ሳተናው ወጣት አቶ ምግባሩ ከበደ ሳንጠግባቸው የት ገቡ?

ሳተናው ወጣት  
አቶ ምግባሩ ከበደ
ሳንጠግባቸው
የት ገቡ?
„ለሞት እስከ ደርስ ድረስ ሁልገዜ መከራ ተቀብያለሁ
 እና ስለዚህ ነገር እግዚአብሔር ከመከራ ያድነኛል“
መጽሐፈ ሲራክ ፴፩ ምዕራፍ ፲፫
ከሥርጉተ©ሥላሴ
 Sergute©Selassie
05.01.2019
 ከእመ ዝምታ ሲዊዝ

·       ጠብታ።

ዛሬ ክረምቱ ከገባ ለመጀመሪያ ጊዜ አያ ሻሾ መጣሁ ብሎ ብንብን እያለ ነው። ትናንት ሃይለኛ ብርድ ነበር። ከሃይለኛ ብርድ ቀጥሎ አያው ሻሾ እንደሚከተል ልብ ልክ ቢሆንም ከመኝታዬ ስነሳ ሙሉ ለሙሉ አያዋ ሻሾ ከነመጎናጸፊያው ስጋጃውን ዘርግቶ ኑልኝ ይላል ብዬ ነበር። አሁን ግን በስሱ ይዞታል። 

ሌላው የሲዊዝሻ መለያ አያ ሻሾ ሲኖርም ልክ እንደ አውድ ዓመቱ የእማ ዝምታ ነገር ጸጥ ረጭ ነው። እና ሥርጉትሻ ወደ ባዕቷ ገባ ብላ ታጣጥመዋለች። ግርግር የሌለበት፤ ህውከት የሌለበት፤ ኳኳቴ የሌለበት ረጋ ያለ ዓለም ይናፍቃል አይደል? እኔ ለዚህኛው ዓለም የተፈጠርኩ ነኝ። ረጭ ላላው ...  እንደዛ … 

ስለሆነም ዛሬም ምንም እንኳን ዕለተ ቅዳሜ ቢሆንም ጸጥታ አንጻራዊ ይኖራል አይዋ ሻሾ ሳይደክም ወይንም ሳይሰለች ገፋ አድርጎ ከሄደበት ነገ ዳግሚያ ባይናከተን ሆኖ እርፍ እንደሚል ነው። እንጠባበቃለን …

·       የስጋት እንቁላል።

የብአዴን የስሜን አሜሪካ ጉዞ ብዙም ስላልተመቸኝ ጥፌ ነበር። ምክንያቱም እኔ ፈሪ ስለሆንኩኝ። ያልኩትም አልቀረም እነሱ ስሜን አሜሪካ እያሉ ነው በቅማንት ጉዳይ ያደቡ ሃይሎች ስንጥቅ ፈጥረው ጥፋት ያስከተሉት። 

በብአዴን በኩል የአማራር አካሉ ክፍተትም እንዲሁ ሌላው ስጋቴ ነበር። በስጋቴ ልክ ምን ያህሉ እንደታዬ አላውቅም። እኔ ግን ሳዬው የአማራ የብዙሃን መገናኛ ድርጀት ከፍተኛ አመራር አካሎችን ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስን አሁን ቅርብ ጊዜ  አዳመጥኩት። አዬሩን አለወደድኩትም።

ስለምን ብአዴን ትሉናላችሁ ለሚሉ አዲሶቹ ሹመኞችም ራሱን አስችዬ እጽፍበታለሁኝ።  ሌላም የፖለቲካ ሃላፊ ተሹመዋል። አትንኩን አትድረሱብን የሚሉ። ከዬትኛው ፕላኔት እንዳመጧቸው አይታወቅም። እንደመርግ ከብደውኛል።  

ሌላው የብአዴን የለውጥ አካላት ወደ ስሜን አሜሪካ ሲሄዱ የስጋቴ ምንጭ የቆሞስ ተስፋዬ ጌታቸው ዕጣ ፈንታ ይገጥማል የሚል ነገር ነበረብኝ። የምግብ ብከለት ጉዳይ። አቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና ዶር አንባቸው መኮነን በሰላም መመለሳቸውን አዳምጬ ደስ ብሎኝ ነበር። 

አሁን ግን ከቁጥር አንድ ሰው ጎድሎብኛል። አቋርጠው ይመሰሉ፤ ተቋርጣው ይቀሩ አላውቅም። ቀኖችን ሳስተያያቸው ፓስት በተደረግበት ቀን ስለሆነ ውስጠ ፍላጎቴን ሊያረካልኝ አልቻለም። 

ትንታግ ሳተና ወጣት አቶ ምግባሩ ከበደ የት ገቡ? ታመሙ? ተሾሙ? ዘወር እንዲሉ ተደረገ? የት ናቸው ያሉት? ስሜን አሜሪካ ስደትን መርጠው ቀሩን ወይንስ እንደ አቶ ካሳሁን ጎፌ ገፋ ተደረጉ? ወይንስ ለከፈተኛ ትምህርት እዛው ቀሩ? አሁን በማዬው ሁኔታ የሀምሌው ዝምታ ሥራውን እዬሰራ ስለመሆኑ ምልክቶች እያዬሁ ነው።

 የት ናቸው ያሉት አቶ ምግባሩ ከበደ? እንዲህ እዬተጠራረገ ማን ጎልቶ እንዲወጣ ይሆን የሚፈለገው? 

እንግዲህ በግማሻቸው የሌላ ብሄር ብሄረሰብ አባል ካለሆኑ አቶ ምግባሩ ከበደ አደጋው ሰፊ ነው። ሁሉም ከሊቅ አስከ ደቂቅ የሚታመሰብት አብይ ጉዳይ ስለሆነ ወጥ አማራነት። በዛ ላይ ወጣትነት፤ በዛ ላይ ትንታግነት፤ በዛ ላይ ተናጋሪነት፤ በዛ ላይ ተደማጭነት ታክሎበት በዓይነ ቁራኛ ክትትል እንደሚደረገበት ይህ ነፍስ ልብ ልክ ነው።

የት ገቡ እኒያ የብሌን ቁልፍ የስኬት ርትህ? የት ናቸው አቶ ምግባሩ ከበደ? ብቻ አንድ ጥርት ያለ መረጃ ያስፈልገኛል? ወይንስ በቅደመ ሁኔታ እንዲታሰሩ ተደረጉ? አሁን የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ወሬ ሲጠፋብኝ ጭንቅ ነው የሚለኝ። 

 ከአገር ቤት ጋዜጠኛም የተመስገን ደሳለኝ ወሬ ሲጠፋብኝ እንዲሁ ምጥ ነው የሚይዘኝ? ስለሱ ያለብኝ ስጋት መጠነ ሰፊ ነው። ልክም አይወጣለትም። አሁን ደግሞ አብን ላይ አቶ ክርስትያን ታደለ ሌላ ስጋት ላይ የጣለኝ አንበሳ ወጣት ነው። ነገር ግን ለእነኝህ ትንታጎች ማንም ጥላላ ከለለ የላቸውም። ጋሻ መከታ የላቸውም። የአብርሃም በግ ነው መስለው የሚታዩኝ። ፊት ለፊት እዬተማገዱ ነው። 

ወደ ተሜ ስመጣ የእኔ የሚለው ቁርጠኛ ወገን የለውም። በእኔ ዕድሜ እኔ እንደ እሱ መጠኑን ያለፈ ድፍረት የነበረኝ፤ ቁርጠኛ አቋሜም ድንበር ያልተሰራለት የነበረ ቢሆንም  ጓድ ገ/መድህን በርጋን በቅርበት ሲቀዬርም በርቀት፤ በርቀት ጓድ ስለሺ መንገሻን፤ በቅርበት ነፍሳቸውን ይማርልኝ እና ጓድ ገዛህኝ ወርቄ እንዲሁም ጓድ ዘርጋው አስፈራ እና ጓድ አበበ በዳዳ ስለነበሩልኝ ነው ድፍሬት ፍሬያማ ተጋድሎ ሲያደርግ የነበረው።

ቆቅ ነበርኩኝ፤ ለነገሩም ዛሬም ቆቅ ነኝ። ወለም ዘለም የለም። በተከደነ ሁኔታ መኖር ያደግኩበት ነው። ለጋህዱ አለም ብልጭልጭ ቀልብ ኑሮኝ አያውቅም። መዘናጋት የለም እንደማለት። ያን ጊዜ የመጠራቅቁን ጠረኑን ተከትዬ ወዲያው ወዲያው የሚያንዣብብኝን ነገር መረጃ አስጣለሁኝ። ያን ጊዜ የነበረኝ ቅጥል ሥም  የጉራጌ እና የኦሮሞ ቡችላ ስለነበር አጥቂዎቼ የማይመጡበት ሁኔታ አልነበረም። 

እዚህም የተሰጠኝ ደግሞ የኦነግ አባልነት እና ኦርቶዶክስነት ነው። እኔ ግን ያን ጊዜም እውነት ነው ብዬ እማምነበትን መወገን ነው አሁንም እምጋፈጣው እውነት ነው ብዬ እማምነበትን የራሴን እምነት ነው እማራምደው። እነሱ እንደሚሉት ገብሬ ቢሆን ኖሮ ሥርጉተን እንደ ልጁ አድርጎ ባልቀረጻት ነበር። ሥርጉተ አማራ ገብሬ ጉራጌ ነው። ሌሎችም እንዲሁ። 

የዛሬን አያድርገው እንጂ እንደ ወጣት ፖለቲከኝነቴ ያን ጊዜ በዛ ድፍረት ልክ ግን ከላይም ከጎንም በሁሉም ዘርፍ ህይወቴን ከነፍሳቸው በላይ የሚጠብቁልኝ ምርጥ ብቁ መሪዎቼ ስለነበሩኝ በዛ ጥንካሬዬ ልክ መቀጠል ችያለሁኝ። አባቴም በሳል ፖለቲከኛ ነበር የምክር አገልግሎት ይሰጠኝ ነበር። እስኪያስገድሉት ድረስ። እህቶቼም ጋርዶቼ ነበሩ። ሌላው ቀርቶ  ለእረፍት ሰዓት እንኳን ከቤት ነው ሁሉ ነገር ተሰናድቶ ነበር የሚመላለስልኝ። አንበሳ የሆኑ እህቶች ስላሉኝ። 

አሁን እንዲህ እንዳአሻኝ እምሳተፈው በቅርቤ እህቶቼ ስለሌሉ ነው እንጂ ቢኖሩ መከራ ነበር። እነሱ የነፍሴ ጌቶች ናቸው። አናብስት እህቶች ናቸው ያሉኝ። አሁን አሜሪካ ነው የሚኖሩት። 

የገጠር ቤተሰቦቼም እንደዚሁ ናቸው ወያኔ ሃርነት ትግራይ ጎንደርን ሲቆጣጠረው አንዱ አጎቴ በእግሩ ከደባርቅ ፈረስ ይዞ ጎንደር ሲገባ ሌላው አጎቴ ደግሞ በሌላው አቅጣጫ ደፍሬ የወስንኩት ጉዳይ ተቀብሎ የሆነውን ሁሉ አደራጀ። በዚህ ቅንጅት ነው እኔ ህይወቴ የኖረው። እና አሁን እኔ እጅግ በበዛ ፍቅር እምሳሳለትን ጋዜጠኛ ተመስገነን ሳስበው ይጨንቀኛል። አሁን ከሆነ የአብን አቶ ጋሻው መርሻንም እንዲሁ። ድፍረት መልካም ቢሆንም ጥላ ከለለ ሁነኛ ሰው ከሌለ ግን ተበጥሶ መቅረት ይቻላል።

                                                               የእኔ ድንግል ትጠብቅልኝ!


አቶ ምግባሩ ከበደም ያን ያህል እርግጠኛ ሆነው የልባችን ቁልፍ ያገኙበት ጥንካሬ የእኔ የሚሉት ሁነኛ ከሌላቸው ፌድራል ላይ እጅግ ከባድ ነው። ሊቀዘፉ፤ ሊቋራጡ፤ ሊቀጩ ይችላሉ። የእሳቸው አካሄድ የሚሳጋው ሁሉንም ነው።  አሁን ወ/ሮ አዳነች አበቤ እና ሌሎቹ እኩል ጋሻ የላቸውም። 

በፖለቲካ ህይወት ውስጥ በራስ ተፈጥሮ ውስጥ ለመዝለቅ ብርት መዝጊያ የሚሆን ክንድ ያስፈልጋል። በስተቀር መቀንጠስ አይቀሬ ነው። እኔ በዛ ያህል ጥንካሬ እስከመጨረሻው የተጋሁት ምክንያቱ ለጉልበታም አቅሜ በሁሉም መስክ ጠበቂ ነበረኝ። 

የእስልምና ዕምነት ተካታይ ሃጅዎች፤ አርት ዓይናማ ሊቃውነተ ቤተክርስትያናት ቤተሰቦቼ ደግሞ የድዋ እና የጸሎት አጥር ቅጥር ይሰሩልኝ ነበር። በመደበኛ። ያ ነበር የእኔን ነፍስ አሰንብቶ እዚህ ያቆዬው። የትም ቦታ ጠባቂ ስለነበረኝ ነው። ለአጭር ጊዜ ስብሰባ እንኳን ጠንቃቆች አሰናድተው ነበር የሚልኩኝ እንኳንስ ለረጀም ጊዜ ኮርስ። አያምኑኝም ነበር።

አንድ ጊዜ አስታውሳለሁኝ የመንደር ምስረታ ጋይንት ነበር ምድቤ። የቡድኑ መሪያችን ለስብሰባ ማዕከላዊ ኮሚቴ ነበር። ስለዚህ ቡድኑን መርቼ የሄድኩት እኔ ነበርኩኝ። ከዛ ሊቦዎችን፤ ወረታዎችን፤ ደብረታቦር የፓርቲ አካላትን ሳላገኝ ሪፖርት ሳላደረግ ቀጥታ ወደ ጋይንት አመራሁኝ። ገበሬ ነፍሴ ስለሆነ ጋይንት ሳንገባ መንገድ ላይ አንድ ገበሬ መንደር በድንገተኛ ዘው አለን።

እዛ አምሮብን እንድናድር ፈለግሁኝ። ወጋቸውን አውደዋለሁኝ - ተፈጥሯዊ ነው። በተለይ ማታ እሳት ዙሪያ ከበን ቁጭ ብለው ሲወጉኝ ሌላ ዓለም ውስጥ ነው እምገባው። ጣፋጭ የሆነ የማይጠገብ ህይወት አሳለፍኩ የምለው ከገበሬው ጋር የነበረኝ ጊዜ ነው። እና ያለሁበትን ለማሳወቅ እንደዛሬው ሞባይል የለም። ከዛ እኒያ ቅዱስ ደግ መሪያዊ አባት ጓድ ገዛህኝ ወርቄ ሊቦ፤ ወረታ ደብረታቦር ሲጠይቁ አልመጣችም፤ ጋይንት ሲደወል የለችም። በቃ ታፍናለች ወይ ታግታለች በሚል እንቅልፍ አልባ ነበር ያደሩት እንደ ሥማቸው ወርቅ የሆኑት ጓድ ገዛህኝ ወርቄ።

ቢሮ እንደ እኛ ማትራሰ ነፍተው ነበር መሬት ላይ ነበር የሚያድሩት። ጎንደር የጦርነት ቀጠና ነው የነበረው። ሌሊቱን እንቅልፍ አልተኙም እኔ የጣፉሀኝ ቀን። የሚገርመው ጥዋትም በማለዳ አልሄድኩም ወደ ንፋስ መወጫ ከተማ። ልቀቁኝ አይልም ነበር እና የ ብጹዕኑ ሰፈር። አዬ ጋይንት ... እነመጋ ስማዳ ... ስዬቴ! 

አመሻሽ ላይ ንፋስ መውጫ ስገባ ቀውጢ ሆኖ ነበር የጠበቀኝ። ሳገኛቸው እንዳይቆጡኝ በህይወት መኖሬ አስደሰታቸው፤ በታከተ ድምጽ ነበር በፍጹም አባታዊ ሃላፊነት  እና ተጠያቂነት በተሰማው ድምጽ ያናገሩኝ። አንድ ጊዜም ጓድ ገ/መድህን እንዲህ አድርጌዋለሁኝ። ደባርቅ መግባት የነበረብን ቀን አንድ ቀን ሊያልፍብን ሆነ ጎንደር ካደረን የደቡብን ጉብኝት ጨርሰን ወደ ስሜን ነበር ጉዟችን። ቡድኑን እኔ ነበር የምመራው። 

ጎንደር ማምሻ ላይ ገባን ነገር ግን ሪፓርት ሳናደርግ ቀጥለን ወደ ደባርቅ አመራን። መንገዱ ሳይወጠር አንድም ጠበቂ ሳንይዝ። ወጣትነትን አስቸጋሪነትም ነው። ስንሄድ ደባት ላካላችን ሪፖርት ብናደረግ መልካም ነበር። ደባርቅ ነው የሥራ መነሻችን ስለዚህ ወደዛ  በቀጥታ አመራን። ጎንደርም ማለፋችን አያውቅም፤ ዳባትም አያውቅም፤ እራሱ አካሎቻችን ቢሮ አያድሩም ጉድብ ውስጥ ነበር የሚያድሩት። በዛ ድቅድቅ ጨለማ መንገድ ሳይወጠር ጥሰን ገባን። 

መቼም አትሙት ያለው ነፍስ ነው። ሌላው ቀርቶ የክ/ አገር ቡድን ሲንቀሳቀስ ስንሄድ በመኪና ስንመለስ በኤልኮፍተር ነው። ታማኝ የሆነ ነገር ስላልነበር። ደግነቱ ምንም ሳንሆን ገባን ደባርቅ። ሲሰማ እብድ ነው የሆኑት። የክ/ አገር የህዝባዊ ድርጅቶች እና የሙያ ማህበራት መሪዎች  እና አራት የክ/አገር አደራጆች ነበርን።  ወጣትንት የፖለቲካ ኪሳራውን ሁሉ አያሳያችሁም። 

አሁን ሁላችንም ብንታገት ምን ይኮን ነበር? ታላቅ ኪሳራ ነበር። ቁጧ ሸሽተን ነው። የተወሰን ቦታ ላይ ዘግይተን ስለጨረስን። እና ዛሬ እንዲህ ይተሳሰቡ ይሆን እላለሁኝ? እንዲህስ ራስን መማገድ ይነር ይሆን እላለሁኝ። 

ጓዶቻችን ጎንደር ደርሰው ወደ አውራጃቸው፤ ወደ ወረዳቸው ሲሄዱም መድረሳቸውን ማረጋገጥ ዋንኛ ተግባራችን ነበር።  ልክ እንደዛ አሁንም በህሊናዬ ውስጥ ከተመዘገቡት አንድ ብልህ ወጣት ጎድለውብኛል? እርግጥ የብአዴን ሰዎች ለእኔ ጓዴ ሊሆኑ ፈጽሞ አይችሉም። ነገር ግን የኦሮሞ ንቅናቄ እና የአማራ ተጋድሎ ባክኖ እንዳይቀር የተጉ  የአህጉር ባለውለታ፤ ባለታሪክ ዕንቁዬ ስለሆኑ ልናስብላቸው፤ ልንጨንቅላቸው ግድ ይለናል።

ብአዴን አንድ ሰሞን የብአዴን ማዕከላዊ /ቤት የገጠር ፖለቲካና አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አደርጎ መሾሙን አስደምጦን ነበር። ከዚህም ከፍ ባለ ሁኔታ ለብአዴን ጉባኤ ቃል አቀባይ ሆነው ጎላ ብለው ወጥተው ነበር። አማራ መሬት ላይ እንዲህ ዓይነት ወጣት በስንት ፈተና አልፎ ታዬ ብለን እስኪገርምን ድረስ። እንዴት ሾልኮ ከዚህ ደረስ የሚለው የህሊና ጥያቄ ዛሬም መልስ አላገኘም።

በኦርቶዶክስ እና በአማራ ሊሂቃን የደረሰውን የገዘፈ የ27 ዓመት መከራ ለኖረበት ሰው ብርቃችን ነበሩ እኒህ ውስጥ። ግን አሁን ሥማቸው ከተሰወረ ቀናት እያስቆጠረ ነው። ያያችሁ የሰማችሁ መረጃው ያላችሁ ሹክ ብትሉኝ መልካም ነው። 

በዬዕለቱ ስጋቴ እዬጨመረ ስለሆነ። የስሜን አሜሪካ ጉዞ በፍጹም ነፍሴ የቀፈፈው ጉዳይ ነበር። ብዙ የመንፈስ ኪሳራ ነው የሚያስከትለውና። እምጽናናው ፈልፋዩ ሹክሹክታ ምንም ዘሃበሻ አለማለቱ ነው …. በተረፈ ግን በዘለቄታም የአቶ ምግባሩ ከበደ ሁኔታ ልብ የሚያስጥል አይደለም። 

ጽኑ አቋማቸው ከውስጣቸው የቆረጠው ሰብዕናቸው እና አማራነታቸው ስጋቴን ጣሪያ ቢያስነካው ግድ ይሆናል። አፈላልጉኝ ያያቸሁ የሰማችሁ ወገኖቼ … ጨንቆኛል።

ዶክተር አባቸው መኮነን፣አቶ ምግባሩ ከበደ እና አቶ ገዱ አንዳርጋቸው 
በሰሜን አሜሪካ ያደረጉት አስገራሚ ንግግር

https://www.youtube.com/watch?v=3B7XKvkgWOU

በአዲስ መልክ የተዋቀረውን የማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትን የአመራርነት አቅምን በማጎልበት የክልሉን ሁለንትናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ እየሰራ መሆኑን አዴፓ አስታዎቀ

https://amharic.voanews.com/a/amhara-regional-parties-11-13-2018/4656998.html


ህዳር 13, 2018

አዴፓ እና አዴኃን በጋራ ለመሥራት ተስማሙ

https://www.youtube.com/watch?v=SCEGAt799CU

አቶ በረከት ለሰነዘሩት ክስ፣የብአዴን ጽህፈት ቤት ኃላፊና የፖለቲካ ጉዳዮች ተጠሪ አቶ ምግባሩ ከበደ በኢሳት ምላሽ ሰጥተዋል

https://www.youtube.com/watch?v=JhJP4QWThXI

ዶክተር አባቸው መኮነን፣አቶ ምግባሩ ከበደ እና አቶ ገዱ አንዳርጋቸው በሰሜን አሜሪካ ያደረጉት አስገራሚ ንግግር part one

 

„አማራነት ይከበር!“
የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።