የሐሴት ፋናዬ።
የሐሴት ፋናዬ።
ከሥርጉተ ሥላሴ 13.06.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።)
„በዚያ ቀን እንዲህ ይሆናል ታላቅ መለከት ይነፋል።“
(ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፯ቁጥር ፲፫)
ኑሪልኝ እናቴ የተስፋ መንበሬ
ኑሪልኝ እማማ የነፍስ ዝማሬዬ፤
ኑሪልኝ ልዕልቴ የፍቅር ዝናዬ
ኑሪልኝ ልዕልቴ ማዕረግ ሽልማቴ
ኑሪልኝ ንግሥቴ የመኖር አድባሬ፤
ኑሪልኝ መሆኔ የሰው ሰውነቴ
ኑሪልኝ ዕንቁዬ ሚስጢር ገበታዬ
ኑሪልኝ ክብረቴ ፍቅር መስታውቴ
ኑሪልኝ ኢትዮጵያ የሐሤት ፋናዬ!
የኔዎቹ መሸቢያ ጊዜ። ኑሩልኝ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ