ግን ዶር ዳንኤል በቀለ በህይወት አሉን? እስከመቼ ድረስ ይህን ኢ- ሰባዕዊ፦ ኢ- ተፈጥሯዊ ዬአረመኔ ሥርዓት አገልጋይ ሆነው ይቀጥላሉ? መቼ ነው የኃላፊነት መለቀቂያ የሚያስገቡት???? በጉጉት እጠብቃለሁ። ንስኃም፤ ፀፀትም።

ግን ዶር ዳንኤል በቀለ በህይወት አሉን? እስከመቼ ድረስ ይህን ኢ- ሰባዕዊ፦ ኢ- ተፈጥሯዊ ዬአረመኔ ሥርዓት አገልጋይ ሆነው ይቀጥላሉ? መቼ ነው የኃላፊነት መለቀቂያ የሚያስገቡት???? በጉጉት እጠብቃለሁ። ንስኃም፤ ፀፀትም።
ስክነት ስንቃችሁ የሆነው የቤታችን ቤተኞችእባካችሁ ሼር አድርጉልኝ። አመሰግናለሁ።
"አቤቱ የመዳህኒቴ አምላክ
በቀን እና በሌሊትበፊትህ ጮኽሁ፤
ፀሎቴ ወደ ቤትህ ትግባ፥
ጆሮህን ወደ ጩኽቴ አዘንብል፤
ነፍሴ መከራን ጠግባለች እና፥
ህይወቴም ወደ ሲኦል ቀርባለች እና፥
ወደ ጉድጓድ ከሚወርዱ ጋር ተቆጠርሁ፤
ረዳት እንደ ሌለው ሰው ሆንሁ።"
(መዝሙረ ዳዊት ፹፯ ከቁ ፩- ፬)
 










 
ለማከብረወት ለዶር ዳንኤል በቀለ የኢትዮጵያ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር።
አዲስ አበባ።





 
እኔ በምን ሁኔታ ላይ እንደምገኝ ድንግል ብቻ ታውቃለች። መከራን ገድሞ ማስተናገድ የፈተናወች ሁሉ ቁንጮ ነውና። የሆነ ሆኖ ዶር ዳንኤል በቀለ የዘመን መለወጫን በምን ሁኔት አከበሩ? ቀለል ያለች ጓዘ ቀላል ጥያቄ ናት። በዘመኔ ትዝ ሳይሉኝ ሁሉም አውደዓመቶች አልፈዋል። የዘንድሮው መርግ ነበር። ዕንባማ ተራራ።
እኔ አገሬን ከለቀቅኩ በቤተ - እግዚአብሄር ዓውደ ምህረት ላይ ከሚከበሩት በስተቀር አክብሬው እማውቀው ዓውደ ዓመት የለም። ያም ሆኖ ግን ቀኑም፤ ሌቱም፤ ሰከንዱም፤ ደቂቃትም መርግ ሆኖ ያለፈው የዘንድሮው ነው። መሸከም - አልቻልኩም። ማስታገስ - አልቻልኩም። ማስተባበልም አልቻልኩም። ማሰብም - ማስታወስም አልፈለግሁም ነበር ግን እንዴት ይቻል???? የአብይዝም የመቃብር ስፍራው፤ የአሳቻው የአብይዝም ሙሉ ካቢኔያችሁ ደግሞ ድልቂያ ላይ ነበር። ማህበረዕብን። ማህከነ። ተሳህለነ። እግዚኦ!!
#የሆነ ሆኖ! ዶር ዳንኤል በቀለ ሆይ!
ነፍሰወት - አለችን? ትርትር - ትላለችን? መክሊተወትስ አለን ከቦታው። ሲፈጠሩ ፈጣሪ ቀብቶ የሰጠወት የሰባዕዊነት ቀንዲላዊ መልዕክተኝነትስ አድራሻው ተሰወረ? ወይንስ ተሸጋሸገ? ወይንስ ተሰወረ? ወይንስ? ወይንስ?
ዶር ዳንኤል በቀለ ከእንግዲህ እንደ ቀደመው ጊዜስ አፈወትን ሞልተው "እኔ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ነኝ" ብለው መናገር ይችሉ ይሆን? እስከዛሬ ድረስ በልፋት፤ በድካም የገነቡት ሰብዕናወትስ ከእርስወ ጋር በውን ተዋህዶ አሁን አለን? ወደፊትስ ይቀጥላል ብለው ያምናሉን?
ለአንድ የሰባዕዊ መብንት ትጉኃን ይህ የሚደመጠው፤ ይህ የሚታዬው ሰቅጣጭ ፋሺዝም በትዳር? በዕውቀት? በኃላፊነት? በክህሎት፤ በፀጋ፦ መከበርን ያስቀጥል ይሆን? የውነት ምን እዬጠበቁ ይሆን?
ጹሁፋን በጥንቃቄ አክብሬ ለመፃፍ እዬሞከርኩ ነው። ውስጤ የሚለኝን ብጽፈው ከርቤ ነው። ውስጤ መግሏል። ከወር በፊት ያዬኝ ሰው ዛሬ ሲያኝ ይደነግጣል። መንገድ ላይ ያገኙኝ ሰወች ዛሬ ደነገጡ። ጥቁር አለበስኩም። ግን የውስጤ ምግለት ሁለመናዬን አሳጣው። ተቃጠልኩ። ተንገበገብኩኝ። ሙሉ ዕድሜዬን ለዚህ ነበር ብቻዬን ያን ሁሉ መከራ የተቀበልኩትን????
#ዶር ዳንኤል በቀለ ሆይ?
አሁን ይርዱኝ ብዬ አላመለክትም። እንዲረዱኝ ለምሻቸው የሆነውን በተጨማሪነት አስረዳለሁ። መከራ ስቀልባቸው መኖሬን እነሱም ያውቁታል። ለእርስወ ግን አቤት የምለው ከእንግዲህ የኢትዮጵያ የሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽርነት ከሳት የገባ ፕላስቲክ እንደሆነ ስለሚሰማኝ አለን ብላችሁ ብቅ ካላችሁ እሱ የበለጠ ሁለት ሦስትጊዜ ይገድለናል። ስለሆነም ስንብተወት ይናፍቀኛል። መቼ ይለቃሉ ፈቅደው ከኃላፊነተወት??? እኔን የሚሰማኝ ከተሰማወት ላስታውሰው ብዬ ነው።
ተቋመወት #ኤክስፓዬርድ አድርጓል። ተኗል። በኗል። አብይዝም በቁሙ አንድዶ ግርድም እንክርዳድም አድርጎታል። ለእኔ ፈርሷል ብቻም ሳይሆን #ነዷል። የትኛውም ሞተር መልሶ ሊያስነሳው አይችልም።
ይልቅ በሰባዕዊነት በሥሙ አይነገድ። ቀጣዩን የፀፀት፤ የንስኃ ዘመን እንደምን እንደሚያሳልፋ ፈጣሪ ይርዳወት። ለማህበረ ኦነግ ስውር የኢትዮጵያኒዝም ኃይጃክ የሰጣችሁት ሙሉ ድጋፍ ጉልበቱ፤ አቅሙ ይህን መርዛዊ፤ የበቀል ጭካኔ ተንበርክከን እንዝቅ ዘንድ ሙሉ ገቢሩን ፈጽሟል። ትወናው ይብቃ። መጋረጃው ይዘጋ። "እናቴ በእንቁላሌ በቀጣሽኝ" ቢሆን ኑሮ ተያይዞ እንዲህ ንደት ስንቅ ባልተሆነ ነበር። ሞቶም መኖር የማይቻል ሆኗል ተቋማችሁ። መራራ ስንብት ………
ከእንግዲህ እምጠብቀው የስንብት ጥያቄ ደብዳቤወትን ብቻ ነው። መሽቷል ግን በቀጣይ በተጨማሪነት አብረው እንዳይቀቅሉን ማገዶ አቅራቢ ባይሆኑ ምኞቴ ነው። የመጨረሻ መደምደሚያ ደብዳቤዬ ነው። ከሲኦላዊነት ማህበርተኝነት ያዳነኝ አምላክ የተመሰገነ ይሁን። አሜን።
ክቡርነተወትእስር ቤትከነፃነት ታጋዮች ጋር በነበሩበት ጊዜ ከእስር ይለቀቁ ዘንድ ZAU በሚባል የስደተኛ መጋዚን የፃፍኩትን በአባሪነት አያይዣለሁኝ። እስከ አሁንም እረፍት የለኝም። ያው ስጠራ እገላገላለሁ። ሙሉ ዕድሜዬ በዕንባ ተሸኝቷል።
የስልጤ ባለማተበኞች መከረኞችንም ፎቶ አክያለሁ። ይህ ኦክስጅን ሆኖ የኢትዮጵያ ሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ካስቀጠለ እዮር ይዳኜው። አሜን።
"አቤቱ ህግ ተላላፊወችን ጠላሁ።"
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
14/09/2023
መስከረም 3/2016
የፀጋዬ ራዲዮን እና የከበቡሽ ሚዲያ ዋና አዘጋጅ።
ሲዊዘርላንድ ቪንተርቱር ከተማ።


  • አስተያየቶች

    ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

    ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

    እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

    አብይ ኬኛ መቅድም።