የኢትዮ አፍሪካኒዝም ህሊና ፕ/ ማሞ ሙጭ አትዮጵያ መንፈስ ሰጥታናለች" ይላሉ ...

„ኢትዮጵያ መንፈስ ሰጥታናለች! ለዓለምም የመንፈስ ጸጋ የሰጠች አገር ናት!“


አባቶቻችን አንተን ተማመኑ፤ ተማመኑ አንተም አዳንህቸው።
(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፳፩ ምዕራፍ ፬)
ከሥርጉተ© ሥላሴ
2.07.2018
(ከገደማዊቷ ሲዊዘርላንድ።)

ኢትዮጵያ ካሏት ዓራት ዓይናማ ሊሂቀ ሊሂቃን አንዱ ናቸው። ኢትዮጵያዊነት ብቻ ሳይሆን አፍሪካዊነት ከሚንገበግባቸው ጥቂት የምርምር ሊሂቀ ሊሂቃን ቤተኛም ናቸው።

ችግሩ አለተጠቀምንብትም። ድህነታችን ማን ታቅፎ ይኑርልን? እኒህ እውቅ ኢትዮ አፍሪካዊ ሐዋሪያ እኛ ጥበባቸውና እና ዐውቀታዊ ክህሎታቸውን ባንጠቀምበትም ሌሎች ብልሆች ግን ከልጅነት እስከ ዕውቅት በአህጉራዊ እና በሉላዊ ጉዳዮች ላይ ሁለገብ ትውልዳዊ ድርሻቸውን ተወጥተዋል። በዕውቀታዊ ብቃታቸውም ተጽዕኖ ማሳረፍ የቻሉ ብርቅዬ ኢትዮጵያዊ ናቸው።

ፕሮፌስር ማሞ ሙጬ በማናቸውም አገራዊ ሆነ አህጉራዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ተሳትፎ የሚያደርጉ፤ ያደረጉም ቅን ሊቀ ትጉሃን ናቸው።
ቀደም ብዬ እንደገለጽኩት ህሊናችን እና መንፈሳቸውን ግን ዕውቅና ከመስጠት በታዕቆቦ የቆዬ ቢሆንም፤ ታሪክ ግን ምንግዜም ሲያስባቸው የሚኗሩ ባለውለታችን ናቸው።

የሆነ ሆኖ እኛ ባናውቅበትም አፍሪካውያን እንደ ልዩ ዓርማቸው የሚዮዋቸው፤ ልክ እንደ የቅኔው ልዑል ብላቴው ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን፤ እንደ የእግር ኳስ እስፖርት ልዑል አቶ ይድነቃቸው ተሰማ አፍካዊነትን አጉልቶ በማውጣት፤ ጉልበት እንዲያገኝ በማድረግ እረገድ ድርሳን የሆኑ የአፍሪካውያን የጸሎት መጸሐፍ ናቸው።

እኒህ ታላቅ ኢትዮ አፍሪአካዊ የኢትዮጵያኒዝም ፍልስፍናንም በልዩ ክህሎት አቅሙ በልጽጎ፤ ጎልቶ እና ጎልበቶ እንዲታይ ሙሉ ጊዜያቸውን በመሰጠት ላይ ይገኛሉ።

ትልቁ ጸጋቸው ዕውቀታቸውን፤ ተመክሯቸውን፤ ልምዳቸውን ለወጣቱ ለመስጠት የማይሰሰቱ፤ መንፈስን በጽኑ አህጉራዊና አገራዊ ፍቅር ለማነጽ ለጋስ የሆኑ ብጡላችን ናቸው።

ፕሮፌስር ማሞ ሙጭ በእውቀት ላይ የተመሰረተውን የህሊና ብቃታቸውን ሳይቆጥቡ ለኢትዮጵያዊነት የሰጡ፤ ለአፍሪካዊነት የሸለሙ ለዘመኑ ለአላዛሯ ኢትዮጵያ የኢትዮጵያዊነት በኽረ ጥዑም ፍልሰፍና ሉላዊ መልክ በመስጠት እረገድ የንጋት ኮከብ ናቸው።

ኢትዮጵያን ከነፍሳቸው ይወዷታል። አፍሪካንም እንዲሁ ከህሊናቸው ያፈቅሩታል። ኢትዮጵያዊነት እንደ ሃይማኖት፤ እንደ ታቦት እንደ መንፈስ ነው የሚያመልኩት ማለትም ይቻላል። ለዚህ ነው „ኢትዮጵያ መንፈስ ሰጥታናለች“ የሚል ጽኑ አቋም ያላቸው። ለዚህም ነው „ኢትዮጵያ ለዓለምም የመንፈስ ጸጋ አበርክታለች“ የሚሉት።
  
ፕሮፌሰሩ ለአፍሪካ ወጣቶች ያላቸው ሩቅ ህልም መጠነ ሰፊና ድርጁ ነው። አፍሪካዊነት በቃል ብቻ ሳይሆን መሬት የረገጠ በመሆን የከበረ ትስስሩ ቋሚ እና ህጋዊ የሆኑ የግንኙነት ተቋማቱ ከወረቀት ያለፈ፤ ነፍስን ከነፍስ በተለያዬ ሁኔታ ሊያዋድዱ የሚጋባቸው ክህሎቶች መፈጠር አለባቸው ባይ ናቸው።

ፕ/ ማሞ ሙጬ የአፍካኒዝም ጽኑ ተሟጋች፤ የኢትዮጵያዊነት ደግሞ የችሎት ብሩህ አደባባይ ናቸው።

አውሮፓውያን ባልነቁበት ዘመን አፍሪካ የራሷን የሆነ የህብረት፤ የአንድነት፤ የመተባባር ዓላማ ዬያዘች ቀደምት አገር ብትሆንም አውሮፓውያኖች ዘግይተው ጀምረው በሄዱበት የተግባር ክንውኔ ልክ አፍሪካውያን ድፍረቱ ስላልነበራቸው የተገባውን ያህል የአፍሪካኒዝም መንፈሳዊ ውርርስ ህሊና ገዝቶ፤ በሚያሰተሳስር ሁኔታ ዕድገት አላሰዬም ባይ ናቸው።

አሁን ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የያዙት መንገድ ይህን የፕሮፌሰሩን የልዩ ምህንድስና ሃሳብ ወደ ተጨባጭ ዕውነታዊነት የማሸጋገር እርምጃ ሊወሰደው ይችላል የሚል የግል ግምት አለኝ።

ፕሮፌስር ማሞ ሙጭ እሳቸው ባላቸው አቅም ሁሉ የሚደክሙበትን መንግሥታት ደግሞ ባላቸው ሥልጣን ከሃሳቡ ጋር ቢገናኙት፤ ቢያወድዱት ጽንሰ ሃሳቡ ወደ ተሻለ የድርጊት እና የምግባር ደረጃ ከፍ ሊል ይችላል ብዬ አስባለሁኝ።

ፕሮፌስር ማሞ ሙጬ በመግቢያቸው ሲጠቅሱ ዶር አብይ አህመድ የዘገዬ ዕሳቤ እንዳላቸው ጠቁመው አሁን ያለውን ጠንክራ መንፈስ ግን አክብረውታል።

እኔ ግን ምን አልባት ሊቀ ሊቃውንቱ ፕሮፌስር ማሞ ሙጬ ሥራ በዝቶባቸው ካልተከታተሉት በስተቀር የዶር አብይ አህመድ የኢትዮጵያንዝም ሆነ የአፍሪካኒዝም ህልም የቀደመ ነው ብዬ ነው የማሰበው። አንድ ሰው „ስለሰው“ ብሎ ከተነሳ ከብሄራዊውም ከአህጉራዊም ያለፈ ግንዛቤ እንዳለው ነው እኔ የማስበው።

በሌላ በኩል የዶር አብይ አህመድን የቀደሙ ተግባራት ላጠና አንድ ቅን ዜጋም ኢትዮጵያዊነት ከወደቁ ከመሸ በሆዋላ የተቀበሉት አለመሆኑን እጅግ ለማከብራቸው ለፕ/ ማሞ ሙጬ በዚኸው አጋጣሚ ላሳስባቸው እሻለሁኝ በአክብሮት እና በትሁት መንፈስ።

መረጃዎችም ቢጎጎልም ይገኛሉ። ያው ኢትዮጵያ የምታረምደው የ ኤትኒክ ፖለቲካ የግድ የተፈጠሩበትን ማህብረስብ ድርጅት አንዲጠጉ ሁኔታው ካስገደዳቸው ውጮ መንፈሳቸው ሰፊ እና ልቦናቸውም ብርሃናማ ነው።

ቀድሞ ነገር አፍሪካዊነቱ መንፈሱ ከሌላ የተባባሩት መንግሥታትን ጥሪ በቅንነት እና በታታሪነት ለመፍቀድም እጅግ ፈታኝ ጉዳይ ነው። ይህን በርዋንዳ አስመስከራዋል ጠ/ ሚር አብይ አህመድ፤ ይህም ብቻ ሳይሆን ግጭቶን በሰላማዊ መንፈስ ስለመፍታት በሠሩት ጥልቅ የመመረቂያ ጥናታዊ ጹሑፍ ላይም በጥልቅት ውስጣቸውን የሚያሳይ ሉላዊ ዕድምታ አለው። ይህንም በተወለዱበት ክ/ ሀገር በጅማ ከፋ ለገጠመው ሃይማኖታዊ ቀውስ ያስገኙት ፍሬ በራሱ ምስክር ነው።

በኢትዮጵያኒዝም ላይ ዝንጥል ግንዛቤ ያለውማ አይቀጥልም እኮ፤ ስንጥቁን ጠግኖ ቢጀምረውም ፈታኝ አመክንዮ ሲመጣ ፈተናውን መውጣት ስለሚሳነው ሾልኮ ነው የሚቀረው። በዬጊዜው የሚገጥመው ፈተናም ይሄው ነው። ህልማችን እና ህልመኞች ሳይገናኙ ዘመናት የተቆጠሩት በዚህው ጥገናዊና ጊዜያዊ የእውቅና አሰጣጥ ነው።

የሆነ ሆኖ ለንደኖች ቀንቷቸው በአሜኑ „እንደመር ፓለቲካ“ እኒህ ብርቅዬ ኢትዮ አፍሪካዊ ሊቀ ሊቃውትን በሰልፋቸው ላይ ጋብዘው ትንሳኤ ላይ ያለውን ብፁዑ መንፈሳዊ ሰናይ እንዲጋሩ፤ ኢትዮ አፍሪካዊነትን ፍልስፍና ቃለ ምህዳንን ለሰልፉ እንዲሰጡላቸው በመታደላቸው በውነቱ ሰልፉ በቅንነት፤ በንጽህና፤ በቅድስና የተዘጋጀ ስለመሆነ ሌላ ማስረጃ አያስፈልገውም።

ውዶቼ ፕሮፌስር ማሞ ሙጬ ፍልስፍናቸው ትንሽ ከበድ ይላል። ግን ደጋግማችሁ ስታዳምጡት ይረዳችሁዋል ብዬ አስባለሁኝ።  

ለንደኖችም ተደምረዋል Ethiopian in London supporting Dr. Abiy - Part 4

በሌላ በኩል በብሄራዊም ሆነ በአፍሪካም ደረጃ አሁን ያለው የዶር አብይ አህመድ አዲስ መንገድ ለፕሮፌስር ማሞ ሙጭ የቀደም የአፍሪካኒዝም ተሃድሶ ጥልቅነት ጥረት ጋር ብርቱ መንፈስ ጋር ዘመን እንዲህ በሥርዓት ተክሊል ሲያጋባው ደግሞ ፕ/ ማሞ ሙጭ ምን ያህል ቅን ኢትዮጵያዊ፤ ምን ያህል ደግ አፍሪካዊ፤ ምን ያህል ለኢትዮ አፍሪካኒዝም ሩህሩህ ነፍስ እንዳላቸውና ቅርብ እንደሆኑ ፈጣሪ በጥበቡ ገልፆታል።

በዚህ ዓመት ፕሮፌስር ማሞ ሙጭ ጎንደር ከተማ ላይ ከአማራ ብዙሃን ሚዲያ ጋር በነበራቸው ቆይታ የአድዋን ድል በሚመለከት ያላቸውን ሰፊ ፍልስፍና በራሱ አንድ የትምህርት ተቋም ነበር ማለት ይቻለኛል።

እኔ እንዲያውም የአድዋ ድል እራሱን የቻለ የትምህርት ሥርዓት ሊቀረጽለት እና አፍሪካውያን፤ በሌላ ክፈለ ዓለማትም የሚኖሩ ሊማሩት የሚገባ፤ ሊመረቁበት የሚገባ የነፃነት ፍልስፍና ነው፤ ሙያም ነው ብዬ አምናለሁኝ።

የሆነ ሆነ በብሄራው ደረጃ የተጀማመሩ ጉዳዮች ፕሮፌስር ማሞ ሙጭን አሳታፊ እንዳልነበሩ በቃለ ምልልሱ ተረድቸ ነበር። አሁን የአብዩ ካቢኔ ሃብቱን በማሰባሰብ ላይ ስለሚገኝ ይሄን ጉዳይ በአጀንዳው ይዞ ትሩፋቱን ለባላቤቱ ዕውቅና በመስጠት ተቋማዊ ያደርገው ዘመን በአክብሮት ላሳስብም እሻለሁኝ በትሁት መንፈስ እና በአክብሮት። 

የአብዩ መንፈስም ሆነ የሙጬ መንፈስ ዕድሉ የተቃናው በፈጣሪ ፈቃድ ስለመሆኑ እረዳለሁኝ። ይህ ቅዱስ አህጉራዊ መንፈስ ዘመን የሰጠው ስለሆነ በተመክሮ የበቀለው ፍልስፍና ፍሰቱን ወደ ተግባር ለማሸጋገር ሰፊ የሆነ አቅም ዛሬ መንግሥትም አለው ብዬ አስባለሁኝ።

ስለዚህ ሁለቱ ቅናዊ መንፈሶች በኪዳን የሚጋቡበት ሁኔታ ሊፈጠር እንደሚችልም እረዳለሁኝ። ቅንነት ካለ ክትሩ፤ ደንበሩ ሁሉንም ጥሶ የሚያገናኝ ድልድይ አለ ማለት ነው።

እኔም ቤተሰቦቼም አንገናኝም ነበር። ስንገናኝ እንሱም የአብዩ መንፈስ አክትቢስቶች መሆናቸውን ነው የገለጡልኝ። ስለምን?  ከእናታችን የወረሰነው ቅንነትን እና ደግነትን ብቻ ስለሆነ። እናታችንም ትናንት እህቴ እንደ ነገረችኝ መላኩ አብይ አንደምትል ነው ያጫወተችኝ።

መቼም ይሄ ቅብዕ ፈጣሪ እንዴት በህዝብ ውስጥ መንፈሳዊ ሜሮንን ለሁሉ አንዳቀበለው የሚደንቅ ጉዳይ ነው። በመንፈስ ሁሉም በአሃቲ ልቦና ቆረበ። ተመስገን!

በተረፈ ለንድኖች እጅግ አስደስታችሁኛል። እጅግም ኮርቸባችሁ አለሁኝ። መቼም ሊንካችሁን ብለጥፈው አትከፉብኝም ብዬ ለጥፌዋለሁኝ። ያስደሰተኝ ንጹህ ተፈጥሯዊ መሆኑ ነው። ተመስጬበታለሁኝ። ተባረኩ!

ከእኔ ይልቅ እኒህ በ100 ዓመት ትውልድ ከማይተካቸው የአላዛሯ ኢትዮጵያ ሃብትን የአፍሪካዊነት ጽንስ ማህጸን ጋር የጹሁፌ ታዳሚዎች ማህበርተኛ ይሆኑም ዘንድ በትህትና አሳስባለሁኝ።

ስለፕሮፌስር ማሞ ሙጭ ዕውቀታዊ ጥረት ሁለገባዊ ብርታት፤ በመጠኑ ማያያዣ ይሆን ዘንድ ይህን ሊንክ በተጨማሪነትም ለጥፌያለሁ … ለፈቃዳችሁ ቅኖች … ሃብትን ማወቅ ቢያንስ ለህሊና አስማማኝ ትጥቅ እና ስንቅ ይኖረዋል።
  

ለአፍሪካ ሕብረትና ነፃነት፤ ኢትዮጵያዊነት፣ ፓን አፍሪካኒዝምና ህዳሴ ያስፈልጋሉ።

- ፕሮፌሰር ማሞ ሙጬ

Ethiopia | ፕሮፌሰር ማሞ ሙጬ ስለ ኢትዮጵያዊነት Professor Mamo Muchie on Ethiopianism

Prof Muchie on Education in Africa

Prof. Mammo Muchie and Prof. Richard Shambare - an informal chat on Zimbabwe crisis

INTERSOL 2017 Dakar, Senegal

 

ክብረቶቼ የጹሁፌ አንባብያኔ ኑሩልኝ።

 

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!


መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።