እቴ ሆይ!
እቴ ሆይ!
ከሥርጉተ ሥላሴ 14.06.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።)
„ሕዝቤ ሆይ ና ወደ ቤትህ ግባ።“
(ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፭ ቁጥር ፳)
እቴ ሆይ! ሙሽሪት እሸት አማራችቱ
እቴ ሆይ! ቅዲስቲት ፍቅር ናፋቂቱ
እቴ ሆይ! ህብሪቱ የዕምነት እልፍኝቱ
እቴ ሆይ! ፍቅርተ የማተብ ርቱ
እቴ ሆይ! ቀዳሚት የመሆን ሊቂቱ
እቴ ሆይ! ቅኒቱ የዘመን ፍቱኒቱ
እቴ ሆይ! መቻል ነሽ የሥርዬት እትብቱ።
እቴ ሆይ! ድሪዬ ነፍቆት አራሽቱ
እቴ ሆይ! መዲና ህቭር ፈታይቱ
እቴ ሆይ! ምግባሯ ድምቀት አዳይቱ
እቴ ሆይ! ሁሉዬ ትዝታ አብሪቱ
እቴ ሆይ! ግሎባል ሥልጡን እሜቴይቱ
እቴ ሆይ! ማንጠግቦሽ ትዝታን ሳይቱ
እቴ ሆይ! ምንገዶሽ ሥልጡን ዘማናይቱ!
- ሥጦታ ለውቢት ለአዲስ አባባ ይሁንለኝ።
የኔዎቹ ኑሩልኝ። መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ