ጥልፍ የሥነ ቃል ጥልፍ።
ጥልፍ
„አቤቱ ታድነኝ ዘንድ ፍቀድ፤
አቤቱ እኔን ለመርዳት ፍጠን“
መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፴፱ ቁጥር ፲፫
ከሥርጉተ© ሥላሴ Sergute© Selassie
በርን ቤተመጻህፍት ባዘጋጀው የሥነ ጥበብ መሰናዶ።
** ጠብታ! ዘለላ-
የመንፈስ ወለላ
መዳፈ-ጥልፍ
ጠፈፍ!
አልቦሽ ጠረፍ
ብራና ላይ ሲንጠፈጠፍ
ዛላው ሲርገፈገፍ
ጊዜ አይሽረው አይነጥፍ
አይሆን ጠፍ
ጥልፍ!
ብዕረ ምጥ-የቁርጥ
የቀለም ሰርጥ
ንጥር የምናብ መረቅ
ነበልባላዊ መንፈስ አቅልጥ
ጥልፍ!
የቅመም ውቅጥ
የተግባር ነቁጥ
ወልጋዳን ቆንጥጥ፣
ተባደግን አፍርጥ-ደፍጥጥ
ጥልፍ!
ነው ጥልፍ
የኮፒ እንፋሎት፣
ፍ ላ ሎ ----------- ት
ሮ ኆ ቦ ------------ ት
ጥልፍ!
ዘይቢያዊ ንቅሳት
ነቀል - ተከል፣ የሌለበት
ቀድሞ የሚያልፍ፣
አይደለም ግርድፍ
ማገሩ አለው ውብ ዘርፍ
የሚያዘርፍ፤
ጥልፍ!
ገለባን የሚቀርፍ
ድቃቂን የሚያራግፍ፣
ባለ ጥርኙ ጥልፍ
ፍቅርን የሚያሳቅፍ
ጥልፍ!
የአብረንታት ጥልፍ
ደፋር …
የሚያመረቃ ጨረር …
የቅኝት ጥልፍ
የዜማ ጥልፍ
የእስትንፋስ - ጥልፍ
የሕሊና ደም ጥልፍ
የሚታገል ግፍ…
የሌለበት እድፍ
ጥልፍ
እዮር እፍ ያለበት እፍ
የብዕር ጥልፍ!
ቅዱሰ መንፈስን የሚጠልፍ
የሚያራግፍ፤ ግ --------- ፍ፡
ጥልፍ
ቆመ ለዕልፍ
ለሥነ-ተፈጥሮው ህግጋት … አለ እልፍ
እ ------------- ፍ
የርትህ እቅፍ
የማይል ዝንፍ፤
አንባገነንን ’ሚዘነጥፍ
መለመላ የሚያሰነጥፍ
ምሰባክ የእልፍ፤
ጥልፍ
ሰማያዊ ጽንፍ
ረቂቅ ንድፍ
ባለ ትርፍ፤
የማይደክም
ዓራት ዓይናማ - የማያርፍ
የሚዳኝ - ግርድፍ
ጥልፍ፤ ውጽፍተ-ምዕራፍ .....
አፈሬ ነው መስመሬ የሥነ ግጥም ሥብስብ።
አንባቢዋም ጸሐፊዋም ሥርጉተ ሥላሴ ናት።
(23 06 2018)
ጌጦቼ ኑሩልኝ እናንተን አያሳጣኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ