መፍትሄ መፈለግ ብልህነት ነው። በማይታወቅ መንገድ ላይ ነን።
መዘናጋቱ አትራፊ አይደለም።
በእርግታ አይቶ ለወል መፍትሄ መትጋቱ ግን ግድ ነው። እንዲያውም አንድ ቀንጣ የመፍትሄ አፈላላጊ ነፍስ በመጥፋቱ አሁንም ተዘግይቷል።
„በአምላክህ በእግዚአብሄር ፊት የተጠላ ነውና ነውር ወይም
ክፉ ነገር ያለበትን በሬ ወይንም በግ
ለአምላክህ ለእግዚአብሔር አትሰዋ“
ዘዳግም ምዕራፍ ፲፯ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ ሥላሴ 16.08.2018
ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።
- · ግብግብ ከጭብጥ ጋር።
ዶር አብይ አህመድ በሙሉ አቅም ቢሆኑ የቆሞስ ኢንጂነር ስመኛው የጠራራ ጸሀይ ግድያ፤ የቆመስ ፈቃዱ ተ/ ማርያም በሥጋ መለዬት፤ የቆሞስ ተስፋዬ ጌታቸው ድንገታኛ ህልፈትን አገር ቤት ሲመለሱ ቢያንስ ለቤተሰብ ደውለው አያጽናኑም ነበርን?
የደራሲ ምስብዕከ ወርቁ እኮ ሁኔታውን እንደሰሙ ደውለው ነው ቀጠታ በስልክ ያነጋገሩት፤ በሰኔ 16 ቀን የግድያ ሙከራም ላይ ወዲያውኑ መግለጫ ሰጥተዋል፤ ለዛ ድንጋጤ ሳይንበረከኩ ወዲያውኑ ሄደው ለሰማዕታት ጽናትን በየሆስፒታሉ ተገኝተው ነው የመገቡት፤ ለተሰዉት ቤተሰቦች ደውለዋል፤ ቀድመው ሄደው ደማቸውን ሰጥተዋል። የእርዳት ገንዘብ ሁሉ ሲሰብ ነበር።
በደቡብ ያን መሰል ሰው ሰራሽ ችግር ሲመጣም "ችግር ከማድረሳችሁ በፊት ስለምን እኔን አትጠሩኝም ነበር፤ ብር ብዬ እማጣ አልነበርንም?" ብለው በቦታው ተገኝተው የህዝባቸውን ችግር አዳምጥዋል፤ በማህል የኤርትራ ቸር ወሬ ሲመጣም ልመለስ ልቆይ ሳይሉ አባ ቅንዬ ወዲያውኑ እዛው ላይ እያሉ መልስ ሰጥተዋል። ይህም ብቻ አይደለም በሳቸው ጉብኝት ወቅት የሚደሙጡ የወቀሳ ነገሮችን ሁሉ አጀንዳዬ ብለው በዬተገኘበት አጋጣሚ መልስ ሲሰጡ ነበር።
ሌላም ደቡብ አፍሪካ ላይ አንድ የወንጌላውያን ልዩ ዝግጅት ነበር እሱንም ደውለው አበረታተዋል፤ ቀዳማይ እመቤትም መዝሙር አሰመተዋል።
- አሁን ግን?
ጁቡቲ ላይም ሌላ የኢትዮጵውያን ግድያ እዬተፈጸመ ነው፤ ስደተኞች እዬተፈናቀሉ ነው፤ በሱዳን እና በኢትዮጵያ ደንበር ችግር ደረሰ ሲባል ለሱዳን መንግሥት አፋጣኝ ደብዳቤ በውጭ ጉዳይ ሚ/ሩ በኩል በቀጥታ ልከው ነበር።
ኢትዮ ሱማሌ ላይ እሳቸው ቅድስት ተዋህዶን ከስደት አገር ባሰገቡ ማግስት ያን መሰል መከራ ሲመጣ፤ ያን የመሰለ የወል የገፍ ነገር ሲፈጽም ዝም የሚሉም አይደሉም። የቲፒው ጉዳይም ሰፊ የሆነ ጥቃት ተጀምሯል።
ሌላው በቅርቡ በአደባባይ ተገድሎ ተዘቅዝቆ ዜጋ ሲሰቀል ለኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው የውርዴት ታሪካችን ነው ይህን ዝም ይላሉ ተብሎ አይታሰብም፤ በቀጥታ ሄደው የሻሸመኔን ህዝብ ያናግሩ ነበር። ለኢንጂነር ስመኘው ልጆች የተለዬ ሁኔታ ይፈጠር ነበር።
ይህ ሁሉ የሚሆነው በተስፋችን ላይ ተስፋ መቁረጥ መጥቶ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ይመረን እንዲባል፤ አብይ እና መንፈሱ አታሎናል ብሎ ህዝብ ጀርባውን እንዲሰጥ ቀውሶችን በማማባስ አንጃው እና ወያኔ ሃርነት ትግራይ በማህል ገብተው አሰታራቂ መሆን ነው እኛ አለንናለችሁ ዓይነት …
https://www.satenaw.com/amharic/archives/62592 መርዘኛው ጌታቸው ረዳ
ሌላም ማነጻጻሪያ ላቅርብ እንይ እኒህ ትጉህ ንቁ አንስት መራሂት ወ/ሮ ሙፍሪያት ካሚልን በዚህ መልክ ነበር እማናውቃቸውን? ሃዘን ላይ ናቸው ያሉ። የሰራ አካላታቸው ውስጣቸው ድንኳን ጥሎ ተቀምጧል። ደመመን ላይ ነው ያሉት። አሁን አዛዣቸው ሌላ ሃይል ነው። አሁን መሪያቸው ሌላ ሃይል ነው የአቶ ጌታቸው ረዳን ንግግር ሳይሆን ወ/ሮ ሙፍሪያት ካሚልን ብቻ እዮቸው ብዙ መልዕክት አለው። አገር ችግር ላይ ናት።
ለቅኖች የምሰጠው የቤት ሥራውን ወ/ሮ ሞሪያት ከሚል ገጽቸው እንደትመልኩት ብቻ ነው። ጭንቅ ላይ ናቸው። ያሉት አፍ ባለው መቃብር ውስጥ ነው።
· የሊቀ ለቃውንታት መርጃ እና ዕድምታው።
ሌላው በንጽጽር እንድታገነዛቡት እምሻው ቁም ነገር ደግሞ የዲያቆን ዳንኤል ክብርትን የጹሁፍ የማረጋጊያ ጽንሰ ሃሳብ እና ስለታሙት ተጓዣች የሰጠውን ምስክርነት ይዛችሁ በርሃን ቴሌቪዥን ካናዳ ላይ ከሊቀ ካህን ምሳሌ ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ ነው።
ዲያቆን ዳንኤል ክብረት አንድ አባት እና ሌላ ሰው ታሟብን ነበር ነው የሚለው እሳቸው ደግሞ ምንም የደረሰ ነገር እንደሌላ ነው የሚገልጹት። የታመም የለም በሳቸው ገላጸ፤ ግን ወጋ ጠቀም ያለ ሌላ የታመቀ መረጃ ደግሞ አለው።
ከሚነሶታ እስከ አዲስ አበባ (ከዲያቆን ዳንኤል ክብረት)
„አሁን ማረፍ እንችላለን ብለን ወደየወንበራችን ስናመራ አንድ አባት መታመማቸውን ሰማን፡፡ ወደ ኋለኛው ክፍል ስንገባ ታማሚው ራሳቸውን አያውቁም፡፤ ቅዱስነታቸውን ለመንከባከብ ሁለት ነርሶችና አንድ ሐኪም አብረውን ነበሩ፡፡ ሦስቱም የነፍስ አድን ሕክምና ላይ ተሠማሩ፡፡ ኦክስጅን እየሰጡ ወለል ላይ አስተኟቸው፡፡ ሐሳብና ጸሎት ከየአቅጣጫው መጣ፡፡“
„አዲስ አበባ ስንደርስ አምቡላንስ እንዲዘጋጅ ለመንገር ወደ ፓይለቶቹ ሄድኩና ለዋናዋ አስተናጋጅ ነገርኳት፡፡ ከአብራሪዎቹ አንዱ ወጥቶ አነጋገረኝ፡፡ ቦሌ ካሉት ጋር ተነጋግሮ መልሱን ሊነግረኝ ወደ ጋቢናው ገባ፡፡“
„እኛም ወደ ታመሙት አባት ሄድን፡፡ ፈተናው ገና አላለቀም፡፡ የምድሩ ነገር ሲያልቅ የሰማዮቹ የክፋት ሠራዊት ታጥቀው ተነሥተዋል፡፡ እርሳቸውን እያስታመምን ሌላ ሰው ደግሞ ታመመ፡፡ አሁን ውጊያው ከሥጋና ከደም ጋር አለመሆኑን ተረድተናል፡፡ ሁሉም እንደየ እምነቱ ይጸልይ ነበር፡፡ ሐኪሞችና ነርሶቹም ርብርባቸው ሁለቱ ላይ ሆነ፡፡“
- አጋቡት። ወይንም አፋቱት ... በፈለጋችሁት መልክ
Interview with Like Kahen Mesale Engda ኢትዮጵያ ደርሶ መልስ ከሊቀ ካህናት ምሳሌ እንግዳ ጋር#Berhan TV
የብርሃን ቴሌቪዥን ቃለ ምልልስ አድርጊው ወንድም ተፈጠረ ስለሚባለው ችግር ሲጠይቃቸው „ … መክሰስ አንችልም ግን ትክክል እንዳይደለ ነው፤ እኔ የሚታዬኝ እስከዚያ ድርስ እስከማውቀው ድርስ ምንም ችግር የለም“
በዚህ አገላለጽ አውሮፕላን ውስጥ ምንም ችግር ሳይፈጠር በሰላም ነው የገባነው። ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ሁለት ተጓዦች አንዱ አባት ናቸው ሌላው አልተገለጸም ያለውን እኒህ አባት ምንም አልደረስም ባይ ናቸው።
ቀጥሎ ያለውን እርስ በእርሱ የሚቃረነው ደግሞ እንመልከተው። እርስ በእርሱ መቃረኑ እንደ አባት አደሩ ትውፊት ሰው ሞቶ እንኳን ሁሉ ነገር እስኪሰናዳ ድርስ ይደበቃል።
በእኛ ቤተሰብ ይደረግ የነበረው እንደዛ ነው። ሊቀ ሊቃውንታት በሥጋ ሲለዩ በዝምታ ይኮንና ጠላ ይዘለላል፤ እንጀራ ይጋገራል፤ ወጥ ይሰራል፤ እህል ይፈጫል፤ አዋዜ ይዘጋጃል፤ ለቤተ ዘመዱ ሩቅ ላለው መልዕክተኛ ይለካለ፤ አብዬዝግኒ፤ ቀሃ እዬሱስ፤ ደብረ ምቅማቅ፤ ልደታ፤ ቁስቋስም ፤ አጣጣሚ ሚኬኤል፤ ፊት ሚኬኤል፤ ባታ፤ ደፈጫ ኪዳነምርት፤ ደንቢያ፤ ወገራ፤ ደብረታቦር ወዘተ … ይህ ትውፊታችን ነው።
ሞትንም ተሰናድቶ በተደራጀ መንፈስ ማስተናገድ የቆዬ የትውፊታችን አካል ነው።
የሆነ ሆኖ የአባቴን ቃለ ምልልስ ቃል በቃል ጽፌዋለሁኝ በመሃል የተውኩት ብዙም አስፈለጊ ያልሆነውን ብቻ ነው።
ቃለ ምልልስ አድራጊው ስለደረሰው ነገር ጠብቅ አድርጎ እንደ መጠዬቅ አደረገው እና እንዲህ አሉ አባታችን …
„በውነቱ እኒህ ጠ/ ሚር ለሁሉም ሰው የሚያስደስቱ ስለሆነ ሁሉ ይሳሳላቸዋል፤ ነገር ግን እንደዚህ ያለ ያልሆነ ሆነ ብሎ ማውራት ደግሞ ተገቢ አይደለም። አንድ ነገር እንኳን ቢፈጠር ነገሮችን በእርጋታ ማዬት እንጂ ያልተፈጠረውን እንደ ተፈጠረ አድርጎ ለህዝብ ሽብር ማድረግ አይገባም። እኔ የማውቃቸው ሴት በዚህ የተነሳ ታመው እንደነበር ነገረውኛል፤ የሚዲያ ሰዎች በውነቱ ማሰተከካል አለባቸው፤“
አሁንም ደገሙት ...
„አንድ ነገር ቢኖር እንኳን በዚህ ዓይነት አይደለም መደረግ ያለበት፤ በረገጋጋ መንፈስ በተረጋገጠ መንፈስ ነው መደረግ ያለበት፤ እንኳንም ምንም ነገር የሌለውን።“
ቀጠሉ አባታችን …
„ሰው ናቸው ሰው እንደመሆናቸው አንድ ነገር ሊደርስ ይችላል፤ ሰው ናቸው ስለዚህ እኒዚህ ተቃዋሚ የሆኑ ሰዎች ላይ አደጋ ለማድርስ የሚፈልጉ ሰዎች በሳቸው ላይ በዙ ነገር የሚያወሩ ሰዎች ተከትሎ ሚዲያው ማሰተጋበት የለበትም።
ሰለሱት አሁንም አባታችን ...
„አንድ ነገር እንኳን ቢሰማ ያነን ተዕቅቦ አድርጎ መጠበቅ ነው እንጂ ይህን ያህል ያልሆነ ነገር ማስተጋበት ህዝቡን ወደ መሰበር ውስጥ ማስገባት ነው እና ትክክል አይደለም።“
እኔ የእኒህ አባት ጭንቀት ይገባኛል። ህዝቡ ተሸብሮ እርምጃ እንዳይወስድ ነው ስጋታቸው፤ ወይንም ህዝቡ በጭንቀት ብዛት በነፍስ ወከፍ ህመም ላይ እንዳይወድቅ ነው ያስጨነቃቸው። ማህበራዊ ሚዲያዎች አፋቸውን ሊዘጉ ይገባል ነው የሚሉት። ግን ዘመኑ ሉላዊ ስለሆነ አይቻልም። ማንም ይህን የግሎባል ዌብ ማስቆም አይቻልም።
እርግጥ ነው አጋጣሚው የረዳቸው ደግሞ የበለጠ ማበረከታቸው አይቀርም፤ እንደገናም ምንም አልተፈጠረም በማለትም ዝንጉነት እንዲነግሥ የማድርግ ዘመቻም አለ። በቅንነት ያሉት ሥራችን የ አብይ ሌጋሲን እናስቀጥል ነው፤ የጠላፊው መንፈስ ደግሞ በማዘናጋት በ አብይ የተገኘውን የመንፈስ ሃብት ለቀጣይ የጭቆና ተግባር ማከማቸውት ነው ይህም ታቅዶ ነው የሚከወነው።
መንፈሰ ፍነቃዩም ጊዜ እንዲያገኝ፤ በሌላ በኩል ሰው እዬተዘናጋ አብይ የት ነው ጥያቄውን እንዳያነሳ፤ ሌላውም አገር ሰላም ነው ብሎ ወደ አገር እንዲገባ እና ተሰብስቦ ሲጋባ ደግሞ በቀልን በበቀል ለማካካስ … ምቹ ነው።
እኔ እንደ ተረዳሁት ሊቀ ካህን ምሳሌ የገለጹት ...
ወሬውን ጋብ አድርጎ … ነገር ግን አቅም ያላቸው ሰዎች ሊሆን ቢችል ብለው በጽሞና እና በጥሞና ሆነው በተረጋጋ መንፈስ ለመፍትሄ ቢተጉ የሚል የተከደነ ቅኔያዊ ምክር ነው አባታን የለገሱት።
ደጋግሞ አንድ ነገር እንኳን ቢሆን፤ ቢከሰት ቢፈጠር ነው የሚሉት በተጨማሪም ይህ እንዲሆንም ግድ ነው የሁሉ የህሊና ቤተሰብ ስለሆኑ ተቀናቃኞች ይህን መሰል ድርጊት ሊፈጽሙ አይችሉም ብሎ ማሰብ አይገባም፤ ግን እንደ አባት አደሩ ሙያ በልብ ሆኖ መሆን ያለበትን መከውን ይገባል ባይ ናቸው እኔ እስኪገባኝ ድረስ።
ምክንያቱም እኔ በአያቴ እግር ሥር ስላደኩኝ አገላለጻቸውን ከልቤ ሆኜ አዳምጫዋለሁኝ፤ አባቶች ወዘፍ እድርገው ነው የሚናገሩት። አባቶችችን ሊቀ ሊቀውነት ቤተክርስትያናት ተደሞቸው ከቅኔው ነው የሚነጨው፤ ዕድምታቸው ከማይመረምር መንፈስ ነው የተሰጣቸው። እንጸልይላቸዋለን ነው የሚሉት።
የሃይማኖት አባቶችም በጸሎታቸው፤ አቅም ያላቸውም በአቅማቸው፤ አብሶ ውጪ ያለው የዲያስፖራው ወገን በሚችለው ሁሉ ነገሮችን በመዘናጋት ሳይሆን ሊሆን ይችላል ብሎም ሳይዝል፤ ሳይዘነጋ ሳይሸበር ተረጋግቶ እንደ ሰው ሊደርስ ይችላል በማለት መከታትል አለበት ነው የሚሉት እኒህ አባት።
የሚዲያውን ቃጠሎ ዝቅ አድርጎ ግን ተግባር ላይ ተገኙ ነው ሚስጢሩ እንጂ ፌክ ነው ብላችሁ ተዘናጉ አይደለም ዕድምታው።
ምንም አልጠራጠረም እኔ የሆነው ሁሉ ጣምራ ጥቃቱ ተፈጽሟል ብዬ አስባለሁኝ ግድያውም እገታውም። የግድያ ሙከራው በተበከለ ሁኔታ፤ ያ ሳይሳካ ሲቀር ደግሞ የሥልጣን እግዳ።
በነገራችን ላይ እገታው እሳቸው ብቻ ሳይሆኖ ዶር ለማ መገርሳም አሉበት ባይ ነኝ። እሳቸውም ታግተዋል። ለዛ ነው አሁን ለሌላ ፌክ ብአዴን ደግሞ ኤርትራ ሄደ የምንባለው፤ በእግሩ ገባ ብለው እኮ ዜና ሰርተው ነበር እዛ ኤርትራ አለ ስለሚባለው የ አማራ ዴሞክራሲ ታጣቂ።
አቅሙ በተተኪ ነው የነበረ። ሁለቱንም ቦታ ማራቆት የአዲሱ አንጃ እና የወያኔ ሃርነት የጋራ ግንባር ታምራዊ ሂደት ግቡን መቷል። ግብ እንዲመታ፤ መሰረት እንዲይዝ የሚያደርገው ደግሞ አቅም ያለው ሃይል ፌክ ነው ብሎ መዘናጋቱ ነው፤ ለዛውም ሊቃውንትታ። ሁለቱም አዬር ቦሌ ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡበት ሁኔታም ልብ በሉት።
ፌክ በሆነው በአባቶች ጉብኝት የቢዲዮ ክሊፕ ሊሂቃኑም ተሸውደዋል። እርግጥ ነው ያ የቢዲዮ ክሊፕ ከቤተ መንግሥት ውጪ በአበው መኖሪያ ቤት ነው የተከናወነው። ያ እውነት ነው። መንፈሳቸውም ልበ ሙሉ ነው። ይህም እውነት ነው።
ነገር ግን ይህ የተደረገበት ምክንያት አባቶች ደህና ናቸው አብይም አልታገተም ነው። በሙሉ እኮ የወያኔ ሃርነት ትግራይ የመንፈስ ማህበርተኞች ናቸው። ታስታውሱ ከሆነ ፈንጠር ብለው ነበር ብጹዑ ወቅዱስ አባታችን አቡነ ማትያስ ነገር ግን ና ከጀርባ ሁን ተብለው ተጎተው ነው ከበስተሆዋላ የሆኑት። እንደገባኝ እሳቸውም የተረዱት ነገር እንዳለ ይሰማኛ፤ ተባባሪ ናቸው ማለቴ ግን አይደለም፤ እርቁ በቅንነት ነው የተቀበሉት።
የሆነው ቢያንስ መስቀል የያዙትን አባት እመኑ ነው፤ ያ ድርማን እንኳን በማስተዋል ለመመርመር አለመቻል፤ ጅልነት ነው። … ያ ነው ፕ/ አለማርያምን ሽውድ ያደረገው እዩት ደጋግማችሁ …
ሂደቱን በሙሉ እገታው ብትክክል ታዩታላችሁ። በር ሲዘጋ ሲከፈት ወዘተ አቋቋሙን ወዘተ ...እሺ ይህም ይሁን ስለም ዲያቆን ዳንኤል ክብረት አልተገኘም?
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ በአቡነ መርቆርዮስ መኖሪያ ቤት ያደረጉት ሙሉ ቆይታ
ይህም የሆነበት ምክንያት ቅድስት ተዋህዶ ለቀጣዩ ሃላፊነት እንድተጋ ከአብይ መንፈስ የተቀዳ አደራ እንዲኖርባት ለማድረግ ነው።
ሌላም ለአዲስ አመት እንኳን አደረሳችሁም ሊቀጥል ይችላል ለምስል የሚሆኑ ነገሮች ቀጣይ ናቸው … የእኛ የነጻነት ትግል ልብ አልቦሽ መሆኑን እኳ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ በአካል ሲገኙ አንድ የሚሞገት ሰነድ እንኳን ማሰናደት አልተቻለም ነበር። ያው የእኛ ነገር ቅጽበት እና ወጀብ ነው የሚመራን። አሁን ደግሞ የፈጠጠው ጭብጥ እያለ ማዘናጋቱ ቢቀር ዝም ቢባል ምን አለ።
አሁን ተስፋ በርዶታል እንዲያውም በረዶ ውስጥ ነው ሊቀ ካህኑ ምሳሌ እንግዳ አንዳሉት በጸሎት መትጋት ይገባል። ሌላ አቅም ከሌለን ማለት ነው።
አሁን በትጥቅ አሰፈራራለሁ አክትሟል። ኡጋዴን ነበር የቀረው እሱም ገብቷል። ሌሎች በኤርትራ እጅ ናቸው ያሉት። ደምሂት የፕሮቶኮል ሹም ነው ከሁሉም ሳይሆን የሌላ ፍላጎት እና ምኞት ሲሳይ ነው። ቀጣዩ ደግሞ ድርድሩ ከእነሱ ጋር ይሆናል … በዚህ ውስጥ ሌላ ጀግና የሆነ መንፈስ እያዬሁኝ ነው … መስመሩ እና ትልሙ የተሳካለት … ኤርትራ እዬቀደመች ነው።
ቢያንስ … እሺ ሻንጣ እና ሸቀጥ ስትገዙ የከረማችሁት ደግሞ 25% ቅናሹን መጠቀም ነዋ … ሰባራ ወፍ ሳትቀድም ... ብር ነውዋ!
ግን ዶር ለማ መግርሳስ የት ናቸው? በምን ሁኔታ ላይ ይገኛሉ? በሉ ፌክ ነው የምትሉት ትራሳችሁን ከፍ አድርጋችሁ የሰላም እንቅልፋችሁን መጪ በሉት …
እኛ ደግሞ ዕውነት ነው የምንል ደግሞ ሌላ አቅም የለም የጸሎት ትጋቱ ይቀጥላል … መቼስ ተስፋ አያልቅም እና …
ሲጠቃለል በማይታወቅ መንገድ ላይ ነን … ግን የት ላይ ነን?
ቸር ወሬ ያሰመን እንዳንል ሁሉም ምንም አልተፈጠረም ብሎ ትጥቁን ፈቶ አንደመር ይላል። የቀደመው ከአብይ ሌጋሲ ነው የእንደመር ሞገድ፤ አሁን ደግሞ ከአዲሱ አንጃ እና ከወያኔ ሃርነት የመፍንቀለ መንፈስ ጋር ነው … መደመር? ጅልነት ይባል የዋህነት አይታወቅም? ልዩነት አለው በዶር ደብረጽዮን ሌጋሲ መደመር እና በአብይ ሌጋሲ መደመር ...
አደብ ማስተዋል እርጋታ ስክነት አቅም ማወጣት አብይን እስክ ሌጋሲው ከእግታ ማስፈታት ሲቻል ብቻ ነው … በሌላ ነገር ግን መደመር ለወያኔ ሃርነት ትግራይ እንጂ ለዛ ተስፋ ላደረግነው ተስፋ አይደለም።
ይደገማል ዶር ለማ መገርሳ የት እና በምን ሁኔታ ላይ ናቸው?
ነፃነት ለአብይ እና ለሌጋሲው!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
ማለፊያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ