ተፈጥሯዊ አቀባበል።


      ተፈጥሯዊ             አቀባበል።
„አንተ ፊቴን እሹት ባልክ ጊዜ 
አቤቱ ፊትህን እሻለሁ፤
ልቤ አንተን አለ።“ 

መዝሙር ፳፮ ቁጥር ፰
ከሥርጉተ©ሥላሴ 
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ
08.11.2018
  • ·    መነሻዬ።

Ethiopia: የፈረንሳይ ወጣቶችንግስታቸዉንብርቱካን ሚደቅሳ በደመቀ ሁኔታ ተቀብለዋታል!!

ዛሬ ክብርት ዳኝ ብርቱካን ሜዲቅሳ ኢትዮጵያ ገብታለች። የመንግሥት አቀባልን ፎተውን አይቸዋለሁኝ። እኔ የመሰጠኝ ግን የወጣቶቹ ልዩ የቀይ ምንጣፍ አቀባበል ስለሆነ ትንሽ ልልት ወደደኩኝ። ባጋጣሚው አንዳፍታንም ላመስግን ለቅንብሩ ጥራት ሙሉውን ተከታትዬዋለሁኝ።

ክብርት ዳኛ ብርቱካን ሚደቅሳ ውስጧን አቅሟን ጥረቷን በቅንነት ለማበርከት አገር እንደገባች አምናለሁኝ።

እያንዳንዱ እንቅስቃሴዋ የጥጋናዊ ለወጡን በመደገፍ፤ በማገዝ፤ በማበረታት ጥንካሬ በመስጠት ላይ እንደምትተጋም አስባለሁኝ አምናለሁኝ። 

ለረጅም ጊዜ በአካል እንዲህ ልናያት ባለመፈቅዷ ብከፋባትም ዛሬ ሳያት ግን ሰውነቷም መንፈሷም ሙሉ መሆኑን ለመመልከት ችያለሁኝ።

የሆነ ሆኖ ዛሬ በነበረው የጀግኖቹ የፈንሳይ ለጋሲዮን ኢትዮጵያዊ አንበሶች የአቀባባል ዝግጅት ላይ ቁምነገሩ ተፈጠሯዊ መሆኑ ነው ቀልቤን ስቦት ብዕሬን እንዳነሳ ያደረገኝ። 

በነገራችን ላይ በድምጽ እማውቃቸውን ወላጅ እናቷን መኪና ውስጥ ወ/ሮ አልማዝን በጨረፍታ ለማዬት በመቻሌ እንኳን ለዚህ አበቃቸው ማለትን እሻለሁኝ። የኢትዮጵያ እናቶች እንዲህ ዓይነት ልጅ ሲወልዱ ፈተናውም የእነሱ ነውና። እሷንም እንኳን ለአገርሽ መሬት በሰላም አበቃሽ ማለትን እፈቅዳለሁኝ። ይህን ሳያዩ ያለፉት እን ጀግኒት ሽብሬ ደሳለኝ ሲታሰቡ የእሷ ልዩ ዕድል ነው። ተጨማሪም የዘመን ሽልማት ነው። ሽልማቷን እንደማታባክንም ተስፋ አደርጋለሁኝ።

ወደ ቀደመው ምልሰት ሳደርግ ለብርቴ ቦዲ ጋርድ አላስፈለጋትም፤ ለብርቴ ጠበቂ ወታደር አላስፈለጋትም፤ ለብርቴ የደህነነት ሰው መቅጠር አላስፈለጋትም፤ ጠባቂዋ፤ ዘበኛዋ የህዝብ ፍቅር ጠበቃት፤ ተንከበከበት፤ አጀባት፤ አከበራት፤ አደመቃት። ተፈጥሯዊነቱ ይህ ነው ለእኔ።

በዚህ የአቀባባል ዝግጅት ዕድሜ፤ ፆታ፤ ሃይማኖት ሳይል ከአዛውንት እስከ ታዳጊ ወጣቶች ነበሩበት። አብሶ የሴት ወጣቶች እና የታዳጊ ወጣቶች በርከት ብለው አቀባበሉ ላይ መገኘታቸው ልቤን ነክቶታል። 

ይህ አቀባባል አብነቱ ነገን ለሚረከቡ ወጣቶች አብሶ ትርጉም ባለው አገራዊ ጉዳይ ላይ ከመጋቢት 24 ቀን 2010 በፊት ተገፍቶ በነበረው የሴቶች አቅም ላይ ጉልበት ይኖረዋል።

የሴቶች በሁሉም ቦታ በርከት ብለው መገኘት ጠቀሜታው ለአገር እና ለትወልድ ነው። ብቻ ረቂቅ ነው ትርጉሙ። ዛሬ እጅግ ብዙ ሴት ሊቃናት ሥልጣን ላይ እዬወጡ ነው። እሷም ይህን ወርቃማ ዕድል አግኝታ ቤተኛ ለመሆን በመቻሏ ዕድለኛም ናት። እንኳንም ደስ አላት።

የፈረንሳይ ሌጋሲውን የሰንድቅ ዓላማ ብሄራዊ አንበሶች በቀይ ምንጣፍ ነው ተስፋቸውን የተቀበሉ። ይህ ደግሞ በልብ ውስጥ መኖርን ያመለክታል። በዬበራቸው ቁመው ሲጠብቁ የነበሩት የአካባቢው ነዋሪዎችም ፍቅራቸውን በተፈጥሯዊ ለዛ ገልጣዋል።

እኔ ደስታ የሚሰጠኝ፤ ሐሴት የማገኝበት ማናቸውም ግንኙነት እንዲህ ተፈጠሯዊ ሲሆን ነው። መሰናዷው ከልብ የሆነ በድንግልና የተከወነ፤ ያለተከፈለበት፤ ያለተነገደበት ከሆነ መንፈሴን ይገዛዋል። ፍቅር ሸቀጥ አይደለም እና።

ሰው ፈቅዶ ወዶ አምኖት እንዲህ ሲያደረገው ያስደስታል ተስፋም ይሰጣል፤ ነገንም ያሳምራል። ለዚህም የተበቃው በዚኸው ጥገናዊ ለውጥ ነውና እና ይህን አክብሮ መነሳት ከእያንዳንዱ በግል ከሁሉም በጋራ የሚጠበቅ መሰረታዊ ግዴታ ይመሰለኛል።

ሴቶች ጥበቦች ናቸው።
የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።