አንድ ጥበብ የጨለመበት።
አንድ ጥብብ
የጨለመበት።
Eine Art Dunkelheit.
„አንተ ረዳቴ እና መድህኒቴ ነህ አምላኬ ሆይ አትዘገይ።“
መዝሙረ ዳዊት ፴፱ ቁጥር ፩፯
ከሥርጉተ© ሥላሴ(Sergut©Selassie)
የሥነ ጹሁፍ እና የመጋዚን ዝግጅት ት/ቤት
ውዶቼ ይህን ጹሑፍ የጻፍኩት በ2006 ነበር በፈረንጆች። ያን ጊዜ ሳኡ ከሚባል የስደተኛ መጋዚን ዝግጅት ቡድን ጋር እሳተፍ ነበር። ያን ጊዜ የተጻፈ ነበር። ያን ጊዜ ብዙ እርማት ቢያስፈልገውም በጀርመንኛ ብርቱ ጸሐፊ ነበርኩኝ።ታዳሚም አርቱን ዘይቤውን ይወደው ነበር። ለመጽሄቱ ግጥም
የጀመርኩት እኔ ነበርኩኝ። ዛሬ ሳቆመው ቆመ ይባላል። ዛሬ በጣም ደካማ ነኝ። ወደ ቁልቁል ልበለው። ወደ ሦስት ዓመት ሊሆነኝ ነው ስለላውም ስለበዛብኝ ትምህርቱም የማታው ቆመ ጽፌም አላውቅም በጀርመንኛ።
ታሪኩ ዕውነተኛ ነው። ቀን አልፎለት በ2016 ደግሞ የቲያትር ሥልጣና ነበረኝ። እና ለኮርሱ የፍጻሜ ዕለት ለህዝብ በቀረበው
ቲያትር ላይ ደግሞ በድጋሚ በአማርኛ እና በጀርመንኛ በድምጽ ቀርቧል። ከሥርጉተ ቁጥር ሁለት ዩቱብ ላይ በድምጽ የተሠራው ለጥፌዋለሁኝ፤ ወደ
ፊልም የመቀዬር ሃሳቡ ነበረኝ።
እዚህ ሲዊዝ ውስጥ ስትጀመሩት አየር ላይ ነው ትልሙ እንኩት የሚለው፤ ከሃበሻ ጋር ከሆነ። ኢፍትሃዊነት
// እናትን ከሠራሁ በኋዋላ ወደ 10 የተዘጋጁ ፊልም ነበሩኝ ግን እንዴት? አያንቀሳቅሳችሁም። መፈናፈኛ የለም ሁለማናችሁ የታሠረ ነው። ምንም አይቀርባቸውም፤ ከእነሱም የሚደርስ የለም ግን ፍዳ ነበር።
የሆነ ሆኖ ይህን ዕቅድ ላይ ተንጠልጥሎ የቀረ አጭር ፊልም ከአንዲት ጀርመናዊ ሲዊዝ ትኖር ከነበረች የራዲዮ ጋዜጠኛ ጋር
ነው የሠራነው። የእሷ አነባቧ ፈጠን ይላል ዘይቤዋም እንደ ጥልቁ ቋንቋ ጀርመንኛ ተፈጥሮው ነው። የእኔ ደግሞ ዝግ ይላል በስደተኛ የቋንቋ
ችሎታ ቃና ነው።
ብቻ ሲዊዝ ጓደኞቼ አማርኛውን ሆነ እንደ ነገሩ የሆነውን ጀርመንኛ ድምጼን ቃናውን በእጅጉ ይወዱታል። ራዲዮ ፕሮግራሜን
የጸጋዬን በመደበኛ ነበር የሚከታተሉት። ብቻ በድምጽ በጀርመንኛ የሆነወን ለጥፌዋለሁኝ። ፈቃዳችሁ ከሆነ ብታዳምጡት አይከፋም …
የእውነት ታሪክ ነው አገር ስወጣ የነበረ ስሜት እና ሁኔታ ነው …
EINE ARTE DUNKELHEIT 19.09.2017.
አንድ ጥበብ--- የ----ጨለመበት////…
እውነተኛ -----------ታሪከ።
//// ትንሽዋ ጭላንጭላዊ ብራሃን
ወደ ሞት - ተጠግታለች /ሞታለች። ክፍሌን ጥዬ ወጣሁ። ዬት እንደምሄድ? ወደ ዬትም እንደምጓዝ አላውቀውም
ነበር። እቅጣጫ የለሹን ጉዞዬን ጀምርኩት … ተጓዝኩ - ቀጠልኩ ...ተጓዝኩ ... ተጓዝኩ ...
አንድ ጨለማ በከፍተኛ ድምጽ
የታጀበ ወደ እኔ መጣ። ተጠንቀቂ! አለኝ። እኔ ግን ምንም አማርጭም ስላልነበረኝ መቀጠል ነበረብኝ - ጉዞዬን።
መቆዬት አልችልም ነበር - የማይመች!
----------ተጠንቀቂ ------ያ ጨለማ ወፍራም
ድመጽ በደጋሚ መጣብኝ። /////// ጥቂት ዘግይቼ ----//// - እጅግ በሚያባባል ቅን ድምጽ „እ ….. እ … ማን
ልበል አልኩኝ? ድምጼ እጅግ ውብና ለስላላሳ ነበር። ነገር ግን በአካባቢው ማንም--------------- አልነበረም።
////////////////// ለሶስተኛ
ጊዜ ያ ጉልበታም ድምጽ ወደ እኔ በድፍረት መጣ።ያን ጊዜ እምይዘውንና እምጨብጠውን አላውቅም ነበር።
----------
ኦ ኦ ኦ! አምላኬ! ////// በደማናማ
ጭንቀት ተዋጥኩኝ። ፈራሁኝ። ምን ላድርግ? ------- ሌላ አማራጭ ቢኖረኝ መልካም ---- ነበር።
////////// ሃይልና ፍላጎት
አልባ ሆንኩኝ። የነበረብኝ ድካም የመሞት ያህል ነበር። አዎን! ከአንድ ግልጽና ንጹህ ውሳኔ መድረስ ነበረብኝ። - ደረስኩኝ። ማንኛውም
ፍጡር አንድ ቀን መወሰን አለበት። መወሰን ----------------- መብት ይሁን ግዴታ ብቻ
------------------- መወሰን!!
እህህ
------------------- ህህ -------------- የከፋ አጋጣሚ ነበር። -------------- እኔ ግን በወሰንኩት
ውሳኔ መጽናት ነበረብኝ። እናም - ለአዲስ ፈታኝ ህይወት ----------------ምንም ሳላመናታ ጉዞዬን ቀጠልኩ
----------------ኝ
መጓ------------- ዝ። መጓዝ
---------------------ለመከራ ፈቀዶ መጓ -ዝ -----------
//// መንፈሴ ሆነ እግሬ ከጥቅም
ውጪ አስኪሆኑ ድረስ ----------መ ----------------- ቀጠል።
---- ለትናንት ብቻ አይደለም፤
ለዛሬም// ለነገም --------------- ወደ አንድ አፍ ወደ አለው የመቃብር ጉድጓድ መጓዝ
---------------------------------------------////
እርግጥ ነው ባለአፉ መቃብር እጅግ
በረዷማ ---- ቀዝቃዛና ከባድ መሆኑን አውቃለሁ። ከዚያስ?፡?፡?፡ ከዚያስ! ከዚያስ ------------------------////
…
----ከዚያማ
ከወፍራሙ ዕንባዬ ጋር መኖር>>
በቃ! እኔ ጨረስኩ። እኔም አለቅኩኝ። ሁሉ መከራ በእኔ ውስጥ ኖረ። ካለ አውነተኛ ህልም። ምንምን
ታውቃላችሁ? አዎን ምንምነት -----------------
ይህ የትእግስት ጨዋታ
ነው። አሃ! አዎን --- የእኔ ዕድል ልክ
እንደ ስቅለት ቀን
ነው።
ከሆነ ቦታ አንድ ብርኃን ማዬት
እችል ከሆነ እጓዛለሁ። ብርሃኑ ግን እኔ እስክደርስ ድረስ ይጠፋል። ምክንያቱም ብርሃኑ ከእኔ በጣም -- የራቀ -------ነው። እሆሆሆ አዬዬ ዬዬ ------------------ እህህ
----- /// …
ይህ የሚያስቅ
------------- ወይንስ የሚያሳዝን?!!!!!!? ማጣት ሲባዛ
በማጣት። ማጣት x ማጣት። እምምምምምም!
ፈተናን መጋፈጥ የሰው ተፈጥሮ ነው።
የኔዎቹ ኑሩልኝ!
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ