ትውውቅ ተልግመኛው ፖለቲካ።

       ልግመኛው ፖለቲካ።
                                       ከሥርጉተ ሥላሴ 13.06.2018 (ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።)

          „አቤቱ አንተ አምላኬ ነህ፤ ድንቅን ነገር የዱሮ ምክርን በታማኝነትና በእውነት አድርገሃልና ከፍ ከፍ አደርግህ አለሁ። 
                           ሥምህንም አመሰግንህ አለሁ።“ (ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፭ ከቁጥር ፩ እስከ ፪)

ልግመኛው ፖለቲካ ርህርህና፣ አርቆ ማሰብ አልፈጠረለትም። አልሰራለትም። 

የኢትዮጵያው ፖለቲካ መልኩ ልግመኛ፤ ቁመናው ልግመኛ፤ አቋሙ ልግመኛ፤ መንፈሱ ልግመኛ፤ ውስጡ ልግመኛ፤ ቅርጹ ልግመኛ፤ ፎርሙ ልግመኛ። አንጀቱ ልግመኛ። ልቡ ልግመኛ። ኩላሊቱ ልግመኛ። ህሊናው ልግመኛ። ፊንጢጣው ልግመኛ። ጉበቱ ልግመኛ። ፊኛው ልግመኛ። ህሊናው ልግመኛ። ጭንቅላቱ ልግመኛ። አንደበቱ ልግመኛ። ልሳኑ ልግመኛ። ዓይኑ ልግመኛ። ጆሮው ልግመኛ። እጆቹ ልግመኞች፤ እግሮቹ ልግመኞች። ክናዱ ልግመኛ። ኳቴው ልግመኛ። እርምጃው ልግመኛ። ዕይታው ልግመኛ። 

ተስፋው ልግመኛ። ምኞቱ ልግመኛ ግን ባለትልቅ ራዕይ ራዬኛ። ይቻላል በልግም ተባዝቶ በልግም ውጤት ቀመር። ይሆናል በልግመት ተቦክቶ በልግመት ተጋግሮ ማባያውም በልግመት ተቁላልቶ በልግመት ፌርሜሎ ተጥዶ ትልቁን ራዕይን ያሳካል ሲባል በምንም ተባዝቶ ሟርተነን አውግቶ ከምሾ ተጋብቶ፤ ደመርን ቀጥሮ፤ ሳቅነን ፈርቶ፤ ፈገግታን አጣውሮ ደስታን አጨልሞ ተስፋን አስጨንቆ ጭንቅትን ደግሶ ተስፋ ቆራጭነትን ዲል አድርጎ ድሮ፤ አያሆንምን ኩሎ፤ አያቻልምን ግጥግጥ ጠርቶ አይነን በርግጫ ቅልቅል ነፍሱን አጥፍቶ „ትልቋ ኢትዮጵያን“ ያልማል። ቧልተኛ በሉት ልግመኛውን የኢትዮጵያ ፖለቲካ ፈሊጥ።

ልግመኛው ፖለቲካ ሱቅ በደረቴ አለው፤ የጅምላ፣ የችርቻሮ መደብሮች የክት እና የዘወትር አለው። ታዲያንላችሁ ሲመትር በልግመት፤ ሲለካ በልግመት፤ ሲሸነሽን በልግመት፤ ነዶውን ተርትርትሮ ተርትሮ፤ ቆራርጦ ቆራርጦ ሲሳፋውም በልግመት ሲለብሰውም በልግመት፤ ሲያወልቀውም በልግመት፤ አረጀ ብሎ እንደ አልባሌ ሲወረውረው ደግሞ በልግመት እራስ እግሩ በልግመት ተደምሮ፣ ተቀንሶ፣ በዜሮ ቁልቁሊት የሚያሰኘው ጉዳጉድ … ይህም ሆኖ ለሰላም፤ ለፍቅር፤ ለህግ የበላይነት መቼም አይታክተው እኔ እንጃ ልቡ በዬሰከንዱ ደጭ ደጭ እንደሚል አስባለሁኝ የእጬጌው ዴሞክራሲ ነገር፤ በቃ የጥርስ መፋቂያ ሆኗል። አያልቅበት ልግመኛው ፖለቲካ እሱንም እኮ ይመኛል፤ ድንቄም። … እጬጌን ዴሞክራሲ? ህም።

በማይሆን ተባዝቶ አይሆንምን ደምሮ፤ ወልደ ግራን አክሎ ይሆናል ተጠርጥሮ ግን ትልቋ ኢትዮጵያ ተሰልቶ? ይሄው ነው ልግመኛው የኢትዮጵያዊ ፖለቲካ ዘመናችን ብልት አድርጎ ሲያነቅዘን የኖረን። ከመልካምነት ጋር አንብጓሮ ፈጥሮ፤ ከቅንነት ጋር ጉግስ ገጥሞ፤ ከሴራ ጋር እልፍኙን ሰርቶ፤ ከሸር ጋር ማጫ ተማትቶ አቅምን ቀብሮ የሚያውል ግን የታላቋ ኢትዮጵያ ህልመኛ።

መልካምነትን፤ ደግነትነት፤ ሰዋዊንትን፤ እኛዊነትን ፈርቶ ግን ደግሞ እኔ ነኝ አባዎራው ብሎ ሳይሆንበት ሌላው ሲሆንበት ደግሞ እርር ብሎ ተክኖ በግኖ መረቡን ይዘረጋል ፍርሻን አስልቶ እንደ ለመደበት ቀብር ለማዋል ቸርነትን እና ደግነትን። ልግመኛው ፖለቲካ አርቲውን፣ ቡክቡካውን፣ ነጭ ሪያኑን፣ ሰንደሉን፣ ጠጅ እሳሩንም ጭስስ ቢልለት በጅ አይልም ሞገደኛ ስለሆነ። ሞግዶ ገድግዶ መንገድ ሲዘጋ ከራርሞ አሁን አናት ኢትጵያን በቃሽ ሲላት ደግሞ አማኑኤል ፍርሻን መሬት ደብድቦ ናልኝ ሲል ከራርሞ አሁን ደግሞ አሰጋኝ ምንትሶ ቅብጥርሶ ይለናል … የለመነው አይደል፤ ስንጥር ሲለቃቅም ውሎ ያደረው ለዚህም አይደለም? የእናት አገር በሰላም አድራ ውላ ልጆቿ እፎይ ማለታቸው እኮ በቅናት ነው ልግመኛውን ቦለቲካ ሲያብጠለጥለው የከረመው።

ዓይኔም አያይ ጆሮዬም አይሳም፤ አልሰማሁም አላዬሁም ብሎ ጓሮ ለጓራ ቢትበሰበሰም ኢትዮጵያ ወገኖችን ከእስር አስፈትቶ እንደ እናት እቅፍ ክውን አድርጎ የበተ ዘመዱን አብሮ እዬተጫወተ አገር የሚገባ መሪ አገኘች እምዬዋ እቴጌ ኢትዮጵያ። ወይ ጉድ አይደከመውም ይሄ ቅዱስ ሰው ከካይሮ መልስ ቀጥ ብሎ ደግሞ ሄዶ አስታዋሽ አልባ ፍዳውን በሳውዲ የከፈለ የነገ ቅዱስ ተስፋን እንኳን ለአገርህ መሬት አበቃህ በማለት፤ ያቺን ከልታሜን እምዬን እናትንም አይዞሽ ብሎ እሱም መች ሲበቃው ደግሞ በግፈኞች ዓይኑን ያጠውን ያን ቀንበጥ ብላቴና ደግሞ ለማዬት ጎራ ብሎ ድብስ ድበስብስ አድርጎ ፍቅሩን ረድኤቱን ስጥቶ አድንልኝ ልጄን ብሎ አማትቦ፤ ምህረት ለልጁ ተማጽኖ አባትንም ጠጋ ብሎ አረጋግቶ ሁለቱንም የዘመን መከረኞች በመንፈሱ ጸንሶ ሱባኤውን ሰንቆ ተመስገን ሸልሞን ውሎ እንዲህ ያድራል።

ልግመኛው ፖለቲካኛማ ትግረኛ ሲናገር ስለምን? ኦሮምኛ ሲናግር ስለምን? አማርኛ ሲናገር ካይሮ ላይ ደግሞ ስለምን ብሎ ይሆን? እኔ እህታችሁ ልባሟ ቅርቅር ስለሰደረኩኝ አሁን ያለውን ብዙም ባልስማ ከቤተ ሳተናው፤ ከቤተ ዘሃብሻ እና ሰንበት ላይ ደግሞ ከቤተ ኢትዮ ሚዲያ ሳነብ ቅኖቹ እያነሰቡኝ ግን የአብይ ጉዞ ደግሞ መልካምነት እዬፋፋ አያለሁኝ። አይዋ ወያኔ ሃርነት ደግሞ ተራራዬ ትንሽ ዝቅ አለ ብሎ በግራ በቀኝ ጠብ ጠማኝ ብሎ አገር ምድሩን ያመሰዋል። ተመስገን ማለት ሲገባው። ገራሚው ነገር እሱን ሲወቁ የነበሩቱ አብይን አንይህ ብለው ከእሱ ጋር ተዳብለዋል። ፍቅሩ ከዘለቀ። ደጋፊዎችም አሉለት የልግመኛው ፖለቲከኛ የጽዋ ማህበርተኞች … 

ውይ ተዚህች ላይ አንዲት ወርቅ ነገር … እነ አያልቅበት የልግመኛው ፖለቲካ ተንታኝ እና በታኞች ብጥብጥ አሁን ስለተደመጠ በቃ ላሜ ወለደች ነው። እንግዲህ መሬት እዬደበደቡ ይህን መልካም ሰው እባክህን … ማለትም አይቀሬ ነው …
ልግመኞቹ ለግመው አስለገሙን፤ እንዳናዳማጣቸው ጦር ጠማኝ ስለሆኑ ተፋታን። አሁን እኔ የረድኤቱን ቅድስና ከማድመጥ ውጪ ምን በወጣው ህሊናዬ ይባትል? ንጽህናን ዘመን ሲፈቅድልኝ የጥበበኛውን ኢትዮጵያዊ ስለሞን ቤተ መቅደሳዊ ጉዞ ብቻ ነው የማዳምጠው … በቂ ጊዜም በቂ እረፍትም ሙሉ ጤናዬንም አገኘሁኝ። ያን ልግመኛ ኢትዮጵያዊ ፖለቲካ በኪናዊ ጥበቡ ፈጣሪ አምላክ አላቀቀኝ ገለላገለኝ … ተመስገን!

ልቤን ሲያውልቀው ሲያታክተው ነበር የከራራም የልግመኛው ፖለቲካ ግብረ ሰላም፤ እንግዲህ ደግሞ ማህል ቤት ሲቀር ሳብያ እየፈለጉ ምህረት ይጠይቁ እነ አቶ ማይክ፤ አይዋ ብራናን፤ እትዬ ብዕርንም አይቀርብኝ ብላ ጎንበስ ወይ በርከክ ብላ ላወከችው ሳለሙን ለቀማቸው ይቅርታ ትጠይቅ … ሰርቀውናል እኮ በዬተራ ተራረባርበውብናል … የሽታሽቶ ... የአሁኑ መንገድ ተቀልብሶ አቅጣጫ የለሽ ጉዞ ቢጀመር በፆም በጸሎት የተባጀበት ነው ....

ይልቅ ዛሬ ሟርተኞቹ ያሹት የፈለጉት ዛሬ ስለሆነላቸው የስለት ያስገቡ፤ ሰንጋም ይደርድሩ፤ ፈጣሪያቸውን በርከክ ብለው ያመስግኑ … ቀኒት በሰላም ውላ ማደሯ ህመማቸው ስለነበር …

አቤቱ ፈጣሪዬ ሆይ! የልግመኛውን ፖለቲካ ባለጽዋወች ጠሎት አደራ እንዳትሰማ!
አቤቱ ፈጣሪዬ ሆይ! ያቺን የአስራት አገርህን መከራ ታውቀዋለህ እና ጆሮህን ዘንበል አድርገህ አዳምጥ! 
ልጆቿ በሰላም ውለው እንዲገቡ ጠብቅልኝ! 

የኔዎቹ ጠሎታችሁ ከልግመኛው ፖለቲከኛ አትቀላቅለን በቅንነት መንፈስ ጥመቀን ይሁን እሺ …

መሸቢያ ጊዜ። ኑሩልኝ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።