ልጥፎች

እውን ለውጡ በማሸንፍ ወይንስ በንቃቃት ላይ?

ምስል
ስቅዛት በፈቃድ። „ጋሜል። ቀበሮች እንኳን ጡታቸውን ገልጠው ግልገሎቻቸውን አጠቡ።             የወገኔ ልጅ ግን እንደ ምደረ በዳ ሰጎን ጨካኝ ሆነች።“                    ሶቆቃው ኤርምያስ ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፫ ከሥርጉተ©ሥላሴ 22.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ መነሻ። https://www.youtube.com/watch?v=3KaJ74W-az0 Ethiopia: በቡራዮ ከተካሄደው ጥቃት የተረፉ ዜጎች ፖሊስ ሦስት ቀን ሙሉ ስንጨፈጨፍ አልደረሰልንም                       አሜኑ! ይቻላል ወይ በጃዋርውያን/ በኦነግውያን መንፈስ አገር እየታመሰ?  እንዴት ናችሁ ውዶቼ አንድ ኢሜል አንድ ወዳጄ ላኩልኝ። እኔ እኮ መሬት ላይ የጋሞ አዛውንታት የሠሩትን ማቃለሌ አይደለም። ያ መልካም ነገሩ ኦሮምያ ላይ ካልሠራ ምንድነው ፋይዳው ነው ጉዳዩ።  እነኛ ቅኖች መበደልን በበቀል አለመመለሳቸው በፈጣሪ ዘንድ ያስደግፋቸዋል። ነገር ግን መንግሥት የተጠቀመበት የቄሮ ወንጀል እንዲሸፈንለት መሆኑ ነው  እኔ የማይመቸኝ፤ ሌላው አባገዳዎች ኦሮምያ ላይ ጉዳት ሳይደርስ ለቃችሁ ውጡ ማለታቸውን ከኦሮምያ የተፈናቀሉ የአማራ ልጆች ከ6ወር በፊት ገልጸዋል። አባ ገዳዎች እንደ ጋሞዎቹ መሆን ተስነቿው ነው የማዬው። አባ ገዳዎችም የኦነጋውያን መንፈስ እንጂ ለአብይ ካቢኔ ክብካቤያቸውን አላዬሁም። ቡራዩ ላይ አባ ገዳዎች የሉንም? ቢያንስ ሬሳ አስነስተው በክብር ለማስቀብር ምን አገዳቸው? ሞትስ ቢሆን ምን አለ ቢቀበሉት። ሰማዕትነት ነው። ሊቢያ ላይ አኮ አንድ ሙስሊም ሰማዕት ራሱን ቀራኒዎ አውሏል ከወገኖቹ ጋር። አባገዳዎች ከተጠቂዎች ቀደመው ቢሰው የአቡነ ጴጥሮስ ትውፊታቸውን ከወኑ ነበር

ጋሞዎቹ ደሞቼ የፍቅራዊነት መርሆ ወንጌልም/ ቁራዕንም ናቸው።

ምስል
ብልህነት እንደ ጅረት ደግነቱ፤  የውስጥነት አብነቱ ከእትብቱ። „የእግዚአብሄር ቃል ወደ እኔ እንዲህ ሲል መጣ፦---- የሰው ልጅ ሆይ የወይን ግንድ በዱር ዛፎች መካከል ያለ የወይንሐረግ ፣ ከዛፍ ሁሉ ይልቅ ብልጫው ምንድር ነው?“ ከሥርጉተ©ሥላሴ  21.09.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ጤና ይስጥልኝ ውዶቼ እንዴት አላችሁልኝ? ደህና ናችሁ ወይ። ከሰሞናቱ የህፃናት፤ የእናቶች መከራ ጋር ሰውነቴን እዝሎት ስነበት፤ ምግብም በወጉ ሳልወስድ መዳህኒት እወስድ ስለነበር ተጎዳሁኝ፤ ከሁሉ ግን እንቅልፍ አልቦሽ መሆኔ ሰውኔትን አደከመው። እናላችሁ እንቅልፍ አጥቶ የሰነባበተው አካሌ ከአቅሜ በላይ ሆኖ ዲሞ ወጣ እና የማለዳ ተለምዶዬን ከውኜ ገደም ስል ከጥዋቱ ሦስት ሰዓት (09.00) እንደኛው አቆጣጠር አስከ ምሽቱ 1.00 ሰዓት (ከ19 ሰዓት) የት እንደወደቀኩኝ ሳለውቀው ተኛሁኝ። የሬቻም እልቂት መልዕክቴን ለተባባሩት መንግሥታት ልኬ ቤት መጥቼ ልክ እንደ ዛሬው እንዲህ ሆኜ ነበር። አድካሚ ሰሞን ነበር ያን ጊዜም። አድካሚነቱ በመንፈስ ነበር፤ ተስፋ ሲዝል፤ ራዕይ ሲጠወልግ፤ ያመናችሁት ባመናችሁበት ተገኘም አልተገኘም ከእንባ ጎን የመቆም አቅሙ በታመነው ልክ አለመሆን ራስን ይፈትናል። እኔ „ለማውያን ነኝ“ ስል ሰዋዊነት እና ተፈጥሯዊነት ነፍሱን የገዛው መንፈስ ነው በሚል ነበር። የሆነ ሆኖ ውስጤ መወስን ባቀታው ወጀብ ሲንገለታ ነው የሰነባባተው፤ መታመንን ለመስጠት ቅንነት አስፈላጊ ቢሆነም፤ ቅንነት ተቀባዩ ዋጋውን መመዘን ሲሳነው ስስጥን ያዝላል። ሰላም የአንድ አካል፤ ፍቅር የአንድ ወገን ቅንነትም የአንድዮሽ አይደሉምና። ፍቅር ስትሰጥ ተቀባዩ ለመስጠት መፍቀድ ብቻ ሳይሆን በዛ ውስጥ መገኘት ግድ ይለዋል። ብ