የኢትጵያ ህዝብ የፍቅር ስጦታን ኤርትራ አደራውን የት ላይ አኖረችው?
ፍቱት።
„በፊቴም ደጃፉ ሁሉ የተከፈተ ነው፤ በእሳት ቅርጽም የተሠራ ነው።“
መጽሐፈ ሄኖክ ምዕራፍ ፬ ቁጥር ፶፫
ከሥርጉተ©ሥላሴ
07.10.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
እሙ በአንቺ የመንፈስ ድንግልና ብቻ የፍቅር ተፈጥሮ አደራ አለ።
- · ፍቱት አንድ።
እንዴት ናችሁ ውዶቼ? ደህና ናችሁ ወይ? ዛሬ ፍች ያጣሁለት ህልም አዬሁኝ። ስትፈጠር አንድ ጡት ያላት ሴት በህልሜ አዬሁኝ። በዚህ ነጮቹ ሲፈልጉ ጡታቸውን በሰው ሰራሽ እንደሚያስተልቁት በኦፕራሲዮን ወይንም እንደሚያሳድጉት አይደለም።
የሴቶች ጡት በተፈጥሮው ግራ እና ቀኝ ደረት ላይ ነው የሚበቅለው። ይህን እናት ጡት የጠባው ሁሉ ያውቀዋል። ይህ በህልሜ ያዬሁት ግን ማህል ላይ የበቀለ፤ ቅርጹ ሆድ የሚመስል ነው። የደረት ሆድ ልበለው ይሆን? እንደዛ ነው እኔ ዛሬ ሌሊት ያዬሁት።
እንደነዚህ ያሉ ገራሚ ህልሞች ሳይ ስነቃ ቤቴ ራሱ የእኔ መሆኑን እጠራጠራለሁኝ። አንድ ጊዜም „እኔ ድምጻችን ይሰማ ነኝ ስል እንዲህ የሚገረም ህልም አይቼ ነበር። ደፍሬ ልናገረው አልችልም እጅግ ከባድ ህልም ነበር ያየሁት።
ሌላ ጊዜ ደግሞ ሰማይ ላይ ብዙ ሰረጋላዎች የኢትዮጵያ ሰንድቅዓላማ ለብሰው አዬሁኝ። ሌላ ጊዜም አውስትራልያ በጋብቻ ልሄድ ወስኜ ነበር እና አውሮፕላን ሰማይ ላይ ቆሞ የማይንቀሳቀስ፤ የማይሄድ፤ ልክ እንደ መሬት ሞተሩን አውሮፕላኑ አጥፍቶ ግን ሰማይ ላይ ቆሞ እንደ ኩሬ ውሃ ረግቶ አይሁኝ።
ዛሬ ደግሞ ስትፈጠር የደረት ሆድ ያላት ግን ጡት የሆነ ጨፍ ያለው ልስላሴውም ተፈጥሮውም ጥራቱም ኢትዮጵያዊ የሆነ ጡት አዬሁኝ፤ እርግጥ ነው አንድ መሆኑ ከተፈጥሮ ውጪ ነው፤ ይዘቱ ጡት ነው፤ አፈጣጠሩ ማህል ላይ ነው ብቻ ከብዶኛል? ኢትዮጵያ ትሆን? እስኪ ፍቱት ገዶቼ።
- · ፍቱት ሁለት።፡
Ethiopia:ኦነግ በሀገሪቱ ሰላም ለማስከበር እንጂ ትጥቅ ለመፍታት አልተስማም ዳውድ ኢብሳ“
„ጉድን እና ጅራት“ ወደኋዋላ ይላል የአገሬ ሰው። ጉዱ የአቶ ዳውድ ኢብሳ አይደለም የኢትዮጵያ መንግሥት እንጂ። ኦነግን ያህል ድርጅት አገር ሲያስገባ በምን? እንዴት? የሚለው ያልበሰለ፤ ጥሬ እንዳይባል ሰዎቹ ዶር ለማ መገርሳ እና ዶር አብይ አህመድ ናቸው። ብቻ ፍቱት የቤት ሥራ ነው... ምን አልባትም የዕድሜ ልክ የቤት ሥራ ሊሆንም ይችላል።
ኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ ኤርትራ እኔ አመጠሁት ስትል እንደባጀቸው ቄሮን ለኦነግ፤ የአማራ የህልውና የማንነት ተጋድሎን ለግንቦት 7 የመሰጠቱ ሚሰጢር እዬወጣ ነው። የሁለቱ ተጋድሎዎች፤ የዶር ለማ መገርሳ፤ የዶር አብይ አህመድ፤ የአቶ ደመቀ መኮነን፤ የዶር ገዱ አንዳርጋቸው፤ የዶር አንባቸው መኮነን ተጋድሎ እና ውጤት ተጥቅልሎ የተሸለመ ይመስላል። በሞቀ - በለሰለሰ - በጠነከረ ክህሎት - በአፈራ የዕድሜ ልክ ሙሉ መሰናዶ እና ጥረት ያሰበለው የህዝብ ፍቅር ፍሬው እኔ ነኝ አይነት ነው። ታሪክ ሲገለበጥ። አቅመ ቢስ ነበር የለውጥ ሃይሉ ነው ፍሬ ነገሩ … በእኔ ምህንድስና ነው የተከወነው ነው ዕድምታው።
መንግሥት እንደ መንግሥት ከዬትኛውም አካል ጋር የሚያደርገው ንግግር ስምምነት በግልጥ እና በአደባባይ ሊሆን ይገባል። በዚህ በግርዶሽ ትዕይነት ነው ዛሬ ህዝብ እያለቀ ያለው። ታሪክም እዬተዘረፈ ነው። ትውፊትም መቅኖ እያጣ ነው።
የኢትዮጵያ መንግሥት በግል ይሁን በወል ከፖለቲካ ድርጅቶች ጋር ሆነ ከሊሂቃን ጋር የሚያደርገው ንግግር፤ ውይይት፤ የሚደርስበት ስምምነት ህዝብ በስማ በለው ተዛብቶ፤ ተጨምሮ፤ ተቀንሶ፤ ተጨማትሮ ሃላፊነት በሚሳማቸውም ሆነ በማይሰማቸው ሚዲያዎች ከሚያዳምጠው ስለምን መንግሥት ለህዝብ በግልጥ እንደማያሳውቅ ግራ ይገባል።
እስከ መቼስ ህዝብ በጉዳዮቹ ላይ ባይታዋር ሆኖ ይኖራል? እንደ ገናስ እንዴት መንግሥት ለህዝብ የምንሥራ መንግሥት ነን የሚለውን አሳታርቆ እና አስማምቶ ሊቀጥል እንደሚችል ወጣ ገባ ገጠመኝ ነው። ግልጽነት፤ ተጠያቂነት እና ሚዛናዊነት ከአብይ ሌጋሲ ሲጠፋ አይመችም ተገዶ ሊሆን እንደሚችልም አስባለሁኝ። ሌላ ዘርክራ ላይ ቢሆን አይደንቅም። አብይ ነፍሱ መንፈሱ የተሰጠው ፍጹም ድርጁ ስንዱ ነውና። አሁን ግን ሳያስበው መጠራቅቅ ውስጥ የገባ ይመስላል፤ ጥረቱም ስጦ እንዲሆን የተፈለገ ይመስላል …
ከዋልታ ቴቪዥን ጋር አቶ ዳውድ ኢብሳ ቃለ ምልልስ አድርገዋል ከሰሞናቱ መሰለኝ። ዛሬ አገኘሁት እና በተደሞ አዳመጥኩት። የዛሬም የነገም የድምጽ አልባዎቹ እናቶች እንባ በዬዘመኑ በተቀበሩ ፈንጆች ማህጸናቸው መጋዬቱ ሊያባራ አለመቻሉ ጉዳዬ ስለሆነ በዚህ ዙሪያ የምለው ይኖረኛል - ዛሬ።
እኔ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽነር ዘይኑ ጀማል እና አቶ ዳውድ ኢብሳ መንትዮሽ ይመስሉኛል ሰብዕናቸው። የታመቀ፤ ሊናገሩት የማይፈቅዱት ዝግ የሆነ ሰብዕና በሁለቱም አያባቸዋለሁኝ። ገልጠው አይናገሩትም፤ በተገባው ሁኔታ አያባራሩትም ግን ነፍሳቸው ሽምቅ ውጊያ ላይ አንዳለች ይሰማኛል። እንደዚህ ዓይነት ሰብዕናዎች አደባባይን አይደፈሩትም ካልተገደዱ በስተቀር። ኑሯቸውም በተዛጋ ድልድይ ነው።
ውዶቼ --- ይህን ቃለ ምልልስ ቃል በቃል መጻፉን መርጨዋለሁኝ። ቀደም ሲል ጠ/ ሚር አብይ አህመድ አስመራ በነበሩበት ጊዜ አቶ ዳውድ ኢብሳን እንዳወያዮቸው ተገልጧል። እዛ የነበሩ የሌሎች የተቃዋሚ ሃይሎች ድርጅቶችን ያነጋግሩ አያነጋጋሩ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ አይታወቅም። ስለምን ኦነግን ብቻ ከሆነም ስለምን የሚለውን ሌላ የጥያቄ ጥያቄ ያስነሳል?
ግንቦት 7 በሚመለከት አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ ጋር ሰፋ ያለ የግል ውይይት ስላደረጉ በዲሲው ጉዞም እንዲሁ ዝግ ንግግር እንደ ነበር ተደምጧል። ሌሎችስ የሚለው አብሮ የሚነሳ ይሆናል። ዕድሉን ለሁሉም አድርገውት ከሆነ መልካም ነው ካላደረጉት ግን ተባደግ ያደርገዋል ጥረቱን ወይንም ተዛነፍ አያያዝ ያደርገዋል አመራሩን። ብዙዎቹን የፖለቲካ ድርጅቶች ሊሂቃን ኳስ ሜዳ ላይ እንደሚጫወት ተጫዋች ሲሰተናገዱም ዲሲ ላይ ተመልክተናል።
በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግን በሚመለከት ከዶር አብይ አህመድ በተጨማሪ፤ የውጭ ጉዳይ ሚ/ሩ በተገኙበት ዶር ለማ መገርሳም እዛው ኤርትራ ድረስ ሄደው ውይይት እንዳደረጉ እና ስምምነት እንደ ተደረገ ተደምጦ ነበር።
እርግጥ ነው ዶር ለማ መገርሳ ኤርትራ ሲሄዱ አውራ ዜና ሆኖ ሲመለሱ ግን የውሃ ሽታ፤ የውሽማ ሞት ሆኖ ነበር ዜናው። እኔ እንዲያውም የት ገቡ ኤርትራ ቀሩ ወይ እያልኩኝ ብዙ ጊዜ ጽፌያለሁኝ። ገራሚው ነገር ጥድፊያው ወዲያው ከስሜን አሜሪካ እንደገቡ ነበር ዶር ለማ መገርሳ ወደ ኤርትራ ያቀኑት። በመሃል ተጠፋፋን። ከዶር አብይ አህመድ ጋርም ከዶር ለማ መገርሳ ጋርም መገናኘት ማዕቀብ ተጣለበት። ምን ቅድመ ሁኔታ መጣ ሁሉ ብዬ ነበር። እሳቸውን ለመያዣነት?
ብቻ ሲሄዱ ያን ያህል የተዘገበው ሲመለሱ በምን ሁኔታ እንዴት የሚለው ሾላ በድፍን ነበር። ለዚህ ነው ለረጅም ጊዜ ጠረኑን ስጠራጠረው የነበርኩት። ለነገሩ ውጥኑ የተጀመረው ዶር አብይ አህመድ ወደ ስሜን አሜሪካ ጉዞ ሲጀመሩ ባዶ ወንበርም በህልሜ ስላዬሁኝ ጥርጣሬዬ ንሮ ነበር። ይህን ማን አቀናጀው ታሪክ እና ዘመን ያወጣዋል። ካልከሌቱሩ የመደመሩ እኔው ነኝ ያለው አቶ ጃዋር መሃመድ ይህን ይሆን? አገር ቤትም ሁለት አውራዎች አሉለት ብአዴን/ አዴፓ እና ኦህዴድ/ አዴፓ ላይ ... ጠረኑ አሪስኛ ነው። በዛ ላይ አቶ ከይሲ ተስፋዬ ገበረ ሰይጣይንም አሉ ምጥዋ ላይ ነፋሻውን አዬር እዬማጉ ሸር ይጎነጉናሉ።
የሆነ ሆኖ አንድን ዜና መነሻ ከሰጠኸው መድረሻውን መግለጽ ግድ ይላል ማለት ነው። አቶ ለማ መገርሳ ኤርትራ የሄዱበት ምክንያት ተሰካም አልተሳካም ለህዝብ ግልጽ መደረግ ነበረበት። መቼም የራሳችን ጉዳይ ነው እንደማይሉን ተስፋ አደርጋለሁኝ። የኢትዮጵያ ጠ/ ሚር መሆናቸውን አድምጠናል እኛም ባይባልም የሁላችንም መሪ ናቸው ብለንም እናምናለን።
ኦነግ ግንዱ እና ቅርንጫፉ የቱ ነው ለማለት ግራ ቢያጋባም በቅርቡ አቶ ጃዋር መሃመድ እና አቶ በቀለ ገርባ እንደገለጹልን ስትራቴጃዊ ዘዴ እንደ ነበር ተገልጦልናል የቁጥሩ መበራከት የ ኦነጋውያን ድርጅቶች ጉዳይ። ስለዚህ እናት አባቱ አንድ ነው ነው ማለት ነው የኦነግ።
ኤርትራ ስለነበሩት የነፃነት ሃይሎች ትጥቅ ማስፈታትን በሚመለከት ለጠ/ ሚር አብይ አህመድ የጋዜጠኞች ጉባኤ ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት የምላሻቸው ዕድምታ "የታጠቁ ሃይሎች ሰላማዊ ትግልን ሲመርጡ መታጠቅ የሚገባቸው ሃሳብ ነው፤ ጠበንጃ ከሆን ስለምን ይመጣሉ" አሉን።
የኤርትራ መንግስትም በበኩሉ ደግሞ በአቶ ዳውድ ኢብሳ የሚመራው ኦነግ ከፈለገ ኤርትራ ትጥቁን ፈቶ መቀመጥ እንደሚችል እና በስተቀርም ትጥቁን ፈቶ ኢትዮጵያ መግባት እንዳለበት መወሰኑን አዳምጠናል።
ከውሳኔው በፊትም እኔ ይህን ለኤርትራ መንግሥት አሳስቤ ስለነበር የኤርትራ መንግሥትን ውሳኔ ሳዳማጥ ወሳኔውን የተገባ ስለመሆኑ አንድ ጹሑፍ ከምስጋና ጋር ጽፌያለሁኝ። እኔ ድርድሩ የኢትዮ ኤርትራ ቅናዊ ነው ብዬ አስብ ነበር። ነፍሴ ስምምነቱን ስትቀበለው ከውስጧ ነበር። እርግጥ ነው አልፎ አልፎ የማያቸው ተዛናፎች ወሰድ መልስ ቢያደርጉኝም። ምክንያቱም ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ጋር የሚደረግ ማናቸውም ድርድር ልብ የሚያስጥል አይደለም እያልኩ ስጽፍም ነበር። ከልጅነት ጀምሮ ነው እምከታተላቸው። በውሳኔያቸውም ያለው ጽናትም?
አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ አፈጣጠራቸው እንደ ሰው ቢሆንም ለዬት ብለው ከሚፈጠሩት ወገኖች ውስጥም መሆናቸው መዘንጋት የለበትም። ኢትዮጵያን በሚመለከት ለሌላ የደህነት ባለሥልጣን ወይንም ባለሙያ ሳይሆን ራሳቸው ነው የሚከታተሉት ብዬም ጽፌያለሁኝ፤ ይህን ውርስም ለመስቀጥል ነው ልጃቸውን በዛለ አንበሳውም በአዲሱ የአርብ አገር ስምምነት ላይ እንዲገኙ ያስደረጉት። ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂን ነፍስህ ምን ላይ ታተኩራለች ቢባል ኢትዮጵያ ፖለቲካ ላይ ነው የሚሉት። የኢትዮጵያን ፖለቲካ አልባ እንቅልፍ አይወስዳቸውም። ሌላ አጀንዳ የላቸውም።
የሆነ ሆኖ አሁን ይህን የሚያስታርቅ ይሁን የሚያቃርን ቃለ ምልልስ አዳምጫለሁኝ። ለነገሩ በሱዳን በኩል ይሁን በሱማሌ በኩል በህገ ወጥ መልክ የሚገቡት የመሳሪያ ሁኔታ በግፍ መሆን አገር ውስጥ ያለውን ለውጥ የመቀለበስ ይሁን እንዳይቀጥል የማድረግ ሌላ የታመቀ ነቀዝ ጉዳይ እንዳለበት አመላካችም ነው። የሚናፍቀው የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ጉዳይ በቅንነት - በጥራት - በድንግልና መቼ እና መቼ መቸቱ እንደሚከውን ይንፍቀኛል። ያ የፍቅር አደራ የት ነው አድራሻው?ከዛች ቀንበጥ ህጻን መንፈስ ውስጥ ብቻ?
- · ቃለ ምልልሱ እንዲህ ይላል።
አቶ ዳውድ ኢብሳ እንዲህ ይላሉ። ወገኖቼ ከልብ ሆናችሁ አዳምጡት ይህ የአልጀርሱን ስምምነት እንዲተገበር ኢህአዴግ በቅንነት የወሰነውንም ይመለከታል። ውጤቱ የዛ ስለሆነ። „ትጥቅ መፍታት የሚባል በጣም ሴንሲቲብ ጥያቄ ነው። ትጥቅ ፈታ አይባልም። ትጥቅ ፈታ ትጥቅ ፈቱ መባልንም አንፈልግም።“ አራት ነጥብ።
በዚህ ሃሳብ ውስጥ ያለው ትልቁ ጥያቄ የዶግማ ነው። ሌላው የሥነ - ልቦና ነው። ሌላው የኪዳን ጉዳይ ነው። ሌላው ቃል እና ተግባርን የማዋደድ ጉዳይ ነው። ሌላው የኤርትራ ውለታ ባክኖ እንዳይቀር ቀለበት በማህተም አለበት።
ይህን መፍታት ያልቻለ ስምምነት እንዳልተካሄደ ነው እኔን የሚገባኝ። ሾላ በድፍን በሆነ ሁኔታ፤ በህጋዊ ሁኔታ ለዛውም የኢትዮጵያ መንግሥት በአደባባይ እንኳን ደህና መጣችሁልን ብሎ ህዝብ አሰለፎ እያስጨበጨበ ነው የተቀበለው።
ለደረሰው ማናቸውም ጥፋት ለእኔ ኦህዴድ/ ኦዴፓ እና የኢትዮጵያ መንግሥት ይሆናሉ ተጠያቂዎች። ተደራዳሪዎች እነሱው ናቸው እና። የተሰራው ነገር ሃላፊነት የጎደለው ነገር ነው። ይምጡ የመጣው ይምጣ፤ የሆነው ይሁን ተብሎ አቅም የማሰባሰብ እና በሃይልም በግድም በጫናም ኦህዴድ/ ኦዴፓ በግንባሩ በኢህአዴግ እና በኢትዮጵያ ህዝብ በሰጡት ፍቅር የኦነግን ጥንተ ውረስ ቅርስ ዓላማ ማስፈጸም የሚመስል አዬር ነው ያለው። ስናዬው የሰነበትነውም ይህንኑ ነው።
ጭብጡ የሚያስረዳን እንደዚህ ነው። ስምምነት ላይ ካልተደረሰ በአደባባይ ገብተው ማህል አዲስ አባባ እና ዙሪያው እንዲህ መታመስ እንዲፈጠር መደረግ አልነበረበትም።
በዚህ ውስጥ የኤርትራ መንግሥስትም ሚና የት ላይ ይሁን? መሰረታዊ ጥያቄው ይህ ነው። በለውጡ እና ኢትዮጵያ ድንቅ ሙሴ ማግኘቷ ለ ለኤርትራ መንግሥት ከስምምነቱ በፊት እና በኋዋላ ያለው ዕድምታ ምንድን ነው? በጥልቀት መፈተሽ አለበት። ቅናት ይሆን?
የወያኔ ሃርነት ትግራይ ከኦነግ ጋር የኢትዮጵያ መንግሥት ያደረገው ስምምነቱ ይፋ ስላልሆነለት እንደ እኛ በስማ በለው ስለሚሰማው ኦነግ አርማውን ይዞ ሲገባ ህጋዊ ፈቃድ ሰጥቶ አስተናግዶ ወደ ማህል አገር ሸኝቷል።
በዚህም አግባብ ኦፌሻል የሆነ የወያኔ ሃርነት ትግራይ እና የኦነግ ስምምነት ሰሌለ - ውስጥ ለውስጥ ኦነግና ወያኔ ሌላ ስምምነት ሊኖራቸው ይቻላል፤ ኦፌሻል የሆነው ግን የፌድራል መንግስት ስምምነት መልኩ ምን እንደሚመስል ስለማይታወቅ፤ ኦፌሻል የሆነ የኦህዴድ/ ኦዴፓ ስምምነት ስላልተደመጠ፤ ስለማናውቀው ኦነግን ሊያሰጠይቅ የሚችል አንዳችም ነገር የለውም። የተገባለትን ቃል አናውቀውም። በመሃል የኤርትራን ክብር የሚያስጠብቅ ሌላ ሥነ - አምክንዮ እንዳለ ግን አሊማለት አይቻልም።
ምክንያቱም ስምምነቱ አገር ወስጥ ገብተው እንዲታገሉ እንጂ ትጥቅ በመፍታት እረገድ ግልጽ የሆነ አቋም የወሰደ አካል የለም እና። አልተሸነፍነም "የኢትዮጵያ መንግሥት ትጥቅ አስፈቺ እኛ ትጥቅ ፈቺ አይደለንም ነው" የሚሉት አቶ ዳውድ ኢብሳ።
እሳቸው ይህን ቃለ ምልልስ መልዕክት የሚልኩት ለኦሮሞ ህዝብ ነው። ትጥቅ አልፈታነም፤ አልተሸነፍነም፤ መንግሥትም እኛም በአንተ ጉዳይ ላይ አኩል ሃይል እና አቅም አለን ነው የሚሉት። የኤርትራ መንግሥትም በዚህ ወስጥ ሚናውን ለመለካት ህም ይደመርበት። እነ አቶ ጀዋር መሃመድም፤ አቶ በቀለ ገርባም ያሉን ይህንኑ ነው።
ይህ አገለላጽ ወደ 50 ዓመት የነበረው የኦነግ ተጋድሎ የፈሰሰው ደም፤ የጠፋው አገራዊ ሃብት፤ የተጎሳቆለው ቤተሰብ ሁሉም ፈሶ አልቀረም እኛም አሸንፍን ነው የገባነው ነው መሰረታዊ ጉዳዩ።
ኤርትራን መሬቱን ለቀቁ እንጂ የትጥቅ ትግል ዓላማቸውን ወደ ሁለገብ ትግል እንዳሻገሩት ፍንጭም ይሰጣል ይህ ሃሳብ። ዝቅ ብሎ ስለ ሰላም የገለጹት ስላለ …. የኦነግ የተጋድሎ ዶግማ ባለበት አቋሙ ጸንቶ ነው የሚገኘው። ዕድሉ አለ የተጠናከረ መዋቅራዊ ሁኔታ መሬት አለ በመንግሥት ደረጃ። ምን ምን እንደሆነ አይታወቅም። ተቀይጧል። በዕድሉ እንጠቀማለን ነው መሰረታዊ ፍልስፋናው። የጃዋርውያን፤ የበቀላውያን፤ የህዝቃልውያን አለፍ ሲልም ባልጠራ ሁኔታ ኦህዴድ/ ኦዴፓ ውስጥ ያሉ ኦነጋውያን መንፈስ የሚሰማሙበት መሰረታዊ ጭብጥ አለ። የዋሁ የኢትዮጵያ ህዝብ ለግራ ቀኙ ለአብዩ ለለሚ ለኢሱ የተሰጠው ያ ታማኝነት እና ገደብ የለሽ ፍቅርስ ?
- · እስቲ እንቀጥል ወደ ሌላው ሐርግ ከቀደመው ጋር በማያያዝ፤
„ትጥቅ መፍታት የሚባል በጣም ሴንሲቲብ ጥያቄ ነው። ትጥቅ ፈታ አይባልም። ትጥቅ ፈታ ትጥቅ ፈቱ መባልንም አንፈልግም።“ ምክንያቱም ከዚህ ጋር ተያይዞ ያለው ምንድን ነው ከዚህ ጋር ተያይዞ አንዱ ትጥቅ የሚፈታ አንዱ ትጥቅ የሚያስፈታ ይመስላል፤ አይደለም እንደ እሱ አይደለም የመጣነው። እኛ የመጣነው ትጥቅ በመፍታት ስምምነት አይደለም“ ነው የሚሉት አቶ ዳውድ ኢብሳ።
ስለዚህ የኦነግ አርማ አዲስ አባባ ላይ የተውለበለበት ምክንያት እና የሁሉም የኦሮሞ ድርጅት ሊሂቃን ድርጊቱን የደገፉበት መሰረታዊ ምክንያት እውነቱ ይህ ነው። ኦነግ በድል ገብቷል ነው ሚስጢሩ።
ሥልጣኑ የተጋድሎው ውጤት ነው። ለዚህም ነው በሥም ብቻ የተለያዩት ለስትራቴጂ ሲሉ ነው እያሉ የሚነግሩን፤ ይህን የሰሞናቱ የአቶ ጃዋር መሃመድ ቃለ ምልልስም በአንክሮ ገልፆታል መግለጫው የዚህ ቃለ ምልልስ አስኳል ነው።
ስለዚህ በስተጀርባ ያለው አቅም ያለውን መንግሥት ቁልጭ አድርጎ ያሳያል። መንፍንቅለ መንፈስ እያልኩኝ ከስሜን አሜሪካ ጉዞ መልስ ስጽፍ ነበር አይደል? ይህ ሁሉ የለውጥ ይገባኛል የኮፒ ራይት ድራማ የተከወነው ያን ጊዜ ነው። አሁን የኮፒ ራይቱ የለውጡ ባላባት እትጌ ኤርትራ ናት።
ይህን ካልተቀበለ የኢትዮጵያ መንግሥት ሌላ ነገር ይናድበታል። ራሱ የወደብ ጉዳይ ከጁቡቲ ጋር ለመቀጠል ሌላ ጋራ አለበት። ስለሆነም የኢትዮጵያ መንግሥት ህዝብ ያላወቀው መጠራቅቅ ውስጥ እንዳለ ማዬት ይቻላል። ሦስተኛ ወገን እንዳለበት ይታያል እዚህ ላይ።
እግዲህ ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በአገራዊ ደህነንት፤ በሲቢሉም በሚሊተሪውም የደህንንት ባለሙያዎች ሲመሯት የመጀመሪያ ጊዜያዋ ነው። ወርቃም ሁሉ ጽፌዋለሁኝ። ኦህዴድ / ኦዴፓ ከኤርትራ መንግሥት ተጽዕኖ ነጻ የሆነ መሆኑ ነበር ትልቁ ታሪካዊ የለወጡ ዓይነተኛ ዕዕምዳዊ ዕሴት ጉዳይ። አሁን ግን በፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ የማድረግ አቅም የዛ ቢክተም ሆኗል ለውጡ። ተወደደም ተጠላም።
አይደፈርም ተብሎ የታሰበው አቅም እና ክህሎት የተሸነፈበት፤ እጁን የሰጠበት፤ የተበለጠበት የፖለቲካ ሁኔታ ግን ሾላ በድፍን የሆነበት ጉዳይ እንዳለ ይሰማኛል።
ከስሜን አሜሪካ መልስ የተደሞ ሰሞን ነበር። ዶር ለማ መገርሳም ዶር አብይ አህመድም የተሰወሩበት ወቅት ነበር። ያ ራሱን የቻለ አዲስ ሌላ ምዕራፍ ነበር። ታስታውሱ እንደሆን ምዕራፍ አንድ ተዘግቶ ምዕራፍ ሁለት ተጀምሯል ብያችሁ ነበር። አሁን ደግሞ ምዕራፍ ሁለት ተጠናቆ ምዕራፍ ሦስት ተጀምሯል።
የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ስምምነት ቅናዊ ጉዞ የተቀለበሰበት ጭራ ልበለው ውለብልቢት ይታዬኛል። የፍቅር አደራ ታሪካዊ ሃላፊነቱን በጠራ መስመር ለመቀጠል እንከን እንዳለበትም ይታዬኛል።
- · እንቀጥል ወደ ልባሙ የአቶ ዳውድ ኢብሳ ቃለ ምልልስ …
„ትጥቅ መፍታት የሚባል በጣም ሴንሲቲብ ጥያቄ ነው። ትጥቅ ፈታ አይባልም። ትጥቅ ፈታ ትጥቅ ፈቱ መባልንም አንፈልግም። ምክንያቱም ከዚህ ጋር ተያይዞ ያለው ምንድን ነው? ከዚህ ጋር ተያይዞ አንዱ ትጥቅ የሚፈታ አንዱ ትጥቅ የሚያስፈታ ይመስላል። አይደለም እንደ እሱ አይደለም የመጣነው። አጠቃላይ በሰላማዊ አገሪቱ ሰላም እንድትጠበቅ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ያለው ሚና „ፕሬዚላዊ ?“ እንዴት እንደሚሳተፍ በዚህ ውስጥ የእኛ ሚና ምን እንደሚሆን በዚህ ነው የተሰማማነው።“ ይህም ማለት ድርጅቱ ኦነግ በሰላማዊ እና በትጥቅ ትግሉን በሁለገብ መልኩ ይቀጥላል ማለት ነው።
ክብረቶቼ አንድ ቃል ሳይገባኝ አልፏል „ፕሬዚላዊ“ የሚል ነው። ይህ ቃል ቢታወቅ በትክክል ተገልጦ ቢሆን ኑሮ እጅግ የተሻለ ይሆን ነበር። የአቶ ዳውድ ኢብሳ ድምጻቸው ለሆሳሳ ነው በተፈጥሮው። የዚህ አረፍተ ነገር ቁልፍ እዚህ ቃል ላይ ነበር፤ ግን ላዳምጠው አልቻልኩኝም። የኢትዮጵያ የውስጥ ሰላሟ አሁን መዳፏ ላይ ያለው እትጌ ኤርትራ ላይ ነው። ማሳስርም መስፈታትም የክሱን ዓይነት መወሰንም ማስወስንም …
የኤርትራ ሆነ የኢትዮጵያ ህዝብ ስምምነቱን ይፈቅዳዋል። የኤርትራ መንግሥት ግን በኢትዮጵያ ፖለቲካ በአብላጫ የማድረግ አቅም ካልኖረው የሚፈቅደው አይመስልም። የዚህን ሚስጢር ታች ላይ ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን የጸፈውን እና እኔ የሰጠሁትን መልስ ማመሳከር ይቻላል። ኤርትራ ስታግዛቸው ከነበሩት ታጣቂ ሃይሎች ጋር የነበረው ስምምነት ከአልጀርሱ በላይ ስለመሆኑ ፍንጪ የወጣበት አጋጣሚ ነው።
አፈጻጸሙን ነው የኤርትራ መንግሥት ያወቀበት እሱ ባልነበረበት ለውጥ እሱ ባልሰራው የህዝብ ፍቅር፤ እሱ ባልተፈላሰፈበት የአማራር ልቅና የባለቤትነት ጥያቄ የፈጠረው ግጭት ነው አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ህውከት።
ያልተጠራ ስምምነት እንዳለ ነው እኔን የሚሰማኝ። ኤርትራ ትጥቃቸውን ከሳፈታቸው / ካላስፈታቸው መሬት በማጣት ስለነበር ወደ ኤርትራ የሄዱት። አሁን ግን ቀጥ ብለው በአውሮፓላን ገብተው ትናንት ያጡት መሬት ተፈቅዶላቸው የተሻለ ሁኔታ አግኝተው በፈለጉት መልክ እንዲታገሉ ምቹ ሁኔታ ተፈጥሮላቸዋል ማለት ነው ለ ኦነጋውያን ደርቡም ምድሩም ፈትሉም ዘሃውም። ስለዚህ መከራው ቀጣይ መሆኑ ነው የሚታዬኝ። ከግራጫማ ሰብዕና ግራጫማ ፖለቲካ …
- · ፍቱት ሦስት።
በአልጀርሱ ስምምነት ወደ ተግባር ስለመቀዬር ላይ ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን አይሳካም የሚል ጹሑፍ ሲጽፍ ልብ ያለው ስላልነበር ሚስጢር አዋቂም ስለሆነ „የባድም ዕድምታ በሥርጉተ ዕይታ“ የሚል ጹሑፍ ጽፌ ነበር። ጹሑፉ ወዲያው ሰው እያነበበው ነበር ሳተናው ድህረ ገጽ ላይ የተነሳው። እኔ ቀንበጥ ብሎግን የጀመርኩትም በዚህ ምክንያት ነው። እኔ በቅንነት መንፈሴ የሚለኝ ነው የምጽፈው። እምወግነው ፓርቲ የለኝም። ያ ጹሑፍ የተነሳበት ምክንያት አሁን ይልቅ ትንሽ ነገር ታዬኝ?
በሌላ በኩል አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ በካናዳ ጉባኤ ላይ ግንቦት 7 በኢትዮ ኤርትራ ስምምነት ላይ እጁ እንዳለበት ገልጸው ነበር። ይህ ጥያቄም በተመሳሳይ ሁኔታ የጋዜጠኞች ጉባኤ ላይ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ተጠይቀውበት ነበር። አስተውሉ ወገኖቼ የኦነግ ትጥቅ መፍታትም በዚህ የጋዜጠኞች ጉባኤ ላይ ተነስቶ ነበር። በጣምራ ያሉትን ጭብጦች ተመልከቷቸው። ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ከጋዜጠኞች ጉባኤ ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልስ ማግኘት ስለሚቻል ማረጋገጥ ይቻላል እዛ።
ሌላው ከዚህ ጋር እንዲታይ የሚፈለገው የኤርትራ መንግሥትን ከደሙ ንጹሁ ነው ማለት የማያስችለው የግንቦት 7 አቀባባል ልክ እንደ ኦነጉ እንደ ነበር እንስተውላለን። ድርድሩም ዝግ ነው። ከአቶ አንዳርጋቸው ጽጌ ጋርም፤ ሆነ ዲሲ ላይ የተደረገው ስምምነት። ሁለቱም ኤርትራ ነው የነበሩት። በአንድ ጹሑፌም ይህን ጠቆም አድርጌው ነበር።
ግንቦት 7 ኤርትራ የገባው ብዕር ብቻ ይዞ ነው። ሄዶ ቤት ተከራዬ ወይንም ተዳበለ። አዳባዩ የኢትዮጵያ አርበኞች ግንባር ሲበቃው አለኝ የሚለውን ሰራዊት በአውቶብስ እንኳን እንደ ኦነግ፤ እንደ አማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል አላስፈለገውም ድሮም ኪራይ ስለነበረ በጭነት መኪና ባህርዳር ላይ አራግፎ እፎይ ብሏል ግንቦት 7።
እሱ ብዕሩን ይዞ በቻርትር ኢትዮጵያ ገብቷል። ኮልት የለውም፤ ክላሽን የለውም። አንድም አገር ውስጥ የካሄዱ ዲሞዎች የኢትዮጵያን ብሄራዊ ሰንድቅ ዓላማ ይዞ የወጣ የለም፡ ከጎንደሩ/ ከጎጃሙ የአማራ የማንነት ይህልውና ታገድሎ በስተቀር። አማራ የታገለለትን ለብሄራዊ ሰንድቅዓላማው ቀደም ባሉት ሰሞናት ሰማያዊ እኔ ነኝ ብሎ ወጥቶ ነበር። አሁን ደግሞ ግንቦት 7 የተጋድሎዬ እንብርት ነው ብሎ ኦነግም ዓርማውን፤ ግንቦት 7 የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንድቅዓላማ ይዘው ሁለቱንም አታኮሱ የኤርትራ መንግሥት መዲናው ላይ አስማራ ይፍለቀለቃል። የልቡን አድርሷል።
የኢትዮጵያ ርዕሰ መዲና አዲስ አባባ ፍዳዋን የከፈለችው በዚህ ምክንያት ነው። የኦነግን አርማ አስይዞ አነግን፤ የኢትዮጵያን ብሄራዊ ሰንድቅ ዓላማ አስይዞ ግንቦት 7ን። ይህ ማለት የአማራን ተጋድሎ ለግንቦት 7 የኦሮምን ንቅናቄን ለኦነግ አስረክቦ አዲሱ የለውጥ ሃይል ቁልጭ ባለው ሁኔታ ሃብተ ኤርትራ አመራር ሆኖ፤ ጥርት ባለው ሁኔታ የኤርትራ እና የኢትዮጵያ ስምምነት በዚህ ጭብጥ ዙሪያ ያጠነጥናል፤ በስተጀርባ የአረብ ኢምሪት ዶላር ፈንጁን አጥምዶ ሁኔታዎችን ይከታተላል። ድምጽ አልባው ትዕይንት ...
ለዚህም ነው ግንቦት 7 የአማራ ክልል ያን ያህል እንዲያነጥፍለት የተደረገበት ዋናው አብይ መሰረታዊ ጉዳይ። „ወደ ፓርቲነት ለመቀዬር 6 ወር የሚጠብቀው ስለምን ይሆን ግንቦት 7፤ ለመፎካካር ሳይሆን ለማረጋጋት ነው የመጣሁት የሚለውስ ስለምን ነው፤ ምን እርግጠኛ የሚያደርገው ነገር ቢኖር ነው?
ጭብጦቹ ቀጥ አድርገው የሚወስዱን የዚህ ሂደት ጭንቅለቱ ኤርትራ መሆኗን ነው።
ሌላው አስቂኙ ጉዳይ በተደጋጋሚ ጽፌዋለሁኝ ልክ ኦሮምያ ላይ የተፈጠረው ዓይነት ቲያትር ይፈጠር ዘንድ ይመስላል አሁንም ፕ/ ኢሳያስን ያህል መሪ አንድ የእኔ ቢጤ የአማራ ልዑክ ሊያነጋግር ኤርትራ እንደገባ ጦሱ ምን ሊሆን እንደሚችል ደግሞ እሰቡት። ኢትዮጵያን ከሁለት የመተርትር ዓላማ ነው። ሌላ መርዝ ለማብቅል ነው ጥረቱ። የጃውርውያን የባህርዳር ጉዞም ከዚህ ተደሞ አያመልጥም።
አሁን እንዛ ኤርትራ ገቡ የተባሉት የአማራ ልዑክ ቡድን ድፍረት አይሆንም ከዛ ዕድሜውን ሙሉ በደህንንነት ውስጥ ከኖረ የመካካለኛው ምስራቅ አፍሪካን ፖለቲካ ብጥልጥል አድርጎ መላላጫ ከሚያወጣ፤ ሉላዊ መንግሥታትን ሁሉ አልሻም ብሎ ላፈነገጠ ጉልበታም አቅም ጋር ድርድር ብአዴን/ አዴፓ? የስካር ጉዞ ብለው ይሻላል።
አባታችን አቡነ አብርሃም ቃሉ ባይመለካታቸውም ለኢትዮ ኤርትራ ግንኙት ብዙም የሳቸው ከዛ መገኘት የሚፈይደውም የለም። ሰውዬው እኮ ኢትዮጵያዊ ፑቲን ናቸው። ወደ ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ለጤባ ጢቦ ጨዋታ ነው እንዛ ልዑኮች የሄዱት፤ እሳቸውን ለመመጠን ወይ ዶር ካሳ ከበደን፤ ወይ ኮ/ ጎሹ ወልዴ ብቻ ነው የሚመጥኗቸው። ከዚህ ውጪ ድፈረት ይሆናል።
የሆነ ሁኖ የተፈለገው በኦሮምያ በኩል የተገኘው ትርፍ በአማራ ተደግሞ የኤርትራ መንግሥት እንዳሻው የፖለቲካውን መሪ እንዲመራው ነው። ከዚህ ግቡ የማይባሉ፤ ራሳቸውን መግለጽ የማይችሉ የአማራ የብአዴን ልዑክ ቀርቶ ዶር አብይ አህመድ እና ዶር ለማ መገርሳ በሙያም አቻ የሆኑት የቻሉት አይመስልም። ዶር ለማ መገርሳ እኮ ሙያቸው ፖለቲካ ሳይንቲስት ናቸው። ማስተራቸውን የሠሩትም በዓለም አቀፍ ግንኙነት ነው። ዶር አብይ አህመድም ዶክትሬታቸውን በሰላም እና በደህንነት ነው የሠሩት፤ በዛ ላይ ግራ ቀኙ የደህንነት ሙያተኞች ናቸው - ሠርተውበታል። ከእነሱ አቅም በላይ የሆነ ነገር ነው አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለው።
አሁን የኢትዮጵያን ፖለቲካ በበላይነት እያሾረች ያለችው ኤርትራ ናት። ስምምነቱ ቀጣይ ይሆናል ይዘልቃል ወይ? ሌላው ሞጋች አምክንዮ ነው። ትልቁ ዒላማ ግን ተሳክቷል። ዶር አብይ አህመድ የአፍሪካ የመሪነት አቅም ልዕልና እስኪበቃው ድረስ ታውኳል።
ዶር አብይ አህመድ በ100 ቀን የከወኑት ገድል ሁሉ ጠራጠሮ ሆኗል። ምዕራብውያን ለጠ/ ሚር አብይ አህመድ ያላቸው እምነት ጥያቄ ውስጥ ገብቷል። ህዝቡ የሰጣቸው ፍቅር ተጻራሪውን እንደፈጽም ካቢናቸው ተገዶ ደጋፊወቻቸውን በማሰር እራሳቸው አዳምነውታል። ይህ ታላቅ ድል ነው ለኤርትራ መንግሥት እና ላሰመራቻቸው እኩይ መንፈሶች።
ራሱ በዓለም አደባባይ በተባበሩት መንግሥታት የመገኘታቸው ዜና ዓለም እሳቸውን በይበልጥ እንዲያውቅ ከእዮር የተሰጠ መክሊት ነበር። ያ ተሰናክሏል። ተስተጓጉሏል። አዛውንቱ ፓለቲከኛ አቶ ኢሳያስ አፈወርቂ እያሉ ወይንም እሳቸው ሪኮሞንድ የሚያደርጓቸው መሪ እያሉ እንዴት ተብሎ።
ቀን አብረህ ትገናባለህ ሌሊት ደግሞ ትንዳለህ ግራ ምንግዜም ግራ ነው። ያ የምልዕት የመንፈስ ሃብት ዛሬ ጠራጠሮ ነው። ነገስ? በምን ዓይነት ጥበብ የአብይ ለማ ሌጋሲ ከተገባበት ረግረግ እንደሚወጣ አንድዬ ይወቀው? አንድ ጊዜ ከኤርትራ ጋር የሚደረጉ ስምምነቶች ዘው ብሎ ተገብቶ ዘው ተብሎ እንደማይወጣ መግቢያ በር እንጂ መውጫ እንደሌለው ጽፌ ነበር።
በስል እዬተሰለሰለ ያለ ክብር አለ። በስል እዬተሸረሸረ ያለ አቅም አለ። በስል የድምጽ አልባዎቹ እናቶች እንባ እንዲቀጥል መታወጁ ኢትዮጵያ ህዝቧ ያን ሁሉ ጥቁር ቂም አሸንፈው እጃቸውን ዘርግተው በፍቅር የተቀበሉት ኢትዮ ኤርትራዊ ነፍስ አደራ እና ሴራ ፊት ለፊት ተፋጠዋል?
- · ለማገናዘቢያ በምለሰት።
- ልብ መርምሪው ጹሑፍ።
ይህ ጹሑፍ 07.06.2018 የተጻፈ ነው። መያያዝ ስላለበት ነው ያቀርብኩት። ሙሉውን "የባድም ዕድምታ በሥርጉተ ዕይታ" የሚል ጹሑፍ ስላለ ማንበብ ትችላላችሁ። የተወሰኑ ጭብጦችን ነጥዬ ማቅረቡ ከአቶ ደውድ ኢብሳ ቃለ ምልልስ እና እኛ ሆን መንግሥታችን የሄደንበት የቅንነት መስመር ምላሹ መላሾ ዓይነት ስለመሆኑ ለማጠዬቅ ነው።
„የአልጀርሱ ስምምነት ህወሀትን ዋጋ ማስከፈሉ እንደማይቀር ሲነገር ነበር (መሳይ መኮንን)“
ልብ የሚመረምር ጹሑፍ ከጋዜጠኛ መሳይ መኮነን አነበብኩኝ - ዛሬ። መነሻዬም ይሄው ነው። የሆነ ሆኖ ዛሬ በጻፈው ጹሑፉ ላይ መጨረሻ ላይ እርገቱን ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን የቋጨበትን ብቻ ላንሳ …
„የጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አስተዳደር ከኤርትራ ጋር ያለውን ችግር ለመፍታት እነመለስ ዜናዊና ሃይለማርያም ደሳለኝ በመጡበት መንገድ የሚሞክሩ ከሆነ ትርፍ የለውም። ችግሩንም የአልጀርሱን ስምምነት በመቀበል የሚፈታ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰው ከሆነ ተሳስተዋል። ወይም ችግሩን ለመፍታት ከልብ ቆርጠው አልተነሱም። አልያም ኤርትራን ዲፕሎማሲያዊ ቅርቃር ውስጥ ለመክተትና ጊዜያዊ ድል ለመጨበጥ በሚል ብቻ የተወሰደ እርምጃ ሊሆን ይችላል“ ጋዜጠኛ መሳይ መኮነን።
እኔ ደግሞ ከዚህ ላይ ለኤርትራ ተቆርቋሪነቱን ቢያሳጣበትም ኤርትራ እሺ ብትል ቀጣዩስ ዕጣ የሚል ስጋትም አድሮበታል … እንግዲህ እኔ እንደ ሥርጉተ ሥላሴ ነው የምጽፈው፤ ወደፊት ወደ ኋዋላ
የሚጎትተኝ ጣጣ ምንጣጣ የለብኝም።
የጋዜጠኛ መሳይ መኮነን ግን ጣምራ መንፈሶች አሉበት። አንደኛው ሚዲያው ኢሳት፤ ሁለተኛው
ግንቦት 7፤ ሦስተኛው የጋዜጠኛው ሥነ - ምግባሩ፤ አራተኛው ሰብዕናው።
ከዚህ አንፃር ሲታይ ከራሱ ገፊ አመክንዮ ብቻ ቆንጥሮ፤ በስሜት ተጋፋፍቶ የሚያመጣው ነው ብዬ አላስብም። በዛ ላይ ጋዜጠኛ የውስጥ አዋቂ ነው
የሚባለውም እውነታዊ መሰረት ያለው አባባልም አለ።
- · ምን ነበር ይሆን ምክክሩ? ልብ ጥልጥል ታደርጋለች ይህቺ ነጥብ፤ ክፉኛ ሳበችኝ።
„ችግሩንም የአልጀርሱን ስምምነት በመቀበል የሚፈታ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰው ከሆነ ተሳስተዋል።“ ተረገጥ አለበት። ከዚህ በላይ ስምምነት ነበር ወይ ከዛ ኤርትራ ላይ ድርጀቱ ግንቦት 7 የመሸገበት አምክንዮ? ይህን ጥያቄ ማንሳት ግድ ይላል። ቀጥዬ የጻፍኩትም እንዲህ ይል ነበር።
· ግንቦት 7 ሥልጣን ተረክቦ ቢሆንስ ለኤርትራ መንግሥት ከአልጀርሱ ስምምነት
በላይ ምን ታጮቶለት ነበር? የናቅፋን የሙት መንፈስ ወይንስ የአፍረካዊቷን የሲንጋፖር-የአንበሶች አገር ድርሻን በባለቤትነት ለማስፈጸም፤ ወይንስ የፖለቲካ የበላይነት ልዕልና ባለድርሻ፤ ባለ ሙሉ መብት አራጊ ፈጣሪነት ሥልጣነ - መንበር? በዚህ መንፈስ ውስጥ ብዙ ነገሮችን ማንሳት ይቻላል። ጉዳያችን በአልጀርሱ ስምምነት ብቻ ነው ወይንስ የሥነ - ልቦና የማንነት ሽግግር የሚጠዘጥዝ አመክንዮ? ቀድሞ ከደገፋቸው ተፎከካሪ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር የነበሩ የጓሮ ፖለቲካዊ ስምምነቶች ፍንጭ የሚወጡት ያን ጊዜ ነው።
… „ችግሩንም የአልጀርሱን ስምምነት በመቀበል የሚፈታ ነው የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሰው ከሆነ ተሳስተዋል።“ የዚህች ጥያቄ መልስ ያን ጊዜ ትፈርጣለች። አሁን ተዚህ ላይ የጋዜጠኛ መሳይ መኮነን እና የእኔ ሙግት የሚስጢር ፍንጪ አሁን የተገኜ ይመስለኛል በአቶ ዳውድ ኢብሳ ቃለ ምልልስ። ኤርትራ ከአልጀሩስ ስምምነት ውጪ ከዛ ከነበሩ አንጋፋዎቹ አውራዎቹ የተቃዋሚ የፖለቲካ ድርጅቶች ጋር የነበራትን ሁነት ይገልጣል። ኤርትራ በአብይ ቅናዊ ጥረት እንዳልረካች የሚሳዩ ፍንጮች ከዚህም ከዚያም ይታያል። የሚያሳዝነው ግን ህዝቡ ነው። ያ ፍቅር እና ሰላም የናፈቀው ህዝብ ራዕይን እንዲህ በተከደነ የሊቃናት ሴራ መታመሱ ነው። ነገስ? አንድዬ ይወቀው።
- · ፍቱት ሦስት ነፍስጡሩ የአጥንት ጉም።
አንድ ወዳጄ በአቶ ንጉሡ ጥላሁን አባ ኮስትር፤ ዳግሚያ ኮስትር ትያቸው ታደንቂያቸው አልነበረም ምነው አሁን? ብለውኛል። አቶ ንጉሡ ጥላሁን አባ ኮስትር፤ ዳግሚያ ኮስትር ስለመሆናቸው እርግጥ ነው።
እርግጠኝነታቸው፤ በራስ የመተማመን አቅማቸውን እወደዋለሁኝ። አባ ኮስትር አርሲ ላይም ይፈጠራል። ብነግራችሁ ከወላጅ አባቴ ጋር መንትያ ነው የሚመስሉት። አንዲትም ቅንጣት ልዩነት የላቸውም የፊታቸው ገጽ ሆነ ደርባባነታቸው። እስከዚህ ድረስ ሰብዕናቸውን በአውንታዊነት እከታተለዋለሁኝ።
ነገር ግን እኔ የፖለቲካ ልባቸው ሸምቀቆነት ነው የማይመቸኝ። ለብዙ ፍላጎቶች ሊንክ ናቸው። ልባቸው መረብ አለው። የኢትዮጵያ ፖለቲካ ኔቱ ያለው በሳቸው ልብ ውስጥ ነው። ሰብዕናቸው የመሸገበትን ፍላጎት ለማግኘት ፈታኝ ጉዳዮች አሉበት። የሳቸውን ልብ የሚፈቱ ኢትዮጵያዊ ሊሂቃን ሁለት ብቻ ይሆናሉ። ከዛ የተረፈው አይችለውም።
ተዚህ ላይ አንድ ምሳሌ ላንሳ አቶ አለምነህ መኮነን አፍቅሮተ ወያኔ ሃርነት ነው ያለባቸው። እሱም አፈጻጸሙ በመደዴ ነው። አቶ ንጉሡ ጥላሁን ይህን ያኛውን ፖለቲካ ይደግፋሉ፤ ይህን ያኛውን ዓላማ ያራምዳሉ ተብለው አጥር ሊሰራላቸው አይችልም። ድንበር አልባ ናቸው።
የዓለም የፖለቲካ ቋንቋ አውታሮችም እንዲህ ዓይነት ሰብዕና ያላቸውን ያጠምዳሉ። ተጠምደዋል ማለቴ ግን አይደለም። ይህን የሚያውቀው ፈጣሪ ብቻ ነው። ዓለም በዬዘመኑ እንዲህ አይነት ሰብዕና ያላቸውን ታስተናግዳለች፤ እርካቡን ካገኙ መዳፋቸው ውስጥ ከገባ አደጋው የከፋ ነው። ደግነቱ ጠ/ ሚር አይደሉም አሁን ምሁዋርነት እንጂ።
ብቻ አቶ ንጉሱ ጥላሁን /አባ ኮስትር/ከሳጅን በረከት ስምዖን በላይ ድብቅ እና የተመሰጠሩ ሰው መሆናቸውን እረዳለሁኝ። መከራው ያለው ከዚህ ላይ ነው። እንዲዚህ ዓይነት ስብዕና ደግሞ ለፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ተፈላጊ እና ተመራጭ ነው። አንድ ጊዜ ስለ አቶ ጃዋር መሃመድ ስጽፍ ይህንኑ ገልጫለሁኝ። ግራጫማ ሰብዕና ለኤርትራ መንግስት ቀጥተኛ ፍላጎት ማስፈጸሚያነት ንጹህ አዬር ነው።
ለዚህም ነው የአቶ ጃዋር መሃመድ የመንፈስ ጽንሰት ጽናጽሉ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ወደፊት የማምጣትን አመክንዮ አበክሮ ሲገልጽ የነበረው። አሁን ተወደደም ተጠላም በቀጣዮቹ ጊዜያት የምናያቸው ዕውነቶች ሊኖሩ ይችላሉ። ሪኮመንዴሽኑ የአቶ ጃዋር መሃመድ ስለመሆኑ ግን አትጠራጠሩት። ለፌድራል የኮምኒኬሽን ቦታ አጭቷቸው ነበር። ከዚህም በላይ ተመኝቶላቸው ነበር።
እሳቸው የዶር አብይ ሌጋሲ መንፈስ ያላስጠጉት ስለመሆኑ ባለፉት ጹሑፎች ገልጫለሁኝ። አሳዛኙ ነገር አማራ ሁልጊዜ በዬዘመኑ መሞከሪያ ጣቢያ መሆኑ ብቻ ነው። አሁን ሳጅን በረከት ስምዖን ተላቀቅኩ ብሎ አማራ ዎህ ብሏል። ሌላ የእሾኽ ስንቅ፤ የጭጎጎት ተክሊል እንዳለ አላስተዋለውም የዋሁ አማራ። ለዛውም የጃዋርውያን መንፈስ። ከአንድ ትውልደ ኤርትራዊ ወደ ሌላ መንፈስ ኤርትራዊ።
ለአቶ ጃዋር የንግሥና አቀባባል የተመረጡት አቶ ንጉሡ ጥላሁን ነበሩ። ለአማራ ዴሞክራሲያዊ ድርድርም ተመራጭ የሆኑት ለኤርትራ ጉዞ እሳቸው ናቸው አቶ ንጉሡ ጥላሁን።
ለኦዴፓ ጉባኤ ብአዴን/ አዴፓን ወክለው የተገኙት እሳቸው ናቸው አቶ ንጉሡ ጥላሁን፤ አሁን የኢህአዴግ ጉባኤ ማሳረጊያም አሳቸው ነበሩ አቶ ንጉሡ ጥላሁን። ፖለቲካው እጅ እጅ ስለሚለኝ ምን እንዳነበቡ አላደማጥኩትም። ርትህ አድራሻዋ እዬጠፋብኝ ነው።
ቀደም ባው ጊዜ የፖለቲካው አናት አቶ በረከት ነበሩ። አሁን አቶ በረከትን የተኩት እሳቸው ናቸው - አርሲኛ አሰኛው ለውጡ።
በዚህ ውስጥ አርሲኛ ሲሰላ ከኤል ቲቪ ጋር የአብን የሰሞኑ ቃለ ምልልስ ሁለት ሊንኮች ማጤን ይገባል። አንዱ ያለው ዲሲ ነው ከጋሼ ሙሉጌታ ሉሌ ህልፈት ጋር የተያያዙ ውልብልቢቶች አሉበት፤ ሌላው አርሲኛ ደግሞ ባህርዳር ነው። ስለዚህ የዶር ደሳለኝ ጫኔ ህይወት በእጅጉ ያሳስበኛል።
አንድ ማያያዣ ላንሳ ስለምን ይሆን ለኦነግ ጉዳይ ዶር ለማ መገርሳ ኤርትራ እንዲሄዱ ይለፍ የተሰጠው? ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ተቀምጠው አቶ ንጉሡ ጥላሁን የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል አደራዳሪም የኤርትራም መንግሥትን ጋባዥ የሆኑበት ሚስጢር ምንድን ነው? ፍቱት ድምጽ አልባውን ትዕይንት እንዲህ እና እንዲያ ወዲያና ወዲህ ይተውናል።
ሌላም ጉዳይ አለ የጠ/ ሚር አብይ አህመድ የኤርትራ ጉዞ አፋር እና ትግራይ አስተዳዳሪዎቻቸው እንዲገኙ ተፈልጎ ትግራይ አለመገኘቷን አድምጫለሁኝ። ስለምን አማራ አልተገባዘም? አማራ እኮ በጎንደርም በወሎም በኩል ከኤርትራ ጋር ይወሰናል።
በዚህ የውክልና ጉዳይ በማይጠይቀው ጭብጥም የተዳፉኑ ጉዳዮች አሉበት? አማራ ሊሂቃንን የኤርትራ መንግሥት የመፍቅድ ጉዳይ? አሁን በዚህ ዝርግ ሁኔታ ነው የኤርትራ መንግሥትን የአማራ መንግሥት ግብዣ እንዲያቅርብ የተፈለገው? አንዲት ሉዕላዊት ሀገር ተመልሳ ዘመነ መሳፍንት ላይ? ምን ተፈልጎ? ምን ለማትረፍ? አዲስ አባባ ላይ ሌላ ቤንዚን ባህርዳር ላይ ደግሞ ሌላ ክብሪት።
- · የፍቱት ጊዜያዊ ክወና።
ውዶቼ ቀጣዩን ዋልታ ቴሌቪዥን ከአቶ ዳውድ ኢብሳ ጋር ያደረገውን ቃለ ምልልስ አስፈላጊ በመሆኑ ቀስ እዬተባሉ ይፍታታሉ። አቶ ዳውድ ኢብሳ ከዋልታ ቴሌቪዥን ጋር ያደረጉት ቃለ ምልልሱ አጭር ሲሆን ግልጽነቱ ደግሞ እንቆቅ ነው።
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።
ቅኖችኑ ያበራክትልኝ፤ ይባርክልኝም አምላኬ። ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ