ህመም።

የተደከመበት እሾኽ በቀለበት።
„እግዚአብሄር እንዲህ ይላል፤--- በዳዊት ዙፋን ላይ ተቀማጭ አይኖርለትም፤
ሬሳውም በቀን፤ ለትኩሳት በሌሊትም ለውርጭ ይሰጣል።„

ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ ፴፮ ቁጥር ፴
ከሥርጉተ©ሥላሴ 05.10.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።


  • ·       ህመም።

የጎንደር የአማራ የማንነት የህልውና አብዮት የወለደው የጣና ኬኛ አብዮት ሥጦታ የሰማይ ነበር። መክሊቱም የሰማይ ነበር። ሶሻሊዝም የዘራውን የሴራ የመከራ ምንጭ ከሥሩ ለመንቀል የሚያስችል እዮራዊ መልዕክት ነበር።

ሶሻሊዝም ንደፈ ሃሳቡ ብቻ ሳይሆን በዚህ ፍልስፍና ውስጥ ያሉ ሰውን የሚፈትኑ የራስ በሽታዎች አገርን ህዝብን፤ ሰብዕናን የሚንዱ ረቂቅ የወረርሽኝ ጠንቅ አምራችነቱ የግራው ፍስፍና የማህበርስብ ሞራል ጠንቅንም ነው። ህመም!

የጎንደሩ አብዮት መንፈስ የጠራው ያ የጣና ኬኛ አብዮት ይገላግለናል ብለን ብዙ ደከምን። ብዙ ለፋን። አሁን ሁሉም ታጥቦ ጭቃ ሆነ። ለውጡ ከሴራ፤ ከተንኮል፤ ተሰርጎ ገቦች  ጥቃት መዳን አልተቻለውም። 

እንደ ገና አሁን እንደ ተለመደው በዬጎጆው ጉግስ አለ። ጦርነቱ ጦፏል። ዕንባም መጠጊያ አጥቷል። በዬቀኑ ቤት አልባው ህዝብ ቁጥር እያሻቀበ ነው። ዕንባም የትም ቦታ በዬትኛውም አድርሻ ማግኘት ይቻላል። ዕንባ አብቃይ መሬት መቼ ትዝታ ብቻ ሆኖ እንደሚቀር፤ "ነበር፡ የምንልበት ዘመን መጣ ሲባል ጥሎን ሄደ ….. ሄደ ሄደ ነጎደ ነጎደ ….ተስፋን እዬጎራረደ፤ የራይ ጥሪትን እያንጓዳጎደ። ህመም!

ለችግሩ መንስኤ እኔ ነኝ የሚል አልተገኘም። የችግሩ መንስኤ ግን ቅናት ነው። ቅናት ደንበር ዘለልም ነው። ቅናት የፈጠረው ጦርነት ነው አሁን ይህ ሁሉ ህውከት የሚታዬው። በማንም በምንም አይመከኛም። በቅናት ወረርሽኝ የተበከለው መንፈስ የፈጠረው ህውከት ነው አሁን  የኢትዮጵያ ዕናቶችን እንባቸው እንዲቀጥል የፈረደው።

ሌላው ሁለተኛው የኮፒ ራይት ጉዳይ ነው። አንዱ የአሸናፊው መንፈስ እኔ ወራሽ ነኝ ሲል የኦሮሞ ንቅናቄ ላመጣው ለውጥ ዓርማውን ይዞ ወጣ፤ ሌላው የአማራ የህልውና  የማንነት ተጋድሎ ይዞት የወጣው ዓርማ የእኔ ነው ሲል ቀዝቃዛው ጦርነት ተፈቅዶለት ተከፈ። ሁለቱም ተጋድሎዎች ከድርጅቶች ማንፌስቶ ውስጥ ያልተቀመሩ አመክንዮችን ይዘው ነው የተነሱት። 

የግንጫው አብዮትም ሆነ  የጎንደሩ አብዮት ዬራሳቸው ባህሬ ዓላማ እና ግብ የነበራቸው ሲሆን፤ ባለቤቱም ህዝብ ነበር። የትኛውም ማንፌስቶ ማህበርተኛ አልነበሩም የተጋድሎዎቹ መሰረታዊ መነሻ። የከፈሉትም መስዋዕትነት ለተነሱበት ዓላማ ብቻ ነበር። በዚህ ላይ ጥንቃቄ ሊያደርግ የሚገባው  ብአዴን/ አዴፓ፤ የኦህዴድ/ ኦዴፓ የለውጥ ሃይሎችም ፍጹም ታሪክ ይቅር የማይለው ግድፈት ፈጽመዋል። እራሳቸውን ያጣፉትም ራሳቸው ናቸው። በረከትን የመናቅ … ብቻም ሳይሆን ጥበብም ምርቃቱ አንሶበታል። 

በዚህ ውስጥ አትራፊዋ እትጌ ኤርትራ ናት። ምክንያቱም የህዝብ ተጋድሎ እና የ50 ሺህ እስረኛ መከራ ተዘሎ የብስራት አማጭ የተሰጠው ለእሷ በተደላደለ መንፈስ ነው። አቀባበል ይመስክር። ትርፉ እጥፍ ድርብ ነው ለእትጌ ኤርትራ። በሰውር የአማራ ይህልውና የማንነት ታገድሎ ድርድር ውል ተፈጽሞበታል። አማራ ነኝ ብሎ አማራ ከሚታገል ህብረ ብሄር ውስጥ ገብቶ ቢጨፈለቅ ነው ምርጫው። ሌላው ግን እንዳሻው የመደራጀትም የመመራትም መብት አለው። መብት አልቦሹ የግዴታ ታራሹ ግን አማራ ብቻ ነው። ይህን ገልጠን መናገር አለብን። 


የዚያ ፍርድ አላግባብ ስለሆነ ነው አሁን መሬት ላይ የምናዬው መከራ። የእንጅባራው የቀስተዳመና ታምርም የመጣው ከዚህ አንጻር ነው ፍርድ ስለተጓደለ። መሬትላይ ፍርድ ሲጓደል እዮር መልስ ይሰጣል። ሌላው ብልሁ ጉዳይ ማቆላመጫም ነው ብአዴን ከኤርትራ ጋር የጎንዮሽ ንግግር እንዲያደርግ የተፈቀደለት። የብአዴን ሊሂቃንም ገና አልተገለጠላቸውም። ቁጭ ብለው የ የአማራ የማንነት ተጋድሎ ለሌላ መሸለሙን አብሥሩ ሲባሉ አሸሼ ገዳሜ እያሉ ፈጸሙት።

ብዙ ነገር በህይወት ይወናል። ነገር ግን አለመሳከቱ ዘወትራዊ ከሆነ አንዳንድ ጊዜ ዕድል ስለመቀጠሉ ወይንም ስላለመቀጠሉ ቁጭ ብሎ ከእጬጌው ዕድል ጋር መወያዬት ያስፈልጋል። በተሞከረው ልክ አለመሰካት ከሆነ ከዕድል ጋር ቁጭ ብሎ ፊት ለፊት መሟገት መነጋገር ያስፍልጋል። ስለሆነም ለባለ ዕድሉ መፍቀድ ግድ ይል ነበር። 

የሰው ልጅ በልፋት መድከም መታከት ያለበት አድጎ ሊያው በሚችለው አመክንዮ እንጂ በሞተ ላይ ሌላ አምክንዮ አብቅዬ አፈራለሁ ከሆነ ከቀደመው ሞት ይልቅ የባሳ ሞት ይመጣል። ለዚህ ነው ጎንደሮች „ከሞቱ አሟሟቱ“ የሚሉት። ሬሳ ሃሳብ አይበቅልም፤ አያበቅልም፤ አያድግም አያሳድግም። በበቀለ ሃሳብ ላይ ሌላ ሬሳ ሃሳብ አበቅላለሁ ከሆነ ራሱን ይዞ ነው የሚጠፋው። የምናዬውም ይኸውን ነው።  

ከዚህ ጋር በተያዬዘ ማንሳት እምሻው ቁም ነገር በቃኝን ማን ይወቀው? ይበቃኛልን ማን ይወስነው? አቅም ጠፋ። ጊዜ ራሱ ወሰነ። ዘመን ራሱ ወሰነ። በቃችሁ ያለው ዘመን ጊዜ ብቻ ነው። በሰው ጥበብ፤ በሰው ቀመር በሰው ልቅና አልነበረም ይህ ለውጥ ሰተት ብሎ በዬጓዳችን የገባው። ጥበቡ የሰማዩ ዳኛ ነበር። የሰማዩ ዳኛ የሰራው ጥበብ የፈቀደለት አካል አለ። 

ያ አካል ሲፈቀድለት ሌላው ድካሙ ስለተቃለለት ተመስገን ብሎ ሊረዳ፤ ሊያግዝ፤ ሊያበረታት ሲገባ በማይታይም በሚታይም፤ በተሰወረም በግልጽም የእዮር ስጦታ ተሰቀሰቀ። አሁን ከነበርንበት በባሰ ሁኔታ ላይ መገኘት ግድ አለን። ገዱ ለሁሉም የተረፈ እና የሚበቃ ነበር። ምክንያቱም ሥጦታው ሰው ሰራሽ፤ ጠበንጃ ሰራሽ ስላልነበረ።

ዘመን - ወቅት - ጊዜ የሰጠውም መንፈስ ቢሆን ጥንቃቄው ጎደሎ ነበር። ሥጦታውን ሰውኛ  ተደረገ እና በማቅረብ እና በማራቅ፤ በማግልል እና በማቀፍ ማህል ፓለቲካዊ ጨዋታ ሲጀመር መንፈስ መናድ ጀመረ። ሽልማቱ የህዝብን ተጋድሎ አሳልፎ በመስጠት በውስጥ ስምምነት ተከወነ። ምርቃት መነሳት አህዱ አለ። 

አንድ የልዑል እግዚአብሄር ሥጦታ ተቀባይ ጸሐይ ለሁሉም እኩል ብርሃኗን አንደምትለግሰው ሁሉ እኩል ብርሃኑን ለመለገስ መፍቀድ ይገባ ነበር። እያንዳንዱ እርምጃ በነበረው ሙቀት ልክ፤ በነበረው አያያዝ ልክ መሆን ይገባው ነበር። የህዝብ መስዋዕትነትም ለድርድር ለሽልማት የሚቀረብ መሆን አይገባውም ነበር። በራስህ ላይ የማታደርገውን በሌላ ላይ መጫን ምን ዓይነት ሥም ይውጣለት? ማጣበቂያውም አርፊሻል ስለሆነ የሳሙና አረፋ እና ጤዛ ነው የሚሆነው። ለአክሮባቲስቶች የቀጣዩ ፕሬዚዳንትን ምርጫ ሊያሳጭ ቢችልም በጸሎት ካልተደገፈ ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው ... በሰማዩ ዳኛ ዘንድ። የጋህዱ ዓለም መርህ ምድራዊ ነውና።   

ደም ለከፈለ ህዝብም የደሙ ዋጋ የራሱ እንጂ ለሌላ መወድስ መዋል አልነበረበትም። ስለዚህም ቁጣ ከሰማይ ታዘዘ። ካልታወቀበት ይህ ግድ ይላል … ቧልት ሲባዛ ባዶ ቸረቸራም ያነባል እና … 

ስጦታው መንፈስ ቅዱስ በታደመበት ቦታ አይደለም ወደ መሬት የሚተረጎመው። መሬት ላይ በዥጉርጉር ማሳ ላይ ነው። እናት ዥንጉርጉር ባህሪ ያላቸውን ልጆቿን የምታስተናግድበት ጥበብ እዮራዊ በመሆኑ አብዛኛውን ጊዜ ይሳካላታል። እርግጥ ነው እናትም ቀረብ የምታደረገው ልጅ ይኖራታል። የሆነ ሆኖ ግን የእናት አንጀት ለሁሉም እኩል ነው።

አንድ የለውጥ ሐዋርያን በሴትነት የሚገኘው እናታዊ ጸጋ ባይኖረውም፤ የኢትዮጵያ ፖለቲካ የወንዶች ስለሆነ ቢያንስ ራስን አሸንፎ ዥንጉርጉሩን ሰብዕና እንደዬ ባህሪው እኩል ለማቀፍ ባለቤት የለሾችን ምንዱቦችንም በባለቤትነት ስሜት የእኔ ለማለት ራስን ማሸነፍ አብዝቶ ይጠይቃል።

የዚህ ሁሉ ንቃቃት መንስኤ አንድ ነገር ነው። አንዲት ቦታ ላይ የተፈጠረች ዳጥ። ሁሉንም ይዛ ላጥ። የአንዱ የቤተ መንግሥት ባለሟል እና አማካሪ መሆን የሌላው ደግሞ መገለል። በተመሳሳይ ሁኔታ ለተጎዳ ቤተሰብ ተመሳሳይ አያያዝ ይሻል። ካደረጉ ለሁሉም ዕድሉን መስጠት። ከቀረ ደግሞ ለሁሉም መንሳት ይገባ ነበር። የታዬው ግን የዘበጠ ሚዛን ነበር። ትናንት የተከበረውን በማክበር ትናንት የተገፋውን በማግለል።

ስለሆነም መከፋት አዲስ ሥም የለሽ ምንጭ አፈለቀ። የመከፋት ምንጭ ቂምን አበቀለ። የቂም ጫፍ ላይ አወጣ እና መሰሉን አሰባበሰበ። ያ ጫፍ ላይ የወጣው ቂም ሌላውንም መንፈሳዊ አቅም ደረመሰው። የሚገርመው ቀስ እያለ አይደለም የተሸረሸረው፤ ቀን ጠብቆ ድምጥምጡን በአንድ ጊዜ በሽታሽቶ አጠፋው።
  
አሁን የቀደመውን መታመንን በነበረው ልክ እንዲቀጥል ለማድረግ ፈጽሞ አያችልም፤ የሚደክም የለም ከእኔ ጀምሮ። ሰምተን ሳይሆን ከልባችን ሆነን መረመረን። ጩቤው በማን ላይ እንደተሳለም አስተዋልን።
ያ የቅንነት የጊዜ ተቋም ነበር። 

በቅንጅት ጊዜ ይህ ታይቷል። ይደገማል ሳይባል በእጥፍ ድርብ ተበራክቶ፤ ልምልሞ በዬቤቱ የገባ ቅዱስ መንፈስ፤ የሰማይ መላዕክት ወርደው ያበጁት የመሰባሰብ መንፈስ ልቆ ተፈጠረ። ተዋድጅነትን ማዬት የማይፈቅደው አብዛኛው ተጽዕኖ ፈጣሪ ፖለቲካኛ በተመቸው መንገድ የተመቸውን አደረገ - መነጠረው። 

ተመንጣሪውም እራሱ በማድመጥ ያገኘውን ምርቃት አሳልፎ ሰጠ በአዳባባይ። አሁን ሃብቱ ባክኖ ቀረ። ነገ ያ ሞገድ መልሶ ማግኘት የሚቻለው ፎቶ ወይንም ቪዲዮ በማዬት ብቻ ይሆናል። ሁሉ ነገር በርዶታል። የተፈለገውም ይህ ነበር። እንኳን ደስ አላቸው ለቅናት ማብረተኞች። ኢትዮጵያዊነት በዚህ ውስጥ ሲለካ አድርሻ የለሽ ሆኖ ታዩታላችሁ።

ደስታው የእኔ የራሴ ወገን ነው። ደስታ ፈጣሪውም የእኔ ነው ሲባል ነው ኢትዮጵያዊነት በውስጥ ስለመኖሩ የሚረጋገጠው። ደስታውን ጫፍ ደረስ ደስ አይባለችሁ ተብለን ሁሉ ነበር። ደስታው ራሱ ተቀናቃኝ የተፈጠረበት ወዲያው መጋቢት 24 ቀን ደስታ እንደ ታወጀ በቅጽፈት ነበር። ኢትዮጵያዊነት ይህው ነው። የኢትዮጵያዊነትን ፈተናውን ስንቱ አለፈ?"ኢትዮጵያዊነት" ልጥፍ አይለደም። በመሆን ውስጥ የበቀለ የደም ሚስጢር እንጂ። 

በምድር ወስጥ ደስታን ተጻሮ የሚኖር ፖለቲካ የእኛ ብቻ ሳይሆን ይቀራልን? ለክርስትና ዕምነት ተከታዮች ትንሳኤን ስቀን እንዳናሳልፍ ሌላ ጫን ተደል የጭንቅ እና የመከራ ጥርጣሬ ነበር የተጫነብን … ለዛውም በታሪክ በህማማት መቅድመ ዕለት የምሥራች ሲታወጅ የመጀመሪያው ነበር … የትንሳኤም ጥርጊያ መንገድም ዓዋጅም ነበር ….

የአላዛሯ ኢትዮጵያ ፖለቲካ እፉኝት መንፈስ የተጠናወተው ነው። ሲረገዝ አባቱን ሲወለድ እናቱን ማጥፋት። ከዚህ ያፈነገጠ ዘመን በመምጣቱ ያ ተኝቶ የኖረ የእፉኝት ቆሌ ተነሳባት እና ጦሮውን ላከ። ይኸው ብጥልጥሉን አውጥቶ መና ከንቱ አድርጎ አዬር ላይ በነበር አስቀረው። 

ሁሉም የፍቅራዊነት መንፈስ አልተራቆተም የሚሉ ሊኖሩ ይችላሉ። ያላለቀው የገሃዱ ዓለም ነገረ ጉዳይ እንጂ መንፈሳዊ ሃብት በዬፊናው ተብትኗል። በረከት እኮ ሲሰጥ በፆም፤ በጸሎት፤ በሰጊድ፤ በሱባኤ ለሰጪው ታማኝ በመሆን ነው። እኛ ደግሞ በረከታችን በአግባቡ ለማድረግ አልችል ብለን ደለቀን፤ ፍቅር የተበረከተለትም ፈቀዶ ራሱን አደበዘዘ፤ ዘመንም እዬተንከተከተ አሽሉኮን በሰጋሩ መጪ አለ ….

አሁን ሙሉ የህዝብ ድጋፍ እያገኜ የመጣ አንዲት ውጥን ነፍስ አብን ላይ ሲታይ፤ አፎቱ ወደዛ አዞረ እፉኝቱ። የቀረው እሱ ነውና በእሱ ላይ ርብርብ ተጀመረ። ብዙ ሃሳቦች የአብን እና የኤልቲቪ ቃለ ምልልስ ሙግት ጃዋር ሠራሽ አድርገው ይመልከቱታል። ከዚህ አቶ ጃዋር መሃመድ እጁ የለበትም። 

ስለምን ነው የሌለው ሚደያው OMN ራሱ አቶ ጃዋር መሃመድም የአማራ የማንነት የህልውና ተጋድሎ የሚለውን ፍልስፍና ደፍሮ ታግሎለታል። ዕውቅና ሰጥቶታል። የአማራ የህልውና ታገድሎ አክቲበስቶችንም ዕድሉን ሚዲያው ሰጥቶ አወያይቷቸዋል። ይህን ማድረግ የተሰናው መንፈስ ነው አሁን በሌላ ሚዲያ ቤተ መንግሥት በተገባባት ልክ ገብቶ የድርጅቱን ማህበራዊ መሰረት ለማፋለስ ሙከራ እያደረገ ያለው። ስንት ሊሂቃን እኮ ባክነው ቀርተዋል በዚህ መርዘኛ መንገድ። 

ማዕከል ላይ ቀደም ብዬ ስጠቅሰው ነበረው ማዕከላዊ መንግሥት የራስ ተሰማ ናደው ጠረን ሸተተኝ ስል ነበር። አሁን እሱ ነው ሻታ እዬዞረ ያለው። ወይ አብን ከሁለት ይተረትሩታል፤ ወይ መሪውን በአደባባይ በጠሐይ ደመ ከልብ ያስደርጉታል። የቃለ ምልልሱ ጭብጥ አብን ተፈልጎ አይደለም፤ ማህበራዊ መሠረቱ እንደ ተለመደው ለማሳጣት ታቅዶ የተከወነ ነው። 

ለጊዜው አልተሳካለቸውም። ይልቁንም እልህ እና ቁጭት ፈጠሯል። ጉልበት እና አቅም በሚገርም ፍጥነት አሰባስቧል።  ቀጣዩ ቀደም ብዬም ጽፌበታለሁኝ፤ አሁንም እንደገለጽኩት ድርጅቱን መክፈል፤ ወይ ደግሞ መሪውን ማጥፋት ቀጣዩ ትልም ይሆናል። የአብይ ሌጋሲን እኮ አይነው አኮ።  ያን የመሰለ ፍቅርን የዘራ መንፈስ በስል ሰተት ብሎ አንድ ቀንጣ መንፈስ በወዳጅ በዘመድ ገብቶ በቁሙ ነው የዘረሩት …. እንኳንስ ይህ ዕንቡጥ ድርጅት …

ቅናት እናትንም አይምርም። ቅናት ልጅንም አይምርም። ቅናት ፈጣሪን ቢያገኝም አይምርም። ቅናት ወዳጅም የለውም። እዬገደለ፤ እያጠፋ፤ እዬደረመሰ መኖር ነው የቅናት ተፈጥሮ። ቅናት እፉኝት ነው። ሲረገዝ አባት ሲወለድ እናቱን በማጥፋት ህውከት ማዋለድ የለመደበት ነው።

ያ በአንድ ብሄራዊ ቅን ሙሴያዊ ንግግር ጸጥ ረጭ ያለው ህዝብ ዛሬ ደግሞ ተስፋው እዳሪ አዳሪ ሆኗል። ይህ በሚገባ በቅናት ፕሮጀክት ዲዛይን የተደረገ ነው። ተስፋን በስፋት ሰንቆ መኖርን የተለመው ያ ምስኪን እና እህሩህ ህዝብ የማህበረ ሊሂቃን መከራ ከሰማይ ታዞበት እንደ ገና ከሰለ፤ እንደ ገና አንገቱን ደፋ። ለ6 ወራት የዓለም አብነት የሚዲያ አምድ የነበረው የአብይ ሌጋሲ ዛሬ ደግሞ ያ ተገልብጦ መርዶ ሆነ ቁርስ ምሳ ራቱ …. ራሱም የፈጠረው ግድፈት እንዳለ ግን ልነገረው ግድ ይላል።

ኢትዮጵያ አንገቷን ደፍታ እንዲያዩ የሚመኙትም በቅርብም በሩቅም አሉ አገሮች እኩል ለኩል ስለመሆናቸው አረጋገጡ። ብልሆች አተረፉበት። ስለምን? የፈጣሪ ስጦታ ሊሰጥ የሚገባው እንክብካቤ እና ክብር፤ ጥንቃቄም ስለተነፈገ … ምርቃቱ ተነሳ። 

ምርቃት ተቀባዩ ምርቃቱን በአያያዝ ግድፈት ማጣቱ ቢያርመጠምጥም የቀደሙ መረጃዎችን ከግምት በማስገባት ትቢያ ላይ ያሉ ዜጎች የሰጧቸውን ማሳሰቢያዎች የእኔ ብሎ ካለመሳጠጋት በመጣ ግድፈት ይኸው በዬትኛውም ዘመን የማይገኝ መታመን፤ ንጹህ ፍቅር አይሆኑ ሆኖ ባክነ። ረግጦ መግዛት ይቻል ይሆናል፤ ተወዶ መግዛት እና ማሰተዳደር ግን? 

ፍቅር እኔ የማውቀው ድንግሉ ፍቅር እናት ላይ እና ስፖርት ማልያ ላይ ብቻ ነበር። ያ ተገልብጦ በዚህ ዘመን አዬን ቁጭ ብለን ለሙሴ ሲሰጥ። በምልስት ሲታሰብ በህልም እንጂ በውን የሆነ አይመሰልም። ከሰማይ የተሰጠ ጸጋ ገዳቢ ስላልነበረው ፈቅዶ ወደ ፍቅርን ለመቀለብ አደባባይ የወጣው ሚሊዮን ነው።

ቤቱ ውስጥ ቁጭ ያለው አደባባይ ከወጣው በላይ ነው። ማህጸን ውስጥ ያሉ ህጻናት ለዛ የፍቅራዊነት መረህ የጸጋ ስግደት ሰግደውለታል። መኖር ተፈቅዶላቸው ስለነበር። ያን ፍቅር ፈቅዶ የሰጠው በተሰጠው ልክ አደራን በመቀበል በመከውን እረገድ ያዬነው አዬን።

ያን ጊዜ ወጀቡ ወጮፎው ነጎድጓዱ በርካታ ነበር። ነገር ግን ፍቅርን የተራበ ምልዕት አሉታዊ ጉዳዮችን ሁሉ ጥሶ በጣጥሶ፤ የሞገድ አሉታዊ ውጉያዎችን ንቆና አቃጥሎ፤  ምቀኝነቱን እና ሸሩን ደርምሶ፤ ቅናቱን እና የኢጎ አርበኛውን የወል ዘመቻ ጠቅጥቆ አብይ የእኔ ያለው ቅናዊ ፍቅር ዛሬ በዚህ መልክ ተደመደም። ኦዴፓም፤ ሊቃናቱም፤ የሚራው ህዝቡም ተስፋነቱም ባይመክንም ተጎሳቆለ። ታመመ። ደከመው። ቀዘቀዘው። ዛለ። ጥበብ ጠፋ።

በዚህ ማህል የነበረው እና ያለው አማራን የመጫን መከራ ልዑል እግዚአብሄር ፍርድ ይሰጥበታል። ቅንነት ሰው ሰራሽ አይደለም እና። የዋህነት ሰው ሰራሽ አይደለም እና። በደቦ ፍርድ በመንፈስ የተገለለው ማህበርሰብ አማራ ነበር ….

ለዚህ ነው እንጅባራ ላያ ታምራቱ የተገለጠው፤ መሬት ላይም ርደቱ … ወደ ራስ መመለስ፤ ወደ ህሊና መመለስ፤ ወደ ነፍስ መመለስ በተደሞ ይጠይቃል በሚሉት ልክ ሆኖ ለመገኘትም ፈቃደ እግዚአብሄርን መጠዬቅ። አማራም ኢትዮጵያዊ ነው። እንደ ሌላው መብቱ ሊጠበቅለት ይገባል። ጫን ተደል ጫነው ሊነሳለት ይገባል። የልዑል እግዚአብሄር ቅብዕ የኳስ ሜዳ ጨዋታ አይደለም። 

ማን አተረፈ ሲባል ቅናት ነው ያተረፈው። ግራ ዘመም ፖለቲካ ነው ያተረፈው። ሸር፤ ምቀኝነት፤ ጥላቻ፤ ቂም እና ቁርሾ ነው ያተረፉት። አንዲት ትንሽ ግድፈት ቤተ መንግሥት ውስጥ በድንገት አቆጠቆጠች፤ ተባች፤ አፈች፤ አሰበለች፤ በታዳሚው ዘንድም ተቀናቃኞችን ቀስቅሳ እልህ አመረተች፤ የፍቅር ድንቅ ልዩ ዘመን ሰጥ ተቋምን መለመላ አስቀረች …

አሁን ለሁሉም ቅናት ማህበርተኞች እፎይታ ነው። የቤት ሥራቸውን አጠናቀዋል። አኩል ተሆና! ወርቅ ከቀለጠ ይፈሳል። ታሪክ ያበጀው ወርቅ፤ ዘመንም የሰጠው ወርቅ እንዲሁ ቀልጦ ፈሰሰ።

„ልብ ያለው ሸብ!“
የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ።  

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።