ኡኡ የአድማጭ ያለህ! ሰሚ ቢገኝ!

ማመዛዘን - ማገናዘብ - ማያያዝ - ማወራረስ - መመርምር - አቅጣጫን ማወቅ።

„በዬሰባቱ ዓመት መጨረሻ የዕዳ ምሕረት ታደርጋለህ።“
ኦሪት ዘዳግም
ምዕራፍ ፲፭ ቁጥር ፩
ዕንባ በጣምራ ኢትዮጵያ ላይ በተደሞ ቀጥሏል .. ወንበሩ ባዶ ነው ....

ከሥርጉተ© ሥላሴ
16.08.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ

ከሰሞናቱ „አክ ወሬዎች“ የሚል ከሊቀ - ሊቃውነቱ የፕ/ሃይለማርያም አለማርያም አንድ ጠንከር ያለ ጹሁፍ ቀርቧል። አታሟርቱባቸው ዓይነት ነው። የሊቀሊቃውነቱ ቅንነቱ ብቻ ሳይሆን ንጹሁ የሆነ መንፈሱ ይመርካል ውስጣቸው ንዑድ እንደሆነ ያመለክታል። ግን የሆነውን ነገር ግን፤ በመሆን ላይ ያለውን ነገር ግን ... አልዳሰሰውም ..

  አብሶ ፕሮፌሰሩ የዶር አብይ አህመድን የብፁዕን አበውን  ጉቡኝት መንፈሱን በማዬት ሙሉ ለሙሉ ዶር አብይ አህመድ  ደህና መሆናቸውን በሥራ ብዛት እንደ ተሰወሩ ነው ያመኑት። አብይ ምንም አልሆነም ነው የሚሉት። እንዲያውም በዚህ ዙሪያ የሳሳበቸው ወገኖችን ያልተገባ መስዋዕትነት አድርገው ነው ያዩት፤ እንደ አፋቸው ቢሆን መልካም በሆነ ነበር። ግን የሆነው፤ በመሆን ያለው ነገር እሳቸው እንዳሰቡት አይደልም።

በሳቸው ምትክ የተወከሉት ለጊዜው ዶር ሙላቱ ተሾመ ናቸው። በማዕካለዊ መንግሥት ደረጃ በተጠሪነት ሁለቱንም በአማካይ በፊርማ እዬከወኑ የሚገኙት።

እርግጥ ነው ዶር አብይ አህመድ በድሮው አቅማቸው በመንፈስ ነፃነት ያወጧቸው ቃሎች በሙሉ ሙሉ ለሙሉ አብይ ከእነ ሙሉ ነፃነቱ ለማለት ያስደፍራል። ያ ያስደሰተኝ ለእኔ እንደገና የመወለድ ያህል ነው። ያ የሆነው ግን አዌርነሱ ስለጠነከረ ነው፤ ለማዘናጊያ፤ ትጥቅ ለማስፈታት ነው። 

እኔ እንደ ማስበው ከዚህ ጉዳይ ጋር አንድ ግዙፍ መሰረታዊ አምክንዮም አለ የቅድስት ተዋህዶ ማህበረ ምዕመናን ጉዳይ። አስከ አሁን ባለው ሁኔታ በተደሞ የተቀመጣ አቅም ነው። ይህ በተደሞ የተቀመጠ አቅም ደግሞ ሌላ ንቅናቄ መፍጠሩ አይቀሬ ነው። አብይ ማተቡ ሆኗል እና። አባቶቻችን አንድ መሆናቸው ለማህበረ ምዕመኑ ያስገኛው የመንፈስ እርፍት ይህ ነው አይባልም። በድምጻችን ይሰማ በኩልም መሰሉ ተፈጽሟል። አማንያን የሃይማኖት ነፃነትን ይኖራል ብለው ተስፋ ሰንቀዋል ግን ቀጣይነቱ እጅግ አስፈሪ ነው ... ባለታወቀ መንገድ ላይ ነን። 

 የብጹዕኑ አገር መግባት ዶር አብይ አህመድን ላለማሰከፋትም ብቻ ነው እሺ አብረንህ እንሄዳለን ያሉት። እንጂ ውሳኔው ለመስከረም 8 ነበር። መስከረም 8 ቢሆን ኖሮ ብፁዕና አባቶቻችን ቅስቅስ አይሉም ነበር። አሁን ላለው ቅብ የዴኮሬሽን ሁኔታ ወደ አገር ቤት ዘው የሚባልበት ምንም ነገር አልነበረም። እሳቸውም ተናግራዋል ፅዋው ከእኔ አይለፍ ብለው። ህልምም ያዩ ይመሰልኛል። 

እርግጥ ነው አበው ቃል አስገብተዋቸዋል ለዚህም ነው „ቃል ብርቱ“ ነው ያሉት። በዛ በጭንቅ ሰሞናት ምን እንዲሆነልህ ትፈልጋለህ ቢባሉ እኒያ ብርሃን መሪ ዶር አብይ አህመድ ብጹዕና አባቶችን ሄጄ ማዬት ማለታቸው አይቀሬ ነው።  

የብፁዑ አቡነ መሪቅርዮስ ጤነንትን ማረጋገጥ ለእኒያ ቅን መሪ ቀዳሚው ጉዳይ ነበር። እሳቸውን አመነው ነው እና መስቀላቸውን ይዘው አገር የገቡት። ስለዚህም ይሄ ተፈቀደላቸው። በቃ የሆነው ይሄ ነው። 

የነበሩት በሙሉ የወያኔ ሃርነት ትግራይ መንፈስ ብቻ ነው …. ብጹዑ ወቅዱስ አቡነ ማትያስን ሳይጨምር። እኔ የእርቅ መንፈሱ ፌክ ነው ብዬ ስለማላስብም።

ከዚህ ባሻገር ያለው ነገር ግን ፌክ ነው። አርቲፊሻል ነው። ቅብ ነው። እንደ ሊቀ ሊቃውንቱ እንደ ፕሮፌስር አለማርያም ያሉ ዕንቁዎች ማድርግ ያለባቸው ለተባባሩት መንግሥታት፤ ለአሜሬካ መንግስት፤ ለ አፍሪካ ህብረት፤ ለ አውሮፓ ህብረት፤ ለሃያላን መንግሥታት፤ ለሰብዕዊ መብት አስከባሪ ድርጅቶች ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የቁም እስር ላይ ስለመሆኑ ማሳወቅ ነበር።

የአብይ ሌጋሲ ተመችቶኛል የሚለው ሁሉ ወያኔ ሃርነት እና አዲሱ አንጃ ውህድት ፈጥረው ለፈጸሙት መፍንቀል መንፈሳዊ ደባ በማጋለጥ ሽንጣቸውን ገትረው መታግል እንጂ የሆነው ሁሉ ነገር እንዳልሆነ አድርጎ መውሰድ እንደ ዓለም የህግ ሰውነታቸው የተገባ አይደለም። እሳቸውም ተሸውደዋል ዕንቁው ሙሁር ፕ/ አለማርያም። እንዴት ነው የትዳር ጓድ የለችንም? ሴቶች ብልሆች ስለሆን። በርቀት ነው ጠረኑን የምናሸተው …

ሌላው ዕንቁ ዶር አቦንግ ኢትዮጵያ ሜቶም ቢሆን የሰብዕዊ መብት ረገጣ ላይ ሁለት ጊዜ አዝኖ ያወጣውን የቪዲዮ ክሊፕ አይቻለሁኝ፤ አዳምጫዋለሁኝ። እሱም ቢሆን አብይ የት ነው አላላም? ዶር ለማ መግርሳስ ቢሆኑ የት ናቸው?

የውጭ አገሩ ሞገድ ተፈርቶ እኮ ነው አሁን እዬተድበሰበሰ ያለው። ሥርዓት አልበኝነት የነገሰው እኮ አብይ መምራት አልቻለም ነው።
  
የአብይ ሌጋሲ እኮ ልክ ባዶ ሳጥን ነው። ልብስህን አስገበትህ እንደምትጓዘው፤ አብይ አሁን ህዝብን ለማረጋጋት መጓጓዣ ነው። አብይ ያለውን ሁሉ ዘርግፎ ለተተኪው አስርክቧል። ስልክም ኢንተርኔትም ከሌላበት ቦታ ነው የታገተው። 

ዛሬም ያዬዩሁት በድጋሚ ህልም ወንበር ፍልጋ ላይ ነበር። ህልሜን እጠብቃለሁኝ ብዬ ነበር። አሁን ህልሜ የነገረኝ ባዶ ወንበርን ሳይሆን ወንበር ፍለጋን ነው። 

ባዶ ወንበሩ ደግሞ የመጀመሪያው ማህል ላይ ነበር። አሁን ሰገንት ላይ ሆኖ ግን ጥግ ላይ ሆኖ ያዬሁት ወንበር ፍለጋ ላይ የሆኑ ሰዎች እዬተራወጡ ነው ያዬሁት። የቀደመው ባዶ ወንበር፤ ማህል ላይ ተቀምጦ፤ የዛሬው ጥግ ላይ ወንበር ለማስቀመጥ የሆኑ ሰዎች ወንበር እዬፈለጉ ነው። 

ራሱ ባዶ ወንበርን አላዬሁም። ለመሆኑ ዶር ለማ መግርሳስ የት ናቸው? አቶ ደመቀ መኮነን የት ናቸው? የአብይ ካቢኔ የት ነው? የአብይ ካቢኔ ታሟል፤ አደጋ ላይ ነው። ቀይ መስቀል ያስፈልጋዋል።

አሁን የሚፈራው በዬስብሰባው ደፍሮ የተናገረው ግለሰብ ሳይሆን ሚሊዮን ነው ያ ሚሊዮን ከተናደ እሰቡት…. እንደገናም ለ እርዳታ አብይን አምነው ቃል የገቡ የዓለም መንግሥታት ሁሉ እጃቸውን ይስባሉ … ስለዚህ ቅብ ነገሮች ግድ አሉ እና አብይ ካለከራባት ወጥቶ ታዬ ...

 ትናንት በኢትዮጵያ ኢንባሲ የአሜሪካ ቃል አቀባይ የሰጡት መግለጫም ህዝብ የነፃነት አያያዙን አለማወቅ ስለመሆኑ እንጂ የአብይ ሌጋሲ መታመሙ አልተገለጠላቸውም … 

አሁን የተፈለገው የአብይ ሌጋሲ ሞት ሰላማዊ በሆነ ሽግግር ነው የተፈለገው፤ ስለምን ዓለም አዲሱን መንፈስ ሊቀበል እንደማይችል ይተዋቀል፤ የ አፍሪካው ህብረትም እንዲሁ፤ የግብጽ ዓይነት ሂደት ነው። አሁን እኮ ዶር አብይ አህመድ ከአቶ ሃይለማርያም ደስአለኝም ባነሰ ነፃነት ውስጥ ናቸው። እስረኛ ናቸው ጠ/ ሚር አብይ አህመድ። ይህን አምኖ ለመቀበል መውጣት መውረድ አያስፍልገም፤ ጊዜው እዬተቃጠለ ነው ...

ከአሜሪካ መልስ የሆነው ነገር ሁሉ የጨላማ ጉዞ ነው። እንጂ እኛ አይደለነም ጨለማ የሆነው፤ አክ ወሬ አራጋቢዎች የምንባለው። ሌላው ቀርቶ ስልክ ቢፈቀድላቸው በተፈቀደላቸው ልክ ነው የሚናገሩት። አዲስ ሃይሎች ወደ ፊት እዬመጡ ነው። የጠ/ ሚር ቢሮ ሃላፊው ነው ወደ ፊት እዬመጡ ያሉት 90 ቀን 900 ጉዳዮችን ሰልጥነዋል። በሌላ በኩል ጃዋርውያን ነው ያሉት።

ጅማ ለሚባለው ጅማ ላይ ነውጥ እንዳይነሳ ነው እሱም ዕውነት ከሆነ። ጅማ በታሪኳ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው የአገር መሪ የሆነው። ሳይንቲስት እንጂነር ቅጣው እጅጉን አጥታለች። አሁን ደግሞ በህይወት እንዳይኖር የተፈለገው በፈጣሪ ፈቃድ በህይወት ኖረዋል። ስለዚህ በህይወቱ ኖሮ ባዶ ሻንጣ ልብስ እንደሚሞላበት እንደዛ ነው እዬተሠራ ያለው።

ያ አዲስ አንጃ ከወያኔ ሃርነት ጋር ግንባር ፈጥሯል። ስለዚህ ያ የአብይ ሌጋሲ ቅስሙ ተሰብሮ ሁሉም ነገር 27 ዓመት ወደ ነበርንበት የመልስ መንገድ ጉዞ ላይ ነው። እንግዲህ ታሪክ ወደ ኋዋላ ሲመለስ እያዬን ነው።

 ብቅ ብቅ ያሉ የነፃነት ቀንበጥ መንፈሶች ዕድሜ ይስጣችሁ ቀስ እያሉ ይሸበሸባሉ። ተፎካካሪ ሃይሎች ሁሉም ገብተዋል። ከግንቦት 7 በስተቀር። የሚጠበቀውም እሱ ነውይግባ እና ያገኛታል።

 ልጅ መሳይ መኮነን ሁሉ መካሪ ሆኗል ይለናል። እኛ ነፍስ ጉዳያችን ስለሆነ እንጂ በግንቦት 7 ሥም የታረደ ህዝብ እትብተኞች ነን። ጎንደር አቀባባል እንዲያደርግ የሚፈለግበት ምክንያትም፤ ባህርዳር አቀባባል እንዲያደርግ የሚፈለገብትም ትናንት ለተፈጠረው ሰቆቃ ወደፊትም ለሚፈጠረው ሰቆቃ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ያሰርኩት፤ የቀጠቀጥኩት በትክክለኛውም አማራው የግንቦት 7 አባል ነበር ለማለት ለማረጋገጫነት ነው። በዚሐው አጋጣሚ ለ አማራ እምመክረው ወገን ወደ አገር ሲገባ መቀበል መልካም ቢሆንም ይሄኛው ግን ለማረጃ መሆኑን አውቆ ቤቱ መቀመጥ እንዳለበት ነው። ምን የጥያቄ እና የመልስ ሄደትም አያስፍለግም። 

ስለዚህ ትናንትም ነገም የሚሆነው ነገር ከልብ ሆኖ መመርመር እንደሚገባ ጠፍቶኝ አይደለም። ግን እንደ ሰው ጠቃሚው ነገር መኖራቸው ስለሆነ መንትዮሹ ባሄዱ ማለት ወንጀል ሆኖ ሊቆጠር አይገባም። እንደ ዜጋም መብታችን ነው። ከ እሱ በፊት ሥርጉተ ሥላሴ ግንቦት 7 አቅም እንዲኖረው የተጋች ሴት ናት በዛ ላይ ጉዲት የተባለችበትም ከ8 ዓመት ላለነስ በራሱ ሰዎች እና በወያኔ ሃርነት ትግራይ ማህበርተኞች ስቃዮን በልታለች። 

እነሱም ኢትዮጵያዊ ናቸው ወገኖቼ ናቸው፤ ሰዎች ናቸው፤ አካሎቼም ናቸው፤ በዛ ላይ እኔ አንጀቴ ቡቡ ነው።  ዶር ሙሳ ኮንቴም ገብተዋል እሳቸው ደግሞ ዶር አብይ አህመድን ለሰላም ኖቤል ሽልማት ያሳጩ ናቸው ፈጣሪ ይሁናቸው …

የሚገርመኝ መድርክ ያላቸው፤ ሁነኛ ሚዲያ ያላቸው፤ ሊቀ ሊቃውንታት ምን እዬሆነ እንዳለ ከልባቸው ሊገባ አለመቻሉ የተደገመባቸው ስለመሆኑ ነው ምልክቱ። 

አቅም ያላቸው የተዋህዶ አባቶች አሁን እዬተመለሱ ነው። ይሄ መልካም ነገር ነው። ተመሰገንም ያሰኛል። ብጹዑ ወቅዱስ አባታችን አቡነ መርቀሪዮስ ግን የፈለገ ነገር ቢሆን አገር መግባታቸው ትክክል እና አግባብ ነው። ይህም የሰው ሥራ አይደለም የልዑል እግዚአብሄር ታምር ነው። ዋናው ነገር ሃይማኖታችን አንድ መሆኗ ለመንፈሳዊው ህይወት ጠቃሚ ነው።
ነገር ግን የወያኔ ማንፌሰቶ ገዢ ሆኖ ከወጣ አሁንም ታጥቦ ጭቃ እንደሚሆን ደግሞ የታወቀ ነው። ለነገሩ የፊት የፊቱን …ይላል ጓያ ነቃይ ...

አሁን ከመጋቢት 24 ቀን 2010 በፊት ወደ ነበርነው ተመልስናል፤ እንደያውም የከፋ ይመስለኛል። ዕውነታው ይኸው ነው። በቀሉ እጅግ በከፋ ሁኔታ ቀጣይ ነው። አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና ሂደቱንም ይጠበቃል ….

ይደገማል ዶር አብይ አህመድ አሁን የጠ/ ሚር ቦታቸውን ለቀዋል። ማንም ወንበሩን አልተቀመጠበትም። የጎንዮሹ ባለስልጣን የጠ/ ሚር ቢሮ ሃላፊው፤ ፕሬዚዳንቱ ናቸው። በበላይ ጁንታው እና ወያኔ ሃርነት ትግራይ በጋራ ነው የሚመሩት። በጣም በበላይ ደግሞ የውጭ መንፈስ አለበት። ይሄው ነው። 

ስለዚህ ከነሃሴ ጀምሮ እስከ መስከረም መጨረሻ ድርሰ አገር ለሚገቡት በ25% ሽወዳ ህዝብ የአብይ መንፈሱ፤ ሌጋሲው አለ ብሎ ሆ! ብሎ ወደ አገር እንዲገባ የሚደረገበት ምክንያት ከመዳፍ እንዲሆን የሚፈለጉ ተጽዕኖ ፈጣሪ መንፈሶች ስለአሉ ነው። ዲያስፖራ ላይ ያሉ ተጽዕኖ ፈጣሪ መንፈሶች አቶ ታማኝ በዬነም ጨምሮ አደብ ቢይዙ መልካም ነው። 

ይልቅ እኔ እንደ ልዩ አክባሪነቴ ለሊቀ ሊቃውንቱ የኢትዮጵያ ሁነኛ ለፕ/ አለማርያም አገር ጤና ነው፤ ጠ/ ሚሩ በሙሉ መንፈስ አገኛለሁ ብለው አገር እንዳሄዱ ነው። ይህን ለማስደረግ ደግሞ ቀላሉ ሂሳብ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ስልክ በቀጥታ እንዲደውሉላቸው ሊያደርጉ ይችላሉ። 

ምን ያህል እኒህ ሊቀ ሊቃውንት የዋህ እንደሆኑ እያዬሁ ነው፤ መሆን ያለበት ይልቅስ ጠ/ ሚር አብይ አህመድን አድንዝዘው አፍዝዘው ሳያሳጡን ሊሆን የሚገባውን ቢያደርጉ እጅግ አምርጣለሁኝ።

ፖለቲከኛ ትንሽም ይሆናል ብሎ ማሰብ ይገባል። ይህ ዕድል የዶር አብይ አህመድን መንፈሱን ካመለጠ ሙሉ ስብዕናቸው፤ ጤናቸውን ሁሉ ልናጣ እንችላለን።

አንዳይናገሩ የተደረገበት ምክንያት በአብይ ሌጋሲ ላይ ድንጋይ እንዲወረውር ነው … ለውጡ ተቀልብሷል። በሙቀቱ ግን የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማንፌሰቶ እና የሄሮድስ መለሰ ዜናዊ የሙት መንፈስ ሠረጋላ ላይ ነው ... 

ለረዥም ጊዜ የራስ ተሰማ ናደውን ዘመናዊ አድማ ስገልጽ ኖሪያለሁኝ። የሆነው ይሄው ነው። አቦይ በረከት ስምዖን፤ አቦይ ስብሃት ነጋን የተሸከመች አገር አንዲህ በቀላል የሂሳብ ቀመር መቀመር አይቻልም።

የአሜሪካኑም ጉዞ ቅንብሩ ምቹ ሁኔታ ለማመቻቸት ነው። የሰኔ 16ም ህዝባዊ ስብሰባ እንዲሁ። እንዲያውም እኔ አውሮፕላኑ መሬት ላይ ከማረፉ በፊት የሆነ ነገር ይሆናል የሚል ስጋት ሁሉ አለኝ ብዬ ጽፌ ነበር። 

ነገር ግን የብፁዕን አባቶች መኖር ነው ያተረፋቸው … መርዙም ትክክል ነው እሳቸው ከመድረሳቸው በፊት ግልበጣው ተከናውኗል። ሳጥን ሳያዘጋጁ፤ ሲናሪዮ ሳያዘጋጁ፤ የቀብር ሥርዓቱን ሴሪሙኒ ሳያዘጋጁ አልቀሩም ነበር።

ምክንያቱም ባዶው ወንበሩን ያዬሁት ሐምሌ 19 ለሐምሌ 20 አጥቢያ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ጉዞ ላይ ሆነው ነበር። ደንግጬ ከእንቅልፌ ተነስቼ ሁሉ ጸሎት አድርሼ ነበር ደግሜ የተኛሁት።

የቲያትሩ በር ይሄው ነው፤ የ4ወራቱ የአብይ ሌጋሲ ምዕራፍ አንድ ክርችም ብሎ ተዘግቷል።፡ ይልቅ ነፍስ ያለችሁ ሁሉ ከነሙሉ ሰብዕናቸው ከነሙሉ ጤንነታቸው ልክ እንደ አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ ከዚህ ሰቆቃ የሚወጡበትን መንገድ ቢፈልጉ መልካም ነው።

ለነገሩ አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ አሁንም ሄጄ እማገዳለሁ እያሉ ነው። ያገኟታል፤ ፉከራ ግን አይደለም። ነፍሳቸው መትረፉ ቢያንስ ለልጆቻቸው እና ለትዳራቸው ይበጃል። ስለምን ስክንት እንዳጡ ይገርመኛል እሳቸው እራሳቸው። 

እርግጥ ነው የአብይ መንፈስ ያጓጓል። ግን መስተጓጎሉን ልብ ማለት ደግሞ ይገባል። የሆነው ሁሉ ዕውነት ነው። የጠ/ ሚሩ ወንበር ደግሞ የሐምሌ 19 ለሐምሌ 20 ዋዜማ ብቻ ሳይሆን ዛሬም ወንበሩን ጠርዝ ላይ ለማስቀመጥ የተወሰኑ ሰዎች ወንበር ፍለጋ ሲወራከቡ ነው ያዬሁት።

የሆነ ሆኖ ዶር ለማ መገርሳስ የት ናቸው? ዶር ለማ መገርሳ የት ናችው? ዶር ለማ መገርሳ በምን ሁኔታ ላይ ናቸው?

ልብ ይስጣችሁ ለሊቃ ሊቃውንታት፤ ለሰባዕዊ መብት ተሟጋቾች፤ ለጋዜጠኞች፤ ለጸሐፍት፤ ለፖለቲካ ተንታኞች፤ ለራሱ ለኢሳት ሚዲያ። ግን ኢሳትም አብሮ ከግንቦት 7 ጋር አገር ሊገባ ደግሞ ብቻ እንዳይሆን? ብቻ ይህን ካደረጋችሁ እብደትም ነው። 

አዲሱ የለውጥ መንፈስ ኩዴት ደርሶበታል። "ዋ! አንቺ አገር ኢትዮጵያ" አሉ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የሆነው ይሄው ነው።
  
የጹሑፌ ታዳሚዎች አቅም ያላችሁ ይሄ የዲያስፖራ ፈንድ ራይዚንግ ሹመት ምንትሶ ቅብጥርሶ ቀልዱን ቆሞ አድርጎ ወደ  እውነቱ ዘልቆ ዕውነትን ለማስፈታት ብትተጉ ይሻላል። አገር እንገባለን እንሄዳለን የምትሉትም እንዲሁ …

ወያኔ ሃርነት ትግራይ እንደ እኛ ትግል ቀፎ አይደለም … ወደ መንበሩ ተመልሷል። አላያችሁም አንባሳደር አባይ ጸሐይ ቻይና  ለዴፕሎማሲ ተግባር መላካቸውን። 

ከትናት በላይ ዛሬ ያስፈራል … ከኖርነው በላይ ዛሬ ይጨንቃል … የ97 ዳግም ውድቅት ነው የተከሰተው … ጥበብም ጎደለ፤ ቅንነትም ካልልክ በዛ …

ነፃነት ለአብይ እና ለሌጋሲው!
መሸቢያ ጊዜ።



አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።