!ዳግማዊ አባ ኮስትር አቶ ንጉሡ ጥላሁን የማን ናቸው?

!ዳግማዊ አባ ኮስትር
አቶ ንጉሡ ጥላሁን
 የማን ናቸው?!

„አንተ በህይወት ሳለህ አእምሮህም
 ሳለች ግብርህን አትለወጥ።“
መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፴ ቁጥር ፳፱

ከሥርጉተ©ሥላሴ
05.01.2019
 Sergute©Selassie
ፍቅር በፍቅር!


·       ከእመ ዝምታ ከእናቱ ሲዊዝ

ዋው ሻሾ ፍጥነቱን ጨምሯል ዛሬ የታደለ ቀን ነው። ሻሾን እወደዋለሁኝ እንደ አድዮ ነው የማዬው። በቃ በዚህ ከቀጠል ነገ ነጭ ስጋጃ ለሰንበት ሙሽራ አንጥፎ ይጠብቃል ማለት ነው። ግን ውዶቼ እንዴት ናችሁ ደህና ናችሁ ወይ?

·       ወግ ቢጤ ….

ሰሞኑን አንድንድ ዜናዎች ከዚህም ከዚያም ሲወርቡ ደፍሬ መጻፍ አልቻልኩም። የጠራ መረጃ በግራ በቀኝ ማግኘት ስለነበረብኝ። አቶ ንጉሡ ጥላሁን የጠ/ሚኒስተር ጽ/ቤት የፕሬስ ኃላፊ ሆነው መሾማቸው እርግጥ መሆኑን ዛሬ የበለጠ አረጋግጫለሁኝ። ስለሆነም በዚህ ዙሪያ የምለው ይኖረኛል።

·       አቶ ንጉሡ ጥላሁን የማን ናቸው?

ለመሆኑ አቶ ንጉሡ ጥላሁን የኢትዮጵያ? - የአማራ? - የጉራጌ? - የኦሮሞ? - የዜግነት? - የዞግነት? ከቶ - የማን ናቸው። እንደ ሥርጉ ሥላሴ አቶ ንጉሡ ጥላሁን የራሳቸው ብቻ ናቸው። እድግመዋለሁኝ አቶ ንጉሡ ጥላሁን የራሳቸው ብቻ ናቸው። ለሁሉም መስመር ደግሞ ሊንክ አገናኝ ድልድይ ናቸው። ለውጩም ለአገር ውስጡም። ዘለግ አድርገን ስንሄድበትም ከዚህም ያለፈ ይሆናል። ወደ ሌላ ዓለም ይዶለናል። ለጊዜው በቁጠባ ይያዝ ... 

እንዲህ ዓይነት ሰብዕና በጥንቃቄ መያዝ ይኖርበታል።  ለሁሉም መስመር ሊንክነታቸው አሉታዊ ከሆነ አደጋው ሰፊ ነው። አዎንታዊ ከሆነ ግን ትርፍን መቸርፈስ ነው እስኪበቃ። ስለምን ልባም የሆነ አቅም ከደልዳላ ሰብዕና አገር ስለአላቸው። ድፈረታቸው እና በራስ የመተማማን አቅማቸው ይመሰጥኛል እኔ በምምኛላቸው ድንግልና ቢገኙ ልብም ለመሸለም ዝግጁ ነበርኩኝ። ግን ዛሬ እና ዛሬ ፍጣጫ ላይ ናቸው? ለዛሬም ዛሬም እራሱ እሱ አንድዬ ይሁናቸው ... 

እዲያውም እሳቸው ከመንግሥት ሥራ ይልቅ የግንባራቸው የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ ቢሆኑ ብዙ ብዙ ማሰበል ይቻል ነበር። ሰብዕናቸው የሚፈቅደው የተፈጥሮ ጸጋ አለ ለድርጅት ዘርፍ። ደልደል ሰከን እርጋ ማለታቸውን እኔ አብዝቼ እወደዋለሁኝ። የህሊና አቅማቸውም ብቁ ነው። 

ችግሩ የሰብዕና ደልዳለነታቸው ጸጋ በዛ ልክ መሆን አለመቻላቸውን ያሳጣው ለአነጋውያን፤ ለጃዋርውያን ያሳዩት ከፍ እና ዝቅነት ለጠ/ሚር አብይ መንፈስ ጋር ሲመዘን አቅማቸውን በለቅ አስመታው - ለእኔ በግሌ። የክብር ደረጃቸውንም ቀረጣጠፈው።  በጣም የምመሰጥባቸው ፖለቲከኛ ስለሆኑ። በሁሉም ባንስማም ሞጋች እና ኮስተር ያለ ነፍስ ግን ግጥሜ ነው። ይህ እንግዲህ እንደ መታደለም እንደ መረገምም ሊወሰድ ይችላል …
  
ማንም ሰው አቶ ንጉሡ ጥላሁንን አውቀዋለሁ ማለት አይችልም። ማንም ሰውም አቶ ንጉሡ ጥላሁንን መዳፌ ውስጥ ነው አለ ማለት አይችልም እኔ በርቀት እንደምታዘበው ከሆነ። ባህካል ፕሬዚዳንት ፑቲን እና ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ናቸው - ለእኔ። ሰብዕናቸው ብቻ ሳይሆን የማይደፈረው ውስጣቸውም ልግመኛ ሆኖ ነው እማዬው። ምን እንደሚያስቡም ለማወቅ የማይደፈር ተፈጥሮ ነው ያላቸው።

በዚህ ቀውጢ፤ ርጋታ በነሳው፤ ባለረጋ የፖለቲካ ሙቀት ይህን የመሰለ ደፋር እርምጃ የጠ/ሚር አብይ መንፈስ ሲወስድ ሪስኪውን ማሰብ ይኖርበት ነበር። እሳቸው እራሳቸው ሰብዕናቸው ላስተዋለው ድርጅት ናቸው። እርግጥ ነው ዶር ለማ መገርሳ በሳቸው ላይ ሙሉ ዕምነት እንዳላቸው በርቀተም ቢሆን ጠረኑን አውቀዋለሁኝ። ይህ የሹመት ጉዳይ ለእኔ  Overconfidence የሚሉት ዓይነት መጠኑን ያለፈ ደፋር እርምጃ ነው ለእኔ።

 ልክ ከውጭ አገር አብሶ መሳሪያ ታጥቀው ኢህአዴግን ሲፋለሙት የነበሩትን ግቡ እና ሆታውን አስነኩት ብሎ የለማ አብይ ካቤኔ ካቴና እና እርምጃውን በአዲስ አባባ ንጹሃን ላይ ብቻ እንዳነባበረው ማለት ነው። ያልተመጣጠነ በራስ የመተማመን አያያዝ ነው እኔ እማዬው።

አሁንም የምዕራብ ወለጋ ጉዳይ ከአያያዝ አጠቃም ግድፈት የመጣ ነው። ኦዴፓ በራሱ ውስጥ ያለውን የኦነጋውያን መንፈስ ሳያጠራ ነበር በሩንም ልቡንም ቧ አድርጎ የከፋፈተው። ስንት የአማራ እና የኦሮሞ ወጣት ህይወት የገበሩበትን፤ የህዝቡ ኑሮ የተቃጠለበትን፤ ስንት ቂም የተቋጠረበትን ውጤት መና ለማስቀረት አፋፍ ላይ ደርሶ ነበር መሰክረምን ላዬ።

ገና በለጋ ዕድሜው ለውጡ ሴራ እና ሸር ለባጀበት ፖለቲካ እንደ ጎርፍ ውሃ የደገፈውን መንፈስ በማዳፌ ላይ ነው ያለው ብሎ እንደ ወሰደው ተዘናጊ እርምጃ ማለት ነው አሁን  የአቶ ንጉሡ ጥላሁን ይህን ቁልፍ የመረከብ ጉዳይ እኔ በግሌ የማዬው። ደጋፊ ጎርፍ ነው የገበያ ውሎም ማለት ነው።

የህሊና ተግባር ነው መተማመኛ ዋስትናው። በሩን በአራቱም ማዕዘን ባልተጋባ ልቅ መብት መክፈቱ ነው አሁን ለውጡን ቀዝፎ የያዘው። ሌላም የመፍንቅለ መንፈስ ፈንጅ ሰሞኑን ተጠምዶለታል - ለውጡ ራሱ። ተከታዩ ጉዳዬ ይሆናል … ኦዴፓ በሚወሰደው እርምጃ  የአማራ ተጋድሎ የህልውና አብዮትንም ከግምት እያሰገባ ቢሆን የተገባ ነው። እነሱ ብቻ ያመጡት እንዳልሆነ ያውቁታል። 

በዚህ ላይ የሚስጢር አተረጓጎም ችግር አለ። የ ዶር ለማ ገዱ አንዳርጋቸው ሆነ የአቶ ደመቀ መኮነን የም/ ሚኒስተሩ ዕይታም ሚዛን ሲዛባ ማስተካከል ይገባው ነበር። ለዘብተኛ ነው። ቀፍጣነነት ይጎድለዋል አብዝቶ። በ አንድ ቀንጀ በሬ አርሶ አይደለም ኦዴፓ ከዚህ የደረሰው። በአንድ እጅ አይጨበጨበም፤ አንድ እንጨትም አይነድም። የወልን ድል በሆነ ባልሆነው ማባከን የተገባ አይደለም። 

አሁን እኔ ወለጋ ላይ ስላላው የ እናቶች ጭንቀት አንጀቴ እርር ነው የሚለው። ለዚህ ድል አማራ ሁሉንም ተቀብሎበታል፤ እዚህ እንኳን ስንት ቅራኔ እኔ ገብቸበታለሁኝ እንኳንስ መሬት ላይ ያለው ወገኔ። የወለጋ ልጆች እንዲታገዱ አልነበረም ትጋታችን። ዕድሉን ለምለሙን ያሰረከበው ለኦነጋውያን እራሱ ኦዴፓ ነው። መጠዬቅ ካለበት የእሱ ኤንም ቢንም እንዳይከፋው ጉዞ ነው ከዚህ ያደረሰው ... 

ኦዴፓ ወለጋን  ለኦነጋውያን ነጻ መሬት ፈቅዶ ሲያስረክብ  የአማራ የህልውና ተጋድሎ መስዕዋትነት ከቁጥር አላስገባውም።  ኦነግ ስል የትኛው ኦነግ የሚል ጥያቄ ሊኖር ይቸላል በመንፈስ አብዛኛው የተጋባ ነው። አብዛኞቹ አንድ ናቸው። ለዚህ መተማመኛ ያደረገው ኦዴፓ ፈሪማኛው የብአዴኑን አቶ ንጉሡ ጥላሁን ብቻ ነው። የተለዬ ልዩ ቀረቤታም ግንኙነት እንዳላቸው ይሰማኛል። ይህን ደፍሬ እማናገረው ነገር ነው። 

እሳቸውን ብቻ ነጥሎ ልዕለ አድርጎ ማውጣት ግን ዋጋ ያስከፍላል። ያን ያህል ለኦነጋውያን መብት አዲስ አበባ ላይ ድጋፉ ሲለቀቅ በግራ ቀኝ መድረክ በሚሊዬነም አዳራሽ እና በስታዲዬም ለአማራ መንፈስም መሰሉን መከውን ግድ ይል ነበር። ንጥሩ ቀርቶ ግርዱ አልተሞከረም። 

የ አማራ የተጋድሎው ዋጋ ተድጦ ነበር የታለፈው። መዳጡ ምንም አይደለም ነገን ለማስቀጠል ግን አዳጋው ሰፊ ነው። ሃብት ማለት የገበያ ውሎ ሳይሆን የመንፈስ ቋሚ፤ ጽኑ ተከታታይነት ያለው፤ ሃላፊነት የሚሰማው ሰብል ማለት ነው። 

ይህ በዚህ እንዳለ … 
      
አዲሱን ለውጥ ፈጣሪ ተማልዶት የኡጋዴ ነፃ አውጪ ግንባር ከሰላማዊ ታጋዮችም በላይ ልስሉስ ሆነ እንጂ በዚህም ዘርፍ እራሱ ስጋቴን እኔ ጽፌ ነበር። ለውጡ በግራ በቀኝ ተሰቅዞ ትንፋሽ እስኪሰበሰብ ትንሽ መታገስ አለበት ሁሉ ብዬ ነበር። በላይ በላይ የሚጨማመሩ ነገሮች ከአቅም በላይ ሲሆኑ ለመግራት ፈተናው ከፍ ያለ ስለነበር።

የሆነ ሆኖ የኡጋዴ ነፃ አውጪ ግንባር ተወካይ ከፋና ጋር በነበራቸው ቆይታ ያዬሁትን ቅንነት ሙሉ ድርጅቱ ወደ አገር ሲገባ ያሳዬው የሞራል ልቅና እና ለህግ ተገዢነት በታማኝነት ውስጥ ለመቀጠል መወሰኑ ልዩ ስጦታ ነው። ለኢትዮጵያ አዲስ የድል ቸርነት ምዕራፍ ነው።

የኡጋዴ ነፃ አውጭ ድርጅት የታወቅ ድርጅት ነው። የዓለም ሚዲያም ማህበርተኛ ነው። በአውሮፓውም ህብረት ብቁ ዕውቅና የነበረው ነው። አሁን የደረሱበት አቋም ግን ተመክሯቸው ብስለታቸውን እንድንመዝን አስችሎናል። ድርጁ እና የበቁ መሪዎች እንዳሉትም መረዳት ችያለሁኝ እኔ በግሌ። ለብሄራዊነትም መንፈሳቸውን ፈጽሞ አያቃማም። ይባረኩም ብለናል። እንኳንም መጡልን ብለናል። 
  • የልቤ ደረስ ይበል አቶ ጃዋር መሃመድ።

ወደ ቀደመው ጉዳዬን ስመለስ ግን የአቶ ጃዋር ሪኮምዴሽን ሥራ ላይ ውሏል። አቶ ጃዋር መሃመድ ቅቤ ያጠጣ እርምጃ የአብይ ለማ ካቢኔ ወስዷል። አቶ አዲሱ አረጋ እና አቶ ንጉሡ ጥላሁን ወደ ፌድራል እንዲመጡ ነበር ፍላጎቱ የአቶ ጃዋር መሃመድ የቀደመ ህልምና ምኞቱ። እና አሁን ተሳክቶለታል።


የሚገረመው እኔ ይህን ጉዳይ ሊሆን ይችላል ብዬ ጽፌ ነበር በጉባኤያቸው ሰሞናት። ሁለት ዕድል ይኖራቸዋል ብዬ ነበር። አንዱ አፈ ጉባኤነት ሁለተኛው ጠ/ሚር ቢሮ አንደበትነት። ምክንያቱም በኦህዴድ ውስጥ ላሉ የኦነግ መንፈስም ሆነ ለራሱ ለለማ መንፈስ እጅግ ቅርብ ነው የአቶ ንጉሡ ነፍስ።  ለኦህዴድ ጉባኤ ተወካይም እሳቸው ነበሩ የተላኩት ከብአዴን። ለኢህአዴግ ጉባኤም እርገት እሳቸው ነበሩ ምርጡ። ሰንሰለቱ ሃዲዱን እትብት ይፍታው …

·       የብቃት አቅም።  

የአቶ ንጉሡ ጥላሁን ለዚህ ሃላፊነት ቦታው በጥንካሬያቸው ልክ ስለመሆኑ ምንም ጥርጥር የለኝም። ችግሩ ግን ይህ የሃላፊነት ቦታ የለውጡ ኩላሊት ላይ ይመሰጥበታል ወይ ነው? ለውጡን ይደግፋሉ በሙሉ ልብ አቶ ንጉሡ ጥላሁን። ከህውሃት ጋር ምንም ንክኪ የላቸውም - አቶ ንጉሡ ጥላሁን። ግን የአብይን መንፈስ አንድም ቀን አስጠግተውት አያውቁም። እንደ ተቀናቃኝ ዓይነት ነው እኔ የማዬው። ቁርጥ ጃዋርውያን ነው። 



ከጠቅላይ ሚር አብይ አህመድ ከሳቸው ጎን ቁመው ለቅጽበት ያዬናቸው አንዲት ጊዜ የመጀመሪያ የባህርዳር ጉብኝታው ሲጋብዟቸው ብቻ ነበር። ለዛም የነበረው የሚዲያው ጥራት አራባ እና ቆቦ የረገጠ ነበር። ከዛ ወዲህ ጠ/ሚር አብይ አህመድ በተለያዬ ሁኔታ ማህበራዊ ኑሮን አክሎ እዛው ነበሩ አማራ ክልል ብዙ ጊዜ ተገኝተዋል። ከአጠገባቸው ድርሽ ብለው አያውቁም። የጋራ ፎቶም እራሱ ያላቸው አይመስለኝም። 

አሁን ይልቅ ዕለታዊ ግንኙነቱ እንዴት እና እንዴት ሊሆን ይሆን ከጠ/ሚር አብይ አህመድ ጋር ገጥ ለገጥ መሆን ግድ ይላል ቢሮው አዲስ አበባ ከሆነ? ጋዳ ነው ገድጋዳ በጎሪጥ ወይንስ በቀን ይልፍ ሊኮለም ... ወይንስ ርግጥ የሚያረግ የሐምሌ ዝምታ ነገር ... 

ባደመጥኩት ልክ በቃለ ምልልስ ሥማቸውን ሲጠሩ አልሰማሁም። ጠ/ሚሩ ነው የሚሉት። ኢትዮጵያም ሲሉ አዳምጬ አላውቅም አገሪቱ ነው የሚሉት። ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን መምጣታቸውን አስመልክቶ የትናንቱ ተወዳጅ OBN ጋር ቃለ ምልልስ ነበራቸው። አንዲትም ቦታ ኢትዮጵያ ሲሉ አላደምጥኩኝም። በአገሪቱ ተጀምሮ በአገሪቱ ተጠናቀቀ።

ስለዚህ አቶ ንጉሡ ጥላሁን በአንድም በሌላም በሳላ አምክንዮ እኔ በግሌ ስመዝናቸው የራሳቸው ብቻ ናቸው ለማለት ደፍሬ ነው የምናገረው። ለዶር ለማ መንፈስ ዝንባሌ ቢኖራቸውም ለአብይ መንፈስ ግን ርቀቱ እኛ በርቀት እስክንታዘብ ድረስ ለ ዕውነት ህሊና በፍጹም ሁኔታ የተጋለጠ ነው። 

ለቀጣዩ ሲሞላ እና ሲጎድል በዬጊዜው የተለያዩ ገጾች ስለሚፈራረቅበት ቦታ ቀጣዩ ዕዳ ወይንስ ትርፍ አብረን እምናዬው ይሆናል። ልብ የማያስጥል አለመሆኑን ግን ደፍሬ መናገር እችላለሁኝ።

ኦህዴድ ውስጥ ያሉ ኦነጋውያን ግን ለዋንጫችን ከአቶ ጃዋር ጋር ማድረጋቸው አይቀሬ ነው። አቶ ጃዋር እንግዲህ ፌስ ቡኩ በለመለመ መስክ ይፈራንሰስ … የሐምሌው ዝምታ ቀስ እያለ ሥራውን እዬሰራ ነው ያለው። በአንጻሩ ብቁው አቶ ካሳሁን ጎፌ ተገፍተዋል። በጠ/ሚር አብይ አህመድ የጠራ እና የነጠረ ምልከታ ስላላቸው።

በሌላ በኩል የአቶ ምግባሩ ከበደም ሁኔታም ከዚህ ጋር የሚታይ ይሆናል። አሁን ላሉት የጠ/ሚር ጽ/ ሃላፊ አቶ ምግባሩ ከበደ የሚመጥን አቅም አላቸው። ብአዴን ላይ ራሱ ሌላ የፖለቲካ ሃላፊ ተመድቦበት ነው ያዬሁት። ለዛውም ገረር ያለ ምልከታ ያላቸው። ከወታደር ቤት የመጡ ነው የሚመስሉት። ቀጣዩ እንግዲህ የአቶ አዲሱ አረጋ ዕጣ ፍንታ ይሆናል … ለሁለገቡ ጉዳይ ኒይኩለስ ናቸውና …

·       ሊሆን ይጋባ የነበረው።

የፕሮቶኮል ደረጃውን እኔ አላውቀውም። ከፍ ይበል ዝቅ ይበል። በድምጽ አሰጣጥ ካቢኔው ላይ አንድ የፌድራል ሚኒስተር ሙሉ መብት እንደየሚኖር ግን ይረዳኛል። እንደ እኔ ግን አቶ ንጉሡ ጥላሁን የትራንስፖርት ሚኒሰተር ሆነው ወ/ሮ ዳግማዊት ሞገስ ይህን የጠ/ሚር ቢሮ የፕሬስ ሰክረታርያት የጽ/ ቤት ሃላፊ ቢሆኑ ምርጫዬ ነበር። በጣም ሴንሲቲብ ቦታ ነውና። ፍጹም የሆነ የልብ የሆነ አክብሮት እና ታማኝነትን ስለሚጠይቅ። 



ለአቶ ንጉሡም ደልደል ያለ ሰብዕና ከአቶ ጃዋር መሃመድ አቀባባል ባሻገር ሲቃኝ ሚኒስተር ቢሆኑ መልካም ነበር። ታምኝነታቸው ጉዳይ ይልቅ ለላቀረቡት መንፈስ ያስረክባሉ ለማለት አልችልም። በሚነስተር ደረጃ ግን ሙሉ አቅማቸውን ለመጠቀምም ይቻልም ነበር። በሌላ በኩል ንቅንቅ ለማይለው የራስነት ሰብዕናም አሰተማማኝነት ያለው ሁኔታ መዳፍ ላይ ይሆን ነበር። አቅምን ካለ ግጭት እና ጥርጣሬ ለመጠቀም ይረዳ ነበር። ሴቶች ጠንቃቃ ብቻ ሳይሆን ታማኝነታቸውም ረቂቅ ነው። በሥልጣን ጉዳይ አጀንዳቸው አይደለም። 

·       ?! - !?

ጥያቄ በቃለ አጋኖ፤ ቃል አጋኖ በጥያቄ ምልክት ግን ቢሯቸው ባህርዳር ላይ ነውና ወይንስ በደርሶ መልስ ዕሳቤ ነው ጉዳዩ የሚፈጠመው? ይህም አልገብቶ ነው …

ነው ኦዴፓ ሁለተኛ የፕሬስ ሴክራታርያት ቢሮ ባህርዳር መከፍት ፈለገ? እዛው ባህርዳር እንዳሉ ሆነው ነው መግለጫውን የሚሰጡት … እዛው ያለውን የተማሪዎች ጉዳይም የእኔ ብለው እዬታታሩበት ነው። ኦዴፓ የሁለቱንም ልብ ለማያያዝ ልቡ ያለው ከሳቸው ዘንድ ስለሆነ በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ እንዲሉ ሆኖ ይሆን? ምክንያቱም ለወያኔ ሃርነት ማንፌስቶ በርካቶች ሳጅኖች ነበሩ፤ ለኦዴፓ ግን አንድ  ለእናቱ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ብቻ ናቸው የልቡ።

ምን አቶ በረከት ስምዖን አዲስ አባባ ሆነው አልነበረም አማራ ክልልን እንደ ጉድ ሲሸረሽሩትም ሲያሾሩት የነበረው። ያው በተለመደው መስመር ወክ እንዲህ ማለት ነው። ዘመን ይሄዳል ዘመን ይመጣል አማራ መሬት ተብሎ በተከለለው ግን የዳማ ጨዋታ ነው የሚታዬው … ብቻ የቆዬ ሰው ይዬው … 

ኦዴፓ በዚህ በፕሬስ ዘርፍ ከ አማራ ሰው አመጣሁ የሚለን የራሱን መንፈስ አንጥሮ ነው። ቀልባቸው ለጠ/ሚር አብይ አህመድ ጋር ቢሆን አስደሳች ዜና ነበር፤ ነገር ግን አሁን እንደ አገርም አሳሳቢ ነገሮች ዘው እያሉ ነው … በራሱ ፍላጎት ውስጥ ያለ ሰብዕና የፈለገ አቅም ቢኖረውም እንዲህ ውስጥን ገልጦ መስጠት ምን ሊባል እንደሚችል ፈጣሪ ይወቀው። ያው ሲወቃ ሲያልቅ ነው የሚያውቀው ሊሂቅ የሚባለውም … አናያለን - እንተያያለን …

አቶ ንጉሱ ጥላሁን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት የፕረስ ሴክሬታሪያት ኃላፊ ሆነው ተሾሙ።



ሰው የማይፈታውን ጊዜ ባለ ቁልፉ ዕውነቱን ይናገራል።





                                          የኔዎቹ ኑሩልኝ።

                                          መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።