ግልበጣ በዬፈርጁ። ድንግዝግዝ በብርዝ ዲቃላዊ መንፈስ።

ቆራጣ ነገር ለሚዛናዊ ዕይታ።
„እውቀትን ለማን ያስተመረዋል፤? ወይስ ወሬ ማስተዋልን ለማን ይሰጣል? ወተትን ለተው ወይስ ጡትን ለጣሉ ነውን? ትእዛዝ በትእዛዝ፣ ትእዛዝ በትእዛዝ ‚ሥርዓት በሥርዓት፣ ሥርዓት በሥርዓት፣ ጥቂት በዚህ ጥቂት በዚያ“
ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፲ ከቁጥር ፱ እስከ ፲
ከሥርጉተ ©ሥላሴ 16.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።


·         መነሻዬ።

https://www.youtube.com/watch?v=orfish9aARg

Ethiopia - በአዳማ ከተማ የተነሳው ብጥብጥ ዝርዝር መረጃ ይመልከቱ


  v     መንትዮሽ እይታ በዚህ ዜና ውስጥ።
  • ·      አንደኛው።

አንደኛው ዶር ለማ መገርሳን አዬሁኝ። ግን ከቀደሙት አመራሮች ከማውቃቸው አንድም ሰው የለም። ተሳታፊው ኬፕ ተዘጋጅቶለታል። ዓርማው  ኦህዴድ የቀደመው ዓርማ ነው። ኬፑን እራሱ ሁሉም አላደረጉም። ስለምን የ ኦነግ አርማ ከዚህ እንዳልታዬ አላወቅም፤ ሚሊዬነም አዳራሽ ያን ያህል የፏለለ አርማ ... 

ታዳሚው እንደምርጫው መብቱ ተጠብቆለታል። ዶር ለማ መገርሳ ተዝቆ በማያልቀው የስሜን አሜሪካ የህዝብ ፍቅር ከተጠመቁ በኋዋላ ዛሬ ሳያቸው በዛ የሞራል ልዕልና ውስጥ ሆነው አይደለም። አብሶ የሚኒያ ንግግራቸው ድፍረት፤ ወኔ ቆራጥነት የጉድ ነበር፤ የማላውቃቸው እስኪመስለኝ ድረስ። እኔ ብቻ አይደለሁም ሌሎችም መሰል ዕይታ ነበራቸው ...

ዶር አብይ አህመድ ጠ/ ሚር ሲሆኑ ደስታቸውን የገለጹበትም ዘይቤ ልዩ ነበር።  በተለይም የአንቦው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ የነበራቸው  የዶር ለማ መግርሳ የማሸነፍ ለዛ እና ውስጥ ዛሬ የለም። በቀዘቀዘ እና በደመነ መንፈስ ውስጥ ነው ያዬኋዋቸው። ሰላም መሆናቸውን ማዬት ግን ጥሩ ነው ብያለሁኝ። እውነት ለዚህ ጉባኤ ብቻ ካልሆነ፤ ምክንያቱም ዛሬ በሌላ ምዕራፍ ውስጥ ናት ኢትዮጵያ። ያልታወቀው መንገድ ትእይንቱ ቀጣይ ነው ... ተኝተን በለኝም ስላልን።

·      ·      ሁለተኛው

በዚህ ዜና ላይ አንድ የሴቶች ዓለም አቀፍ ኮንፈረንስ እዬተካሄደ እንደ ዜናም ተዘግቧል። የዓለም አቀፍ የሴቶች ቡድን በአዲስ አባባ የሰላም ኮንፍረንስ እያካሄደ ነው። በዚህ ጉባኤ ላይ የቀድሞው / ሚር የአቶ ሃይለማርያም ባለቤት / ሮማን ተስፋዬ ናቸው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት። ግልበጣ በዬፈርጁ እንዲህ አምሮበታል። 

እናስ ይህስ ከምን ይመደብ ነው ጥያቄው? ዳማዊ እምቤት / ዝናሽ ታያቸው የት ሄደው ነው በክብር የተሸኙት ቀዳማዊ እመቤት / ሮማን ተስፋዬ ጉባኤውን በንግግር እንደዲከፍቱት የተደረገው? ነው ወይንስ እንደ ቅዱስ ሲኖዶስ ደግሞ አሁንም ሁለት ቀዳማይ እመቤት ተመደበልን? መቼም የቋንቋ ጉዳይ ነው አትሉኝም። እያንዳንዱ አገር በራሱ ቋንቋ ንግግር ማድረግ ይችላልና።

ስለዚህ ወደ ማጠቃለያው ስንመጣ / ሚር አብይ አህመድ ከነቤተሰባቸው ነው ታግተው ያሉት ያልኩትም ይህንኑ ነው። እዛው ቤተ መንግሥት ግን እስር ውስጥ ናቸው።

እንግዲህ ይሄአክዜና ከሆነ መዝኑት።

የብፁዑ አቡነ መርቅሪዮስ ጉብኝት ሆን ተብሎ ለቅብ እና ለማረጋጋት የተሰራ ነው። ክንፍ ሁሉ አውጥተው ይበሩ ይመስል በሩ እንዴት እንደ ተዘጋ ተመልከቱት። ወታደሩ ውጪ ሆኖ መጠበቅ ሲጋባው በሩን ዘግቶ ነበር የቆመው።
ጠ/   አብይ አህመድ በአቡነ መርቆርዮስ መኖሪያ ቤት ያደረጉት ሙሉ ቆይታ ልክ የኢምሬትን፤ የሳውዲን ልዑክ ሲያነጋግሩ የነበረው ዓይነት የጨለማ ትዕይትን ነው ያለው።

የሚያሳዝነው ልብ ያላቸው፤ አቅም ያላቸው ሃይሎች የተሳሳተ መረጃ ነው እያሉ የሚያዘናጉት ነገር ነው። ጊዜው እያለፈ ነው ስንት ጉዳይ ሊፈጸም ሲገባ ድግምት ያለበት መስሎ በረዶ ሆኗል።

ገራሚው ነገር የቁም እስረኛውን / ሚር ጉዳዬ አጀንዳዬ ከማለት ይልቅ ዴያስፖራው ስለ አጤ ሚኒሊክ፤ ስለ አኖሌ ሃውልት እና ወዘተ ይሟገታል። ዙሮ ተመልሶ ከዛው ይዳክራል። መቼ እንደሚዘጋ ይሄ አጀንዳ አይታወቅም። ውሻ ሥጋ እዬተጠለለት እንደሚናከስ በዚህ እና በዚያ አቅም ሲፈስ ውስጠ ተስፋ በተናደ መሰረት ላይ ስለመሆኑ ልብ ሊባል አይገባም። 

አሁን እኮ አስቸኳይ ስብሳባ፤ አስቸኳይ ቴሌ ኮንፈርስ አንድርጎ የተጠናከረ ዘመቻ ማድርግ ይገባ ነበር ነገ ደግሞ ገድለው እስከያውጁ ከመጠበቅ … ማወቅ ለሚገባቸው አካላትም ቢያንስ ስጋታቸውን ማሳወቅ ይገባቸው ነበር፤ ግን ሁሉም ጸጥ ረጭ ብሏል። 

ሌላው አሳዛኙ ጉዳይ ፌክ የወያኔ ሃርነት ትግራይ እና የጠላፊዎችን ዜናዎችን አምነው ነገ ሌሎችም ቀሪዎቹ ደግሞ ወደ አገር ቤት ይገባሉ። ይህ እንግዲህ መራራው ዜና ነው ደግሞ። 

/ ሚር አብይ አህመድ ስላልሞቱላቸው አግተዋቸዋል እስከ ቤተሰባቸው ድርስ። ይህን ባትጠራጠሩት እና የሚሆን ነገር ብታደርጉት መልካም ነው፤ አብሶ ውጪ አገር ለፈንድ ራይዚንግ ሹመቱ የተሰጣችሁ ለዚህ የመከራ ቀን ፈጣሪ ነው አስቀድሞ ያሳነዳችሁ እና።

ዛሬ ዲያቆን ዳንኤልም ሌላ ጉባኤ ላይ አይቸዋለሁኝ። ለበጉ ሰዎች ሽልማት ከሚያመቻች አንድ ቡድን ጋር፤  ያነንም ቪዲዮዎ በዛ ንቃቱ፤ ግርማው ልክ ሆኖ አላዬሁትም? እኔ ዜናው ሳይሆን የውስጥ ገጹን ነው ማዬት እምሻው። ምን እዬሆነ ነው? ድንግዝግዝ በብርዝ ዲቃላዊ መንፈስ

Ethiopia: 2010 ‘የበጎ ሰው ሽልማትእጩዎች ይፋ ሆኑ!

ነፃነት ለአብይ እና ለቤተሰቡ መንፈስ! 
ቸር ወሬ ያሰማን፤ ወደ ልቦናች ይመልሰን። አሜን!

የኔዎቹ ኑሩልኝ!
በጸሎት እንትጋ!

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።