ኡኡ የአድማጭ ያለህ! ሰሚ ቢገኝ!
ማመዛዘን - ማገናዘብ - ማያያዝ - ማወራረስ - መመርምር - አቅጣጫን ማወቅ። „በዬሰባቱ ዓመት መጨረሻ የዕዳ ምሕረት ታደርጋለህ።“ ኦሪት ዘዳግም ምዕራፍ ፲፭ ቁጥር ፩ ዕንባ በጣምራ ኢትዮጵያ ላይ በተደሞ ቀጥሏል .. ወንበሩ ባዶ ነው ... . ከሥርጉተ© ሥላሴ 16.08.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ከሰሞናቱ „አክ ወሬዎች“ የሚል ከሊቀ - ሊቃውነቱ የፕ/ሃይለማርያም አለማርያም አንድ ጠንከር ያለ ጹሁፍ ቀርቧል። አታሟርቱባቸው ዓይነት ነው። የሊቀሊቃውነቱ ቅንነቱ ብቻ ሳይሆን ንጹሁ የሆነ መንፈሱ ይመርካል ውስጣቸው ንዑድ እንደሆነ ያመለክታል። ግን የሆነውን ነገር ግን፤ በመሆን ላይ ያለውን ነገር ግን ... አልዳሰሰውም .. አብሶ ፕሮፌሰሩ የዶር አብይ አህመድን የብፁዕን አበውን ጉቡኝት መንፈሱን በማዬት ሙሉ ለሙሉ ዶር አብይ አህመድ ደህና መሆናቸውን በሥራ ብዛት እንደ ተሰወሩ ነው ያመኑት። አብይ ምንም አልሆነም ነው የሚሉት። እንዲያውም በዚህ ዙሪያ የሳሳበቸው ወገኖችን ያልተገባ መስዋዕትነት አድርገው ነው ያዩት፤ እንደ አፋቸው ቢሆን መልካም በሆነ ነበር። ግን የሆነው፤ በመሆን ያለው ነገር እሳቸው እንዳሰቡት አይደልም። በሳቸው ምትክ የተወከሉት ለጊዜው ዶር ሙላቱ ተሾመ ናቸው። በማዕካለዊ መንግሥት ደረጃ በተጠሪነት ሁለቱንም በአማካይ በፊርማ እዬከወኑ የሚገኙት። እርግጥ ነው ዶር አብይ አህመድ በድሮው አቅማቸው በመንፈስ ነፃነት ያወጧቸው ቃሎች በሙሉ ሙሉ ለሙሉ አብይ ከእነ ሙሉ ነፃነቱ ለማለት ያስደፍራል። ያ ያስደሰተኝ ለእኔ እንደገና የመወለድ ያህል ነው። ያ የሆነው ግን አዌርነሱ ስለጠነከረ ነው፤ ለማዘናጊያ፤ ትጥቅ ለማስፈታት ነው። እኔ እንደ ማስበው ከዚህ ጉዳይ ጋር አንድ ግዙፍ መሰረታዊ