ወጥ ወረርሽኝ የበታችነት ስሜት ባይረስ ...

እንኳን ደህና መጡልኝ
 ወረርሽኝ።  
ከሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
27.03.2019
ከእመ ዝምታ ሲዊዘርላንድ።


ጤና ይስጥልኝ ውዶቼ እንዴት ናችሁ? ደህና ናችሁ ወይ? እሽት ያደረገኝ ጹሑፍ ነው። ዛሬ የተሜን ጹሁፍ ከዘሃበሻ ሳዳምጥ ነበር። እና ከሥር አስተያዬነት ሳነብ የተጸፈ አገኘሁኝ ከልቤ ከትክት ብዬ ነው የሳቅኩት ጉዳዬም ይኸው ስለሆነ እንደ እኔ ሳቁ …

"ሽንት ቤት  ትሄድና ሰው አለ ትላለህ? በኦሮሚኛ ካልመለሰልህ ጥለኸው ትሄዳለህ እንደገና አሁንም ተመልሰህ በኦሮሚኛ ሰው  አለ? ትላለህ ሰዉዬውም አይመልስም #በመጨረሻ ላይ እንቢ ብሎ ካልመለሰልህ  ሰውዬው #ሱሪህ ላይ #ትለቀዋለህ😂😂😂😂😂like በቀለ ገርባ“
„Tikdem Tikdem
1 hour ago

·       ወረርሽኝ ተህግ ጥሰት አንጻር።

ወረርሽኙ ከህግ ጥሰት አንጻር ሲባል ከሃይማኖታዊው፤ ከብሄራዊው፤ ከዓለም አቀፍ ድንጋጌዎች ጋር እንደማለት ነው። ሌላም ይተበሃል አለን፤ የህግ ባለሙያዎች ላይስማሙት ቢችሉም ሁሉጊዜም አዘውትሬም እንደምለው ኢትዮጵያ በተጻፈ ህገ መንግሥት እንደሚተዳደሩት አገሮች የተጻፈ ህገ መንግሥት አላት፤ ባልተጻፈ እንደሚተዳደሩትም ያልተጻፈውንም ይሁነኝ ብላ በህሊናዋ መስጥራ ትኖርበታለች።

ምን ማለት ነው ይኼ ሁለቱንም አጣምራ የያዘች አገር ናት ለማለት ነው። እንዲያውም ከተጻፈው ይልቅ ያልተጻፈው የበለጠ ተግባራዊ ይሆናል። ህዝቡ ፈቅዶ ስለሚወሰነው። እንዳሁኑ የ ኦዴፓ አውራነት በ ገዳ ተዳደሩ ተብለን አቅጣጫ የለሽ ወጀብ እንደምንናጠው ግን አይደለም።

አሁን ከሆነ የሚታዬው ደግሞ ያልተጻፈውንም የተጻፈውንም ሲጣስ ነው።ብዙ ሰው በአቶ በቀለ ገርባ ንግግር በሰጨኝ ብሏል። ይህ በሊሂቃኑ የነበረ፤ ያለ ጊዜ ሲጠብቅ የቆዬ ነው አሁን እዬተንጠባጠበ የሚታዬው። 

ቀን እዬጠበቀ የምለው ቤተ መንግሥትን በበላይነት የመመራት አቅም እስኪያገኙ ድረስ። ወደ ሲዳሞ፤ ወደ ሀርርጌ ሲሄዱ ስለኩሽ ቋንቋ ቤተሰብ ይሰባከል። በወደ አማራ ክልል ሲሄዱ ደግሞ ስለሰርገኛ ጤፍ ይቀደሳል … ብቻ አሁን ትልማቸው ስልታቸውም አይጥ የተነፈሰበት ወይንም ብል የዳነሰበት ጨርቅ ሆኖ ብትክት አለባቸው እንጂ … ኢትዮጵያ የፈጠራት አምላክ አላት እና።

·       የኦሮሞ የፖለቲካ ሊሂቃን ቅርጽ አንጂ ይዘቱ ወጥ ነው …
እንዲህ ይሉናል አቶ በቀለ ገርባ። ግን እዘኑላቸው ይህን ያህል ዘመን እጅግ ሊዩት ከማይፈልጉት ህዝብ ጋር መኖር፤ መጋባት ለዛውም ሊሰሙት በማይፈልጉት „ገው ገው“ …
·       ሀ.

„ለምሳሌ ከሶስት ወይም ከአራት ዓመታት በፊትና አሁን ያለውን ብንወስድ፣ የኦሮሞን ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ቁጥር አሁን አዲስ አበባ ውስጥ ለውጥ አለ ወይስ የለም? “ለውጥ አለ” (የአድማጮች መልስ)፡፡ 

በየሄድንበት ሁሉ የኦሮሞን ቋንቋ ነው አይደል የምንሰማው አሁን? ለምን ይመስላችኋል? የቋንቋው ደረጃ (ስቴተስ) ስለተለወጠ ነው፡፡ ደረጃው ነው የተለወጠው፡፡ ደረጃው ደግሞ አንድም በስልጣን የሚመጣ ነው፤ በፖለቲካ ስልጣን፡፡ የፖለቲካ ስልጣን፡፡

አሁን ያሉት ይጥቀሙንም፣ አይጥቀሙንም፣ ምንም ይሁኑ ምን ኦሮሞ መሆናቸውን ብቻ ሰዎች ያውቃሉ፡፡ እናምሰዎቹ እንዲህ ናቸው፤ይላሉ፡፡ አሁን ይህ ቋንቋ ይፈለጋል፤ ገብያ አለው፡፡ ነገ ከሌለን [ስልጣን] እዚህ ቦታ ላይ አይኖርም፡፡

ከሁለት ዓመት በፊት በታክሲ ስትሄዱ፣ ወይም ሌላ መኪና ስትሳፈሩ፣ ወይም አውሮፕላን ውስጥ ስትገቡ ከአንድ ቋንቋ በስተቀር የሚዘፈን የለም፡፡ ናዝሬት ብትሄዱ፣ ጎባ ብትሄዱ፣ ነቀምት ብትሄዱ፣ ሻሸመኔ ብትሄዱ፣ አዲስ አበባ ብትመጡ፣ አንድ ቋንቋ ብቻ ነው የሚዘፈነው ታክሲ ውስጥ፣ገገው፣ ገገውይላል፡፡

አሁን ሁኔታ የለም፤ ብዛት የለውም፡፡ አቅም ነው፤ አቅም ስለተለወጠ ነው፡፡ አቅም ሲለወጥ ቋንቋችንም እየተለወጠ ይሄዳል፡፡ ስልጣን እያገኘ ይሄዳል፤ ጉልበት እያገኘ ይሄዳል፡፡ የፖለቲካ ስልጣን የምንፈልገው ለዚህ ነው፡፡ መጥፋት አንፈልግም፡፡ ቋንቋችን እንዲጠፋ አንፈልግም፡፡ ስለዚህ ስልጣን መያዝ የቋንቋችንን ደረጃ ይለውጣል፡፡ ወደ ላይ ከፍ ያደርገዋል ማለት ነው፡፡“

ነጋዴ በኦሮምኛ ካልሸጠ አትግዙአቶ በቀለ ገርባ
March 23, 2019
ለዚህ ነው ብአዴን ሰጥ ለጥ ብሎ እያደገደገ የሚገኘው። የፖለቲካ ስልጣን የሚፈልጉበት ምክንያት ቅንቅጩን ተናገራውል። ፕ/በዬነ ጵጥሮስ እና ድርጅታቸው፤ አቶ ብርሃም ደስታ እና ድርጅታቸውም በመድረክ ቤተኝነታቸው ምን እያሰሉ ይሆን? ለነገሩ መድረክ የፈረሰው እኮ ከጦረኛው ኦነግ ጋር አብሮ ለመሥራት ኦፌኮን ነበር መድረክ ኦፊሻል ባልሆነ መንገድ መፈረሱ የተገለጠው። ያው ኢትዮጵያን ለመግዛት ብሄራዊ ሆኖ መውጣት ግድ ይል ስለነበረ ነው ይህ የተፈለገው አሁን ገመናው ተዘረጋግፏል …

·       ለ.
 ፕ/ መራራ ጉዲና „ለማ ፊቱ ኦሮሞ ይመስላል“ ሲሉ ኦሮሞ ሆኖ መፈጠር የተለዬ ፊት እንዳለው ነበር የገለጹልን። እሱ ብቻ አይደለም ውስጡም ኦሮሞ ስለመሆኑ ደፍሬ መናገር አልችልም ማለታቸውም ነው።  ይህን ይዛ አንዲት ወጣት አቶ ታከለ ኡማ የኦሮሞ ወጣቶችን ብቻ በአዲስ አባባ ሰብስበው በነበረበት ጊዜ „ፊትሽ ኦሮሞ አይመስልም ይሉኛል፤ ኦሮሞ ፊቱ ምን ይመስላል?“ ብላ ጠይቃለች።

ለፊትም ለውስጥም ኦሮሞነት የተለዬ ስለመሆኑ ስንዳምጠው „ሰው“ የሚለው ሃይለ ሰብዕና መዳጡን ልብ ልንለው የሚገባ ይመስለኛል። ይህን ቅኔ በአግባቡ ያዬውም የተነተነውም በሰጨኝ ያለበት ሰው አላዬሁም አልሰማሁም።

እኔ ግን ብዙ ጊዜ ጽፌበታለሁኝ። ስለምን ቢባል „ኦሮሞ ፊት እንዲኖር አባትም እናትም ኦሮሞ መሆን ግንድ ይላል ነው ቅኔው“ ይህንን ነው አሁን አቶ በቀለ ገርባ የነገሩን። ይህም ብቻ ሳይሆን ለ ኦሮሞ ነፍስን የመስጠት አቅምንም ያጠይቃል።

·       ሐ.
አቶ በቀለ ገርባው የሰው ጥፋት ሳይንቲስት¡እንዲህም ይላሉ ..
„ሌላው ላነሳው የምፈልገው ነገር፣ የራስን ቋንቋ ከሚገድል ነገር መካከል ወይም የራስን ቋንቋ ጉልበት ከሚነሱ ጉዳዮች መካከል አንዱ ከሌላ ማህበረስብ ጋር የሚደረግ ጋብቻ (ትዳር) ነው፡፡ ይኸውም ልምንድን ነው፣ የህዝብ ስብጥርን (ዴሞግራፊ) አንድ ቋንቋ የሚጠነክረው ያን ቋንቋ የሚናከር ህዝብ ቁጥር ሲጨምር ነው፡፡ 
ያን ቋንቋ የሚናገረው ህዝብ ቁጥር ደግሞ የሚጨምረው ሁለት ነገሮች ከተሟሉ ነው፡፡ አንደኛ፦ የመራባቱ መጠን ከመሞቱ መጠን በላይ ሆኖ ከተገኘ ነው፤ ፈርቲሊቲው፣ የመራባቱ መጠን፣ የሚወለዱት ሰዎች ቁጥር ከሚሞቱት ሰዎች ቁትር በላይ ከሆነ ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ አዲስ አበባን ብንወስድ አሁን፣ አዲስ አበባን ብንወስድ፣ ወደ አዲስ አበባ የገቡ ሰዎች ቁጥር ወይስ ከአዲስ አበባ የሚወጡ ሰዎች ቁጥር ነው የሚበዛው? ወደዚህ ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ ሰዎች ቁጥር ይበልጣል ይመስለኛል፡፡ 
ወደ አዲስ አበባ የሚገቡት ሰዎች ግን ቀደም ባሉት ዓመታት የነበረው ችግር፣ ወደዚህ የሚገቡት ሰዎች ሁሉ አንድ እንስራ ውስጥ ታጭቀው (ተቀቅለው) አንድን ቋንቋ ብቻ ወደ መናገር ወደ ታች ነበር የሚወርዱት፤ ሁሉም፡፡ ይሄ ትልቅ አደጋ ነው፡፡ ከሌላ ቦታ ወደዚህ የሚመጡት ሰዎች ሁሉ ቋንቋቸውን እየተዉ ነበር የሚሄዱት፡፡ 
አሁን ግን ወደ አዲስ አበባ ቢገቡ እንኳን ሰዎች በራሳቸው ቋንቋ መጋባት ጀምረዋል፡፡  ወደዚህ ቢመጣ እንኳን ቋንቋውን መልቀቅ ትቷል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ህዝብ እየበዛ ሲሄድ፣ ያንን ቋንቋ የሚናገረው ህዝብ ብዛት እየጨመረ ሲሄድ፣ ቋንቋው እያደገ ይሄዳል፡፡ ቋንቋውን የሚናገረው ሰው ብዛት እያነሰ ሲሄድ ደግሞ ቋንቋው እየሞተ ነው የሚሄደው፡፡“
ነጋዴ በኦሮምኛ ካልሸጠ አትግዙአቶ በቀለ ገርባ
March 23, 2019
·       መ.

እርእሰ መሰተዳደር ዶር ለማ መገርሳ ሁለቱን እያስኬዱት ስለሆነ ፌድራሉንም ክልልኑም፤ ውጭ ጉዳይ ሚኒስተርነቱንም ... 

የከተማ ፖለቲካን (አርበን ፖለቲክስ) ማጤን አለባችሁ፤ ችላ ልትሉት አይገባም፤ያላችሁት፣ ትክክል ነው፡፡ የከተማ ፖለቲካ (አርበን ፖለቲክስ) ሊጤን ይገባዋል፣ ምክንያቱም የዚህ ሀገር ፖለቲካ ማእከል (ሴንተር ኦፍ ፖለቲክስ) ከተሞች ስለሆኑ ነው፡ የዚህን ሀገር ፖለቲካ የሚወስነውም ከተማ ነው፤ ከተሞች ናቸው፡፡ የከተማ ውስጥ ፖለቲካ ማለት አንድ ቁጥር ዲሞግራፊ (የህዝብ ስርጭት) ነው፡፡ እዚያ ላይ አንዱን ወደዚያ መግፋት፣ አንዱን ወደዚህ መጎተት፣ አንዱን ጠቅሞ ሌላውን ለመጉዳት ሳይሆን፣ እንደ ኦሮሚያ ብዙ ነገሮች እየሰራን እንዳለን መገንዘብም ያስፈልጋል፤ በቂ ነው ማለት ግን አይደለም፡፡ የጀመርነው በጣም አበረታች ነው፡፡ ከሶማሌ የተፈናቀሉትን 500000 (አምስት መቶ ሺህ) በላይ የሆኑ ሰዎች፣ እንደምንሆነው ሆነን፣ ገፍተንም፣ ምንም ብለን፣ ከዚህም ከዚያም ብለን፣ የገዳ አባቶችንም፣ ሽማግሌዎቻችንንም ይዘን፣ እንደለመድነው እርቅ ፈጥረን፣ አቅፈን፣ ስመን ወደ ነበሩበት ቦታ ልንመልሳቸው እንችል ነበር፡፡ ቢያንስ ቢያንስ መመለስ ይቻል ነበር፤ እኛ ግን ልንመልሳቸው አልፈለግንም፡፡ ያንን ችግር ወደ መልካም እድል ለውጠን፣ ለኦሮሞ አንድነት፣ ያንን ችግር ወደ መልካም እድል ለውጠን፣ ዛሬም ችግር ላይ ያሉ ቢሆንም፣ ገጠር አላሰፈርናቸውም፤ ከተማ ነው ያሰፈርናቸው፣ እነዚህን ሰዎች፣ እወቁ፡፡ በአንድ ጊዜ 500 000 (አምስት መቶ ሺህ) በላይ ሰዎችን፣ እንዲያውም አዲስ አበባ ዙሪያና አዲስ አበባ ውስጥ፡፡ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 6000 (ስድስት ሺህ) አስገብተናል፤ አዲስ አበባ ዙሪያ ብቻ አይደለም፡፡ እኒህን ከዚያ የተፈናቀሉትን ሰዎች፣ የዚህን አካባቢ ባህል የማያውቁ ሰዎች፣ በብዙ ነገሮች ከአካባቢው ጋር የማይመሳሰሉ፣ ይቸገራል መችም፣ ይቸገር፤ ዛሬ ችግር የማያጣው ቢሆንም፣ ከተቸገረም እዚሁ ከተማ ውስጥ ይቸገር፡፡ ቢያንስ ቢያንስ በእግሩ የሚቆምበት መሬት ይኑረው፤ እሱ ቢቸገርም ለልጆቹ የሚሆን ስለሆነ፣ ብለን ህዝባችንንም አስቸግረን ካለን ነገር ላይ አዲስ አበባ ዙሪያ ነው ያሰፈርናቸው፡፡ አብዛኛው የሀረርጌ ሰዎች ናቸው፣ እወቁ፡፡ ቦርደዴ ማስፈር ይቻል ነበር፤ ምስራቅ ሀረርጌ ልናሰፍራቸው እንችል ነበር፡፡ ማስፈር ትክክል ከሆነ እንዲያውም እዚያው አካባቢ ነበር ማስፈር የሚገባው፤ ያን ባህል ነው የሚያውቀው፣ ያን አየር ነው የሚያውቀው፡፡ ወደማያውቀው ባህል እዚህ አምጥተን አዲስ አበባ ውስጥ አሰፈርነው፡፡ ቢቸገር ቢቸገር ሁለት ዓመት ነው ሊቸገር የሚችለው፤ ከዚያ በኋላ ሰው ሆኖ ይወጣዋል፡፡ ይሄ በፖለቲካ ላይ ያለው ፋይዳ፣ ሄዶ ሄዶም በኢኮኖሚ ላይ የሚኖረው ፋይዳም ከፍተኛ በመሆኑ፡፡ ያም ብቻ ሳይሆን በብዙ መንገድ ስለሚፈይድ፡፡
ወጣቱንም ስራ እናስይዛለን ብለን በንግድ ስም፣ በሌላም ነገር ስም ብዙ ነገር ስናደርግ ነበር፤ እናም አብዛኛውን ከተማ ውስጥ አስገባነው፡፡ ወደ ከተማ ስናስገባው የሚኖርበት ቦታ ኖሮት ነው፡፡ 500 000 (አምስት መቶ ሺህ) በላይ የሚሆኑ የኦሮሚያን ክልል ሰራተኞች ዘንድሮ መሬት የሰጠናቸው ገጠር ውስጥ አይደለም፤ ይብዛም ይነስም ከተማ ውስጥ ነው የሰጠናቸው፡፡ ግማሽ ሚሊዮን ለሚሆኑ ነው የሰጠናቸው፡፡ ብዙ ልንቆጥር እንችላለን፡፡ ይሄ በቂ ነው ብዬ አይደለም፤ ሊሰራበት ይገባል፡፡ ሆኖም ችላ ያልነው ነገር አይደለም፤ እየተሰራበት ያለ ነገር ነው፡፡ ስንሰራም በከፍተኛ ጥንቃቄ መስራት የሚያስፈልግ በመሆኑ፣ ይህም በዚሁ ረገድ ቢታይ መልካም ይሆናል ብዬ ነው የማየው፡፡“


አቶ ለማ መገርሳ አንድ ሚሊዮን ኦሮሞዎችን አዲስ አበባ ለማስፈር ሲባል ሆን ብለው ከሶማሌ ክልል ራሳቸው እንዳፈናቀሏቸው ተናገሩ
የሦስቱም የጭብጥ መሰረት ኦርማይዝድ ስለማድርገ ነው ኢትዮጵያን አፍልሰው።
ሌላው የዶር ለማ መገርሳ ሁኔታን በምልሰት የስሜን አሜሪካ ጉብኝት ብትቃኙት እኔ ከቤተሰብ ጋር ተወያይቼበታለሁኝ፤ ኦን ላይ ላይም ላይፍ እሳቸው እዬተናገሩ አስተያዬት ይሰጥ ስለነበር ግራሞቴን ገልጫለሁኝ።

በሌሎች ጉባኤዎች ላይ በምናከብረው ሰብዕናቸው ተረጋግተው ከቆዩ በሆዋላ ሚኖሶታ ላይ ሲደርሱ ምን ያህል እኛን ባረቀ መልኩ እና ከሌላ ማህበረሰብ ከባዕድ ጋር የቆዩ ይመስል ሚኒ ላይ ያደረጉት ንግግር ውስጣቸውን ፍንትው አድርጎ ያሳያል። በኦሮምኛ መናገራቸው አይደለም ታሥሮ ቆይቶ የተፈታ ያህል ስሜት ነበራቸው ፍለቅልቅ ፍንድቅድቅ ነበር ያሉት። ያ የሚነግረን ብልህነት አለ።

ሌላው በመከላከያ ባዕል ላይ ያደረጉት ንግግርም ሌላ ሚስጢር ሹክ ይላል … አዲሱ የመከላከያ የማሻሻያ እርምጃ መዳፋቸው ውስጥ መከላከያው ስለመኖሩ የጎሰመላቸው የተስፋ ነጋሪት በአስተውሎት ደግሞ ማዬት እና ውስጡን ማንበብ ነው።

ወደ አቶ በቀለ ገርባ ምልሰት ስናደርግ እስር ቤት ዳኞች ሲገቡ መነሳትን አልፈቀዱም? በሰላማዊ ምንገድ እታገላለሁ ሲል አንድ የፖለቲካ ድርጅት ያ አገር መንግሥት የሚተዳደርበትን ህግ መቀበል፤ መጠበቅ ማክበር የተገባ ነው። 

ለዛውም እነሱው ያበኮቱ እና የጋገሩት ሆኖ ሳለ ማለት ነው። በብሄራዊ የህገ መንግሥት ጉባኤው ውይይትም ሰብሳበቢው ዶር ነጋሶ ጊዳዳ መሆናቸው ይታወቃል። በአንድ በኩል በፌደራሊዝም በህገ መንግሥቱ ላይ አንደራደርም ይሉናል በሌላ በኩል ደግሞ ጥሰት ሲፈጽሙበት እናያለን 

… መላ ቢሶች … እሳቸው እራሳቸው የ5 የ ኦሮሞ ድርጅቶች አዲስ አባባን በሚመለከት ያወጡት መግለጫ ላይ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓለማን አስመልክቶ ህግ ተጠሰ ሲሉ ነበር። በሌላ በኩል እንሱ አገር እንመሰርታለን የሚሉትን የድርጅት ዓርማ በኩራት በርዕሰ መዲናዋ አውለብልበው ማለት ነው…

ሌላም የህግ ጣሽነት ሥነ - ልቦና በሚመለከት የመጀመሪያው እና የሁለተኛው አሰቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጥሰት ሪከርድ ፕ/ መራራ ጉዲና በጥሰዋል። በሁለተኛው  የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ጥሰትም አቶ በቀለ ገርባ ተደራቢ ናቸው። በዚኸው  ከአስቸኳይ ጊዜ አሳጅ ጋር በተያያዘ ጦማሪ አቶ ስዩም ተሾመም እንዲሁ … ጥሰት አድርገዋል። እና ህግ ይከበር እርስ በእርሱ በጥፊ የሚለላስ ገመና ነው … ያለባቸው።

·       ወጥነት።

ብዙ ሰው የ አቶ በቀለ ገርባ ንግግር ላይ አትኩሮት አደርጓል። የሳቸው በጥሬው እንደወረደ ነው። ስለተ ቢስ ጉዳይ ነው። ምን አልባት ኮከባቸው ሳይጃስትሪት ሊሆን ይችል ይሆናል፤ የሆነ ሆኖ  ሥልጣኑ ማስፈጸሚያ መሳሪያውን የመንግሥትን ስላልያዙ ቁንጫናቸውን፤ ታምቆ የቆዬ ንዴታቸውን የሚያወጡት የጥላቻ ማንፌስቶ በማውጣት ነው። አቅም የማስፈጸሚያ መሳሪያ ስሌለቻው። ቢኖራቸው ተራፊ ሰውም የለም።

ወጥነቱ አህቲነቱ የሳቸው የአቶ በቀለ ገርብ አስተሳብ „የለማ ፊቱ ኦሮሞ ይመስላል“ ቅኔ  ከፕ/ መራራ ጉዲና ጋር ተመሳሳይ ነው። ወጥም ነው። ይኽኛው ለስላሳ ነው። ድፍን ነው። የተከደነ ነው፤ እንጂ ምንም ልዩነት የለውም።

በሌላ በኩል የአቶ ታዬ ደንኣ በጦላይ ስለታሰሩት ወገኖች ያስተላላፉት መልዕክት ጦማሪ አቶ ስዩም ተሸመ ተቃውመው የወጡበት መንገድ ስንመረምረው የአቶ ታዬ  ከእነ አቶ በቀለ ገርባ ጋር ወጥንት ያለው የጭካኔ መንፈስን የዋጠ ነው።

የዶር ለማ መገርሳም የዲሞግራፊ ለውጥ በሥነ - ልቦና ድፍጠጣ፤ በባህላዊ ቅርምት፤ በትውፊት ድርመሳ፤ በህዝብ ስብጥር ብወዛ አቶ በቀለ ገርባ ከተናገሩት ልዩነት የለውም። የሴንትሜትር ያህል ልዩነት በፍጹም የለውም። ልዩነቱ ኦፌኮ የመንግሥት ስልጣን የለውም፤ የማስፈጸሚያ መሳሪያ የለውም ኦዴፓ ግን ቀንጮ ነው። 

ስለዚህ የልቡን ለማድረስ በሁኔታዎች በፍጥነት እዬተጠቀመ ነው። አይዋ ብአዴን ደግሞ እንደለመደበት ይህንኑ ለማስፈጸም አብሮ ተስልፏል። ደፋ ቀናም እያለ እራሱን እያጣፋ ነው። አቶ በቀለ ገርባ ሲናገሩ „ባዕድ“ ነው የሚሉት። ወ/ት ቦንቱ በቀለን ከቶ ምን ሊያደርጓት ይሆን እንደገና ተረገዢ ወይንስ ከሁለት ተሰንጠቂ? በግማሹ ጥላቻ እና በግማሽ ፍቅር ምን ያህል በደል ፈጽመውባት ይሆን?

„በዚህ ውስጥ ከራስ ማህበረስ ውጭ (ከባእድ ጋር) የሚደረግ ጋብቻ የሚለውን ነጥብ ድጋሚ ላንሳ፡፡ አንድ ባልና ሚስት የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚናገሩት ነገር፣ የተለያዩ ቋንቋዎችን የሚናገሩት ነገር፣ ልጆች ሲወልዱ ልጆቻቸው ከሁለቱ የየትኛውን ቋንቋ ይናገሩ ይሆን? እንደ አዲስ አበባ ነዋሪ የትኛውን ቋንቋ ይሆን የሚወስዱት? የትኛውን ነው የሚወስዱት? ያንኑ ነው የሚወስዱት፤ ይሄ የታወቀ ነገር ነው፡፡ ስለዚህ አንደኛው አደጋ ከራስ ማህበረሰብ ውጭ የሚፈጸም ጋብቻ፣ ይህን የምናገረው የቋንቋ ሳይንስ ስለሆነ ነው እንጂ የጥላቻ ወይም መውደድ ጉዳይ ስለሆነ አይደለም፤ ይሄ ቋንቋን ወደ ታች ከሚያወርዱ ጓዳዮች መካከል፣ አንድን ቋንቋ ከሚገድሉ ጉዳዮች መካከል አንዱ ነው፡፡ ምክንያቱም ከሚወለዱት ልጆች ላይ ቋንቋውን የሚያተባቸው በመሆኑ ነው፡፡ እናትና አባት አንድ ቋንቋ የሚናገሩ ቢሆኑ፣ ልጆቻቸውም ያን ቋንቋ ወስደው ለማደግ ትልቅ እድል ይኖራቸዋል፡“

ይቅጥላሉ ዓለምን ጉማም ለማድረግ የሚታታሩት ... አቶ በቀለ ገርባ ...

„ሌላው ላነሳው የምፈልገው ነገር፣ የራስን ቋንቋ ከሚገድል ነገር መካከል ወይም የራስን ቋንቋ ጉልበት ከሚነሱ ጉዳዮች መካከል አንዱ ከሌላ ማህበረስብ ጋር የሚደረግ ጋብቻ (ትዳር) ነው፡፡ ይኸውም ልምንድን ነው፣ የህዝብ ስብጥርን (ዴሞግራፊ) አንድ ቋንቋ የሚጠነክረው ያን ቋንቋ የሚናከር ህዝብ ቁጥር ሲጨምር ነው፡፡ ያን ቋንቋ የሚናገረው ህዝብ ቁጥር ደግሞ የሚጨምረው ሁለት ነገሮች ከተሟሉ ነው፡፡ አንደኛ፦ የመራባቱ መጠን ከመሞቱ መጠን በላይ ሆኖ ከተገኘ ነው፤ ፈርቲሊቲው፣ የመራባቱ መጠን፣ የሚወለዱት ሰዎች ቁጥር ከሚሞቱት ሰዎች ቁትር በላይ ከሆነ ማለት ነው፡፡ ለምሳሌ አዲስ አበባን ብንወስድ አሁን፣ አዲስ አበባን ብንወስድ፣ ወደ አዲስ አበባ የገቡ ሰዎች ቁጥር ወይስ ከአዲስ አበባ የሚወጡ ሰዎች ቁጥር ነው የሚበዛው? ወደዚህ ወደ አዲስ አበባ የሚገቡ ሰዎች ቁጥር ይበልጣል ይመስለኛል፡፡ ወደ አዲስ አበባ የሚገቡት ሰዎች ግን ቀደም ባሉት ዓመታት የነበረው ችግር፣ ወደዚህ የሚገቡት ሰዎች ሁሉ አንድ እንስራ ውስጥ ታጭቀው (ተቀቅለው) አንድን ቋንቋ ብቻ ወደ መናገር ወደ ታች ነበር የሚወርዱት፤ ሁሉም፡፡ ይሄ ትልቅ አደጋ ነው፡፡ ከሌላ ቦታ ወደዚህ የሚመጡት ሰዎች ሁሉ ቋንቋቸውን እየተዉ ነበር የሚሄዱት፡፡ አሁን ግን ወደ አዲስ አበባ ቢገቡ እንኳን ሰዎች በራሳቸው ቋንቋ መጋባት ጀምረዋል፡፡  ወደዚህ ቢመጣ እንኳን ቋንቋውን መልቀቅ ትቷል ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ህዝብ እየበዛ ሲሄድ፣ ያንን ቋንቋ የሚናገረው ህዝብ ብዛት እየጨመረ ሲሄድ፣ ቋንቋው እያደገ ይሄዳል፡፡ ቋንቋውን የሚናገረው ሰው ብዛት እያነሰ ሲሄድ ደግሞ ቋንቋው እየሞተ ነው የሚሄደው፡፡“
ነጋዴ በኦሮምኛ ካልሸጠ አትግዙአቶ በቀለ ገርባ
March 23, 2019
የሚገርመው መናበብ አለመቻለቸው አንጻራዊ ሲሆን ምንም ቢሆን የእኛዎቹ ስለያዙት ከምንፈለገው የበለጠውን እናገኛለን ብለው ማሰባቸውን ግን አቶ በቀለ ገርባ አጫውተውናል።

„ለምሳሌ ከሶስት ወይም ከአራት ዓመታት በፊትና አሁን ያለውን ብንወስድ፣ የኦሮሞን ቋንቋ የሚናገሩ ሰዎች ቁጥር አሁን አዲስ አበባ ውስጥ ለውጥ አለ ወይስ የለም? “ለውጥ አለ” (የአድማጮች መልስ)፡፡ በየሄድንበት ሁሉ የኦሮሞን ቋንቋ ነው አይደል የምንሰማው አሁን? ለምን ይመስላችኋል? የቋንቋው ደረጃ (ስቴተስ) ስለተለወጠ ነው፡፡ ደረጃው ነው የተለወጠው፡፡ ደረጃው ደግሞ አንድም በስልጣን የሚመጣ ነው፤ በፖለቲካ ስልጣን፡፡ የፖለቲካ ስልጣን፡፡ አሁን ያሉት ይጥቀሙንም፣ አይጥቀሙንም፣ ምንም ይሁኑ ምን ኦሮሞ መሆናቸውን ብቻ ሰዎች ያውቃሉ፡፡ እናምሰዎቹ እንዲህ ናቸው፤ይላሉ፡፡

በሌላ በኩል ፕ/ መራራ ጉዲና አማራ ክልል ላይ በነበራቸው ጉባኤ ሰው አላስተዋለውም ምንም አላለውም እንጂ አንድ ኮሚቴ በዩንቨርስቲ ሊቋቋም ታስቦ እጩ ሲቀርብ ኦሮሞ፤ አማራ፤ ትግሬ ሳይስማማ ሲቀር መጨረሻ ማዕከላዊ ተብለው የተመረጡት ሶስቱ የጉራጌ ብሄረሰብ ሆነው ተገኙ ያው የሳቸው እንዳጋጣሚ ሆኖ አትቀርም፤ 

ልባሙ ጉዳይ እኛ ስንተራመስ እድሉን ለሌላ አሳልፈን እንሰጣለን እና እኛ ሥልጣኑን ብንይዘው፤ ብንጠቀልለውም አትጎዱም ሌላው ከሚይዘው አይነት የማነጻጸሪያ ልባም ጉዳይ ወዘፍ አድርገው አቅርበው ነበር። ዕድሉን ስጡን እና አምቀን የያዘነውን አሟልተን እስክናበቃ ለሽ በሉ ነው። ይህንም እማ ቶ ገዱ አንዳርጋቸው እኮ ገልጠዋል። „ሥልጣን አያስፈልገነም ብለው፤“ አሁን ተሰሞኑም በታሪክ እና በቁራጭ መሬት አንሻም የሚልም ሌላ ዕድምታ በ አዲሱ የብአዴን የጽ/ቤት ሃላፊ ተደምጧል። ቀደም ባለው ሰሞን „ባሪያ ለ ለ አማራ እነሆናለን“ ሲሉ ደግሞ አዳምጠናል …

/ መራራ ጉዲና እና ዲያቆን ድንኤል ክብረት በባህርዳር አስደናቂ ንግግር አደረጉ Ethiopia Abiy Ahmed


በሌላ በኩል በአቶ ሌንጮ ለታ የሚመራው ቡድን በደቡብ ክልል ደግሞ ሲዳማን ብቻ ለይቶ ስብስቦ የነፍስ ሃዲድ አሃታዊነት ለመፍጠር ተሞክሯል ይኽ ደግሞ ኩሸኛ መሆኑ ነው። ሲዳማ ላይ የሚታዬው መታመስም በዚህ ስልት የተቀየሰ ነው።

በመንግሥት ሥልጣን ባለው ኦዴፓ አማካኝነት ኢትዮጵያን ኦሮማይዝድ ለማድረግ አንዱ በአጋርነት ሌላው በዝለት ክኒን ሲያጦዙት የሰማዩ መላዕክ ደግሞ ሆድ ዕቃውን ዘርጋግፎ ሁሉንም ከእንቅልፉ ቀሰቀሰው። 

በነገራችን ላይ የፕሮፌሰር መራራ ጉዳኒ ሆነ የአቶ ሌንጩ ለታ ጉዞ አሁን ያለውን የኦሮማይዝድ ለውጥ ደግፉት እኛ የተሟላ አቅም አግኝተን ሙሉ ለሙሉ ሁለመናውን በፍላጎታችን ልክ እስክናዋድድ ነው። እኛ እነሱን በውስጣችን አስቀምጠን በእነሱ ውስጥ ግን እኛ ሙሉ ለሙሉ የለንም። ለዚህም ነው ኦፌኮን ወፊቱ ሳትቀድመው ከኦነግ ጋር ኦዴፓ ከኦዴግ የተቀናጁት። ስለሆንም በስልትም፤ በጥበብም፤ በቅኔም ተግባሩ እዬተከወነ ነው።

 ለባርነት ትክሻን ማሰናዳት ወይንም አሻም ማለት ምርጫው አንድ እና አንድ ነው። አሁን ሁሉም ታይቷል። ሁሉም ተለክቷል። አውራውም ምኑም … ስለዚህ ልብ ያለው ሸፕ ነው።
አብዛኛው ሰው በጣም አዝኗል። እኔ ደግሞ ለመልካም እንደሆነ ስለማስብ ደስ ብሎኛል። ማዬት መልካም ነው። ሞገድ ላይ የነበረውም መሬት ወርዶ ተፈተሸ። ማህል ላይ ሆኖ ሲዋልል … ቤተመንግሥት የገባውም በራሱ ጊዜ ተሸረሸረ፤ ፈጣሪ ደግሞ አንድ ድምጽ ላከ፤ ድምጹንም በሰማዬ ሰማያት ገድል አመላከተ …

በ ኦነጋውያን ፍልስፍና በግራ በቀኝ የ ኢትዮጵያን ህዝብ እያዋከቡት ነው። አንዱን እያዛናጉ ሌላውን እያነቃቁ የኦነግን ዓላማ ማስፈጸም ታቅዶ እዬተሰራበት ስለመሆኑ በንቃት መከታተል ያስፈልጋል።

በቀኝ የሚነፍሰው ንፋስ፤ በግራ የሚነፍሰው ንፋስ፤ በምስራቅ የሚነፍሰው ንፋስ፤ በምዕራብ የሚነፍሰው ንፋስ በኦሮሞ ሊሂቃን ዘንድ ከሆነ ወጥነቱ የነጠረ የተበጠረ ኢትዮጵያን ኦሮማይዝድ የማድረግ ተልዕኮ ነው።

በቀጣይ ምን እና ምን ይኳሆኑ ሲባል ግን እነሱ ተባበረው ይሰራሉ ሲባል ግን በምንም ደረጃ አይቻቻሉም። አሁን አንድ ያደረጋቸው ኢትዮጵያዊነት የማዳከሙ ላይ ነው። ከዚያ ልክ ማህሉ እንደተሰበረ መስታውት ፍንጥርጥር ነው የሚሉት። እኔ በፕ/ መራራ ጉዲና፤ በ አቶ በቀለ ገርባ ታስረው በነበረ ጊዜ ልባም ጹሑፍ ጽፌ ነበር 100 ሰው ነው ሼር ያደረገው። እሱም አማራው ነው። አሁን ያገናኛቸው ማዕከላዊ መንግሥትን የማዳከም ጉዳይ ብቻ ነው … ወይንም ጫና ፈጥሮ የመበተን …

ሌላው ግን በቋንቋ ጉዳይ ላይ ያላቸው ዕሳቤ የሌሎችን ቋንቋ ተጭኖ የመውጣት እና በሥመ ኩሽ ሌሎችን ደፍጥጦ ኦሮምኛን የማንገስ ተልዕኮ ነው። ለዚህ የግንባር ቀደም ተጠቂው ሱማሊኛ እንደሆነ አቶ በቀለ ገርባ ነገረውናል … ቀጣዩ ደግሞ ሲዳምኛ … 

„አቅም ሲለወጥ ቋንቋችንም እየተለወጠ ይሄዳል፡፡ ስልጣን እያገኘ ይሄዳል፤ ጉልበት እያገኘ ይሄዳል፡፡ የፖለቲካ ስልጣን የምንፈልገው ለዚህ ነው፡፡ መጥፋት አንፈልግም፡፡ ቋንቋችን እንዲጠፋ አንፈልግም፡፡ ስለዚህ ስልጣን መያዝ የቋንቋችንን ደረጃ ይለውጣል፡፡ ወደ ላይ ከፍ ያደርገዋል ማለት ነው፡፡

"የኩሾች ቋንቋ ድሮ አንድ ነበር፡፡ ሆኖም ቀስ በቀስ በጊዜያት መካከል፣ የተወሰነው ቡድን ከብቶቹን እየነዳ በዚህ አቅጥጫ ሲሄድ፣ ሌላው ደግሞ በሌላው መንገድ ሲሄድ፣ አንዱ በግራ፣ ሌላው በቀኝ ሲሄድ፣ በዚህም ምክንያት መገናኘት ሳይችሉ ሲቀሩና የአንድን ቋንቋ ልዩ ልዩ አካባቢያዊ አነጋገሮች (ቀበሊኛ) እየተነጋገሩ እየሄዱ፣ በዚያው ቀስ በቀስ የተለያዩ ቋንቋዎችን ወደ መነጋገር ይሄዳሉ፡፡ ጥንት እኛ ኦሮሞዎች ከሶማሌዎች፣ ከአፋሮችና ከሲዳማዎች ጋር አንድ ቋንቋ ነበር የምንናገረው፤ የኩሽ ቋንቋ፡፡ እየበዛንና ወደ ልዩ ልዩ አቅጣጫዎች እየተበታተንን መሄድ ስንጀምር፣ ቋንቋችን እየሰፋ፣ እየተዋለደ ሄደ ማለት ነው፡፡ ከአሁን በኋላ ግን እዚህ ዓለም ላይ እንዲህ ዓይነት እድል አይህኖርም፡፡ ከዚህ በኋላ ግን የቋንቋ መወለድ አይኖርም፡፡ ምክንያቱም አንድ ቋንቋ ወደ አንድ ዓይነትነት እያደገ ይሄዳል እንጂ ወደ መለያየት እያደገ ስለማይሄድ ነው፡፡“

ከሱማሌ የተፈናቀሉት ወደዚህ እንዲዛወሩ የተደረገበትም ይህው። ከሱማልኛ ቋንቋም እንዲለዩም ጭምር ነው።

እዚህ ላይ ግን በፕ/ ላሪቦ የተነሳውን ወጀብ ጸጥ የሚያደርግ አንድ ማስረጃ እራሳቸው አቶ በቀለ ገርባ ሰጥተውናል። ያን ጊዜ ከከብት እርቢ ጋር የኦሮሞን ታሪክ ሲገልጹ ከፍተኛ ወጀብ ተነስቶ ነበር። አማራ የለም ይል ነበር ቃለ ምልልሱ እኛ ጉዳይ አልሰጠነም እንጂ። የበታችነት ስለሌብን። የኦሮሞ ሊሂቃን እና አክቲቢስቶች ግን ማዕቱን አፈሰው ነበር፤ ክስም ድረስ ደርሰው ነበር። በኢሳትም እንዲሁ አንድ መግለጫ ወጥቶ ነበር። አሁን አናት አናታቸውን እንዲህ ሊቀጠቅጧቸው። አሁን አቶ በቀለ ገርባ ተዚህ ላይ ይባረኩ ብያለሁኝ … የፕ/ ሃይሌ ላሪቦን ክስ እውነት ነው ነበርን ብለዋል …

„የኩሾች ቋንቋ ድሮ አንድ ነበር፡፡ ሆኖም ቀስ በቀስ በጊዜያት መካከል፣ የተወሰነው ቡድን ከብቶቹን እየነዳ በዚህ አቅጥጫ ሲሄድ ሌላው ደግሞ በሌላው መንገድ ሲሄድ፣ አንዱ በግራ፣ ሌላው በቀኝ ሲሄድ፣ በዚህም ምክንያት መገናኘት ሳይችሉ ሲቀሩና የአንድን ቋንቋ ልዩ ልዩ አካባቢያዊ አነጋገሮች (ቀበሊኛ) እየተነጋገሩ እየሄዱ፣ በዚያው ቀስ በቀስ የተለያዩ ቋንቋዎችን ወደ መነጋገር ይሄዳሉ፡፡“

ከዚህ ላይ ጨዋታን ጨዋታ ያነሳዋል እንዲሉ …  ሌላው የገረመኝ ግን ጠ/ሚር አብይ አህመድ ስሜን አሜሪካ በነበሩበት ወቅት ሊሂቃኑን እያጠሩ ሲያነግሱ ሲያወድሱ፤ ፍቅር የያዛቸውንም የህሊና ቀለበት ሲያስሩ የኢትዮጵያ ድምጽ የሆኑትን ፕ/ ሃይሌ ላሪቦን ማንሳት አልፈለጉም ነበር። ለምን? ቂመኛ ናቸው ማለት ይሆን?

 እሳቸውን ብቻ አይደለም በተለያዬ ሁኔታ ያነሳሉ ሌሎችንም። አሁን በቅርቡ ፕ/ ፍቅሬ ቶለሳን እኔ እንዲያውም እንዴት ማዕቀብ ተጣለባቸው ብዬ ጽፌ ነበር  እሳቸውን ሲያነሱ አዳመጥኩኝ  የኢትዮ አፍሪካዊነት እጬጌውን ፕ /ማሞ ሙጬን ግን ሳት ብሏቸው አላነሱም። ለምን? ያው አሁንም ስለ ኢትዮጵያዊነት እዬተነገረን ስለሆነ …

ወደ ቀደመው ስንመለስ በወል ማለት ነው የኦሮሞ ድርጅቶች አንድ ወጥ ፍላጎት ነው ያላቸው። ኢትዮጵያን ኦሮማይዝድ ለማድረግ ማዕካላቸው አዲስ አበባን መናገሻ ከተማ ማድረግ ነው። አንቦ ላይ „ቄሮ ጀግና“ እንዲሉ ም/ጠሚር የተፈለጉበት ምክንያት „ድሉ የቄሮ ነው ዘመኑም „ ይኸው ነው ዕወጃው። አሁን ተሰሞኑ የኬክ ቆረሳ መግለጫም ይኽንኑ ሰምተናል። ለነገሩ አገር እዬገዙ ኮንደሚኒዬም የሚናፍቃቸው ናቸው…

በዚህ ውስጥ ትግሉን ማዕቀፍ እንዲኖረው ምክንያታዊ እንዲሆን ያደረገው የአማራ የማንነት የህልውና ታገድሎ ሰምጦ እንዲቀር፤ ታሪኩ የውሽማ ሞት እንዲሆን በውጭ አገር ግንቦት 7 እስከ ሚዲያዎቹ በአገር ውስጥ ኦዴፓ ጠንክረው እንደ ግብ የቆጠሩት ጉዳይ ነው። የተስማሙበትም መሰረታዊ ጉዳይ ይኸው ነው። መስዋዕትነቱ በተገፋ ቁጥር የባለቤትነት ስሜቱ ብቻ ሳይሆን የታሪክ ባለድርሻነቱንም ቅስም መሰበሩ ማንም ልብ ብሎ የተመለከተው የለም።

ኢትዮጵያዊነት በአማራ የህልውና የማንነት ተጋድሎ ውስጥ ነው አቧራውን አራግፎ ቀና እንዲል የተደረገው። የኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቅ ዓላማ በክብር በአደባባይ አንገቱን ሳይደፋ ቀና አድርጎ ነፃነቱ የታወጀለት በጎንደር/ ጎጃም የአማራ የማንነት ተጋድሎ ነው። ይህ እኛ ያለንበት ታርኪ ስለሆነ ሊታጠፍም፤ ሊቆረሰም፤ ሽልማት ሊሰጠም አይችልም።
ይህ ተዘሎ ይህ ተደፍጥጦ እንዲኬድ የተደረገበት ምክንያት ኢትዮጵያ በሙሉ ክብር እና ማዕረጓ አንድትወጣ ስለማይፈለግ ነው። ለዚህም ነው በመዲናዋ ከፍተኛ በሆነ ገዢ ቁጥር አዲስ አባባ ላይ ብወዛ በፍጥነት እንዲካሄድ የተደረገውም። እንዲሁም ሌሎች ከተሞችም የከተማ ብሄር አልቦሽ ባህሪያቸውን የፈጠረው ማህበረሰብ እንዲከሰል ብወዛ መደረጉን  የኦሮምያ ርዕሰ መስተዳደር ዶር ለማ መገርሳ የነገሩን።

„ከሶማሌ የተፈናቀሉትን 500000 (አምስት መቶ ሺህ) በላይ የሆኑ ሰዎች፣ እንደምንሆነው ሆነን፣ ገፍተንም፣ ምንም ብለን፣ ከዚህም ከዚያም ብለን፣ የገዳ አባቶችንም፣ ሽማግሌዎቻችንንም ይዘን፣ እንደለመድነው እርቅ ፈጥረን፣ አቅፈን፣ ስመን ወደ ነበሩበት ቦታ ልንመልሳቸው እንችል ነበር፡፡ ቢያንስ ቢያንስ መመለስ ይቻል ነበር፤ እኛ ግን ልንመልሳቸው አልፈለግንም፡፡ ያንን ችግር ወደ መልካም እድል ለውጠን፣ ለኦሮሞ አንድነት፣ ያንን ችግር ወደ መልካም እድል ለውጠን፣ ዛሬም ችግር ላይ ያሉ ቢሆንም፣ ገጠር አላሰፈርናቸውም፤ ከተማ ነው ያሰፈርናቸው፣ እነዚህን ሰዎች፣ እወቁ፡፡ በአንድ ጊዜ 500 000 (አምስት መቶ ሺህ) በላይ ሰዎችን፣ እንዲያውም አዲስ አበባ ዙሪያና አዲስ አበባ ውስጥ፡፡ አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 6000 (ስድስት ሺህ) አስገብተናል፤ አዲስ አበባ ዙሪያ ብቻ አይደለም፡፡ እኒህን ከዚያ የተፈናቀሉትን ሰዎች፣ የዚህን አካባቢ ባህል የማያውቁ ሰዎች፣ በብዙ ነገሮች ከአካባቢው ጋር የማይመሳሰሉ፣ ይቸገራል መችም፣ ይቸገር፤ ዛሬ ችግር የማያጣው ቢሆንም፣ ከተቸገረም እዚሁ ከተማ ውስጥ ይቸገር፡፡ ቢያንስ ቢያንስ በእግሩ የሚቆምበት መሬት ይኑረው፤“  

ይህ ተመክሮ ደግሞ ህወሃት በለስ ሲቀናው ወልቃይት ላይ ያደረገው ይኽንኑ ነበር። ሪፍርደም የሚሉትም ለዚህ ነው። ስለሆነም ህውሃትን የምናውገዘውን ያህል ኦፌኮንምም ኦዴፓንም እኩል ማውገዝ ይኖርብናል። እንደ ዜጋ እኛ እንደምናስበው ህወሃትም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ነው፤ ኦፌኮንም ኢትዮጰያዊ ዜጋ ነው። ኦዴፓም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ነው።  
ፍርዳችን እኩል ይሁን ነው የዚህ ጹሁፍ ዓላማ። ሚዛናችን አይዛባ ነው የዚህ ጹሑፍ ዓላማ። አንዱ ኢትዮጵያዊነት ለመደርመስ በሥልጡን ሁኔታ ስለገለጸው፤ ሌላው በቅኔ ስለተቃኛው፤ አንዱ በማዛል ስለፈጸመው ማበላለጫ ሊኖር አይገባም። ሁሉም በግራ በቀኝ ሁኔታ ሲታይ ዲስክርምኔሽን ብቻ ሳይሆን ዕሳቤው የፋሽዝም ቅኝት ስለመሆኑ ማሰብ ይገባል። የሰው ልጅ እንደ ሊጥ አይቦካም ወይንም እንደ ዋልካ ጭቃ ጭፍልቅልቅ አይደረገም። 

የተዘመተው ዘመቻ ... ሰው ጠል ነው። ተፈጥሮ ጠል ነው። ሃይማኖት ጠል ነው። ታሪክ ጠል ነው። ትውፊት ጠል ነው። ባህል ጠል ነው። ቋንቋ ጠል ነው። ኢትዮጵያዊነትን ጠል ነው። ፓን አፍሪካኒስትነት ጠል ነው። ሉሲን ጠል ነው። በነገራችን ላይ የዓለምን የኢንተግሬሽን ሂደት ሁሉ ለመገደብ ከመስመር ያለፈ፤ ከመስመር የወጣ ጉዳይ ነው።

ዓለም ይህን ጉዳይ ተብራርቶ ቢገለጽለት ፊቱን ወደ ኢትዮጵያ ሊያዞር የማይችልበት ምንም ምክንያት የለም። የተባበሩት መንግሥታት የጸጥታ አስከባሪ ሃይል ሁሉ የሚያስፈልግበት ሁኔታ ሁሉ ነው አሁን ተጨባጩ የሚነገርን። እነሱ ሃይል በሁሉም መስክ እያዘጋጁ ነው። ከጎረቤት አገራት ጋር ምን እዬተመከረ እንደሆነ እምናውቀው።

በጣም የታፈነ፤ በጣም የሚያቀትት፤ በጣም ጭንቅ ውስጥ ያለ አዬር ነው ኢትዮጵያ ላይ ያለው። መከላከያውንም ሪፎርም አድርገናል ብለው የሚቀልዱት በራሳቸው አምሳል የቀረጹበትን መንገድ ነው።

ለነገሩ ጠ/ሚር አብይ አህመድ እኮ በሳንጃ እንፈታታሽ ሲሉ ባለ ብዕሩን ጋዜጠና እስክንድርን እኮ ጥሪ አቅርበዋል። ያ የዲሞግራፊ ትልም በአፍጢሙ ከመደፋቱ በፊት አዲስ አበባን የጦር አውድማ ለማድረግ ታጥቀው ተነስተዋል። እንደ እብድ ነው ያደረጋቸው። እኔ እንዲያውም ጠ/ሚር መሆናቸው ሳይሆን ካድሬነታቸው ነው ጎልቶ የታዬኝ። ከ አቶ ጀዋር መሃመድ የተለዬ የስሜት ርጋታ አላዬሁም።

ውስጣቸው በጣም ነው የተነካው። አይመረኛ ላልምርህ አይነት ነው የሆነው። ልክ አብን በቃልኪዳን ሰነድ ፊራማው ግን „አገር እንመራለን“ የሚለውን እንዳባጨሉበት እና ተከታይ ቅጥቀጣም እንዳደረጉት ማለት ነው። ለዚህም ነው የሰሞናቱ አዲስ ወግ ላይ አቶ ሌንጮ ለታ እና አቶ አበርሃም ደስታ ተዋናይ እንዲሆኑ የተፈለገው … በዚህ ውስጥ የታመቀ ጥላቻ እና የበቀል እልህ እኔ ይታዬኛል …

አሁን አነስ ባሉ ብሄረሰቦች የተጀመረው በራህብ የመጨረስ እና የማህበረሰብ ስብጥርን የመበውዝ ገዱይ ነገ በእያንዳንዱ ላይ የማይቀር ትልም ነው። ስለሆነም ይህን የዕብደት ምህንድስና ውልቅልቁን ማውጣት የሚቻለው ሁሉም በጉያው የሸጎጠውን የኢጎ ገመና አራግፎ ንጽህናን ቅደመኝ ሲል ብቻ ነው። አንዱን ባለከራበት ሸኝቶ ሌላ ገበርዲን አይደለም ጉዳዩ አሁንም ፍትጊያው ያው ስለሆነ።

አሁን በዚህ ሂደት ጠ/ሚር አብይ አህመድ ለስልጣናቸው ስስት እንዳለባቸው ሰብዕናቸውን ለመገንባት እንደማይታክቱ አሁን ከሆነ ጎልቶ ይነገራል፤ ሌላውስ ሊሂቅ? ምን እዬሠራ ነው ሠራዊት አሰልፎ ብቅ ሲል አቅም እዬሄደ የሚላተመው ለጽድቅን ነውን? የግጭቱ መንስኤ እኮ ላይ መውጣት አይፈቀድም። ተቀባይነት ብሎ ነገር የለም እኮ ነው። እያንዳንዱ የራሱን አንሷል። ንጉሱም ኢጎውን ቆልሏል። ስለዚህ የተጠጋበት ማህበረሰብ ኮሽ ባደረገ ቁጥር ያዙኝ ልቀቁኙ ይኸው ነው …

በነገራችን ላይ ከፌድራሉ እና ከአዲስ አባባ አማራን ከፖለቲካ ውሳኔ በማግለል ክልሉን በተለያዬ ቀውስ የማምስ ጉዳይም ሆን ተብሎ ታቅዶ ነው የተከወነው። ልክ ከሱማሌ አፈናቅሎ አዲስ አባባን የመስፈር ትልቅ ስትራቴጂ ተደርጎ እንደተያዘው ማለት ነው። ለዚህ በአማራው አካባቢ ያለውን መታመስ እዬሠራ ያለው የጃውርውያኑ የአቶ ንጉሡ ጥላሁን ኔት ነው።

ጎንደር የአማራ ታገድሎ ገናና አብዮት የተካሄደበት ስለነበር የዛን ቅስም ለመስበር መከላከያውም መሪ ድርጅቱ ኦዴፓም ከጃውርውያኑ አቶ ንጉሱ ጥላሁን ጋር የተሰራ ተውኔ ነው። በዚህ ሂደት ህወሃትም አማራን በሚገድሉ ጉዳዮች ላይ ፓሊስው ስለሆነ አቅም ማዋጣቱ እንዳለ ሆኖ ማለት ነው።

ህውሃት አልገባውም እንጂ ጎንደር ሲጣፋ በዚህ ውስጥ የሚጠፋው ዮሖንስ አንገቱን የሰጠለት ታሪክም ጭምር ነው። ይህ ቅንጥብጣበው እዬታዬ ሚወናጨፈው ጉዳይ ታሪክ በግራኝ አህመድ የተፈጠረው ክስለት ሊገጥመው እንደሚችል ልብ አላለውም። ማለት ቢያንስ ቤተ ተጋሩ በጥልቅት ማሰብ ይኖርባቸዋል።

ኦሮማይዜሽን የሚቀረው የለም። ርህርህና ብሎ ነገር አልተፈጠረለትም። ለዚህ ነው በፕሬስ ጉባኤ ላይ „ኦሮሞ የሌለበት የለም ትግራይ ውስጥ በራያ አለን ያሉት“ አይጠግቡም። ከዚህም ያልፋሉ በጉባኤቸው የአፍሪካ ነበርነታችን በኦሮማማ ንቅናቄ ብለውን የለንም? ሁሉም  ነገ ሊከስል እንደሚችልም ልብ ሊለው ይገባል …

ቀደምት የአክሱም፤ የሮሃ ፤ የፋሲል ስልጣኔ አብስንያ በሚል የጥቅል ቅጥያ ሥም የሚደረገውን ዘመቻ ልብ ብሎ ሁሉም ሊያስብበት ይገባል። እያተቀጣለ ስላለው አደራ … የቀደመቶች  ሌጋሲ … የ ዕምነት ተቋማት  ወዘተ ..

·       የበሽታው ዓይነት።

አሁን ያለው አዬር ህወከቱ በሽታው ባይረሱ ምንድን ነው ብትሉ የበታችንት ስሜት ነው። የበታችነት ስሜት ያለበት ግለሰብ፤ ድርጅት ምንግዜም ባካኝ ነው። አይሰክንም። እንዳይሰክን የሚያደርገው ደግሞ የበታችነት ስሜቱ ነውጥ ከጭንቅላቱ የበቀለ ሪህ ስለሆነ ነው። መከበር፤ መወደድ፤ ተቀባይነት ማግኘት በዓዋጅ አይሆንም። ፈቃድ እና ሁነት ሲጣመሩ ነው ሁሉም ሁለመናውን የሚሰጠው። ፈቃዱ የሰብ ብቻ ሳይሆን የፈጣሪም ቅብዕ አለበት። በዚህ ውስጥ ኩዴታም ሊኖር ይችላል።

ትናንት ፕሮፖጋንዲስት አልነበረውም አብይወለማ ሌጋሲ። በተናጠል እኔም ሳተናውም በትጋት፤ ጥቂት ሁለት ፍሬ ቅን ጋዜጠኞች በብዕራቸው የተወሰነ ነገር ብለዋል። በተረፈ በሁሉም ሚዲያ ነበር  በአሉታዊነት ወከባው። ያን አስበን የሚሊዮኖች ድጋፍ እና ሞገድ በትርፍ ሲቀና፤ ዛሬ ደግሞ ብሮድ ካስትን በኦዴፓ መሪነት፤ የአማራን ማስ ሚዲያ በጃውርውያኑ በአቶ ንጉሱ ጥላሁን፤ በተጨማሪም እኒሁ ድፍን ሰው የጠ/ሚር አንደበት ያው በሳቸው እዬተዘወረ ስለሆነ በወዘተረፈ

ፕሮፖጋንዲስቱ ይህን ያልህል ተሰልፎ የቁጣውን ማዕበል ማስቆም አልተቻለም … ትናንት ለድጋፍ ካለ ፕሮፖጋንዲት፤ ዛሬ ደግሞ ሙሉ የመንግሥት ሚዲያ በዛ ላይ እዬሠራ አልሆነም፤ ያው ተፎክሯል ለመዘጋጋት ይሞክሩት ጠ/ሚሩ። ህውሃትም አልቻለም እንኮን መላ ቅጡን አጥቶ ዝርግፍግፉ በዬሰከንዱ የሚዘካተል ድርጅት … ቀርቶ …

ለዛውም አልጀመርነውም ስንጀምርው መከራ ነው … ይልቅ ኢ- ሰውኛ፤ ኢ - ተፈጥሯዊ የሆኑ ድርጅቶች እና ግለሰቦች ስለ አበዱ አማሙኤል ይግቡ … በቃላት መነባበር ልብም ህሊናም አይሸለምም። አሁን የማያግባባን ቋንቋ ምን እንዲሆን ሰማን ሳይሆን አዬን። በማዘናገት፤ በማለዘብ፤ በማለዘዝ፤ በጫናም፤ በጉልበትም የሚሆን ነገር የለም። አፈር ከመልበስ በፊት ማድመጥን ማስቀደም የተገባ ነው።

… የጠ/ሚር ቢሮ ሆነ አወራው ድርጅት አገረ ገዢው ኦዴፓ ከማድመጥ ጋር ስለተማማለ መዳን የሚችልበት ሁኔታ ብዙም አይታዬኝም … አሁንም አማረብኝ ብሎ የቆረሰው ኬክ እና የሚነግረን አደንዛዥ ዕጸ በለስ ገመናውን ሸፍኖ ይቅርታ የሚያሰጥ አይደለም እና …
 መረቡን ዘርግቶ እስኪጨርስ ድርስ ነው ማደንዘዣ መርፌ የሚወጋን … ልክ እንደገዲኦ መንፈስ አርስቶ ሁሉንም እስኪያደርግ ድርስ። 

እንደ እኔ ከሚዲያ መሰውርም መልካም ይመስለኛል እያቅለሸለሸን ስለሆነ … መናገር በመሆን ውስጥ ነው ሲሆን ነው የሚደመጠው። ቃል የ ዕምነት ዕዳ ነው ብለዋል የንጉሶች ንጉስ አጤ ጤወድርስ ለዚህም ነው በ150 ዓመት መንፈሳቸውን ሙላቱን ለቀቅቅ ያደረገው …
ዕምነት ጎድሏል፤ ቃል ተበልቷል። እንገና ወደነበርንበት እንመለስ ዘንድ ያው በግርባው ብአዴን የተጀመረው ሁሉ ከንቱ የከንቱ ከንቱ ነው … እኔ ቀድሜ ተናግሬ ነበር ኮ/ ጎሹ ወልዴ አማካሪ ይሆኑ ዘንድ

… እንዲህ እንኩት ከማለት በፊት። ግን አድማጭ የለም። ገዳይ ዶር አረጋይ በርሄን አማካሪ አድርጎ መዳን አያቻልም። በሳቸው የውስጥ አመራር ብአዴን አለቱን ከላስታ አስመጥቶው ድንጋይ ይዞ ከሄርድስ መለስ የሙት መንፈስ ሥር መነጠፍ ነው። ይህም እሳት የላሰውን የ አማራነት ነበልባል ቢያጋግለው እንጂ ረብ አያደርገውም። ውስጣችን ያለው የተደፋነ ረመጥ በሁለማ እንድንከስል እንደተመከረብን መጸሐፍ ገላጭ ቤት አያስፈልገንም …  

·       ይጠቅለል … 
ማወቅ ከችግር ማደን ብቻ ሳይሆን ገመናን ገልጦ እርዳታ መጠዬቅም የማወቅ የብስለት የማስተዋል ፓለቲካዊ መፍትሄ ነው። ….

ውዶቼ ከዚህ ቀጥሎ የምለጥፍላችሁ … ልባም ውይይት ስለሆነ ብትከታተሉት መልካም ነው። ሁሉም ጠቃሚ ነው፤ የታሪካችንም አካል ነው። ሁሉን መቀበል የግድ አይደለም፤ መቀበልም አለመቀበልም መብት ነው እኔ ግን ኢትዮጵያን ቁምነገር በማድረግ ዓላማ ያለውን ተልዕኮ ያዝን ብለው ክህደቱን በሚገባ የሚያብራራ ስለሆነ ከልቤ  ወድጀዋለሁኝ።
በጸጋዬ ራዲዮም ይቀርባል ወደፊት … ታሪኬ ልለው የምችል ብቻ ሳይሆን ውይይቱ መምህርነቱ ዝልቅም ስለሆነ። እኔ ማን ይሁን ማን አውነት አለበት ብዬ ካመንኩ ልቤን እሸልመዋለሁኝ። አነሰ ካለም ህሊናዬን … ርዕዮት ሚዲያ ጥሩ እዬሰራ ነው …

ስለ አቶ በቀለ ገርባ ማንፌስቶ ጥልቅ ትንተና።
ስለ ዶር ነጋሶ ጊዳዳ ትርክት ጥልቅ ትንተና።
ስለ ሦስቱ ጥምር ሲኦል መንገዶች።
ስለ ኢትዮጵያ ህልፈት ድውለት በሊቃናት ሲፍታታ ..
ነገረ አዲስ አባባ

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!

የኔዎቹ ቅኖቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።