ፍቅርን መቀበልም ማብቀለም ፈተና ነው።

                            ፍቅርን መቀበልም ማብቀለም ፈተና ነው።

                                      ከሥርጉተ ሥላሴ 16.06.2018 ከመነኩሴዋ ሲውዝዬ ነፍሴ።
                               „ምስጋና የሚገባውን እግዚአብሄርን እጠራለሁ፤ ከጠላቶቼም እድናለሁኝ።“ 
                                             (መጽሐፈ ሳሙኤል ካልዕ ምዕራፍ ፳፪ ቁጥር ፬)


  • ·         መክፈቻ

እንዴት ናችሁ የኔወቹ የልቦቹ አባ እና እማ እነ ቅንዬ? ዛሬ ቀኑ ፈታ ብሏል። ብላlች ልዕልተይ። አሁን  አንድ ጹሑፍ ከብራና ሳተናው አነበብኩኝ። ከማከብራቸው ጸሐፊ አቶ ስዩም ተሾመ ነው። ወቅታዊ ነው ብዬም አላምንም። ጭብጡ ለአብይ መንፈስም ተቀራራቢ አይደለም ብዬ አምናለሁኝ። ተቀራራቢ ያልሆኑ መንፈሶች ሃሳብን ከመክፈል ውጪ ለምናስበው ተስፋ ጠቃሚ አይደለም። ክብሩነታቸው በማህበረ ደራጎን ታፍነው ባሉበት በዚህ ወቅት የሚያጽናና እና የሚያበረታታ፤ ሃሳብን የሚደግፍ እንጂ እንዲህ ያሉ መንፈሶች እንብዛም ለተሰፋ አይረዱም። ስለዚህም ሚዛኑን ማስጠበቅ ታሪካዊ ድርሻዬ ስለሆነ የግድ መጻፍ ነበረብኝ። ተጥፏልም።  አሁን እንደ አዬሁት ወደ 362 ሰው ሸር አድርጎታል። ያው ብሶትን ማባበል የተለመደ ስለሆነ። በስተጀርባ በስተፊት ጠቀሜታ እና ጉዳቱ ለማን እና ለምን የሚለውን ብዙም አናስብበትም። የራሳችን አቅም በተሰበረ ቁጥር የትውልድ ብክነት ቀጣይነት አይታዬነም። የእኛ ፖለቲካ ልግመኛም መሆኑ ብቻ ሳይሆን የሚያሳዝነው ከግል ምኞት ጋርም የተጠባቀ መሆኑ ነው።
  • ·        መነሻ።

„ለሀገር ሰላም፣ ለሕዝብ ደህንነት ሲባል የህወሓት አመራሮች ለፍርድ መቅረብ አለባቸው! (ስዩም ተሾመ)“
http://www.satenaw.com/amharic/archives/58561

ይቅርታ የሚደረገው ለሰዎች አይደለም ይቅርታ የሚደረገው ለክፉ ተግባራቸው ነው። ይቅርታ ሰው ሰለ ወደደ እና ስላልወደ ሳይሆን በሃይማኖት ደረጃ ዶግማ ነው። ስለዚህ ይህን ዶግማ ለመፈጸም ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ጥንካሬያቸውን ያሳያል። የ አመራር ብቃታቸውን ደረጃ ከፍታ ያመሳጥራል። እነሱ ይለወጣሉ ብለው አስበውም አይመስለኝም ግን ትውልድ ይቅርታ ማድረግን ሲማር በቀል እና ቂምን ትወልድ እናዳይወርስ ለማድረግ ነው እንጂ ደራጎንም ደራጎን፤ ፈርዖንም ፈርዖን፤ ሄሮድስ ሄሮድስ፤ ናዚም ናዚ መሶሎኒም መሶሎኒ ነው።
ተከታዮቻቸውም ይሄኑ ይዘው ሄያጆች ናቸው። አሁን ትንሽ ሰከን አለ እንጂ ባለፉት 2/3 ዓመት ጀርመን ኦስትርያ ሲንጣቸው ነው የባጀው የሶርያ ስደተኛ መበራከት እንደ ገና ናዚዝም አገርሽቶበት በተለይ ጀርመኖች አዲስ ፓርቲ እስከ መፍጠር አድርሷቸዋል። ግን በፍቅር ዙሪያ በሚተጉ ትጉሃን መሪዎቻቸው አማካኝነት ወጀቡን አስታግሰውታል። እራሱ ታላቁ ብርታኒያ ከአውሮፓ የወጣችበት ሚስጢርም ይሄ ራስን የማፍቀር ሁኔታ ካለልኩ የመወጠር አዝማሚያ ነው።

  • ·        አብይ መንፈስ ነው።

የሆነ ሆኖ ዋናው ቁምነገር የአብይ መንፈስ መሠረታዊ እሳቤ በቂም፤ በቁርሾ፤ በበቀል ውስጥ ሁሉ የተከዘነውን ሥነ - ልቦና ማጽዳት ነው። ቢያንስ መቀነስ፤ የተወጠረውን የክፋት አዚም ማላላት ይህን ማርገብ ነው። በተለያዩ ሁኔታዎች ከወያኔ ሃርነት ትግራይ ጋር ብቻ አይደለም በዚህ በሶሻሊዝም ርዮት ቂም በቀል ሂደት ኢንትሪግ ብዙ ሰው እንደ ጠላት ነው የሚተያዬው። ውጪ አገር እኮ ልብ ለልብ መገናኘት የለም። እንደ አገር ልጅ መተያዬትም ከቀረ እኮ ዓመታት ተቆጥረዋል። ቀድሞ ሁላችንም እንተዋወቃለን በአንድም በሌላም፤ አሁን እኔ ከማውቀው ይልቅ እማላውቀው ኢትዮጵያዊ በብዛት ነው ያለው። ከማውቃቸውም ጋርም ቀረቤታ የለኝም። ስለምን? ውስጥ የሚያመክኑ ገጠመኞች ስለተበራከቱ … ቢያንስ የስደቱን ጊዜ ዘመነ ሱባኤ በማድረግ ከፈጣሪ ጋር ለመኖር መቁረጥ የተሻለም የውስጥ ሰላማም ስለሆነ። ጤናም ነው። 

በሌላ በኩል ስልክ ሲደወል አይነሰም። ስለምን? ሰው ለመነጋገር ሲፈቅድ ሌላው ደግሞ ሪከርድ አዘጋጅቶ የግል ነፃነትን ተፃሮ ነው የሚደውለው ወይንም ሌላው በጎን ውይይቱን እንዲሰማው አድርጉ። ገመናችንም ዕዳችንም በርካታ ነው።

አሁን አቶ ስዩም ተሾመ በራሳቸው ቢያስቡት ሲታሠሩ ትልቅ የሚደያ ሽፋን ተሰጥቶታል፤ ሲፈቱ  ደግሞ ከቁጥር አልገቡም። እንዲህ ሲጽፉም ሁሉም እኩል አያስተናግዳቸውም። ስለምን? ሁሉም ራስ ወዳድ ነው። ራሱ ክብሬ ኩራቴ ካለው መንፈስ ጋር ካልተቀራረበ በጅ አይለም ስሜት። ከተፈላጊው ሃሳብ ጋር ቢቀራረብም ይለፍ በውስጥ መስምር ካልተሰጠው ጥሶ ለመውጣት እጅግ ፈተና ነው። ሸር ለማድረግ እኮ ማዕቀብ የተጠላብን ፍጡራን አለን እኮ። ይህ ደግሞ የፍቅር ተፈጥሮን መርህ ካለማወቅ የተነሳ ነው። ማንም በማንም መፈረድም አይችልም። ስለምን? ዓለም እራሷ ይህን አሉታዊ፤ ቅናዊ ያልሆነ መንገድ የምትገራበት መሳሪያ በእጇ ስሌለ። የፍቅርን ተፈጥሯዊ መርኽ በተለምዶ እንጂ በት// ቤት ደረጃ የተማረው አንድም የዓለም ዜጋ የለም።

አሁን አቶ በኮ ሃራም ተወቃሽ ናቸው። ለእኔ ደግሞ አቶ በኮ ሃርም ስለፍቅር ዱዳ የሆኑት ዓለም ፍቅርን የሚማሩበት የዘረጋችላቸው አጋጣሚ ስሌለ በቀጥታ የተቀላቀሉት ከጭካኔ መንፈስ ጋር ነው። ጨካኞች፤ ፋሽስቶች እኮ ይዘውት አልተወለዱም ጭካኔያቸውን ሆነ ፋሽስታዊነታቸውን። ማንኛወም ልጅ ሲወለድ ክፋትን፤ ምቀኝነትን፤ አሉታዊነትን፤ ገዳይነትን፤ ዘረኝነትን፤ ጭካኔን፤ ሰው ማሳዘንን፤ ሰላም ማወክን፤ ሰው መጨቆንን፤ አስገድዶ መድፈርን፤ ማውደምን፤ ማማትን፤ ማጣላትን፤ መጥላትን፤ ማሳደድን፤ በጠቅላላ ዲያቢሎሳዊ ምግባሮችን ይዞ አልተፈጠረም።

ልጆች ሲወለዱ ንጹህ ህሊናን ይዘው ነው የሚወለዱት። ለምሳሌ አንድ ህጻን ኢትዮጵያዊ ጀርመን ከተወለደ የጀርመንኛን፤ አሜሪካ- አውስትራልያ- ኒዮዝላንድ - ለንደን ከተወለደ እንግሊዘኛን፤ ፈረንሳይ ከተወለደ ፈረንሳይኛን፤ ራሽያ ከተወለደ ራሺያኛ፤ ስፔን ከተወለደ ስፓንሽኛን ወዘተ ቋንቋን ከእነ ዘይቤው ይችላል። ያንኑ ተላምዶ ነው የሚያድገው። ለምሳሌ እኛ ድብቆች ነን። ውጪ ተወልደው የሚያድጉ ደግሞ ግልጽ እና ቀጥተኛ ናቸው። ሚስጢር የሚባልም አያውቁም። ጠያቂዎችም፤ ሞጋቾችም ናቸው። ለምን? ስለምን? እንዴት? መቼ? የት? ይህን ማወቅ ይሻሉ። በእኛ ደግሞ አትጠይቅ አቅምህ/ አቅምሽ አይፈቀድም ይሄ አይባልም ወዘተ ነው …
ሌላ ሥርዓትን ተምሮ በማደግ ረገድ የንጉሣውያኑ ወጥ የሆነ ምግባር አላቸው። 

የንጉሣውያን ቤተሰቦችን ሲወለዱ ከተወለዱባት ቀን ጀምሮ ሞራላዊ ሥርዓታቸውን አጥንተው ያድጋሉ። ስለምን? የሚቀበላቸው አዬር ያ ስለሆነ። ሌላው ግን ቤት የተሻለ ሞራላዊ ሁኔታ ቢኖር መንገዱ፤ የሚማርበት ቦታ፤ የሚጫወትበት ሥፍራ፤ አዬሩ ራሱ ድብልቅልቅ ያለ ስለሆነ በዛ ውስጥ ስለሚያድግ ያንኑ ተላምዶ ያድጋል። እርግጥ ነው መልካም ቤተሰብ ያላቸው በጥዋቱ ስለሚገሯቸው ያን ተከትለው ያድጋሉ። ያም ሆኖ አካባቢያዊ ተጽዕኖም ስላለ ከክፉ ነገሮች እና አስተሳሰቦች ጋር ንክኪ የላቸውም ማለት አይቻልም። ሥርዓቶች ራሳቸው ከሰው ጋር የተጣሉ ናቸው። አባትህ ተገድሎ፤ እህትህ ታስራ፤ አጎትህ ተሰዶ እንዴት ያለ መንፈስ አዲሱን ልጅ ይቀርጸዋል። እርግጥ ነው ከንፍሮ ጥሬ ካወጣቸው እነሱንም ቢሆን ቁጥራቸውን በፐርሰንት ማውጣት ይቸግራል።

ሌላ እስያ ተወልደው የሚያድጉ ልጆች የጨዋነት ደረጃ ከወላዊ ተልዕኮ ከማዬው ከሜዲቴሽን ጋር በተያዬዘ ይመስለኛል የቡድን ሥራ ውስጥ ስክነት አይባቸዋለሁኝ። ሜዴትሼን ብስጪትን፤ አገሬሲብ የሚያደርጉ ነገሮችን የመግራት አቅም አለው። ቁጡነትን ሁሉ ያስተካክላል። መፍላትን ይገራል። ዮጋ በራሱ ዲስፕሊኑ የተለዬ ቀለም አለው። ራሱ የዮጋ ቡድን አባልተኝነት ትርጉሙ የተለዬ ንጹህ ሆኖ መንፈስን አጽድቶ የመቅረብ አቅም አለው። እኔ ለዚህ ለፍቅራዊነት Loveism ፕሮጀክቴ ራሴን እንደ አንድ የምርምር ኦብጀክት አድርጌ አይቸዋለሁኝ። በፍጹም ሁኔታ ጥበቡ ቀለማም እና ያን በመደበኛ ሁኔታ የሚወስዱ ሰዎችም ውስጣቸው የተረጋጋ ነው። በጣም ነው የሚደንቀኝ። ለጥናቴ እንዲረዳኝ የተለያዩ የኮርስ ታዳሚዎችን በተለያዩ ወቅቶች እጥንቻቸዋለሁኝ። የሰብዕና ደረጃቸው ወደዛ የሚመጡት በራሱ ለሰማላማዊ ኑሮ የፈቀዱ ብቻ ናቸው። ትህትናቸው ቁሞ ያስተምራል። ሰው ለመርዳት ያላቸው ፈቃደኝነት ልዩ ነው። ጤናማ አዬር ጤናማ መንፈስ ይፈጥራል። ከድብልቅልቁ ዓለም ወጥቶ ወደ ዮጋ ወደ ሜድቴሽን ሲኬድ ሌላ ዓለም ነው። አዎን! ለዚህ ይመስለኛል የእስያ ልጆች ወጣቶች በተለይ ስክን ያሉ የሆኑት። መንፈሳቸው የተገራ ነው።

  • ·        ልጆች እና ዕጣቸው።

ልጆች ወደ ዚህች ዓለም ሲመጡ ድብልቅልቁን፤ ቅይጡን ዓለም እንዳለ ነው የሚቀላቀሉት። ይህን ወጣ ገብ የሆነውን የዘበጠ ሰብዕና ለመግራት ልጆች ይህችን ምድር ሲረግጡ ቤት ውስጥ ስለ ተፈጥሮ ስለፍቅር፤ ስለሰው ልጅ ክብር የሚማሩበት ሁኔታ ቢኖር፤ ልጆች በሚውሉባቸው አካባቢዎች ያሉ ነገሮች ሁሉ የፍቅርን ተፈጥሮ የሚገልጹ፤ ሰው ተኮር የሆኑ ነገሮች ላይ የሚመሰጡ ቢሆኑ፤ ለትምህርት ሲደርሱም የፍቅርን ተፈጥሮ በመደበኛ ትምህርት እንዲማሩ ቢደረግ ዓለም አስፈሪ አትሆንም ነበር፤ የፍቅር ተፈጥሮ ህግጋት እኮ ዓለም አጀንዳዋ አይደለም። በፍቅር ተፈጥሮ ላይ ዓለም ተወያይተበት አታውቅም። ምንም ዓይነት ተቋምም የላትም። ፍቅር እኮ የነፍስ ማደሪያ ነው። ፍቅር የነፍስ አካል ሳይሆን ራሱ ነፍስ ነው።

Sergute Selassie YouTube

ስለዚህ እንደ ወያኔ ሃርነት ትግራይ ዓይነት ጭካኔን ብቻ ዶክትሬን አድርጎ ለቆዬ ድርጅት ፍቅርን ለመቀበል ቢከብደው አይደንቅም። አዕምሯቸው ተደፍኗል። የሚያሳዝነው ያን የተከተለ ትውልድ ማፍራታቸው ነው ችግሩ። አንድም ሰው ወደ ቅንነት ለመምጣት አቅም ማጣቱ እጅግ አሳዛኙ ነገር ነው። ይህን በፍቅር ገበታ በሆነው እግር ኳስ ጨዋታ እንኳን ማምጣት አልተቻለም። አጅግ ዘመንም፤ ታሪክም ዓለም ዓቀፍ የስፖርት ቤተሰብነትም ያወረደ ተግባር ነው እዬተፈጸመ የሚደመጠው። ካለልክ ከፍ ያለ የሥነ ልቦና መወጠር ያመጠው ነው።
በግለኝነት ውስጥ ነው ትግራዊነትን ያሰረጡት። ትግራይ አትነካ ሌላው ይንደድ ነው መርሃቸው። 

ስለዚህ ቋሚ የሆነ ሥነ - ምግባር አይታይም እዛ አካባቢ። ሁሉም ችግር ትግራይን ሳይነካ ማለፍ አለበት ነው ተጋድሏቸው። ይህ የአብዛኞቹ ከሊቅ እሰከ ደቂቅ የተጠናወታቸው በሽታ ነው። አሁን እኛ ፊት ለፊት ያሉትን ብቻ ነው እምናዬው። ግን ወደ ውስጥ ዘልቀን እንመርምርህ ብንል ያ እኛ የበላይ ነን የሚለው የአንባገነንነት መንፈስ አለባቸው። ያ ዝቅ ሲል ነው ብስጩም አግሬስብም የሚሆኑት። አሁን ስፖርት የግድም መወደድን አታተርፍም። መወደድ በምግብር እና በሥራህ ነው። እነሱ ደግሙ በገዢነታቸው ብቻ ፕሮሚ እንሁን ባዮች ናቸው። ፍቅርን ለስጠት ፍቅር ሰጩ ፈቃደኛ መሆን አለበት ሊያህ ያለፈቀደን ፍቅር አልሰጠህኝም ብለህ ብታንጓጠው የሚሆን አይደለም። ፍቅር በጠመንጃ አይገኘም። ፍቅር ከላቀ የሞራል ብቃት የሚመነጭ ነው። ፍቅር መሊኪያ መስፊሪያ አለው። ፍቅርን መለካት እና መስፈር ግን አይቻልም።

ወደ ቀደመው ስመለስ የትግራይ ገበሬዎች ምን ዓይነት መንፈስ እንዳላቸው አላውቅም። አብሪያቸው የተወሰነ ጊዜ ብኖር እና ሥነ - ልቦናቸውን ባጠናው ደስ ይለኛል። የሆነ ሆኖ ችግሩ የፍቅርን ተፈጠሯዊ ህግጋት ሙሉ ለሙሉ ያለመቀበል የእነሱ ብቻ አይደለም። የሁሉም የዓለም ዜጎች ችግር ነው። የፍቅርን ችሮታ ደፍሮ የተቀበሉ ሚዲያዎች ይሁን ሊሂቃን በጣት የሚቆጠሩ ናቸው። ያን ብንቀበል እማ ኖሮ ወጀብ በመጣ ቁጥር አጋፋሪ፤ አራጋቢ ሆነን ባልተገኘን ነበር። ለዚህ ነው ኢትዮ አፍሪካዊው የቅኔው ልዑል ብላቴ ሎሬት ጸጋዬ ገ/ መድህን „ፍቅርን ፈራን“ ያለው።

የሰው ልጅ ፈርቶት የሚኖረው ተፈጥሮ አለ ቢባል የፍቅርን የተፈጥሮው ህግጋቱን ነው። ፍቅርን ስታገኘውም ስታጣውም፤ በሆነ ነገር እሺ ስትባልም አይ ስትባልም፤ ይሆናል ስትባልም አይሆንም ስትባልም ስተሰጥም ስትነፈግም ደስ ሊልህ ይገባል። ስታጣው - አይ ስትባል- ስትነፈግ ስለምን ስለመሆኑ ማሰብ ያስፈልጋል። አንተ ያልታዬህ ሌላው ያን የወሰነበት መንገድ ይኖረዋል። ስትሞገስ ደስ እንዳለህ ሁሉ ስተወቀስም ደስ ሊልህ ይገባል። ፍቅር ማለት እንዲህ ዓይነት ሞጋች የሆነ ተፈጥሮ ነው። ፍቅር ሞጋች ነው። ኑሮን ሆነን ነፍስን የሚሞግት አቃቢ ህግ ነው ፍቅር። ሲያሰኘውም ችሎት።

ስለተወደስክ የምታፋቅር፤ ስለተወቀስክ የምትጠላ ከሆንክ አንተ ከጫካ ባለተመክሮው ከወያኔ ሃርነት ትግራይ በምን ትሻላለህ? በምንም? እኩል ለእኩል። እኩል ለእኩልነታችን መሰረታው አመክንዮ ወጥ የሆነ የፍቅራዊነት ተፈጥሯዊ ህግጋትን አልተማርነውም በትምህርት ቤት ደረጃ። አንድ የሂሳብ ሙሁር ቋንቋ ካለገደው ዬትኛውም አገር ዩነቨርስቲ ሄዶ በሙያው መሥራት፤ ማገልገል ይችላል። አንድ ሃኪም፤ አንድ የኮንፒተር ሳይንስ ሙሁርም። ወጥ ነው። የሥልጣኔው ደረጃ ከፍ እና ዝቅ የማለት ሁኔታ ሊኖር ቢችልም እነኝህ ቅንጣት ነገሮች ናቸው። አብዩ ጉዳይ መዋቅራዊው የዕወቅት ጭብጥ ግን ተመሳሳይ እና ወጥ ነው። ወደ ፍቅር ተፈጥሮ ስንመጣ በተለምዶ ነው ፍቅርን ያህል ዓለምን የፈጠረ ክስተት እዬተመራ ያለው። ፍቅር እኮ የሰው ልጅ፤ ፍጥረታት ከመፈጠራቸው በፊት የተፈጠረ ነው። „ቃል“ እኮ ፍቅር ነው።

ሌላው ፍርድ በሚመለከት ህዝብ እኮ ፍርድ እዬሰጠ ነው። አንድም ቦታ እና ሁኔታ ስለወያኔ ሃርነት ትግራይ የ27 ዓመት ቀጥቅጠህ ግዛው ዘመን ቀጣይነት ቀርቶ አጀንዳው ያደረገ መንፈስ የለም። ለመታዬትም፤ ለመደመጥም፤ አልተቻለም። ሰው ሲጠላህ ደግሞ እግዚአብሄሩም ስለመሆኑ ማወቅ ይገባል። ይህ ቢያንስ በተከታዩ ትውልድ ላይ ቀጣይ እንዳይሆን ነው የአብይ መንፈስ እዬታተረ ያለው። ይህ መንፈስ ደግሞ የዛሬ አይደለም ከዶር ምህረት ደበበ ጋር የፈጠረት Mindset ፕሮጀክት የቆየ ነው። አሁን ያን ብሄራዊ አቅም ሰጡት። 

በፍቅር ውስጥ ዓይን ያወጣ ዓይን ያውጣ፤ እግር የቆረጠ ይቁረጥ የሚል መርህ የለም። በፍቅር ውስጥ ዓይን ያወጣው የጎደለው የአዕምሮ ብሎን አለው እና አዲስ ይገጠምለት፤ ከሰው ወደ እንሰሳው ባህሪ የተቀዬረውን ሥነ - ልቦናዊ በሽታ ወደ ሰው መልሶ ማምጣጥ ነው። ጭካኔ እኮ የእብደት በሸታ ነው። የዕብደት በሽታን ለመፈወስ ደግሞ ጊዜ ይጠይቃል። ለዛውም ተቋም የለም። ሚዲያዎች እራሱ ጠብ እና ግጭት ነው ሲያፋፍሙ ውለው የሚያድሩት። ሌላው ፈተናው እንዲህ በቀላል ከዚህ ጫካዊ መንፈስ ጋር መገለገል አይቻልም። ሁሉም ዓይነት መዋቅር የተደራጀው በዚኽው መንፈስ ነው። 27 ዓመት እኮ ቀላል አይደለም፤ ተተክለዋል። በቅለዋል። ጸድቀዋል። አስበለዋል። ከላይ አስከታች እኮ እነሱ ናቸው ትናንት ሳተናው ብራና ላይ የወጣው  የሚዲያ አውታር ትላልቅ ባለስልጣናት ብቻ ወደ 98 ይጠጋል።

ወይ ግዜ ደጉ! ህወሃት ኢቢሲ (የኢትዮጵያ ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬሽን EBC) ላያ ማለቃቀስ ጀመረች!“

ከዚህ ባለፈ በዬቦታው በሚካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ ማስቲካቸውን እያኘኩ ጎልተው በብዛት የሚታዩት ገላጮች፤ አወያዩች፤ ተንታኞች፤ በታኞች እነሱ ናቸው። ፍ/ ቤት፤ አቃቢ ህግ ዳኞች ደብዳቢዎች፤ አሳሪዎች፤ ገራፊዎች፤ ጋዳዮች፤ አሳዳጆች እነሱው ናቸው። እና ስንቱ ተከሶ? ስንቱ ተፈርዶበት ስንቱስ ቅጣት ተሰጥቶስ ይቻላል? ዘባኛው እራሱ እኮ ከሥራ አስኪያጁ በላይ ሥልጣንም፤ ተደማጭነትም አለው። ቀድሞ ነገር ለሰው ህይወት ምን ካሳ አለው? በምንስ ይወራረዳል?

በሌላ በኩል ጊዜውም አይደለም እነሱን ከላይ አስከ ታች ልቅምቅም አድርጎ ለፍርድ ለማቅረብ። ስለሆነም ጸሐፍት ጊዜውን የሚመጥን ነገር መጻፍ አለባቸው። ባለፈው ጊዜ „ስለምን በህዝብ መጓጓዣ አውሮፕላን አልተጎዙም ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የሚል አነበብኩኝ ጽፌበትምአለሁኝ፤ ከዛ የቀጠለው፤ ሰው ሰው የሚሸት መሪ ጠማኝ“ የሚል ሁሉ አንብቤያለሁኝ። መጻፍ ስለተቻለ ሁሉ አይጻፍም። ሰው ሰው ለሚለው የዛሬው አደበባይ ላይ የዋለውን ሳይሆን የቀደመውን ታሪክ በጥሞና ማጥናት ይጠይቃል። „ነፍስ ጎሳም ዜግነትም“ የላትም ማለት ምን ማለት ነው? ልጅ ለታመመባት ሰራተኛ ምን ልረዳሽ ገንዘብ አለ ብሎ ከመጠዬቅ ቆይተሽ ጠይቂኝ፤ የሐኪም ወረቀት አምጪ ማለት የተገባ ስላለመሆኑ፤ ሰው ከሌለው ትላላቅ ከተሞች ውስጥ በቀትር መሄድ አስፈሪ ስለመሆኑ፤ ሰው ጸሐይ ነው እስከ ማለት የደረሰ አምክንዮዊ ፍልስፍና እዬለ ነው ያ ጹሑፍ የተበተነው። በህዘብ አውሮፕላን መጓጋዣ መሄድ አለባቸው የሚለውም በፍጹም ሁኔታ ኢትዮጵያ ያለችበትን የፖለቲካ አጣብቂኝ፤ የሻብያ ጉዳይ የተጠና አልነበረም፤ ንድፉም ሆነ ስሜቱ የቸኮለ ነበር። ለነገሩ ጊዜ ደግ ነው ለዛ ጹሑፍ ጊዜ እራሱ መልስ እዬሰጠው ነው።

ትናንት ሥርነቀል ለውጥ ካልመጣ ብለህ ሞጥረህ ጥፈህ ዛሬ ደግሞ አብይ ደጋፊ አጣ የሚሆን አይደለም። ትናንት „ዋስተና የሌለው ቃል ብቻ ብለህ፤ አርበኛው ለንድን መግባቱ እዬታወቀ ኤርትራን ቅርቃር ከተተ ብለህ በበነገታው ደግሞ የአንዳርጋቸው መፈታት የአብይን ላይ ያለኝን መንፈስ ቀይሮታል“ ጨዋታው ወልደ ግራ ነው። ለዛውም የሞገተህን ጹሑፍ ባለው የቤተ መንግሥት ሥልጣን እንዲነሳ አስደርገህ ፈርተህው፤ ድፍረቱን አጥተህ፤ አሁን ደግሞ ተለወጥኩ በጣም በበነገታው እንዲህ ያለ ዝብርቅርቅ ያለ አቋም ያሳዝናል። ቆይተህ ደግሞ „የሚደመጠው አስፈሪ ነው።“ ያም የወያኔ ብቻ ምኞት ነቅናቂ እያለ ማን ጥሩ ይጠጣል ነው። እንደ ሸንብር ቂጣ ሲገላበጡ ውሎ ማደር።

አንድ የቀለም ውጤት ምን ያህል መንፈስ እንደሚሰበሰብ እና አንደሚበትን መጠንቀቅ ያስፈልጋል። በዬተሄደብት ሽምጥ ለመጋለብ ዕድሉ ቢኖርም ርካቡን መግቻ ያስፈልገዋል። የሰው ልጅ መንፈስ በሰዓታት መገንባት አይቻልም። ከሁሉ የሚከፋው የሰውን ልጅ ሥነ - ልቦና እንደ ጥንቸል የመሞከሪያ ጣቢያ ማድረግ ወንጀልም ነው። የተያዘውም የተረዘዘውም ይሄው ነው።

በፈለገው ሂሳብ ብዙ ፍላጎት ሊኖር ይቻላል። ብቻውን ሌት እና ቀን ከአለ አንድ የተፎካካሪ ፓርቲ ደጋፊ፤ ካለ እንዳች መጠለያና ደጋፊ ሚዲያ እዬባከነ ያለውን መንፈስ የሚወጥሩ ቅናዊ ጉዞውን መሃል ላይ የሚገትሩ እንደዚህ ልብ አንጠልጣይ እና መንፈስን ከፋይ እሳቢዎችን ለማንሳት ወቅትን ማድመጥ ያስፈልጋል። የሥርዓት ግንባታ ጢባ ጢቦ ጨዋታ አይደለም።

ስለፍቅር ደግሞ ሁሉም ሐዋርያ ነው መሆን ያለበት። ሁሉም ለፍቅር ዘብ አደር መሆን አለበት። ሁሉም ለፍቅር የደህነንት ሰረተኛ መሆን አለበት። ፍቅር እኮ ፈተና ነው። ለመቀበልም ለመስጠትም ፈተና ነው። ለማድመጥም ለመደመጠም ፈተና ነው። ማንኛችን ነን ቅናዊ እሳቤ ያለን? ቅቦች እኮ ነን። አይፈረደብንም። ፍቅርን በተለምዶ እንጂ በእውቀት በተደገፈ አልተማርነውም። ዛሬ ዓለም ስለፍትህ ሥርዓት ህግ ባትደነግግ፤ ተቋም ባትፈጥር ውላ ታድር ነበርን? ስለጸጥታዋም ሥርዓት ያለው ጠበቃ ሃይል ባታደራጅ ምን ትመስል ነበር ዓለም ራሷ። ሥርዐተ አልበኛዋ ዓለም ትሆን ነበር። 

ፍቅርም ይህን የተስተከካለ ዕውቅና ስላለገኜ ባለቤት፤ ባሊህ ባይ አካል የለውም። ፍቅር ባለቤት የሌለው የሥርዬት ርካብ መንበር ሆኖ ተፈጥሮ ግን ዓለም ከምንም ያልቆጠረችው፤ ያላቋጠረቸውም፤ አትኩሮትም ዕውቅናም፤ ተቀባይነትም ያልሰጠችው የደስታ ማህንዲስ ነበር።

ስለዚህ ከሰውኛ ተነጥለው ጎልተው የወጡ የአራዊት መንፈሶች ብቻ ሳይሆን በእያንዳንዳችን በግል፤ በሁላችንም በጋራ በሽታው አለ። ምቅኛነት አንዱ ነው። ራስ ወዳድነት ሌላው ነው። ጥላቻ አንዱ ነው። ክፉነት ሌላው ነው። ቂም አንዱ ነው። በቀል ሌላኛው ነው። ጨቋኝነት አንዱ ነው። ማን አህሎኝነት ሌላው ነው። ትዕቢት አንዱ ነው ቅናት ሌላው ነው። አሉታዊነት አንዱ ነው ማጣጣል ሌላው ነው ወዘተ ወዘተ … እራሳችን ማሸነፍ ገና አልቻልነም። ሁላችንም።

ዛሬ በዚህ አሳብ ዙሪያ የወያኔ ሃርነት ትግራይ መሪዎች ለፍርድ ይቅረቡ ሲባል የትናንቱም ይቅረብ ማለት ነው። ህዝብን እመራለሁ ብለህ ወጥተህ፤ ህዝብን እረኛ አልባ ለበላሃሳብ ጥለህ፤ ነፍስህን ማትረፍ፤ ቤተሰብህን ማዳን፤ አንተን ብሎ የደገፈህ - የረዳህ ግንባሩን የሰጠልህ ህዝብ የት ወደቀክ ያላልክ፤ መልሰህ ደግሞ በአዲስ ሥም እና ዝና ተሰዋልኝ እያልክ እዬተሰዋም፤ መጣሁልህ እያልክ ከሃላፊነት ተጠያቂነት መዳን አይቻልም። የተጠያቂነቱ ደረጃ ይለያይ እንጂ በልግመኛው ፖለቲካ በመንፈስህ ያገለልካቸው፤ የተጫንካቸው፤ አሽቀንጥርህ የጣልካቸው፤ የሳደምክባቸው ሰዎች ናቸው፤ ዜጎች ናቸው። ስለዚሀም ሁሉም ተጠያቂ ነው። 

በሁሉም ለሁሉም  የኢትዮጵያ እናቶች ዕንባ ፈሶበታል። የኢትዮጵያ እናቶ ልጆቻቻው ሲታሰሩ፤ ሲገደሉ፤ ሲደበደቡ ብቻ ሳይሆነ በስደትም ልጆቻቸው ሲገለሉ፤ ሲሳደዱ፤ ሲታደምባቸው ያለቅሳሉ ያነባሉ። እግዚኦ! ያንት ያለህ! ኤሉሄ ይላሉ!  የእኔ እናት እኔ ስለመገለሌ አሳምራ ታውቃለች፤ እኔ ፍዳዬ በግራ በቀኝ እንደጠና አሳምራ ታውቃለች ስለዚህም እኔ በሚፈታታኑኝ ክፉዎች ላይ እጃቸውን ከእኔ እንዲያነሱ አቤት ትላለች ለፈጣሪያዋ ለመዳህኒቷአለም። ስለዚህ ጉዳቱ የሥነ - ልቦና ስለሆነ ረቂቅ ነው። ጎጂው ሁሉ ለፍርድ ይቅርብ ቢባል ፈራጅም ዳኛም እራሱ ተጠያቂ የሚሆንበት ሁኔታ ሊፈጠር ነው።

ይህን በዙር ተመለስ መዳከር ለማሰቆም ደግሞ ራስን አሸንፎ መገኘት ይጠይቃል፤ ሰውን በድለህ ብድሩን መልሰህ የምታገኘው እርካታ የለም። ወደ ህዝብ መመለስ ያለበት ትልቁ እሳቤ እዬተመለሰ ነው ታላቁ ኢትዮጵያዊነት። ሲዳለን አሸንቀጥረን ማጣፊያው ሲያጥረን ደግሞ አድነኝ የምንለው። ይሄ እኛ ከመንወራከበት የአራት እግር አንጨትም ዶላርም በላይ ነው። ራስህን አጥተህ ኑረህ ራስህን የሰጠህን ብሩህ ለውጥ በፍቅር ጎልቶ ሲያወጣ ያ ነው የጥቁሮች ድል። ከምንም መሥፈርት ጋር ልታያይዘውም ልትመትረውም አይቻልህም፤ ኢትዮጵያዊነት መስፈሪያ ወቄት፤ መመዘኛ ኪሎ፤ ቁመት መለኪያ ሜትር አልተሰራለትም።

የግብጽ ፈግገታዊ ፍቅር ለሰነቀ፤ የዩጋንዳን፤ የኬንያን፤ የሱዳን፤ ሳውዲን፤ የአረብ ኢሚረቶችን ልብ ማርኮ ኢትዮጵያዊነት ከፍ ላደረገ፤ ስለነገ ትውልድ ጥሪት ለሚባትል የዘመን ጀግና በሃሳብ እዬወጠርክ መንፈሱን እያወክ ከላጊዜው የሚነሱ ጫሪ ሃሳቦች እያፈለቅክ ብትነሰት ራስህን ከመሳገመት በላይ ትርፍ የለውም። አሁን ያለው መንፈስ የሃሳብ ተጠዋሪ አይደለም። ሰከንድ አያጠፋም። ፋውል አይደለም። እድሜውን ሙሉ የተዘጋጀ ስንዱ ነው። የተባሩን ቅደም ተከተል ነድፎ፤ ጥበባዊ አንደበቱን በህሊናዊ ሰሌዳው ቀምሮ የተሰናዳ ሊቀ ጠበብት አብይ ነው።

አሁን „ኦቦ ሌንጮ ለተ እኔ አሶሳ“ አልነበርኩኝም የሚል ቃለ ምልልስ ሰጥትዋል። ድሮስ እሳቸው ቦንብ ይዘው ሄደው ሊጥሉ ኑረዋል። ድርጅታቸውን መሪ ስለሆኑ ትእዛዝ ብቻ ነው የሚሰጡት። ነፍስ በእጄ አልጠፋም ማለት አይችሉም፤ ሌለችንም መሪዎች ስታይ በዬዘመኑ አዳዲስ ፓርቲ እዬፈጠርክ በዛ ለሚያልቀው ነፍስ እኔ አልጠዬቅም ማለት አይቻልም የታሰሩ፤ አካላቸው የጎደለ የሞተው ለዛው ለወረቅት ማንፌሰቶ ነው አንተ ግን በህይወት አለህ አክተር ነህ።
  
መድረክ አቶ ገብሩ አስራትን አዲሱን ምላጭ አቶ አብርሃም ደስታን፤ ሸንጎ ዶር አረጋይ በርሄን ይዞ ነው ነገ ውድድርም ድርድርም የሚያደርገው። እርቅና ምህረት ሲባል ስንቱ ተከሶ፤ ስንቱ ተፈርዶበት ስንቱ ተገሎ ይቻላል። በኢትዮ ሱማሌ እና በኦሮምያ ግጭቱ መንስኤውና ሂደቱ አብረን አይተነዋል። የጠ/ ሚር አብይ የሸሙት ማግስት ዘንባባ ይዞ ሄዶ እራሱን ለፍቅር አዋርዶ የተበደለውን ትቶ እንደ በዳይ የተጎዱቱን በራሱ ትራንስፖርት አምጥቼ አስረክባለሁ ነው ያለው። ከዚህ ልንማር ይገባል።

  • ·        ህዝብ ፍርድ ሰጥቶበታል።

ከሁሉ በላይ ዓይናቸውንም ድምጻቸውንም ሰው ማድመጥ አይፈልግም የወያኔ ሃርነት ትግራይ ማህበርተኞችን። ከዚህ በላይ ዳኝነት የለም። ሊያህ ባልፈቀደ፤ ሊያደምጥህ ባልፈቀደ ህዝብ ማህል ለመኖር መወሰን እራሱ ዕብንነት ነው። ስውር ቦንብ ነው ይሄ እራሱ። እነሱ ከነምስላቸው ሲመጡ አቅም ኑሮት የሚያዳምጣቸው የትኛው ዜጋ ነው? ሂድልኝ፤ ልቀቀኝ፤ በቃህኝ፤ ላይህ አልፈቅድም፤ ጠልቸሃለሁኝ በጣም ከባድ እኮ ነው። ላዛወም እኮ ምልዕት እኮ ነው። ዓለምም አሁን ከሆነ የሚለው ይሄው ነው። የኬንያ ሚዲያ እኮ እንዴት አድርጎ አበጥሮ አንተርትሮ እንደተዋዬበት። በመጨረሻም ያለው እንጸልይለት ለአብይ ነው ያለው።

https://www.youtube.com/watch?v=BFEWVI4r9TI
የወያኔ ሃርነት ትግራይ ጥቁር የሆነ ታሪክ ከነጠባሳው ህዝብ ፊት በመንሳት ብይኑን ሰጥቶታል። ቀጣዩ ሥራ ይህ ሁኔታ እናዳይቀጥል ውርስ እና ቅርስ እንዳይሆን መትጋት ነው። ማግሥታውያኑ እዬሠሩ ያሉት ይሄንኑ ነው። እነሱ እኮ ዘመናቸውም አልቋል። በምርኩዝ ነው የሚሄዱት። ልዛውም የሚኖሩት በፍርሃት እዬተንዘፈዘፉ ነው።  
በሌላ በኩል መሪነት የገበጣ ጨዋታ አይደለም። ስለትም ጥበብም ይጠይቃል። የሚነኩ ነገሮች ይኖራሉ። በስልት ራቅ ብሎው እንዲቆዩ የሚደረጉ ነገሮች ይኖራሉ። በጥንቃቄ መያዝ ያለባቸው አምክንዮዎች ይኖራሉ። ጭራሽ የማይነኩ ነገሮች ደግሞ ይኖራሉ። ይህ ለአንድ ጥበበኛ መሪ ክህሎቱ ነው። የክቡር ጠ/ ሚር ዶር አብይ አህመድ ጥልቅነታቸውም ከዚህ ነው የሚመነጨው። ግልብ ፖለቲከኞች ይጣደፉበት፤ የፈለጋቸውን ቀለም ይለቅልቁት ለለማ አብይ መንፈስ ግን ግጥሙ አይደለም ጥላቻም ሆነ ዘመን ሰጠኝ ብሎ ሌላውን ማሳደድ።
  • ·        ክወና።

ትውልዳዊ ድርሻ በበቀለ ቁርሾ መጀመር የለበትም። ትውልዳዊ ድርሻ ከራስ በላይ በሆነ ከፍ ባለ የሃሳብ ልቅና መመራት አለበት። ትውልዳዊ ድርሻ ኮንደምንዬም ቤት አይደለም። ዛሬ ገንብተኸው ነገ የሚናድ። ትውልዳዊ ድርሻ ሰው በሙሉ ሰብዕና ተቀርፆ ትወልድ የሚቀጥልበትን ታሪካዊ አደራ የሚረከብ የቃል ኪዳን ሰማይ ነው። ሰው እኮ ከገብያ ተሂዶ አይሸመትም አይቀነም። የሰው ልጅ ርካሽና ውድ የለውም። ሰው ቅዱስ ፍጡር ነው። ቅዱሱን ፍጡር ለመምራት ከቅድጽና ጸረ ሃሳቦች ጋር መፋታትን ይጠይቃል። ግን አብይን የመሰለ ጀግና ከተገኘ ነው።

ኢትዮጵያዊነት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር።

የኔዎቹ እጅግ አድርጌ አከብራችሁ አለሁኝ። ማን? እኔ ሎሊያችሁ ሥርጉተ ሥላሴ። ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ።  

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።