ክቡር ፈቃዱ ተክለማርያም።

  !እባክህ አንጣህ?
                                 ከሥርጉተ ሥላሴ 15.03.2018 (ከጭምቷ - ሲዊዘርላንድ።)

ብርቱ የሆነ እርሱ ታላቅ ሥራን በእኔ አድርጓልና፤ ሥሙም ቅዱስ ነው። ምሕረቱም ለሚፈሩት ከትውልድ ትውልድ ይኖራል።
              ስለዚህም ምክንያት ፍጥረት ሁሉ ያመሰግኑኛል” (ሉቃ. ምዕራፍ ፩፥ ከቁጥር ፵፱ ፶፩)

!እባክህ አንጣህ?
እምዬ ትጠጋህ
ድንግል ትዳስስህ
እሷ ትሁንልህ
ምህረቷ ይዳብስህ።

!እባክህ አንጣህ?

ምልጃዋ ይሁንህ
አለሁህ ትበልህ፤
ችልህ ውስጥህ
የዕምነት ደግነትህ።

!እባክህ አንጣህ?

ትኑርን ነፍስህ
ይኑርልን ጸጋህ
ይሁንልን ግርማህ
ማቱሳላ ዕንቁህ።

!እባክህ አንጣህ?

ፈቃዱ ይሁንህ
ለእኛ ሲል ያኑርህ፤
ትጠብቅሃለች የተስፋ ሐገርህ
የንጋት መንበርህ
የምህረት አድባርህ፤
ድንግል አደራሽን
እናቴ አደራሻን - እንዳታሳፍሪን፤
ቅዕባሽ ይሁነን - ስለእኛ ሁኝልን
ቀድመሽ ተገኝልን፤
ቸሩነ አብስሪን።
  • ·         ርኩዝ።


„ከፈቀዱ ተ/ መርያም ጋር እንጨዋወት።“
„Ethiopia: በአርቲስት ፍቃዱ ተክለማርያም የህክምና ጉዳይ ላይ የተሰጠ ጋዜጣዊ መግለጫ“

  • ·         ለዬኔዎቹ ቅኖቹ።

ጥበብ አባቱ፤ ለዘመን ዋርካው ለአርቲስት ፈቃዱ ተ/ ማርያም - ይሁንልኝ። ዝብርቅ ባለ በመረባበሽ ስሜት ነው የሠራሁት።
             ውስጤ የሚለኝን ሁሉ ለመግለጽ አቅም አነሰኝ። ሁመናዬ ተረበሸ። (15.03.2018 ዙሪክ.  15.38)                                                                        
           የእኔ ድንግል፤ እናቴ፤ አጽናኝዬ፤ ሁነኛዬ አብራው ሆና አራሷ ተገኝታ የምሥራቹን ዜና ታሰማን። አሜን!
           አባታችን ቅዱስ እግዚአብሄርም ምህረቱን ያሰማን። አትያዝ አይባልም፤ ምህረትህን እንጂ …
           እግዚአብሄር ይስጥልኝ።






አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።