#ቁሞ አስቀዳሹ፣ #ጋደም ብሎ ጸላዩ ሜሲ አሳካ።
"አቤቱ ንጹህ ልብ ፍጠርልኝ።" አሜን።
ግብጽ ሁለት አርጀንቲና ሦስት።
ሜሲ በ2026 የዓለም ዋንጫ ሁለት ጊዜ #የቅጣት ምት ዕድሉን ሚስ ቢያደርግም፣ በሁለቱም ጨዋታወች ያባከናቸውን የጎል ዕድሎች በማካካስ ዕድሉን #መላሽ የመሆን አቅም አዳብሯል።
ብዙ በሩጫ፣ በግፊያ የሚያባክነው ጊዜ የለም። ሰርግ ላይ ያለ ነው የሚመስለው። በመራመድ ይህን ያህል ብራንድነት የሚደንቅ ክስተት ነው።
ሌላው እንደ ሆላንዱ ሪበሪ፣ እንደ ጁርመኑ ሙለር አርጀንቲና #የቅጣት ምት ዕድልን አቅዶ መፈጸም ይችሉበታል።
ሁለለት ለባዶ የመራው አፍሪካዊው የግብጽ ቲም በመደበኛ የጨዋታ ጊዜ ተሸንፎ ወደ አገሩ ይጓዛል።
ቢያንስ ጨዋታው #ተራዝሞ፣ በፔናሊቲ ይለያያሉ የሚል ተስፋ ነበር። በቅጽበት ሁኔታው ተለዋውጦ ቲም ሜሲ ዝንጥ ብለው ለቀጣዩ ጨዋታ አለፋ።
ብዙ #በመቆም። ትንሽ በመራመድ የኳታሩ ባለዋንጫ ለተጨማሪ ዕድል ለቀጣዩ ዙር አለፈ።
እምዬ ሲዊዝ ዛሬ ምሽት ከኮሎንብያ ጋር ተጋጥማ፣ ዕድል ከቀናት ከሜሲ ጋር ይሆናል ፍጥጫው። እስኪ የዛሬውን ጨዋታ ይቅናት። ኮለንብያወችን ስለማላውቃቸው ጭንቅ ብሎኛል።
ሌላው አርጀንቲናም ቀጠለ። ፈረንሳይም ቀጥሏል የካታሩ ታሪክ ይደገም ወይንስ ሌላ ባለድል ይመጣ ይሆን። እኔ አርጀንቲና በቃው ባይ ነኝ።
አርጀንቲና ቀጣዩን ተፋላሚውን እየጠበቀ ነው ቴብሉን ሳየው። #ቆሞ ለመጠበቅ ሜሲን ማን ብሎት?
Sergute©Selassie.
07/07/026.
ኳሲዝም ለምልም ግን #አታዳላ!
See less
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ