ፍቅር፤ ምህረት፤ ይቀርታ ታማኝነትን ይጠይቃል።

ፖለቲካም ታማኝነት 
ይርበዋል፤ ይጠማዋል፤
ይናፍቀዋልም። 
„ልባችሁ አይታወክ በእግዚአብሄር እመኑ፤
   በእኔም ደግሞ እመኑ።“

የዮሖንስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፬ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
06.10.2018 ከጭምቷ
ሲወዘርላንድ።
                                                     ክብር ናችሁ! ኑሩልን!
  • ·       መቅድም።

እንኳን ደስ አላችሁ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ፤ እና አቶ ደመቀ መኮነን። እንኳን ደስ አላችሁ ቅድስት ኦርኦቶዶክስ ተዋህዶ እና ድምጻችን ይሰማ። እንኳን ደስ አለህ የ ኢትዮጵያ ቅን እና ቻይ ህዝብ። 
  • ወግ። 

ክብርት ወ/ሮ ሙፍሪያት ካሚል የእቴጌ ጣይቱን ዘመን ጠገብ የብርሃን ውቅር መክሊት ሥጦታ አስጠብቀዋል። ቀደም ባሉት ጹሑፎቼ የቀደመው ዓላማ ዲዛይን ይኸው መሆኑን አስቤ የኢትዮጵያን ሴቶች የፖለቲካ ብልህነትን አነገት እንዳያስደፉ ማሳሰቢያ ጽፌ ነበር። አሁን እሳቸው ያደረጉት ይህን ነው። የኢትዮጵያ ሴቶችን ታማኝነት ልቅና አሳይተዋል። ለፖለቲካ ፍጹም የሚያስፈልገው የአቅም ምንጭ ታማኝነት ነው። የ አገር ፍቅር ብሄራዊ ስሜትም እንዲህ ይገለጣል። ከኢጎ በላይ አገርን ማዬት ይኸው ነው አብነቱ። 

በዚህ ማዕቀፍ ውስጥ በህልሙም የማይገኘው ግን አፍቅሮተ ግራ ፖለቲካ ነው። ታማኝነት በግራ ፖለቲካ አሞራ በረረ ቅሉ ተሰበረ ነው። ቀን ሲገነባ አብሮ ይውላል ግራ ዝንባሌ ማታ ሲንድ ያድራል። „ጌታ ሆይ! ጌታ ሆይ!“ ያለው ሁሉ አማኝ እንዳልሆነው ሁሉ እንደ ማለት ….

አሁን የለውጡ አማራር ሊሂቃን ቁጥር ከፍ ብሏል። ወ/ሮ ሙፍሪያት ካሚል፤  አቶ ሚሊዮን ማቲዮስ፤ አቶ ደመቀ መኮነን፤ ዶር ለማ መገርሳ፤ ዶር ገዱ አንዳርጋቸው፤ ዶር አንባቸው መኮነን፤ ዶር አብይ አህመድ። ለውጡ እና መሪዎቹ በውል ሆነው አሁን „ማን ይፈራል ሞት“ ማለት ይቻላሉ።

ትግራይ ውስጥም ሥ/ አስ/ ኮሜቴ አባል አይደሉም ግን መንፈሳቸው ጤናም የሆኑ አንዲት ብልህ ሴት ወደ ትግራይ ክልል የማዕከላዊ ምክር ቤት መጥተዋል። እሳቸው ቢያንስ ትግራይ ውስጥ ላለው የመብት ረገጣ ጧፍ ይሆናሉ ብዬ አስባለሁኝ፤ ሌላው ቀርቶ የማዕከላዊ ምክር ቤቱ የትግራዩን ማለቴ ነው ፎቶ ሲነሱ አዲሶቹ እንዳይታዩ ነባሮቹ ጋርድዋቸው ነው የተነሱት። አዲሶቼ በቁመታቸው ራሱ አጫጭሮች ናቸው።

በሃሳብ ረጅም ሆነው ትግራይ ከተፈረደባት የጫካ አስተምኽሮ ትላቀቅ ዘንድ መትጋት ይጠበቅባቸዋል። ስለ ነገ የትግራይ ህፃናት መከራ ዛሬ መትጋት ይጠበቅባቸዋል። ለጊዚያዊ ከንቱ ውዳሴ ሳይሆን ዘላቂ የሆነ ትውልዳዊ ድርሻቸውን መወጣት ይኖርባቸዋል። ትግራይን ሳይነካ ያለው ይህ ሁሉ የዕንባ ጎርፍ መንስኤው ማን እንደሆነ እንቆቅልሹን መፍታት ይጠበቅባቸዋል።  ምክንያቱም ነገን ለልጆቻቸው፤ ለልጅ ልጆቻቸው ዕጣ ፈንታ ደርቆ መምጣት ዋነኛ ገፊ ሃይል ነውና ይህ ሽምቅ የሴራ ምኽዋር እና ድር።

የሆነ ሆኖ አሁን ሦስቱ ኦዴፓ/ አዴፓ/ እና ደኢህዴን 

በአንድ መንፈስ ውስጥ ማዬት የሚያስችል አቅም ፈጥሯል ይህ ጉባኤ ግን በተወሰነ ደረጃ፤ በአንጻራዊነት ነው፤ ኦዴፓ ገና እጅግ ግዙፍ ጣጣ አለበት፤ ራሱ አመራሩ ኦሮሞ ሥልጣኑን መያዙን እንጂ ኢትዮጵያዊ መንፈስ ጋር ገና ጊዜ እዬጠበቁ ፈንጆች ይኖሩበታል። ታሪክን በማሽሎክ የተፈጠረው ግድፈት ለማስተካካል ሆኖ መገኝት ይጠይቃል። የተንጠራሩ መንፈሶች በልካቸው እንዲሆኑ ሊገሩ ይገባል። 

ኢትዮጵያዊነት መናጆ ማንነት አይደለም።፡ኢትዮጵያዊነት አውራ ማንነት ሁሉንም የሰጠ፤ ሁሉንም የፈጠረ፤ ሁሉንም ማድረግ የሚችል፤ ሁሉንም ለዚህ ክብር እና ልቅና ያበቃ ረቂቅ ሰማያዊ ስጦታ ነው። ኢትዮጵያዊነት ቢቀበሉት ቢሆኑበት ጸጋን ቢያበረክት ቢያሰከብር እንጂ ታናሽ የሚያደርግ ማንነት አይደለም። ቅዱስ ወንጌልም፤ ቅዱስ ቁራንም ያከበሩት ትንቢት የተነጋሩልት ድንቅ የገድል ማንነት ነው። 

የአዲስ ምዕራፍ አህዱ ሊጀመር የሚገባው ከዚህ አስኳል ሊሆን ይገባል። አሻቅቦ ከማዬት ቁሞ ቀር የሆነውን „ኢትዮጵያ ሱሴ ናትን“ መድፈር በእጅጉ ያስፈልጋል። ሌላው የኦዴፓ ፈተና ምልዕት ለሰጠው እዮራዊ ዲካ የላሽ መታመን እና ፍቅር ያለው ታማኝነት ከራሱ፤ ሰውሮ ከያዘው ፍላጎቱ ጋር ማስታረቅ የመቻሉ አቅሙ የሚታይ ይሆናል። የሊሂቃኑ ታማኝነት ዘላቂነት ዘለግ ብሎ ለማዬት የምንሻ ፍጥረቶች አለን እና።

ለመሆኑ ዛሬ ክብርት ወ/ሮ ሙፍርያት ካሚል የከፈሉትን መስዋዕትንት ምን ያህል በክብር ይዘልቃል በኦዴፓ መንፈስ ውስጥ?

ይህን የምለው ያለምክንያት አይደለም። ከግዞት ወደ ነፃነት በተካሄደው ተጋድሎ ያን ረጅም የጨለማ መጋረጃ የቀደደው የአማራ የህልውና የማንነት ተጋደሎ መንፈስ ቅርብነት በውል የተጋባው የብአዴን/ አዴፓ ቅንነት "ጣና ኬኛን" ያስተናገደበት ጥበብ ሃቀኝነት እና ታማኝነት ዘላቂ መሆኑ መክሊቱ አድራሻው ስለሚጠፋብኝም ነው። 

ከጣና ኬኛ ቀጥሎ ጫናውን ብቻውን ተሸክሞ የባጀው የአማራ ክልል እና የሞተሩ የአቶ ደመቀ መኮነን ከጠ/ ሚር እጩነት ውድድር ራሳቸውን ማግለል ብቻም ሳይሆን ብአዴን/ አዴፓ ድምጹን ሙሉውን ለኦህዴድ/  ለኦዴፓ አምኖ በክብር መስጠቱ ነበር ጎኽ በኢትዮጵያ እንዲቀድ ያስደረገው።

ለዚህ የተጋድሎ ሥጦታ የኦህዴድ/ የኦዴፓ ታማኝነቱ ለእኔ ምንም ነበር። ራሱ  የኢትዮጵያ ህዝብ ይህን ብልሃት ተገልጦ አልተነገረውም። ይህ ቢገለጥ ይህ ቢታወቅ ኖሮ ልዕልት ቤቲ ታፈሰ በሌላ ገፊ ሃይል አቋም ይዛ ቃለ ምልልሱን ከ አብን ጋር ብትደረግም የ ዕውነት ዕርሾ ስለሚኖራት አንድ አቀጣጫ ተከተላ ያን መሰል ቃለ ልልስ ዝግጅት ባልነበራት። የመረጃ እጥረት አለበት ራሱ የ ኦሮሞ ህዝብ። ክብር ለሚገባው ክብር ተነፍጎ ወጣት የአማራ ሊሂቅ ዶር ደስአለኝ ጫኔ በኤል ቲቪ በነበራቸው ቆይታ ጋር ምጥ አናስተናግድም ነበር። ወቅቱን የጠበቀ መረጃ መስጠት ከዚህ መሰል የህዝብ መንፈስ መከፈል ይታደጋል።  

የሆነ ሆኖ ከዚህም ያለፉ ቁም ነገሮችን ዛሬ ማንሳት እሻለሁኝ። ምርጫው ነፍሴ ዲዛይን ባደረገቸው መልክ ስለ ተከወነ፤ አሁን የተከፋሁባቸውን ነጥቦች ማንሳት እችላለሁኝ። ባለፉት 6 ወራት አማራን ጫኝ ፓሊሲ ነው የነበረው የአብይ ካቤኔ። እንደ ህዝብ፤ የአማራ ህዝብ፤ እንደ ድርጅት ደግሞ ብአዴን/አዴፓ፤ እንደ መሪ አቶ ደመቀ መኮነን ለሰጡት ታማኝነት ብቻ ሳይሆን አቶ ደመቀ መኮነን ከበታቼ የነበረው የበላይ ሆኖ መጣ ሳይሉ ዝቅ ብለው ሲታዘዙ፤ አብረው ሲባትሉ አዲሱ ለዛ መሰረታዊ ታማኝነት የተሰጠው አክብሮት ቁልቁል ኤሉሄ ያለ ነበር። እኔ ግልጽ እና ቀጥተኛ ሴት ነኝ። 

ይህን አመክንዮ በዝርዝር ልሄድበት የምሻው ነገ መደገም ስሌለበት ነው። ዛሬ ደኢህዴን/ የደቡብ ህዝቦችን እና የኢትዮጵያ ሴቶችን የወከሉት ክብርት ወ/ሮ ሙፍሪያት ካሚል የሰጡት ፍጹም መታመን ነገ ደግሞ ምላሹ ቁሞ ቀር እንዳይሆን ስለሚያሰገኝ ጭምር ነው። ተጠቅመህ እንደ አሮጌ አካፋ እና ዶማ መወርወር በዚህ 6 ወራት ያዬሁት ጉዳይ ስለሆነም።

ለእያንዳንዱ የለውጥ አካል አንዱ ለሌላው ታማኝ መሆን ግድ ይላል። ስለ ፍቅር፤ ስለምህረት፤ ስለ እርቅ ሲነገር ሲወደስ መጀመሪያ ለዛ ያበቃው ልዕለ መንፈስ ክብር ዕወቅና መስጠትን ይጠይቃል። "የኦሮሞ ደም ደሜ ነው" አስተምህሮ መሰለኝ የህሊና ሃዲድ የሠራው። ያ ዕውቅና በ አደባባይ ለማን እንደተሸለመ ተመልከተናል። መንፈስን መሸለም ባይቻልም ... አማራ ዛሬ ጸሐፌዎች አለንለት። ለቃጣዩ ትውልድ ታሪኩን አሳምረን እንሠራለት አለን። 

ዛሬ ራሱ ከራሱ ከለውጡ ሐዋርያ በላይ ሌላ የውጭ ሃይል ይብልጥብኛል ብሎ የራስን አቅም ማግለል ያመጣው መከራ ነው መሬት ላይ የምናዬው ይህ ሁሉ ምስቅልቅል ሆነ ህውከት። የአብይ ካቢኔ የበለጠበትን አስበልጧል። የ አብዩ ሌጋሲ የሚበልጠብትን አቀስሷል። የሚበልጥበት ቀን ሞት እንኳን ፈቅደው አብረው የተሰለፉት የካቢኔው አባላት እና አካላት መሆን ይገባቸው ነበር። የአብይ መንፈስ „ሳይቸግር ጤፍ ብድር“ ፍለጋ ሲሄድ መሃል ላይ ክፍተት ፈጥሮ ታሪካዊውን እዮራዊ ሥጦታውን አሽሉኮት ነበር። ለድንገት ለጥቂት ተርፎለታል። ነገ ልብ ከሰጠው ደግሞ ይታያል ... ከተማረበት ማለት ነው። ሁሉን አስደስቶ መጓዝ አይቻልም። ሌላው ገራሚዊ ነገር የ አዋሳው ጉባኤ ቅደመ መሰናዶ ... 

ስለምን እንዴት? እንዴት ማለት ጥሩ ነው ይላሉ ጎንደሬዎች። አቶ ደመቀ መኮነን ሳይመረጡ እንደ ታቀደው ዶር አንባቸው መኮነን የአዴፓ ሊቀመንበር ቢሆኑ ኖሮ፤ ጉባኤው ከሁለት ይሰነጠቅ ነበር። ዶር አንባቸው መኮነን ወደ ምክትል ጠ/ ሚር የማምጣት ዕሳቤው ፌክ ነው የነበረው። ደግሞም አይቻልም ነበር። ይህን በእርግጠኝነት እገልጠዋለሁኝ። 

የታሰበው ወ/ሮ ሙፍርያት ካሚልን ምክትል አድርጎ ማምጣት ነበር። ይህን ደግሞ የወያኔ ሃርነት ትግራይን ሙሉ ለሙሉ የሚያስደስት በተወሰነ ደረጃ ወያኔ ሃርነት ትግራይም የለውጡ አካል ለመሆን የሚፈቅደበት ሁኔታ ይመጣል ተብሎ ዲዛይን የተደረገ ነበር። ለዚህ ነው አማራ መሬት ላይ ጫናው ከፍተኛ የነበረው። አማራ በራሱ የቤት ሥራ እንዳይጠመድ፤ እንግዳ በማስተናገድ የውቂ ደብልቂ ጊዜ እንዲያሳልፍ ፍርጃውም ይኸው ነበር። 

ወደ ቀደመው ምልስት ሲሆን ዶር አንባቸው መኮነን ለእጩ ምክትል ጠ/ ሚር ተወዳድረው ቢሆን ኖሮ በምንም ታምር ወ/ሮ ሙፍርያት ካሚል ራሳቸውን ከእጩነት አያገሉም ነበር። ምክንያቱም ብሩኽ ዕድል ነበራቸው ጠ/ ሚር ለመሆን ሁሉ። ስለምን? እሳቸውን ሙሉ የደኢህዴን እና ሙሉ ወያኔ ሃርነት ድምጽ እንሚሰጣቸው እርግጠኛ የሚያደርጉ ጭብጦች ነበሩ።

ለጠ/ ሚር አብይ አህመድ ኦዴፓ እና አዴፓ ድምጽ ይሰጡ ነበር። እኩል ድምጽ ከመጣ ሰብሳቢው የሚሰጠው ድምጽ የመጨረሻ ይሆን ነበር።  የአስመራጭ ኮሜቴው ሰብሳቢ ደግሞ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ፈቃድን አስፈጻሚ ናቸው።
ስለዚህ ክብርት ወ/ሮ ሙፍርያት ካሚል ጠ/ ሚር የመሆን ዕዳላቸው ሰፊ ይሆን ነበር። የኦዴፓ ዲዛይንም ውሃ የበላው ቅል ይሆን ነበር። ሁለት ያጣ ጎመን ይሆን ነበር አጤ ኦዴፓ / ኦህዴድ። 

እኩል ድምጽ ያልኩት ያም ላይሆን ይችላል፤ ዶር አንባቸው መኮነን ተወዳደሪ ከሆኑ አዴፓ የራሱን ወኪል ሊመርጥ ይችላል። በዛ ላይ በኦዴፓ እና በአዴፓ ያለው ታማኝነትም ከሁለት ይተረተር ነበር። በሥም መመሳሉን ያህል ቀላል አልነበረም የሚሆነው።  

ክብርቷ ይህን የጠ/ ሚር ሃላፊነት የመወጣት አቅም አላቸው ወይ ብንል ለዛውም ከዶር አብይ አህመድ ጋር ሲነፃጸር ማወዳደር አይቻልም። በዚህ ምስቅልቅልስ አዴፓ እና ኦዴፓ አብረው በግንባሩ ውስጥ ይቀጥላሉ ሲባል የማይሆን ነበር። ሌላ ትርምስ፤ ሌላ ድብልቅልቅ፤ ሌላ ምስቅልቅል ይከሰት ነበር። ያው ዙሮ ተመልሶ እንደ ሰሞናቱ የዓለም መሳቂያ እንሆን ነበር። 

ኦዴፓ/ ኦህዴድ ሊቀመንበርነቴ አይነካም ብሎ አስልቶት ሊሆን ይችላል የአቶ ደመቀ መኮንን ራሳቸው ማግለልን በሚመለከት። አይምሰለው። የጠ/ ሚር ቦታውን የሚያጣበት ፈርታይል የሆኑ ጥቁር ጉዳዮች ነበሩበት። በዚህ ውስጥ የምናዬው የአቶ ደመቀ መኮነን ቅንነት ነው። የዚህ አቶ ደመቀ መኮነን ከሥልጣን የማግለል የትዕይንት ዲዛይን ማግስትን የሚታደግም አልነበረም። ኦዴፓን ያዳነው ኢትዮጵያን ከውስጡ የተቀበለው መንፈስ ብቻ ስለመሆኑ ሚስጢር ይገለጣል።

አቶ ደመቀ መኮነን በመንፈስ የማግለል ሁኔታ ገና ከውጥኑ የተከወነ ነበር። እንዴት? አሁንም እንዴት ማለት ይገባል። አቶ ደመቀ መኮነን ከለውጡ ማግስት አንቦ ተገኝተው ቄሮ ጀግና እንዲሉ ተደርጓል። ያ የመጀመሪያው ምዕራፍ ነበር። ሁለተኛው ምዕራፍ አቶ ደመቀ መኮነን ጅጅጋ፤ መቀሌ በነበረው ጉዞ የግዙፉ የልዑክ አባል ነበሩ። በዬጉባኤው ዬክልሎቹ መሪዎች ንግግር ለህዝባቸው አድርገዋል።

ራሳቸውን በወከለው፤ እሳቸውን በመረጠው በአማራው መሬት ላይ ግን ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ሲገኙ የብአዴን መሪ/ የአዴፓ ሊቀመንበር አቶ ደመቀ መኮነን አብሰንት ነበሩ። ሌላው ቀርቶ አማራ መሬት ላይ ሌላ ቦታ የታዬው ግዙፍ የመንግሥት ልኡክ አልሄደም። መላጣ ነበር። አዋሳ ላይ፤ ትግራይ ላይ፤ ሌላው ቀርቶ አፋር ላይ ልዑኩ ከ አማራ ክልል በብዙ የተሻለ ነበር፤ ጋንቤላ ላይ ዶር ለማ መገርሳ ራሳቸው ተገኝተዋል። ለዬክልሎች ሰፊ አትኩሮት እና አክብሮት ተሰጥቶ ነበር ለአማራ የተሰጠው ሳጅን አለምነህ መኮነን ነበር። ይህ ንቀትም ጭምር ነው። ለአማራ ህዝብም ውርዴትም ነው። 

ለዛውም ለብአዴን እንደዛ ለተሟሟተ፤ ለዛውም ለአማራ ልጆች ሆ! ብለን ለደገፍን፤ ስለ ኦህዴድ ለሞገትን ስጦታው ምን ታደርጋላችሁ ዓይነት ነበር። ሌት እና ቀን እንቅልፍ አልባ ለተገላታን፤ በስልክ ሰላማችን ላጧ ፡፡፡፡በ ኢሜል ስንት ግልምጫና ፍጥጫ ላስተናገድን ሥጣታው ያ "ምንም" ነበር። መሰረዝ። ይህም ሆኖ የአባቶቻችን አማላክ በሰጠን ጽናት ድጋፋችን ቀጠልን። መልካምነት ቢያተርፍ እንጂ የሚያጎድለው ምንም ነገር የለም እና።

ይህን ምዕራፍ ይዘን ዛሬን ስናይ የሆነው ሁሉ ዴዛይን የተደረገ ስለመሆኑ ልብ እንድንል ግድ ይለናል። ይህን ልብ ስንል የአማራ ህዝብ በመንፈስ ምን ያህል መገፋት እንዳለበትም እናስተውላለን። የአማራ ቅንነት ላደረገው፤ ላበረከተው አስተዋፆ እንኳን እንመስግንህ አለን ቀርቶበት፤ ዕውቅና መሰጠት ቀርቶበት የዛን ሞተር በምን ያህል እርቀት መገለሉ ምን ያህል እንደሆነ ህመሙን ቁስሉን እንመረምረዋለን - በተደሞ። „በሽታውን ያልተናገር መዳህኒት አይገኝም“ እንዲሉ … እንዲህ መገለጥ ይኖርበታል - ዛሬ፤ ምርጫው በፈለግነው መልክ ተጠናቋ እና።  በለማ አብይ መንፈስ አማራ ስለመኖሩ? 

እኔ እሳት ለብሼ እሳት ጎርሼ ማዕቱን ያፈሰስኩት በአቶ ደመቀ መኮነን ነበር። እውነትም ነበር። አዲሱ የአብይ ካቢኔ ልዑክ ተገዶ ይሁን ፈቅዶ ወደ ጎንደር እና ወደ ባህርዳር ጉዞ ሲያደርግ መሪውን አንጎል አልባ ነበር የተጓዘው። አንገት የሌለው ጉዞ ነበር።  መብራት አልባ ነበር የተጓዘው በድቅድቅ ጨለማ።

አቶ ደመቀ መኮነን በጎንደር ህዝብ አደባባይ ላይ እንዲታዩ አልተፈቀደም። ንግግር እንዲያደርጉ አልተፈቀደም። ለግንቦት 7 ሊሂቃን ግን የአብይ ካቢኔ ፈቅዷል። የወርቅ ካባም አሸልሟል። እነሱም ወገን ቢሆኑም፤ እነሱም ህዝባቸውም ቢሆንም ጎንደር፤ ነገር ግን የብርሃን ጉልላቱ መንፈስ ተረግጦ መሆን አልነበረበትም። ጎንደር እና አቶ ደመቀ መኮነን ስለምን እንዲነጣጠሉ እንደተፈለገ እዮር ይመርምረው። ለጎንደር አብዮት ግን አቶ ደመቀ መኮነን ዘውዱ ናቸው መሪውን የተጋድሎውን ኮ/ ደመቀ መኮነን ክብር አላስደፈሩም እና። 

በአሁን የምርጫ መሰናዶ ቀደም ብዬ በሰፊው ጽፌዋለሁኝ። አቶ ደመቀ መኮነን ፈቅደው አይደለም ጫና ስላለባቸው ነው እለቃለሁ ያሉት ብያለሁኝ። ቤት እንዲጠብቁ ተብሎው ነው ብያለሁኝ። ለእጩ ፕሬዚዳንትን እንደታጩ ቀድሜ ጽፌያለሁ። የአብይ ለማ ካቢኔ የምነገረው አማራነት አሞሌ ጨውነት አለመሆኑ ነው። በጥቂት ብጥስጣሽ ከረሚሎ መንፈስን በ አሃታዊ ኢትዮጵያዊነት ማስቀጠል ይከብዳል። የቀደመው ቅንነት ርህርህና ነው የሚበጀው። 

የሆነ ሆኖ ያ የውጫሌ ውል በአማርኛ እና በኦሮምኛ እንዲሁም በትግረኛ ሲጻፍ ፍቹ በተለያዬ አኳኋዋን ይተረጎማል። ግጫው ግጫ፤ ሰንደዶው ስንደዶ፤ አክርማው አክርማ፤ ግርምጣው ግርምጣ ሳይሆን ግራምጣው ግጫ፤ ግጫው አክርማ፤ አክርማው ሰንደዶ ነበር ወፊቱ ሹክ ስትለን።

አሁን አማራ የአባቶቹን ሌጋሲ መንፈስ አብሶ የኢንጅባረው ታምረ ገድል ሚስጢር ገለጠለት እና አቶ ደመቀ መኮነን እራሴን አገላለሁ ድራማ ደረመሰው። አይሆኑ አድርጎ ትቢያ አልብሶ ቀረበው። ይህን ጊዜ የማዕከላዊ የምህንድስና ውቅር መናድ ጀመረ። ይህንንም አስቀድሜ ኮለሜዋለሁኝ።

በዚህ በአዴፓ / ብአህዴን ጉባኤ ለተዘነጉት፤ ለተረሱት፤ ለተገፉት መሪው ክብሩ ግርማው ሞገሶ ብአዴን ጉባኤውን ያካሄደው በልደታቸው ዕለት ካባ አለበሰ። ቅባዕ የሰማይ ተሰጠ። ይህን ያደረገው ሰው አልነበረም የቅኖች አምላክ ክብር ገልጦ እንጂ። ያ የወርቅ ካባ ቃልኪዳን ነበረው። ቃል ኪዳኑ አማራ በአገርም ወስጥ ይኑር በውጭ ከደልዳለው፤ ከአባ ዝምታ፤ ከታማኙ ሊሂቁ ጋር በተክሊል የመንፈስ ጋብቻ የምንፈጽመበት ነበር። አሁንም ለወደፊትም እኛ ከደመቀ መኮንን ጎን እንቆማለን! 

አቶ ደመቀ መኮነን ባይመረጡ የእኔ ምርጫ የነበረው አዴፓ/ ብአዴን ስበሰባውን ረግጦ ወጥቶ ከግንባሩ እግር ብረት ሙሉ ለሙሉ ራሱን መላቀቅ እንዳለበት ነበር በኢሜል ከቅኖች ማህበር ጋር ስንመክርበት የሰነበትነው። ቀደም ባለው ጊዜ ዶር አብይ ጠ/ ሚር እንዲሆኑ በሰራሁት መልክ ስስራ ነው የሰነበትኩት - በትጋት። በተከታታይም እኔ ከአቶ ደመቀ መኮነን ጎን ስለመቆሜ ጽፌያለሁኝ ፈርሜበታለሁኝ።

ስለምን? ሴራ ስለመጸዬፍ። ዕውነት ስላሳዘነኝ። ታማኝነት ስላሳዘነኝ፤ ቅንነት ስላሳዘነኝ ነው። ወደፊትም ቢሆን ክብርት ወ/ሮ ሙፍሪያት ካሜል እና ደኢህዴን እንደሁም የደቡብ ህዝብም የከፈሉት መስዋዕትነት ታማኝነታቸው፤ ቅንነታቸው ኢትዮጵያዊነት ዕውነት ነውና ከእውነት ጎን ለመቆም ያደረጉት ተጋድሎ የአብይ ለማ ካቢኔ ዋጋ እንዳያሳጣው አበክሬ ላስገነዝበው እሻለሁኝ። ዛሬ የሆዴን አውጥቼ እምጽፈበትም ግድፈት እንዳይደገም ነው።

 አሁንም እኔ ከኢህዴን ጎን እቆማለሁኝ። ስለምን? ውገናዬ ዕውነት ስለሆነ። ትናንትም ለማውያን ዕጣ ነፍሴን ስለሆን ዕውነትን ወግኜ ነው። ትናንት ኦህዴድ ጭንቅላት ብቻ ሳይሆን ህሊና አለው፤ ሙሉ አቅም ችሎታ ክህሎት አለው፤ ብሄራዊ ሃላፊነት ይወጣል፤ ኢትዮጵያን መምራት ሙሉ አቅም አለው ብዬ አምኜ ነበር የታገልኩት። ስለምን ዕውነት ወገኑ ዕውነት ብቻ ስለሆነ። የአብይ ለማ ካቢኔ ምርጫ ግን በዚህ መስመር አላገኘሁትም።

እኔ ቀደም ባለው ጊዜ ኦሮምኛ ቋንቋ ሁለተኛ ቋንቋ እንዲሆን ከታገሉት ሰዎች አንዷ ነኝ። አርሲ ጢቾ ህዝብ በቋንቋ የነበረውን ሁኔታ አውቀው ስለነበር። የዛሬው የልብ ወዳጃችሁ ጸሐፊ አቶ ኤርምያስ ለገሰ እንዲህ የእንሱ መንፈስ መሰሉ በቅጅ ሊጠቀምበት ስለምን ኦሮምኛ ትግረኛ አብይ ተናገረ ብሎ ሲያብጠለጥለው ይህን ጽፌያለሁ። ዛሬ እንዲያውም ክብር ለሚገባው ክብር ስጡ ይላል እና ቃለ ወንጌል ዛሬ ሳተናው ድህረ ገጽ በድጋሚ ለጥፎታል።

ቋንቋ ጥበብ ነው ለእኔ፤ እንጂ መወቀሻም፤ መነቀሻም ሊሆን ከቶውንም አይገባም (ሥርጉተ ሥላሴ)
May 6, 2018

አሁን በጠቅላላ ባዬሁት የ5 የኦሮሞ ድርጅቶች መግለጫ፤ የኦቦ አዲሱ አረጋ ሆነ የአቶ ታዬ ደንኣ መንፈስ ራሱ ኦህዴድ/ ኦዴፓ ውስጥ ከኦነግ ወደ አገር መግባት ጋር ያሳዬው ሁኔታ ግን የትግራይ የበላይነት መንፈስን አስወግዶ የኦሮሞ የበላይነት ማስፈን ከሆነ የነፃነት ትግል ማለት ለአማራ ከኦሮሞኛ ይልቅ ግዕዝ ማጥናት አለበት ብዬ አስባለሁኝ።

ስለምን? ቢባል ግዕዝ የፍልስፍና ቋት ስለሆነ። ጀርመን ዩንቨርስቲ ውስጥ ግዕዝ ቋንቋን ይሰጣል ለዜጎቻቸው። ስለምን? የመኖር ሚስጢር ስላለው። የነፍስ ሚስጢራት ስለተቀመረበት። ጀርመን በዓለም በመዳህኒት ፍልስፍና አንጋፋና ሉላዊ ተወዳዳሪ ያደረጋት „መጸሐፈ ፈውስን“ የመፍታት አቅሟ ነው። ይህ ማለት መዳኛዋን በመዳፏ አደረገች ማለት ነው። 

መዳኛ መዳፍ ሲሆን መኖር ያምርበታል። በኢኮኖሚ በጤናም። ስለዚህ በርሊን፤ ሃይድልበርግ፤ ሃቩርግ ዩንቨርሲቲዎቿ የዕውቀት ጭንቅላታቸው ግዕዝ ነው። አማራም የአባቶቹን የጥበብ፤ የፍልስፍና፤ የሳይንስ፤ የምውህር፤ የብልህነት፤  የዕወቅት ሌጋሲ ማስቀጠል ካለበት ግዕዝን ማጥናት ይኖርበታል። የሁለተኛ ቋንቋ ምርጫው ለአማራ ግዕዝ መሆን ይኖርበታል። ግዕዝ ብሄር ስሌላው ነገ ልውረርህ፤ ልፍለጥህ፤ ልቁረጥህ አይልም እና። ግዕዝ መሬት የማፈናቀል ህልመኛ አይደለም። ሰውን ሰው የሚያደረግ የህሊና ጌታ የሚያደርግ የዕውቀት የማድረቅ፤ የማይፈልስ ጅረት ነው።   


  • ልብአልቦሽ አገር?
እያንዳንዱ አገር አገር ልብ አለው። ልቡ ርዕሰ መዲናው ነው። አንድ አገር ልዑላዊ ከሚያደርጉት መሰረታዊ አንኳር ጉዳይ የእኔ የሚለው ርዕሰ መዲና ያለው መሆኑ ነው። አሁን በምናዬው ሁኔታ ኢትዮጵያ በመንፈስ በትውስት መዲና ነው ያለችው። ኢትዮጵያ መዲና የላትም። 

ከዛ የሚወለዱ ልጆችም እንዲሁ መቀበያ መሬት የላቸውም። ኢትዮጵያዊ ዜጋ በሙሉ ከስሜን ጫፍ አስከ ደቡብ ጫፍ፤  ከምዕራብ ጫፍ እስከ ምስራቅ ጫፍ ያለው ኢትጵያዊ መናህሪያ ርዕሰ መዲናዬ የሚላት ማንነት ያላት ዕውቅና የተሰጣት ከተማ የለችውም።

አዲስ አባባ የሚኖር ወጣት ከንቲባ የለውም። የአቶ ታከለ ኡማ ም/ ከንቲባነት ለ6 ሺህ የኦሮሞ ወጣቶች ብቻ ነው። ህመሙ ሥም የለሽ ነው።  ባዬናቸው የተንጠራሩ ሁኔታዎች ኢትዮጵያ ልብአልቦሽ አገር እንድትሆን የተፈለገበት ምክንያት ጋር በዛሬ ውስጥ ሆነን ነገን ስናስብ ኢትዮጵያ ከኢትዮጵያውያን እናትነት ይልቅ ለሌሎች የአፍሪካ አገሮች የበለጠ ክብር የምትሆንበት ድልዳል ለመስራት እንደታሰብ አያለሁኝ።

እያንዳንዱ የክልል ድርጅት መነሳት ያለበት ኢትዮጵያ ከሚለው አውራ ጉዳይ እንጂ አፍሪካ ብሎ አይደለም። ይድፈረው ኢትዮጵያዊ ነኝ ማለትን። የወያኔ ሃርነት ትግራይ የአፍሪካ ነበርነት ሲገርመን ዛሬ ደግሞ በኦዴፓ አፍሪካዊ ፍልስፋና አዳምጠናል።

ሥልጣኔ ማለት ራስን ማክበር ማለት እንጂ አሻግሮ ማዬት ማለት አይደለም። ያ ድንቅ ፈላስፋ የእኔ ልዑል መነሻው እመቤቱ፤ ልዕልቱ፤ ቅደስቱ ኢትዮጵያ ነበረች። ከሷ ነው ያ የጸጋ መክሊት የተቀዳው።  ከአፈሯ፤ ከውሃዋ፤ ከአዬሯ ጠረን ነው ያ የሉላዊ ግርማና ሞገስ ተክሊል የበቀለው። ይህን ያውቃል የቅኔው ልዑል ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን የማይሞት የማያንቀላፋ መንፈስ።

ስለዚህ ኦዴፓ/ ኦህዴድ ከኢትዮጵያ ለመነሳት ሲሳናው ለአፍሪካ አዲስ ፍልስፍና ይዘን መጥተናል ቧልቱን ማቆም አለበት። በተግባር መድፈር ያለበት ድንግል አመክንዮ እፊቱ አለ። የአፍሪካ አውራ ፓርቲ መሪ ሆኖ ለውጣት ከማሰቡ በፊት ኢትዮጵያዊነትን ሙሉ ዕውቅናውን መሬት ያስይዝ። መሰረት የሌለው ጣሬያ መቆም አይችልምና።

የኦዴፓ የውሃ ልክ ኢትዮጵያ እንድትሆን ይፈለጋል። ይህን ይዤ ተነስቼለሁ  ስላለ ነበር ያ ሁሉ ክብር - ግርማ  - ሞገስ ያለምንም ቅደመ ሁኔታ የተለገሰው። ራሱን ማከብር ሲጀመር ሌላውም ሊያከበረው ይችላል።

አፍሪካውያን ሊያከብሩት የሚችሉት ኦዴፓን ኢትዮጵያዊነቱን ማክበር ሲችል ብቻ ነው። ለአፍሪካ ኦሮምያ ሳትሆን የነፃነታቸው ቀንዲል ኢትዮጵያ ናት። ለጥቁር ህዝብ የነፃነቱ ትምህክት ቀለም የሚቀዳው ከነፃይቱ የድንቅነሽ መንደር ከኢትዮጵያ ነው። እኛም የሰማይ ጸጋ ጸጋችን ያለውን በቀጣይነት ልናጸድቅ የምንችለውን „የውሻማ ሞት“ የሆነው ነገር በእርግጠኝነት መሆን ሲችልበት፤ ሲደፈር ነው።

ለኦነግውያን አርማ እኮ የፊት ለፊት ጠበቃ ኦህዴድ/ ኦዴፓ አማራሮች ሆነው ነበር የታዩት። ብሄራዊ ሰንደቅዓላማችን በማጣጠልም የፊት ለፊት ሞጋቾች እንሱው ናቸው። ከሺህ በላይ የታሰሩት የአዲስ አባባ ወጣቶች የበቀል ማወራረጃ የሆኑትም በዚኸው ቁጭት እና እልህ ነው።

ቀድሞ ነገር የአንድ የፖለቲካ ድርጅት ዓርማስ እንዴት ብሄራዊ ከሆነ ሰንደቅዓላማ ጋር ሊወዳደር ሊፎካከር ይችላል? ዶግማው አቅም የለውም። ለኦሮምያ ይሁን ቢባል እንኳን ኦሮሞ ያልሆኑ ዜጎች በክልሉ በመኖራቸው መብታቸው በመዶሻ መቀጥቀጥ አልነበረበትም። ለዛውም ኢትዮጵያዊነት ሱሴ ነው ብሎ ለተነሳው ኦህዴድ/ ኦዴፓ። የሰጠነውን የፍቅር ልክ ያወራርድ ቢባል ኦህዴድ/ ኦዴፓ ከፍሎ ይዘልቀዋል ወይ? 

እኔ ከኦዴፓ ውጪ ያሉ የኦሮሞ ድርጅቶች ለዛ ለኦነግውያን አገር የመሆን ፍልስፍና እና ዓርማ ቢሟገቱ አይደንቀኝም ለኦህዴድ / ኦዴፓ ግን ታማኝነቱን ያከስለዋል። እርምጃውም ውስጣችን አራቁቶታል እንደ ሰው ባያዬንም … 

አሁን የምናዬው የሞገቱት፤ ያከሰሉት፤ ያጣጣሉት ያው በዛው በዞግኛ ቋንቋ ጋር በፍቅር ወስጥ ነው ያለው። በዛም ቢሆነ ጥምልምሉ ሽርብ ገመድ ወስጡ እስኪገለጥለት ድረስ ነው። 

ቅኖችን ኦዴፓ ባይገፋ፤ ቅንኦችንም ባይጋፋም ይበጀዋል። ዳኛው እዮር ስላለ … ትናንትን እስቲ ይሰበው ከ9 ወር በፊት የነበረውን ሁኔታ … ማን ነበር ከጎኑ የቆመው?  
አንድ ሰው ሁለት እግር አለኝ ብሎ በአንድ ጊዜ ከሁለት ዛፍ ሊወጣ አይችልም። ምርጫው አንድ ነው። ኦዴፓ እንደ ኢህአዴግ የግንባሩ መንፈስ ወይንስ በግንባሩ ውስጥ የኦነግን ዓላማ ለማሳካት ይታትራል? ኦዴፓ ክንብንብንቡን ያውልቅ!

አሁን እኔ ጥሩ ንግግር አልሻም። ተገድሎ ተዘቅዝቆ ለተሰቀለ የተሰጠውን የሰብዕዊነት ደረጃ አይቻለሁ እና። ያ ምስኪን እናት አለው።  የእኔ ጉዳይ የድምጽ አልባዎቹ እናቶች ዕንባ ጉዳይ ነው። 

ኦህዴድ/ ኦዴፓ ቃለ አባይ አድርጎናል። እኔ ምስክርነት ለሰጠሁበት መስፈረት አንገቴን አስደፍቶኛል። ምስክርነቱ ከ ኢትዮጵውያንም ያለፈ ነበር። የቡራዩ እና የአዲስ አባባው የበቀል ርምጃማ አልተነካም። ቆሞስ ኢንጂነር ስመኘው አሟሟት እና ምደባውን ተመልከተናል። እኔ ከወዳጆቼ ጋር እንዳወጋሁት ነው የሆነው። 

"እኛ እያለን ኢትዮጵያ አትፈርስም" ለእኔ ስንኝ ብቻ ነው። እኔ እምፈልገው ተጠያቂነት እና የህግ የበላይነትን መሬት ላይ ማዬት ነው። ተቋማት ተገንብተው ማዬት ነው። ነፍሰ ገዳዮች ህግ ሲዳኛቸው ማዬት ነው። ዴሞክራሲ የ አምስት ፊደል ልሳን ነው። ፊደል ነፍስ ከሌለው ነፍስን መታደግ አይቻለውም።

ኦዴፓ በራስ ጥፋተኞች ላይ ፍትህ እያለቀሰች መሆኑን ሊገነዘብ ይገባዋል። ይድነቃችሁ ተብሎ አዋሳው ጉባኤ ላይ ውደሳም አድመጣናል። የደም ግፍ አለው። ማዳላት አለ። ማግለል አለ። መጫን አለ። 

ዛሬም ጠበንጃን ፈርቶ ህዝብ በስጋት እንዲኖር እዬተደረገ ነው። መታመን፤ ታማኝነት፤ ምህረት እና ፍቅር እንዲህ እና እንዲያ መሆናቸው ስለምን? ስለ ኢትዮጵያ አለመፍረስ ይህ የምሥራች ዜና የመሆን አቅም አለውን?!

ተከታዩ የኦዴፓ አቅጣጫ። ቢሆን የእኔ ምርጫ …  

  v የመጀመሪያው ተጋድሎ የኦዴፓ ሥ/ አስ/ ኮሜቴ ሙሉ አባላት  ከኦነግውያን ፍልስፍና ጋር ፍቺ እንዲፈጹም አጀንዳ ይዞ መወያዬት ይገባዋል። ራስን የማጥራት ዘመቻ። እስከ መቼ በሽፍንፍን? 
  
  v  ሁለተኛው ምዕራፍ የኦዴፓ የምክር ቤት አባልት እስኪ ከኦነግውያን ፍልስፍና ሙሉ ለሙሉ ይላቀቁ ዘንድ በተመሳሳይ ሁኔታ አጀንዳ ቀርፆ ይወያይ - ኦዴፓ። ይድፈረው እስኪ። እሰከ መቼ በሽፍንፍን? ዕውን ለኦሮሞ ዕናቶች ዕንባ ለወ/ሮ ታደሉ ዕንባ ኦዴፓ ተቆርቋሪ ከሆነ። ዛሬም የኦሮሞ እና እናት አስመራ ድረስ ተሂዶ ናልን በተባለ ድርጅት ተፈቅዶለት ይኸው የኦሮሞ እና እናት ትፈናቀላለች። ለሃጣን የመጣ ለድቃን ሆኖ ትግሬን ያልነካ መፈናቀል አና ብሏል። አማራ፤ ጋሞ ጉራጌም ፍዳቸውን እዬከፈሉ ነው ...  

  v ሦስተኛው ፍልስፍና ኦዴፓ የሚመራቸው ከላይ እሰከታች ያሉ መንግሥታዊ መዋቅሮችን፤ ማህያ የሚከፍላቸውን ቤተሰቦቹን በሙሉ እስኪ ከኦነግውያን ፍልስፍፍና ፍች እንዲፈጽሙ የህሊና ተግባር ይፈጽም። ህጋዊ እርምጃም ይወሰድ። 

  v አራተኛው ፍልስፍና በዬደረጃው ያሉት የኦዴፓ አካላቱን አስኪ ከ= ከኦነግውያን ፍልስፍና ያድናቸው። ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የራሳቸውን ገመና ከድነው ገና ሦስት ወር ያልሞላውን የአማራ ብሄርተኝነት ለመታገል ከታች እስከ ላይ ያሉትን የብአዴን/ አዴፓ አመራር አካላት አነጋገረዋል ባህርዳር ድረስ ሄደው። ይህን ትግራይ ላይ አደማ ላይ አልሞከሯትም።

  v  አምስተኛው ፍልስፍና እስኪ ኦዴፓ የኦነግውያን ፍልስፍና ያደናቸውን የራሱን የኦዴፓ አባል በሥም ዝርዝር ያሉትን ክፍያ የሚከፍሉትን አባሉትን ይታደጋቸው።

  v  ስድስተኛው ፍልሰፍና የአዴፓን ቅን ደጋፊዎችን እስኪ ከኦነግውያን ፍልሰፍና ያድናቸው።

  v ሰባተኛው ፍልስፍና ፍሬ አልቦሽ የሆነ የኦነግውያን ተጋድሎ ፍልስፋና ልጁን፤ ትዳሩን፤ ኑሮውን ለገበረው የኦሮሞ ህዝብ ሚስጢሩን ይግለጥለት ኢትዮጵያነት ምንም ማለት እንደሆነ። ኦዴፓን እንዴት አድርጎ ክብር እንዳጎናጸፈውም ዕውቅናውን ይግለጥላቸው እመራዋለሁኝ ለሚለው ህዝብም። 

    ህዝቡንም „ሰፋሪ፤ ነፍጠኝ“ እዬተባለ አንገቱን ደፍቶ ከሚረገጠው አማራ ውጪ ያሉት ነዋሪዎቹ ደም እና ሥጋዎቹን የሚያስተዳድራቸውን ሁሉ ስለራሱ የኦዴፓ ዓላማ እና ፕሮግራም ራሱን የቻለ ትምህርት በተከታታይ ይስጥ። ኦነግውያን አለመሆኑን ደፍሮ ይንገረን - ኦዴፓ። 

  v  ስምንተኛው መቼም ቋቅ እስኪለን ድረስ የአብይ ሌጋሲ የአማራ ሊሂቃን እዬተሰበሰቡ ኢትዮጵያዊነት እያሉ ጉልበት ከሚባክን ኢትዮጵያዊነታች ስለሆነ አሁን እያስገለለን ያለው፤ ደማችን ስለሆነ የራሱን የኦሮሞ ሊሂቃን ደፍሮ ኢትዮጵያዊነት አውራ ማንነት ነው ብሎ ያስተምር። 

   አማራ መሬት ላይ ህብረ ብሄር ፓርቲዎች እና ብሄር አልባ ነን የሚሉ የአማራ ልጆችን አሰማርቶ በጫና በተደጋጋሚነት „አማራ ነኝ“ አትበል፤ ብትል ውርዴት ነው እያለ በ እጅ አዙር የ አማራን ልጅ በማሸማቀቀ አማራ በልኩ በልቅናው እንዳይበቅል የመደረገውን ሁሉ እናዋቃለን። በ27 ዓመት ወስጥ አንዲት አማራ ሴት ሊሂቅ ሆና በማ ዕከላዊ ስተወዳደር አላዬንም። ያ እንዲቀጥል ነው የተያዘው።  

    የሆነ ሆኖ ኢትዮጵያዊ ነኝ የሚለው አማራ ኢትዮጵያዊነት ለማስተማር መብትን የተጋፋ ድፈረት ታይቷል። እስኪ ይህን አጀንዳ ይዞ ኦዴፓ የኦሮሞ ሊሂቃን ሰብስቦ ይወያይ። ይህቺ የአፍሪካነት ፍልስፍና ግርዶሽ ናት። ማህሏ ተስታ ነው። ኢትዮጵያዊነት ላይ ኦዴፓ ይነሳ ድፍረቱ ከኖረው። 

    የኢትዮጵያ መሪ ሆኖ ካለድምጽ ልዩነት ተመርጦ የለ? ትናንት እኛ በተጋንበት ዘመን ያልነበሩ ሌሎች ወዳጆችንም አፍርቷል ዛሬ ዛሬ። ለእነሱም መሆኑን ያሳይ … እስኪ … ነኝ እንደሚለው መድረኩን ከፍቶ ህዝቡም ኦሮምያ የኢትዮጵውያን የዜጎች ነው ይበል እስኪ ወዲያ ማዶ ሄዶ ጫን ተደል ጫና ከሚያበራክት … እኛ ኢትዮጵያዊነት ኦህዴድ/ ኦዴፓ ከልቡ ነው ብለን የሚገትልነትን የጨው ሃውልት እንዳይሆን በዚህ ዙሪያ ይባትል። 

„ጣና ኬኛኝን“ ለማሳካት OBN ቀደምት ገድልን ሲዘክር ባጅቶ ነበር። አንድ ቀን እንዲያውም የሰይጣን ኮከቡን እንቁላል ክብ ሰርቶ አውጥቶ በልሙጡ ብሄራዊ ሰንድቅዓላማ አንድ ዝግጅት እንዳቀረበ አስተውያለሁኝ። መቼም ጉድ ያሰኙ ልዩ ዶክመንተሪዎችን አኮምኩሞናል። „አልተቻሉም ለማ እና አብይ“ እዬተባለ። አሁን ግን አደራሻው የት እንደሆነ እራሱ እኔ ለማውያኒቱ ጠፍቶብኛል። ለእኔ  የOBN ኢትዮጵያዊነት አቅጣጫ እንዲህ እንደ ጥዋት ጤዛ የጠፋብኝ ላልንበሩት በመንፈሱ ውስጥማ ጋዳ ነው የሚሆነው።
አብሶ ከመጋቢት 24.2010 ጀምሮ ነገረ ኢትዮጵያ ውሾን ያነሳ ውሾ ሆናል ለOBN ። ሌላው ቀርቶ የጠ/ ሚር አብይ አህመድ የ100 ቀናት ገድል እንኳን ሥራውም አጀንዳውም አልነበረም ለOBN ። ምን ዘገባ ሰራ? ስለምን ዘለለው? ኦነግውያን ጃዋርውያን እንዳይከፋቸው ይሆን?

ኦዴፓ ለውጡን ለኢትዮጵያ ልዕልና ወይንስ ለኦሮሞ ልዕልና ነው የሚፈልገው? ይህን መሬት ላይ ማዬት እፈልጋለሁኝ እኔ ሥርጉተ ሥላሴ ማንም ያለደፈረውን ለማውያን ነኝ እና።

ለመሆኑ ለአብይ ካቢኔ አዴፓ/ ብአዴን ወይንስ ማን ነው ቅርቡ? ቅርበትስ ይቅርበት አማራ እንደ ዜጋ መቼ ነው የሚታዬው - በኦዴፓ መንፈስ? አማራ ነኝ ማለት ወንጀል በአብይ ካቢኔ የማይሆነው መቼ ነው? ጭነቱ እና ጫናውስ መቼ ነው ለአማራ የሚቆመው?

በዚህ ዙሪያ የበጀት ድልድል እና ስልቱን ደግሞ እመጣበታለሁኝ። ዝም ብዬ የባጀሁት ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ደግመው ተመርተው እንዲቀጥሉ እሻ ስለነበር ብቻ ነው። ይህ ማለት ደጋግሜ እንደጻፍኩት አማራጭ ስሌለ አይደለም እሳቸውን የሚተካ፤ ለመወዳደር የሚችልም የፖለቲካ ሊሂቅ የለም የሚል ሙሉ ዕምነት ስላለኝ ነው። የፈቃደ እግዚአብሄርም ቅብዕም አለበት ብዬ ስለማምንም ነው።

ዶር አብይ አህመድ እግዚአብሄር አምላክ በሰጣቸው በድንግሉ ሰብዕና ወስጥ ቢቀጥሉ ራሱ ሰጪው ልዑል እግዚአብሄር ነውና ከተቃጣባቸው ቀስት የመዳን ዕድላቸው 100% ይሆናል። ግን ታማኝ ከሆኑ ብቻ ነው። መቼም ታማኝነቴን አለጎደልኩኝም ብለው ሊሉኝ አይችሉም። እኔ እንደ አንደ ሌሰን ስለማጠናቸው። ጥናቴም የቀደመ ስለነበር። 

ጠ/ ሚር ዶር አብይ አህመድ ቢያንስ ለኢትዮጵያዊ ህግጋት ለማስፈጸም፤ ታማኝነት እንዳቃታቸው ራሳቸውም ያውቁታል። … ህግ በኢትዮጵያ ንጹሃን ላይ ጉራዴውን የሚመዝ ከሆነ የህግ ፋክልቲ በሳቸው ዘመን መዝጋት ይገባል ባይ ነኝ። ለዛ የሚፈሰው መዋለ ንዋይ አላግባብ ነውና።

ይህም ብቻ አይደለም የመንግሥት ሚዲያ ጦላይ፤ ቃሊቲ፤ ዝዋይ እንደ ተፈረደበት ተመልክተናል። በማንም ዘመን አላዬነም ሰው ተገድሎ ተዝቅዝቆ ሲሰቀል። ክርስቶስ እንኳን ተዘቅዝቆ አልተሰቀለም። በዬትኛውም ዘመን አላዬንም ቀኝ እጅ ግራ አንገት ሥርን ገድሎ አደባባይ ላይ ደመ ከልብ ሲሆን። ይህን መሰል የህግ ጥሰቶች እሳቸው የሚመሩት ካቢኔ መድፈር አልቻለም።

የሰንደቅ ዓላማ ተጋድሎን የቁማር፤ የጫት፤ የሺሻ፤ የደረቅ ወንጀል ፓርቲ አባልተኝነት  አድርጎ ነው ካቢኔቸው ታች አውርዶ ያንከረባበሰው፤ ከ10 እስከ 15 ሺህ ለተፈናቀሉት የቡራዩ ምንዱባን 4 ሺህ አልደረሰም ተጎጂ ተጠቂዎቹ ማዕካለዊ መንግሥት ሲገለጥ፤  ሌላው ዜጋ አይደለም። ተዘርዟል ለሳቸው የኦዴፓ / ኦህዴድ የፓርቲ ብጽዕና ሲባል። ለዚህም ነው የእንጅባራ ሰማይ የፈረደው። ደቡብ ላይም የመሬት መራድ የተከሰተው። መታመን ለሰው አይደለም ለሚያምኑት አምላክ በልባቸው ለጻፈው ቃልኪዳንም ነው።

  v  አብይን አፈላልጉኝ እባካችሁ የእኔ  ቅኖች ...

የማውቀው አብዩ / አሜኑ እንዲህ አልነበረም። አሁን እኔ ከዚህ ምርጫ ቦሆዋላ ሴሪሞኒያዊ የቅብ ጉዞ አልሻም እኔ በግሌ። የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚ/ር የነበረውን አብይን ፍለጋ ላይ ነኝ። ለነገሩ አሁንም የማዬው ወንበሩ ባዶ እንደሆነ ነው። እኔ በህልሜ አምናለሁኝ። 

ሌላ ሰው ግማሽ ፊቱም የተሳከለት አልሆነም እንደሚሰማው ከሆነ … ግን አሁን ማነው ጠ/ ሚሩ? ዶር ለማ መገርሳ? ዶር አብይ አህመድ? ወይንስ ሃጅ ጃዋር መሃመድ? ወይንስ እትጌ ኤርትራ በበላይነት የምታስተዳድራት ኢትዮጵያ? ወይንስ የአረብ ኢምሪት የምትመራት ኢትዮጵያ? ማነው የኢትዮጵያ ጠ/ ሚር?

አብይን አፈላልጉኝ እባካችሁ የእኔ ቅኖች … ዛሬ ሐሴት፤ ብሥራት፤ ሰናይ፤ ብርሃን፤ መባቻ ለማለት አልደፍርም። እህቴ ዛሬ ኮንግራ ብላ ደውላልኝ ነበር።፡ደስታውን ለለመቀማት አብሬ ፈቃዷን ፈጽሜያለሁኝ። 

ውስጤ የሚለኝ ነገር ግን የድምጽ አልባዎቹ እናቶች አሁንም ዕንባ እያመረቱ ስለሆነ ሰቀቀን ውስጥ ነኝ። ደስታዬ ርቆኛል። ለማድመጥ አልፈቅደም ንግሮችን፤ መግለጫዎችን። ከፍቶኛል። መከፋቴ ከህመምም ጋር መሆኑ ራሱ እጅግ ከባድ ነው። ሳቄ ሁሉ ጠፍቷል። 

ዶር ነገሬ ሌንጬ ስለ ኦነግ አርማ ሲሟገቱ ብድግ ብዬ ተነስቼ ልብሴን አውልቄ ጥቁር ልበሴን ለበስኩኝ። እነ ኦቦ ሌንጮ ለታ አገር ሲገቡም ውህደቱ ከመጣ ጥቁር እለብሳለሁ ብዬም ነበር። ኢትዮጵያን ለሚረገጥ፤ ለሚንቅ፤ ለሚያቃልል፤ ለሚያንቋሽሽ' ለሚጸዬፍ መንፈስ እኔ ምህረት የለኝም።

እና አዲሱ ምርጫው የመባቻ የሚሆነው መሰንበቻ ሲሆን ብቻ ነው። "ኢትዮጵያ ከምትፈርስ እኔ ልፍረስላት" ከሆነ ፍልስፍናው የዜጎቿ ክብር ይጠበቅ። በማህል አዲስ አባባ ደመ ከልቦች ስንት ናቸው? ትናንት በራሱ ወጪ ሆ! ቲሼርት ለብሶ የደገፈው፤ የተሰዋው፤ አካሉን ያጎደለው/ ያጎደለችው የአዲስ አባባ ወጣት ዛሬ ጦላይ ላይ በምን ሁኔታ ይገኛል? ለመሆኑ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ጦላይ ድረስ እስረኞችን ሄዶ ለማዬት ይፈቅዳሉን?

በታሪክ ተርታ ድሃ ህዝብ ነው ወይ መንግሥት የሚገለብጠው? „አህያውን ሲፈሩ መደላድሉን አይሆንም ወይ?“ አንዱ ምርጥ ዜጋ ካቴና አይነካውም፤ በትጽዕኖ ፈጣሪ ደረጃ ጥበቃው ተሟልቶለት ...  መዳቡ ዜጋ ግን አሁን ሲኦል ተፈርዶበታል።

ነገ የኢትየጵያ የክርስትና የመሰቀል አማንያን ዕጣ ፈንታስ ምን ሊሆን ይችላል? ነገ የኢትዮጵያ ሙስሊም እንደ ተፈጥሮው የበቀለው ዕምነት ዕጣ ፈንታ ምን ይሆናል? እስልምና እኮ ዛሬ ለጠ/ ሚር የምትወዳደር ሴት ሊሂቅ ፈጥሯል፤ አንዳንድ ቀን ሁለት እና ከዛ በላይ ብሄራዊ ኢቤንቶች ሲኖሩ ኢቤንቶችን የሚከፍቱት በከፍተኛ ደረጃ ያሉ የእስልማና ዕምነት ተከታይ ሴቶች ናቸው እና ይህ ዕድላቸው በእስላማውያን ኦነግውያን በዳውዳውያን እና በጃዋርውያን በአሁኑ አያያዝ የኢትዮጵያ እስልምና የሚከተሉ የኦሮሞ ልጆች ነፃነታቸውን እንዴት ይቀጥላል? 

ለመጨረሻ በወልቃይት በጠገዴ በራያ አካባቢ ቀጣይ መፈናቀል ሊኖር እንደሚችል ምልክቶች አሉ። የሰው ዕንባ እንደ ቡራዩ ካልተናፈቀ በስተቀረ ሬሳ ማዬት ከልናፈቅን በእነዚህ ቦታዎች መከላከያ እስቀድሞ የሚሄድበት ሁኔታ መመቻችት ይኖርበታል። የቡራዩ የቤንሻንጉል ትዕይንት ከዛም ይደገማል። ሊደገም ይችላል አይደለም ያልኩት ይደገማል። በወልቃይት ሴቶች ታሰራዋል ባዶ 6 ሊወስዷቸው ይችላሉ …. 

መንግሥት አለ መንግስቴ ይቀጥላል ካለን ኦዴፓ ...የመፈናቀል የሃዘን የስጋት ሰደድ እሳቱ ህይወት በቀጣይነት ከመቅጠፉ በፊት አፋር እና ትግራይ ላይ የፌድራል መንግስት የጸጥታ ሃይል አስከባሪ እንዲገባ ይደረግ።

በመጨረሻ ኢትዮጵያን ለታደጓት ለደቡብ ህዝቦች እና ለመሪያዋ ለክብርት ወ/ሮ ሙፍርያት ካሚል እና ለአቶ ሚሊዮን ማትዮስ ከፍ ያለ፤ እጅግም ትሁት የሆነ፤ እጅግም አክብሮቱ ዝልቅ የሆነ፤ እጅግም ፍቅሩ ዘለግ ያለ ወስጤን እንሆ! ተባሩከ! ተከበሩ!  

የኢትዮጵያ ሴቶች እንኳን ደስ አላችሁ፤ እንኳን ደስ አለን። በአንድ ወቅት ሴቶች መልካም ነገሮች አላቸው ጊዜ እስኪሳጣቸው ድረስ ጠብቀው ይያዙት ዘንድ እመክራቸዋለሁ ብዬ ጽፌ ሞሮሽ ወገኔ እና ዘሃበሻ ለጥፈውልኝ ነበር፤ አሁን ትንቢቴ ስለተፈጸመ ደስ ብሎኛል።  ሴቶች እንዲህ ነን! አሁን መፎከር የምንችል ይመስለኛል።

ጥበብ ህዝብን መጠበቅ ነው!
ጠንቃቃነት ለዜግነት ጥበቃ ይዋል!
ኢትዮጵያዊነት በውስጥ መኖርን ይጠይቃል!

የኔዎቹ ኑሩልኝ። ቅኔቹ አዱኛዎቼ ፌስ ቡክ ያለችሁ ደግሞ ሼር አደርጉልኝ። ትናንት ያዬናቸው ግድፈቶች እና ጉድፎች መደገም፤ መሰለስ የለባቸውም። 

ማለፊያ ሰንበት።
 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።