ጋር በሥነ ልቦና ሃዲድ የእኔ ብላችሁ አነጣጥሩት። ትናንት እና ዛሬ እኛና ተስፋችን ምን እና ምን ስለምን ....  

  v     ቁጥር አንድ ገለፃን በሚመለከት ….
  
ይሄ የመጀመሪያ ስብሰባቸው ነው። ከባለሃብቶች ጋር ያደረጉት፤ ካለ አጋች በሙሉ ነፃነት እና ልበ ሙሉነት የተካሄደ ጉባኤ ነበር የመጀመሪያውም ነበር። ያው ከቸገረኝ ብቻ ነው ወደ ኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እምወስዳችሁ እንጂ ፋና ቴሌቪዥን ከሰራ ጥራቱ ዘመናይነቱ እና ለተመልካች ያለው ሳቢነቱ ሙሉ ስለሆነ ከፋና የወሰድኩት ነው።
  •        በነፃነት።

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከባለሃብቶች ጋር ባደረጉት ውይይት ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች የሰጡት ምላሽ ክፍል 2፤ ንግግሩን ማድመጥ ግድ አይላችሁም። ሰብዕናውን ወደ ውስጥ ዘልቃችሁ በማዬት የተቀማውን ነፃነት ምን ያህል ስለመሆኑ ትመዘኑት ዘንድ ነው። 


·      በእገታ።
ሁለተኛው ደግሞ በእገታ ወህኒ ቤት ሆነው፤ ከሞት ተርፈው ገመምተኛ ሆነው ያካሄዱት ጉባኤ ነው።

Ethiopia: / አብይ ጠፉብን ላላችሁ የበጎ ፈቃድ አገልግሎት ለሚሰሩ 1ሺህ ወጣቶች ገለፃ ሲያደርጉ እነሆ ይመልከቱ


ህሊና ያለው ሰው ከልቡ የበሰለ ኢትዮጵያዊነት፤ የበሰለ ተስፋን የሚሻ ወገን ሁለቱንም ቪደዮዎች በንጽጽር ይምልከታቸው።

  v     ቁጥር ሁለት የውጪ ግንኙነትን ያሰተናገዱበት   ደግሞ እንመልከት።
በሙሉ ነጻነት ያስተናገዱበት ይሄ ቪደዮ በጥሞና ቅኖች መርምሩት …
  •      በሙሉ ነፃነት የተወነው።

https://www.youtube.com/watch?v=bpQ4n3Y07s4

Ethiopia: / አብይ ለኤርትራዉ ፕሬዘዳንት ኢሳያስ በልዑካኑ በኩል ስጦታ ላኩ- አብይ በቅርቡ ከኢሳያስ ጋር እንደሚገናኙም ተገልፅዋል

 

Ethiopia: የኤርትራው ልዑክ በቤተ-መንግስት በአማርኛ ያደረጉት ንግግር፤

 

·      በአገታ የተከናወነው።

 

ውጩ ሁሉ እስር ቤት ነው የሚመሰለው። ኮሪደሩን በርቀት ጮለቅ እያደረጋችሁ እዩት … ወህኒ ቤት ምስጋን ይነሳው።

 

https://www.youtube.com/watch?v=RAGGEdzr21A&t=46s

/ አብይ አህመድ ለሳዑዲ አረቢያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጋር ያደረጉት አቀባበል

ኮሪደሩን እዩት እስር ቤት ነው

 

ሌላም ይታከል … እንደ ክለቱ …

·      በነፃነት የተደረገ የተከወነው እንዲህ ያምርበታል።

 

EBC ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኢምሬት የሁለትዮሽ ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

ጉዳዩ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ አሉበት።


…. ሳልስት እንበል ….
·      በአገታ የተከናወነው

https://www.youtube.com/watch?v=nYhUftsxVdI

Ethiopia - Dr Abiy Ahmed ከተባበሩት አረብ ኢምሬት የአለም አቀፍ ትብብር ሚኒስትር ጋር


  • ·      በሙሉ ነፃነት የተከናወኑትን ደግሞ ይመልኩቱ

በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ ያሉት የሩዋንዳው ፕሬዝዳንት ፖል ካጋሜ ከጠቅላይ ሚኒስትር / አብይ አህመድ ጋር በጋራ may25/2018

   v     ቁጥር ሦስት
·      በእገታ

Ethiopia: / አብይ ስለ ኢትዮጵያ ቡና ምርት ማነቆዎች መግለጫ ሰጡ፤

·      በነፃነት

https://www.youtube.com/watch?v=umT_jCcBDKY

Ethiopia -ከአርቲስቶች ጋር ከነበራቸዉ ቆይታ የተቀነጨበ


  v     አንደ ማጠቃለያ።
አነበሳው ከዚህ ሁሉ ጣጣ በፊት የሳይንስ እና ቴክኖሎጆ ሚኒስቴር በነበሩበት ወቅት፤ አጭር ስለሆነች ብታዳምጧት ደስ ይለኛል።

Ethiopia - Dr Abiy ፈረንጆቹን አሸማቆ መለሳቸዉ!!

 

ወዶቼ እንዳይበዙባችሁ በማሰብ በጥቂቱ ነው ያቀረብኩት፤ ሁለመናውን አንጀት ጉበቱን አውጥታችሁ፤ ብልቱን በዬፈርጁ አደራጅታችሁ እያገላበጣችሁ መርምሩት። ያን ስታደርጉ ሚሰጢሩ ዘንድ ኮለል አደርጎ ያደርሳችኋዋል።

 

ነገር አለማቱ ሁሉ ውሃ የበላው ቅል ሆኗል … አንጸልይ እንዳሉት አበው ጸሎት የሚያደርገው ነገር ካለ ይታያል … መቼስ ተስፋ አይጠላም አያልቅምም …   

 

እንግዲህ የእነ ሳጅን በረከት ስምዖን ተለዋጭ ጠ/ ሚር አመራር እና ካቴና ያማረው ነፍስ ትኬቱን ቆራርጦ ይሂድ። ውጪ አገርም ያው የተጀመረው ተረብ እና "እንቆቅልሽ ምን አውቅልሽ/ህ" ይቀጥል… እገታውን ማስለቀቅ ሲገባ እጅ እና እግር አጣምሮ መቀመጥ ሆኗል።

 

·      አንድ ለመንገድ …


ወያኔ ሃርነት ትግራይ እነ ዶር ገዱ አንዳርጋቸውን ለቀቅ አድርጓል። ለጊዜው ጠላት ላለማብዛት ይመስላል። ኦህዴድን ግን ጫን ያለ መከራ ያለበት ይመስላል። ያው ነው ወያኔ ኤን ለማጥቀት ቢን ይንከባከባል፤ ኤን ሙሉ ለሙሉ መደምሰሱን ሲያብሰር ቢን ደግሞ ይደስቃል፤ ቢን አፈር ድሜ ማስጋጡን ሲያረጋግጥ ሲን ይቀጥላል እንዲህ ነው … የጨለማው የጉጉት ጎትትትትትትትት ፍልስፍና እና የሞት ነጋሪትም።

 

ለዚህ ነው አሁን እነ ዶር ገዱ አንዳርጋቸው፤ አቶ ንጉሡ ጥላሁን አልፈው ተርፈው ቄሮንም እዬተማጸኑ ያሉት … በሉ የተባሉትን ማለት ነው …

 

„የቂጣም እንደሆን ይጠፋል የልጅም እንደሆን ይጋፍል።“


ለነገሩ በወያኔ ፖለቲካ ታማኝነታችን አረጋግጠን እንዴት ተብሎ ተስፋ ይደረጋል። የሆነ ነገር አለ ለማለት እንኳን አልደፈርንም፤ በዜሮ ወሬው ሁሉ ተባዛ እያልን እኮ ነው … 


ለመሆኑ ግን ጅልንታችን ሚዛኑ ስንት ኪሎ ይሆን?መጥኔ ለእኛ ራዕያችን ወጀብ እና ቅጽበት በጥምረት ስለሚያወናጅቡት …  

 

ነፃነት ለአብይ እና ለቤተሰቡ!

የኔዎቹ ኑሩልኝ።


ቸር ወሬ ያሰማን።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።