የጸጋ ስግደት ለሳጅን በረከት ስምዖን የሴራ መረብ¡
እንቀኛኝ።
„በዚያ ቀን ይህ ቅኔ በይሁዳ ምድር ይዘመራል፣--- የጸናች ከተማ አለችን፤ ለቅጥር እና ለምሽግ መዳህኒት ይኖርበታል“
ከሥርጉተ©ሥላሴ
17.08.2018
ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።
የነፃነት ፍላጎታችን ሆነ መሰናዷችን በዚህ
የቢሮ አያያዝ ይታያል።
¡እናምራለን አይደል?¡
ጤና ይስጥልኝ የኔዎቹ እንድምን አላችሁልኝ። መቼም የእኔን ጹሁፍ የምትከታተሉ ቢያንስ ሊሆን ይችላል ብላችሁ ይሆናል ብዬ አስባለሁኝ
ስለ አብይ ሌጋሲ የሞት ፍርድ ሆነ እገታ። እና አሁን ባልታወቅ መንገድ ላይ ስለመሆናችን። ለነገሩ የሳጅን በረከት መንፈስ ድል ላይ ነው ያለው … ትንሽ ገጭ ገው የነበረው ከጃውርውያን ነበር እሱም
በክስምት እንደ ክስምት …
- · ወያኔ ይውደቅ እንጂ …
ይህ በነፃነት ፈላጊው „ወያኔ ይውደቅ“ እንጂ ሌላው ችግር የለውም እራስን ሳይደራጁ፤ ሳይሰናዱ
መንበር ላይ የማስቀመጥ እንደ አንድ አይዲኦሎጂ የተወሰደ ጉዳይ ነበር።
አንድ የበሰለ ንድፈ ሃሳብ ወይንም አንድ የጠነከረ የመንፈስ
አቅም፤ ወይንም አንድ ሶሊድ የሆነ አካል ሳይኖር ነው ወያኔ ስለመወድቁ ብቻ እንሰበው ሌላው ገብስ ነው የጅሎችን ሞቶ ተሸከም የኖርነው።
ሊቃናቱ የፖለቲካዎቹ ማለቴ ነው
ላም እረኛ ምን አለ ብለው ጆዋራቸውን ነካክቷቸውም አያውቅም። ሊቆቹ እነሱው ብቻ ናቸው። ሌላው ደግሞ ዱዱማ … ዱዳም፤
ስለሆነም ነው „ወያኔ ይውደቅ እንጂ“ ሌላው ምንም አይደለም ሳይሆን ምንም እንዳይሆን ምን መሰናዶ
አለ ቢባል አንዲት ቀን ሰብሰብ ይሉና የሽግግር ሰነዱ ይሄውና ነው። ወይንም ደግሞ ከ እከሌ ድርጅት ጋር እንዲህ የሚል አዲስ የሥም
መጠሪያ ፈጥረናል ነው … አገጣሚ ሲመጣ ደግሞ ንደት በንደት … በቁማቸው ፈርሰው አሁንም አለን ሲሉ እንኳን ብጣቂ ሃፍረት አልሰራላቸውም
…
የሆነ ሆኖ ሲደራጁ ሲፈርሱ ሱፈርሱ ሲሰሩ በቃ ከዚያ ያለፈ ያዬነውም የሰማነውም የለም። በፈለገ
ጃኬት ቢመጡ ቢለበጡ የኖርነው ለምናውቅ ሰዎች ለመረመርን ሰዎች አንጥሮ እንዲመለስው እንኳን አይፈቀደልትም፤ አንጥሮ እንዲመልሰው
የሚፈቀደው ሲደመጥ ነው። ማድመጥ ጊዜ ይሻል አሁን ይህን መዝሙር አምናዳምጥብት ጊዜው አልፏል።
ኢትዮጵያ የነጠረ መንፈስ ሰጥቷት ነበር። „ሊታምን አይገባም፤ አስመሳይ ነው“ የተባለው መንፈስ
ምን ያህል ገናና እና ችግርን የመሸከም ብቻ ሳይሆን መፍትሄ አምንጭቶ በመፍትሄው ሁሉንም ተጠቃሚ የማድረግ አቅሙን አሳይቷል። ለዚህም
ነው የሁሉም መንፈስ ቤተኛ ቤተሰብ ለመሆን የበቃው። አቅም ማለት ዕድሜን ሙሉ መሳናዳት እንጂ በሞቀ ውሃ የሚበጠበጥ ያለቀ የሾርባ
ምጥን ማለት አይደለም።
በብዛት በማህበር ድርጅት አለ ግን ግቡ እና አላማው ወንበር ሥም እና ዝና ብቻ ነው። ይህን
ላቀዱ ሰዎች ደግሞ ቅኖቹ ነፃነት ጠማኝ የሚለው ሁሉ ሁለመናውን ገብሮ ራሱን ሲያባክን ኖረ። አሁንም አያለሁኝ ለባከነ መንፈስ አብሬ
ልባክን ብሎ የሚሰለፍ … ሰብዕናውን መውደድ እና ያን ሁለገብ ችግር ያሻጋራል ማለት ልዩነታቸው ሰማይ እና ምድር ማለት ነው …
- · የብክነት ቅጥያ።
የብክነት ቅጥያው የሁለቱ የኦሮሞ እና የአማራ ንቅናቄው ወይንም ተጋድሎችን እንመልከት። በመጀመሪያ
ነገር የኦሮሞ የግንጫ አብዮት ማስተር ፕላን ተኮር ነበር። ይህን ተከትሎ የመጣው የጎንደሩ አብዮት ደግሞ የሥርዓት ለውጥን የጠዬቀ
ነበር። ከግንጫው በፊት አንድ አመት ቀድሞም ጎንደር ላይ „የፈራ ይመለስ“ የጀግንነት ጥሪ ነበር።
የግንጫው እንደ ሳቢያ ቢታይ የጎንደሩ ደግሞ እንደ ምክንያት ማዬት ይገባ ነበር። ከዚህ ቀጥሎ
ለውጡ እድገቱን ቀጥሎ በሚጓዝበት ወቅት ሌላ የጉሮሮ አጥን ተፈጠረ። የምክንያታዊ አብዮትን ነጥሎ የማስመታት እና የኮፒ ራይት የይገባኛል
ግብግብ። እሰቡት ትግሉ ለነፃነት አለመሆኑን በብክነት ቅጥልጥል መቀመጣል ….
- · ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ
በዚኸው ሞገድ ማግስት በራሱ በግንባሩ ውስጥ ሞገዱን የራስ የማድረግ እና ጥያቄዎችን እንፈታለን
የሚል ከግንባሩ ያፈነገጡ ቅን ሃይሎች ተነሱ። ከብአዴንም ከኦህዴድም። ይህን ተጋድሎ አስቀድሞ ቅስሙን እንዲመታ ያደረገው ራሱ የነፃነት
ፈላጊው ነበር። ወያኔ ሃርነት ትግራይ ያደራጀው ሃይል ለውጡን ለመቀልበስ የተደራጀ በሚል ወከባው ቀጠል። ያባከነው ጊዜ ገና እዳውን እናወራርዳትአለን፤ እኛስ እዚህ ነን ያቺ መከረኛ የኢትዮጵያ እናት ...
ከዚህ ጋር ተያይዞ የሚታዬው የኦሮሞን ንቅናቄ አጉልቶ፤ አደጉሶ የመቀበል እና ምክንያተዊ የነበረውን
የአማራ ታገድሎን አብዮት አቃሎና ነጥሎ የመግለል ዕውቅናም የመንፈሰግ። የዛ ውጤት ነበር የሰሞናቱ የጃውርውያን የሠረገላ አታሞ
… ምንም ይሁን ምንም ሚዛን የሚስጠብቅ ሃይልን መንከባከብ ለሁሉም ጠቃሚነው፤ ለምሳሌ የራሺያ መኖር የ ዓለምን ሚዛን ያስጠብቃል፤
የሃያላኑን የመደፍጠጥ አቅም ይፈታተናል ወይንም እንዲመጣጠን ያስገድዳል።
በዚህ ማህል „ጣና ኬኛ፤ አባይ ኬኛ“ የደብርብርሃኑ የ የአማራ እና የኦሮሞ ግንኙነት ግንኙት
ኮንፈረንስ፤ የሚዲያ የአማራ እና የ ኦሮሞ በተወሰነ ደረጃ መነቃቃት
እና መደጋገፍ፤ አንድ መንፈስ ፈጠሩ ‚ኢትዮጵያዊነት ሱስ ነው።‘
ይህም ብቅ ከማለቱ በግራ ቀኝ ተዋከበ።
ዋናው አውራ ፓርቲ ወያኔ ሃርነት ትግራይ እና የትግራይ ሥርዕዎ ምንግስት ሊነቃነቅ ነው ብለው
የፈሩ ተጋሩ ሽንጣቸውን ገትረው ሲታገሉት የነፃነት ሃይሉም ከእነሱ ጎን ሆኖ የማጠናከሪያ የቡላ እና የጎን አጥንት አጥሚት አዘጋጀ።
በሙሉ ሚዲያው፤ በሙሉ ሊቃነቱ፤ በሙሉ ድርጅቶች በወካባው ውስጥ ባለዬለት አቋም እሰጣ ገባው ቀጠለ ግንባሩም በተናጠልም በወልም
ዘመኑ ስብሰባ ላይ ባጀ …
- · ትንፋሽ።
ስብሰባ የባጀው አካል የህዝቡን ጥያቄ የማይመልስ መንግሥት በአፍንጫችን ይውጣ ሲሉ ኦቦ ለማ
መገርሳ ተደመጡ። ነገር ግን ይህንም አቅም ያላቸው ሚዲያዎች እና ተጽዕኖ ፈጣሪዎች ባለ በሌለ ሃይላቸው ሞገተቱ።
ይህም ሆኖ እስረኞችን ለማስፈታት በተደረገው ተጋድሎ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ወሳኝ ውክል አካል የሚባሉት ከእስር ተለቀቁ። አቀባብል
ተደረገላቸው። የነፃነት አካሉ እንደ መደገፍ አኮረፈ። መያዦ ነበሩ።
ከእስር የተፈቱትም በትግላችን ተፈታን በማለት ያን ግቢ ነፍስ ውጪ ነፍስ ለነበረው የለማ የገዱ
መንፈስ ብጣቂ ዕውቅና ሳይሰጥ ገሰገሱ …
ይህም ብቻ ሳይሆን ለውጡ እኛ አምጥተነዋል በማለት ልክ ኢትዮጵያ ሙሉ ለሙሉ ነፃ የወጣች ይምሰል
በጥንቃቄ ሊያዙ የሚገባቸው ጉዳዮች ላይ አትኩሮት አነሳቸው እንዲያውም ለዳግም እስር ተጋለጡ።
ለውጡ እና መንፈሱ እነሱ ሊያያዙ
አልቻሉም። ሳያጠኑት ሳይመረምሩት የሚወስዷቸው እርምጃወች ለድጋሚ መከራ እና ጭንቀት ዳረጎን ነበር። እነዛ መንፈሶች ግን ቀሪውን
ለማስፈታት ይጥሩ ነበር። ነገር ግን ያስፈቷቸው ደግመው እስር ቤት ገቡባቸው ተጨማሪ የቤት ሥራ እስቡት፤ መፈታታቸው በራሱ የሁሉም
ደስታ አልነበረም፤ የተፈቱትም ምርቃቱን ከምንም አልቆጠሩትም በጥንቃቄ ለመያዝ አልሞከሩም … በቃ ሩጫ ብቻ ነው።
- · በመሃል።
በመሃል የሆነው ነገር የጠቅላይ ሚ/ር ለውጥ እና ፊት የነበሩት ወደ ኋዋላ መሆን ሌላ ሞገድ
አስነሳ። ኦቦ ለማ መገርሳን ወደፊት በማምጣት ውድድሩን ኦህዴድ ልግፋበት ቢል የመርህ ጉዳይ አሰረው፤ ስለዚህ ብልሁ ለማ መገርሳ
ዕድሉን ላለማጠፍ እራሳቸውን ሰውተው ፊት ለፊት በመርህ ችግር ከሌለባቸው ሁለቱ አንዱን መርጠው የኦህዴድ ሊቀመንበር አንደርጉ እና
በጠራ መስር የጠ/ ሚር ውድድር ላይ እሳተፋለሁ አለ - ኦህዴድ።
ይህ መንገድ ከሚገጥሙት ውድቀቶች የቀደመ ሲሆን የአደረጃጃት መርህ ለጋነት ያለባቸው ብቻ ሳይሆን በፖለቲካ ህይወት የቆዩት
ሳይቀር በዶር አብይ አህመድ ፊት ለፊት መምጣት፤ ገና ለእጩነት መቅረብ በአፍራሽነት ዘመቻው ቀጠለ። ትልቅ አጀንዳ ነበር „አብይ
በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ውሳኔ“ ላይ አልተገኘም አስመሳይ ነው፤ የወያኔ ጁንታ ነው“ ወዘተ ወዘተ …
ብከነትን ለራስ ራዕይ ከመሸለም በላይ አሳፋሪ ነገር የለም።
በዚህ ማህል ነው ሙያሌ ከሚሊዮን
በላይ 50ሺህ ወገን የተፈናቀለው እና ስደት ወደ ኬንያ የሆነው። እኛ ይሄ አልነበረም ጉዳያችን ሌላ ትርምስስምስ ላይ ነበርን።
እሰቡት ነፃነት በሚፈለግው ሃይል ነው ያ ሁሉ ወጀብ፤ ያሁሉ ቀውስ፤ ያ ሁሉ ወርክብ። አጅሬ
ወያኔም ምርኩዞቹን ይዞ ገብቶ ሞገተ። የነፃነት ፈላጊው ድጋፉን ለወያኔ ሃርነት ትግራይ ለገሰ። አንድም ቀንጣ ሊሂቅ አንድም ቀንጣ
ሚዲያ አንድም ቀንጣ ጸሐፊ ሊደግፍ አልቻለም።
የኦህዴድ መንገዱን በመግለጫው ላይ አሳውቆ ስለነበር ቅኖች ተጽዕኖ ፈጣሪ የማንባለው ብቻ ሲጀር
ጀምሮ በድጋፋችን ቀጠልን። ስለምን የኢትዮጵያ የነፃነት ፈላጊውን አቅም የተለጠፈውን ፎቶ ይመስል እንደ ነበር አሳምረን ስለምናውቅ።
ወደፊትም እንዲሁ …
ይህ ብቻ ሳይሆን አማራጭ በማጣታችን ብቻ ሳይሆን በትክክል ኦህዴድ ፊት ለፊት ያመጣው ነፍስ የኢትዮጵያን መከራ የመሸከም አቅም አለው ብለን ስለምናምን ነው። በዚህ ሁሉ ጃዋርውያን፤
አራርሳውያን ኦኤምአውያን አልነበሩም።
ዛሬ ባለቅ ሰዓት እኛ ተደራድርን እንጂ ትናንትም ዛሬም ኢትዮጵያ በእጃችን ላይ እንደሚሉት አልነበረም።
ያማ ቢሆን ከጅምሩ ይደግፉት ነበር። ቅንጣት መንፈስ አልበራቸውም በዚህ የለውጥ ሂደት። በቅናት አብደው ጄኔባ ላይ ሁሉ ታዳሚው
የማይታይበት የ እንግሊዘኛ መግለጫ ሁሉ ሲሰጡ ነበር። ታዳሚው ያልታዬበት የተሰብሳቢው ቁጥር አናሳ በመሆኑም ጭምርም ነው።
ጃዋርውያን እንዲያውም በማጣጣል እና በማብጠልጠል ነበር የተጠመዱት። ለመሻገሪያ ድጋፍ ዶር መራራ
ጉዲናን እና ኦቦ በቀለን ገርባ እንደ አቅም ማጠራቀሚያ እንደ መደራደሪያ አድርገው ነበር ሲያቀርቡ የነበሩት ስለዚህ ዋሾዎች ናቸው።
ባልነበሩበት ማሳ ነው አሁን ሲፎክሩ የሚሰሙት። እንሱ የነበሩት ቄሮን ናዳው፤ አቁመው፤ አፍልሰው፤ አቃጣልው፤ ዝጋው እዝ ላይ ነበር።
ያ ደግሞ የተደረጃ አልነበረም። በባዶ እጅ የሰለጠነውን ሰራዊት የሚታገል የተበተነ ሲሆን ለዛውም
ሽዋ ላይ ብቻ ላይ ነበር አቅሙ።
የአማራ ተጋድሎም ቢሆን መጨረሻ ላይ ነው ወሎ የተጨመረው፤ አሁን እርግጥ ነው ሽዋም ተቀላቅሏ
ብል ይሻላል ተዋህዷል ከምል። የተዋህዱት የአማራ መንፈሶች የጎጃም እና የጎንደር ነው። እርግጥ ነው ሂደት የሚጠይቁ የህሊና ተግባራት
አለበት ሌሎችን በወጥ መንፈስ አንድ አንደርጎ አማራን ኢትዮጵያዊ ዜጋ የማስደረግ።
ይህም ሆኖ የአማራን ተጋድሎ የመንፈስ አዛዦች ተቋማዊ ስላልነበር ጉልበታም ሆነው ልጅ እንደ
አንጻራዊው ጃዋርውያን ጎልብተው ሊወጡ ስላልቻሉ ከመነግሥት ጋር ያላቸው የመደራደር አቅም እንዳዬነው ነው።
ጃዋርውያን ትልቅ ሚዲያ አላቸው። ለዚህም ነው በአደባባይ እርቀ ሰላም አውረድን የተባለው። ግን ጆዋርውያን ያመነ ጉምን
የዘገነ ነው። አይደለም ለ ኦሮሞ ህዝብ ለዶር መራራ ጉዲና ሆነ ለ ኦቦ በቀለ ገርባ መንፈስም አልነበረም ትግላቸው። ጠ/ ሚር ንጉሥ
ጃዋርን ለማድርግ ነበር። ሌላው ጋር ስምምነቱ ከኖረ።
ነገር ግን አቶ ጀዋር መሃመድ ስብዕናው ግራጫማ በመሆኑ ቀጣይ ዘመድ ሊኖረው
አይችልም። ከራሱ ጋርም ስምም ሆኖ ያልተፈጠረ ሰው ነው። ለዚህ ነው እኔ ልኡል እግዚአብሄርን ባገኘው ስለምን ይህን መሰል ሰብዕና እንደ ፈጠረ እጠይቃዋለሁ ያልኩት።
እንዲህ ዓይነት ስብዕና ይዞ በሃይል አሰላለፍ መስመር ውስጥ መግባት መስመጥ ነው። የአቶ ንጉሱ ጥላሁን ዕጣ በቀጣይ
ያዬው ሰው … ዘው እናዳሉ በብዥታ …
በሌላ በኩል የአማራ የህልውና ተጋድሎን የሰከነ፤ የረጋ፤ ወዳጅ ጠላቱን የለዬ መሪ ቀድሞም ነበረው
አሁን አለው መሬት ላይ። ስለሆነም የመረብ ወይንም የሳይበር ጉጉሱ ተንሳፏል ብዬ አስባለሁኝ።
ያን ተጋድሎ መዳፉ ላይ ያስቀመጠው
ባለቤቱ የራሱ መንፈስ ራሱን የገበረለት ራሱም አብዮቱን ያፈነዳው ውስጠት ነውና። ስለዚህ በዚህ ላይ ያበቃ ጉዳይ ነው። መሪ አለው። ስክነቱ
በዚህ ከቀጠለ ለኢትዮጵያም አቅም ሆኖ የመውጣት አቅል አለው ብዬ አምናለሁኝ … "የናቁት ይወርሳል" እንዲሉ፤ ምህረትን፤ ርህራሄን፤
ይቅርታን በሚመለከትም ችግር ያለበት አይመሰለኝም። ተገሎ መቆዬቱም ለመልካም ነው ብዬ አስባለሁኝ። እርግጥ ነው የሳጅን በረከት ስምዖን መንበር ላይ መሆኑ ፈተናውን እጅግ ውስብስብ እና መስዋዕትነቱም ቀጣይ ይሆናል። ይህን ለማስቀረት የ አብይ ሌጋሲ ተቀልብሷል ብሎ አምኖ የሎቢን ተግባር አጠናክሮ መቀጠል ያዋጣ ነበር። ግን አልሆነም ልጅልነት ማህበርተኝነት ወረፋው በርክቷል ... አሁንም የወያኔ ሃርነት ትግራይ የስልት ጉዞ ድል ላይ ነው። ጠርጥር እንጠርጥር እንኳን የለም፤ በነበረው በቀደመው ሁኔታ እዬተካሄደ ነው ... ይላሉ ... ከትከት ነው...
- · መከራው።
ሌላው መከራው በኦህዴድ ውስጥ ሰርጎ የገባው የኦነጋውያን መንፈስ የአባ ዱላውያንን አክሎ ሌላው
የተሰፋ አረም ነበር። ያ መንፈስ ከብአዴንም ጥግ በማግኘቱ ያን አክሎ ጃዋርውያን በመቀፍ ወደፊት በማምጣት እረገድ የታላቁን የኦሮምውያን
ህልም ለማሳካት ያደረገው ተጋድሎ በሰሞናቱ የታዩት ትእይንቶች ናቸው። ትእግስት የጎደለው እርምጃ ነበር። ስጋትንም በስፋት የናኘ፤ ተስፋንም
የቀማ …
ንጽህና ያላቸው የኦህዴድ አባላት አገግመው ለመውጣት በራሱ
ዘመን ይጠይቃቸዋል፤ ብዙ አቅም አባክነዋል፤ ቅንነትም መታመንም አቃጥለዋል። ከኢትዮጵያዊነት በላይ ክብርም ድምቀትም የለም። ይህን
እዬሳተ የሚሄድ ማንኛውም ግለሰብ ይሁን ድርጅት ያገኘውን ማግኘቱ ድረሳኑን ይመርምረው … የለበጣ ጉዞ በመላጣ ነው ያስቀረው …
ከላይም ከታችም ከግራም ከቀኝም የተማገደው አብያውያን ነበር። አብያውያን አቅሙ፤ ችሎታው፤
እርግታው፤ ትህትናው፤ ብቃቱ፤ ስልቱ፤ ጥበቡ፤ አርቆ አሳቢነቱ፤ ሁሉን አቃፊነቱ፤ አሳታፊነቱ፤ ትጋቱ፤ ጠንካራ ሰራተኛነቱ፤ ቅንነቱ፤
ግልጽነቱ፤ ፍቅርነቱ፤ ይቅር ባይነቱ፤ ምህረት አድራጊነቱ፤ ንጽህናው ሲጀመር ጀምሮ በመከራ የበቀለ ነበር።
አንድም ሚዲያ አብይን በሚመለከት ልዩ ዘገባ አላቀረበም፤ ነበር። ሳተናው በግል ሰፊ ጥረት ካደረገው
በስተቀር። ከመጋቢት 24 እስከ ሰኔ 16 ድርስ በነበረው የአብይ መንፈስ ውስጥ እጅግ በጣት የሚቆጠሩ ቅኖች ብቻ ነበር የደገፉት።
ትንሽ መቀራረብ የመጣው ከሰኔ 16ቱ ማግስት ጀምሮ ነበር። ይህም ቢሆን ያ የህዝብ ፍቅር ሞገድ
ያሰፈራው የሊሂቃን ጉባኤ በመገንባት እና በመናድ ባለዬለት ብዥታ ውስጥ ነበር ዋልሎ ሲያዋልል የባጀው። ጹሁፎች ሁሉ „እንዳያማ
ጥራው እንዳይበላም ግፋው“ ዓይነት ነበር።
- · አድፋጭ ፈጥፋጭ።
አድፋጩ በርካታ ነበር። በራሱ በብአዴን እና በኦህዴድ ውስጥም ነበር። ታላቁ የአድፋጭነት ጉድብ
የነበረው ግን የትግራዩ ወያኔ ሃርነት ትግራይ እና የትግራይ ሊቃናት ነበሩ። እነሱ ሰራዊታቸውን ፌስ ቡክ ላይ ይለቁ እና እነሱ
ግን በመንፈስ አንድነት በማገግም ባጁ።
ሞገዳቸውን ወደ ተግባር ለመለወጥ ሰፊ ሙያዊ፤ ክህሎታዊ እልሃዊ ሁኔታዎችን አጠኑ፤ አቀናበሩ፤
የዞጋቸው ውህደት በሚደንቅ፤ በሚገርም የአንድነት እድምታ ተግባራቸውን ከውነው ቀን መጠባበቅ ጀመሩ።
ተፎካካሪው ዘጋቢ ጋዜጠኛ፤ አልቃሻ፤ ዳተኛ ሆኖ ነው የባጀው።
- · ውጩ በጩነት።
የአሜሪካው ጉዞ ልክ እንደ ሰኔ 16ቱ ያልተመቸኝ ነበር ለእኔ። በዚህ ወቅት እርጋታ እና ስክነትን የሚጠይቁ በርካታ ጉዳዮች ስላሉ።
ምክንያቱም፤ ሊቀድሙ የሚገባቸው መሬት ላይ መሰረት ሊይዙ የሚገባቸው ጉዳዮች ስለነበሩ። መሬት ላይም ሌጋሲውን አስጠብቆ የሚቆይ አልነበረም።
አድፋጩና እድምታው፤ ሴረኛው እና ሳቦታጀኛው
እያሉ አቶ ደመቀ መኮነን ብቻ አምኖ ጥሎ መውጣት ብቻ ሳይሆን፤ የፍቅር ሞገዱ በተሸናፊ ሃይሎች ላይ ሊፈጠር የሚችለው የተፅዕኖ አብዮታዊ ሞገድ አልታሰበበትም።
ደህንነቱ እና ጸጥታ አስከባሪው በመዳፍ መኖሩ እርግጥ ሳይሆን፤ ከላይ አስከታች የተዋቀረው የወያኔ
ሃርነት መዋቅራዊ ግንኙነት እጅግ አስፈሪ ነበር፤ ኦነግውያን ሲጨመሩ አስፈሪ ነው።
ቀደም ሲል አሁን ያለቆመው እያረፈ የተከሰተው
የኢትዮ ሱማሌ እና የደቡብ ህዝቦች የህዝብ ንጠት፤ የቤንሻንጉልን በተጨማሪነት ሲያዝ ስክነትን የሚጠይቁ መሬት ላይ ሊሠሩ የሚገባቸው
ጉዳዮች ቅድሚ ተሰጥቷቸው ቢሆን መልካም ቢሆን በሚል ነው እኔ ጉዞው ትንሽ ገፋ ባለ በሰከነ ጥናት ቢሆን የሚል እድምታ የነበረኝ።
በሌላ በኩል ግን ጉዞው ብዙ ነገሮችን አቀራርቦ ነበር በመንፈስ ደረጃ፤ ግን ቅኖች አገር ቤት አነሱ።
አረሞች በረከቱ። የአረሞች መበርከት ደግሞ ለቅልበሳው ፍርታይል ሆኑ።
ይህ ሁሉ ድጋፍ ቀድሞ ሊደረግ ቢችል ይሄ ዛሬ ያለውን ፈተና የመቋቋም አቅም መወጣት ይቻል ነበር።
አሁን ያሉ ውህድ የድጋፍ መቋጥቆጥ ታይቷል። የቅድስት ተዋህዶም አንድነት ሌላው ታላቁ አገራዊ
ፋይዳ ነው። በዛ ላይ ጠንካራ የጸሎት ሃይል ተፈጥሯል። ቀጣዩን ፈተና አላስብህም ብለን ማለት ነው … የአብይ ሌጋሲ ካልቀጠለ በዚህም
ዙሪያ የታሰበው ሁሉ መቀልበሱ ግድ ይሆናል …
- · መቀነስ።
መንገድ ላይ እያለ የአብይ ልዑክ ብትመለስ ዋ! እንደ ስመኘው እንዘርርህ አለን የሚል መልእክት ተላለፈ። ልዑኩ አሜሪካ
ከመድርሱ ቀመድም ብሎ በምግብ ብከለት ብዬ ነው እኔ የማስበው ብአዴን ቀኝ እጁን አጣው።
አዲሱ አንጃው እና ወያኔ ሃርነት በጋራ የሠሩት ሥራ የምሥራች ነበር የቆሞስ ተስፋዬ ጌታቸው
እና የቆሞስ ስመኛው በቀለ ህልፈት። ብዙም ትኩረቱ ይህን ያህል አለመሆኑ የሚታዬው ሙቀቱ አሜሪካን ላይ እንደ ነበረው መቀጠሉ ነው።
ልዑካኑ የጠረጠሩት አንዳችም ነገር አልነበረም። በዛው በልዑኩ ውስጥ እንኳን አንጃ
መኖሩን አለሳቡበትም። የተለዬ ተልዕኮ ያላቸው ስለመኖራቸው ልብ አልተባለም። ለዚህ ነው እኔ ጤፍ አና ሰናፍጭ ብዬ የጻፍኩት።
መፈንቅል የተካሄደው ቦሌ ላይ አውሮፕላኑ ሲያኮበኩብ ነበር። ለመፈንቅሉ አጃቢ ቀውሶችም በሚገባ
ተደረጃተው እንዲጠብቁ ተደርገዋል።
ያው ሚኒያ ላይ የልብ ልብ የተሰማቸው ኦነግውያን እንዴት ለውጡን በህብረት እና በአንድነት እናስቀጥለው
አልነበረም ተጋድሎው። እንዴት በመነጣጠል ተያይዝን እንውደቅ ነበር። ዲሲ ላይም ቢሆን የለውጡ መንፈስ በምን
ላይ አትኩሮት እንደሚያስፈልግ አልገባቸውም።
አገር ቤት በራሱ በኦህዴድ፤ በብአዴንም የበቀሉ አረሞችን፤ ወያኔን ያህል ጉድጓድ ድርጅት አስቀምጦ
ያን ያህል ጉጉስ ምን ያህል በአዬር ብቻ የተሞላ የነፃነት ፍላጎት እንዳለን ያሳያል። እኛ ምንም ከሌላን ቢያንስ የመጣውን ለውጥ
ለመቀበል ያን ያህል በስም እና በግልሰቦች እሰጣ ገባ አስፈላጊ አልነበረም።
ይልቅ ለእኔ የሎሳንጅለሱ ሥርዓቱ እና የአመራር ጥበቡ የለውጡ መንፈስ የጋባው እና ተምሳሌያዊ
ነበር ማለት ይቻላል። አንተ ነፍስህን ስታገኝ ነፍስህን የምታቆይበትን መንገድ ማስቀጠል እንጂ አቅም ማባከን አይገባም ነበር። ለዛውም
እንዲህ ሆኖ ለቀረው … ብቻ አይዋ ተስፋ የሚለን ከኖረም ይደመጣል … በቀጣይ ቀናት። ለዛም ዝግጁ ሲኮን ነው። ምንም አልተፈጠረም ብለህ ትራስህን ከፍ አድርገህ ተኝተኝ የሚገኝ ብጣቂ ተስፋ የለም።
የሆነ ሆኖ መልስ ላይ „አክ“ ወሬዎች እንደሚባለው ሳይሆን አንጃው የበላይ ሆኖ በወጣበት ጥቂት
ቀናት ውስጥ ጃዋርውያን የአብይን መንፈስ ለመቀለበስ ሰፊ ዘመቻ ሲያደርጉ ተመልክተናል። ዝማሬው ሽብሸባው ፉከራው ቀረርቶው ... ድልቂያው ሁካታው ... ታዬ ...ከሰነበት፤ ካሰነበተ እግሬን አውጪኝ ካለደረገስ ...
በሌላ በኩል አድብቶ የባጀው የትግራይ ሊሂቃን የእድምታ ውሳኔም ጎልቶ ወጥቶ አቅሙን አሳይቶ
አሁን መንበሩን እዬተቆጣጠረ ነው። እንኳንም አላደረገው እንጂ ቢያደርገው ኑሮ እነሱ የቀብር ሥርዓቱን ሁሉ አደራጀተው ነበር የጠበቁት።
ያ አልተሳከም፤ ሳይሳከ ሲቀር ደግሞ ሂድ ሲባል የሚሄድ፤ ቁም ሲባል የሚቆም፤ ተቀመጥ ሲባል የሚቀመጥ፤ ተኛ ሲባል በእንቅልፍ ክኒን
የሚተኛ መንፈስ ፈጥረው እዬቆራረጡ እዬሰነጣጠቁ ቲያትር እዬሰሩ በአብይ በሥሙ እዬነገዱ ይገኛሉ፤ የለውጡ ቀልባሾች።
አሁን ይህን በማድረግ እና በማስደረግ እረገድ ይህን አቅም በመሸከም እረገድ ከሳጅን በረከት ስምዖን በላይ አቅም ያለው ማንም የለም።
አሁን የአብይን ሌጋሲ በመዳፉ ውስጥ አስገብቶ እዬዘነጠ፤ ያለው የአቶ በረከት ስምዖን ሌጋሲ ነው።
በጣም እዬሳቀብን ነው ያለው። ኦህዴድ ውስጥ የበቀሉት አረሞች እና መንፈሳቸው ከጃዋርውያን ጋር ደግሞ ዕጣ ፈንጣቸው በምን ላይ
እንደሚገኝ የትናንቱ ስብሰባ ይናገራል።
ራሱ የኦቦ ለማ መገርሳ በስብሰባው ላይ መታዬት ምስል ነው፤ ፌክ ነው … ለዛቸው ሴሪሞኒ ብቻ
ነው፤ ማዘናጊያ፤ ትጥቅ ማስፈቻም ነው። በር ተዘግቶ ነው የተከወነው። አፋኞቻቸው ውጪ ይጠብቃሉ።
ስለምን ሌላ ቀውስ ደግሞ ኢትዮጵያን ስለሚጠብቃት። እራሱ ኦሮሞ
መንፈሱ አይሆኑ ሆኖ ስንጥቅጥቅ ብሏል። መንፈሱ ተበትኗል። አሁን ሰብሳቢ የለውም። የለማ አብይ ድካም ከንቱ ሆኗል።
አሁን እኔ እላለሁኝ አብይ መንፈሱ ነፃ አይደለም። መሪው የሳጅን
በረከት ስምዖን መንፈስ ነው። ወዮ አማራ! ወዮ ጎንደር! ወዮ ገዱ! ወዮሎሽ አገሬ!
ይህ ሁሉ የሆነው አንድ ድርጅት አንድ አካል፤ አንድ ሚዲያ አንድ ጋዜጠኛ በእጁ ያለ ነገር ሲኖር
ብቻ ነው መዘመን ይገባው የነበረው። አቅምን አባከነው፤ አዋከብነው፤ ሰላሙን ነሳናው፤ በመጨረሻ ደግፈነው በተቀለበሰ ሰዓት ... ያን ጊዜ ኢትዮጵያ ምን እዬሆነ ነው ብለን ለማሰብ እንኳን ፋታ አልነበረነም።
ልዑል እግዚአብሄር ፈቅዶ እኛ ባላሰብነው
ሁኔታ የሰጠንን ምርቃት ችግኙ በቅሎ - አሽቶ - አጽድቆ እንዲያሰብል ከማድረግ ኬኩም፤ ሙሽርነቱም፤ ጫጉላውም፤ ቅልቅሉም፤ ግጥግጡም
ቅብጥ እና ቅልጥ ሲያደርገን ሁሉንም አጥተን ባዶ እጃችን ቀረን።
አገር ቤት የምታዩት ነገር ሁሉ በተቀለበሰው መንፈስ ላይ ያለው የወያኔ ሃርነት ትግራይ ዳንስ
ነው። ገና „ሀ“ ብሎ ሲበቀል ሁሉም ሰው አቅሙን፤ ሃይሉን፤ መንፈሱን ለግሶት ቢሆን ኖሮ፤ ሰላሙ ባይታወክ ኖሮ አቅሙ አይደለም ለ ለኢትዮጵያ ለአፍሪካ የሚደፈር አልነበረም።
ግን አልሆነም።
አብይ እና መንፈሱ የሰማይ ነበር። አብይ እና ብቃቱ እዮራዊ ነበር። አብይ የረቂቃን ጸጋ እና በረከት የታደለው
ቅን እና ንጹህ ሰው ነው። ግን ልብ ለልብ መገናኘት ተስኖን የሆነው ሆነ።
ኦህዴድም አራሱን ያፈረሰ ያስበላም ድርጅት ነው። እድሉን ያነደደ
ድርጅት ነው … ጠንቃቃነት ያተርፋል እንጂ አያከስርም። ኢትዮጵያዊነት እንጂ ኦሮሞነት አልነበርም ድንበር የለሹን የፍቅር ሞገድ
ያበረከተው፤ ያ ተጠቀጠቀ የሆነውም ሆነ … የ97 የ አዬሌ ጫምሶ ቅንጅት አሁንም ይከሰታል ኦህዴድ ላይ ... ብንተጋ ግን ወደ መንበሩ የ አብይን ሌጋሲ የማስመለስ አቅሙ ነበር ግን አብረን ዝም እንበል አብረን ለሽ እንበል ሆነ ነገር አለሙ ሁሉ።፡
- · ክወናው።
ይህም ይሁን በመጨረሻው ሰዓት ደገፍን ከተባለ ደግሞ የደገፉት አካላት ያ መንፈስ ችግር ሲገጥመው
ችግር ደርሶበታል እንዴት በመፍትሄ ላይ እናተኩር ማለት ይገባ ነበር።
የሚያሰቀኝ ደግሞ ከ ኢኮኖሚ ትራንሰፎርሜሽን ወደ ፖለቲካ ትራንስፎርሜሽን የመሸጋጋራችን ራዕይ ነው። ብትን መቆሚያ አፍር ሳይኖር ጥሼ አውጣለሁ ብሎ መፏለሉ ይገርማል።
የአብይ
ሌጋሲ እናስቀጥላለን የሚሉት እራሳቸው በመዘንጋት ውስጥ ሆነው ሌላውንም ተዘናጉ እያሉ ሲያስተምሩ ማዬት ምን ያህል መነሻችንም መደረሻችንም ሳናወቅ ስንባክን እንደኖር ፍሬ ቢሶች መሆናችን ያሳያል …
ስለምንደግፈውም ስለመንቃወመውም ነገር ሳነሳናዳ ነው ነፃነት ፈላጊነታችን … ሲያረጁ አይበጁ ነው የሆነው።
ነፃነት ለአብይ እና ለመንፈሱ!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ