የሥልጣኔ ድንጋጌ ጥሩ ዜና በበተልሄም ብሥራት ሲሰክን!
የማግስት ብሥራት ድንጋጌ ናት የፈጠራ ባለቤቷ ወጣት ቤተልሄም ደሴ።
„ሁሉም በመቅደሱ ምስጋና ይላል።“
መዝሙር ፳፰ ቁጥር ፱
ከሥርጉተ©ሥላሴ
19.10.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።፡
ማስተዋሏ የበረከተ ነው። ቅኝቷ ለምለማዊ ነው። እረቀቷ እዬራዊ ነው። በዓላማው ውስጥ ከዕድሜዋ በላይ የሚጠይቀውን ትዕግስት ተጎናጽፋ በአማኑኤል ተሰጥቷትም ሐሤትን በተሟላ ተስፋ በገፍ አጋርታናለች። ብርክታዊት!
ለኢትዮጵያ አገሬ ሽልማትም ናት። እሷም ደስተኛ ናት። እውነት በማይመስሉ የኮንፒተር ሳይንስ ፍልስፍናዎች እና ውጤቶች ተሰማርታ ስኬታማ ሆናለች። ዕድሜዋን ሳያስቡ ተግባሯን ብቻ ማሰቡ ብቻ ይሻላል።
ዕድሜዋን አስበው የህይወት ጊዜዋን ሲያስተውሉ ልበወለድ ስለሚመስል። „ለእግዚአንሄር ግን የሚሳነው የለም“ ማለቱ ለአማንያን ታምራቱን ያይ ዘንድ የሆነው ሁሉ እንዲህም ሆነው።
ብሩሕ ቢዥነር ናት። እማጅነሽኗ እርቀቱ ይገርማል። የምትገርም ዕንቡጥ ቀንበጥ ፈላስፋ ወጣት ናት። ለ21ኛው ምዕት የተፈቀደላት ባለመክሊት ናት። እውነትም ቤተልሄም የዬምስራች ዓውደ ምህረት የሥልጣኔም ጥሩ ዜና።
የሚገርመው በዚህ ዕድሜዋ ልዑል እግዚአብሄር እኛን የሰጠበት ሚስጥር ደርሳበታለች። አትጨናነቅም፤ መጨናናቅንም አጀንዳዋ አለደረገችውም። ብሩሁን ጭንቅላቷን ማበከን አትፈቅድም እና። ጊዜዋን ባልባሌ ጉዳያዎች አታሳልፈም። ጌዜ ወርቅ ነው ገቢር ላይ ውሏል።
ደስታ ተስጥዖችን ስለመሆኑ እዬኖረችበት ነው። ህይወትን ቀለል ዘና አድርጎ መኖርንም በዚህ ዕድሜዋ ታስተምረናለች። ፍልቅልቅ ያለች፤ ቀለል ያለች ቁጥብ ወጣት ብርሃን ጠገብ ወጣት ናት።
የተስፋ ውሃ ልክ ንጥረ ነገር እርጋታዋ የችግር መፍቻ በእጇ ስላለ ብቻ ሳይሆን ኢማጅኔሽኗ ጥልቅ በመሆኑ ደረጃውን ጠብቆ ሂደት መፍቻውን ያመጣል ብላ ያመነች ትመስላለች።
እርጋታዋ እኮ የከ40 እስከ 50 ዓመት ያህል ሰው ነው የምትመስለው። እርግጥኝነቷ፤ በራስ የመተማመን አቅሟ እራሷን የምተገልጥበት መንገዷ፤ የነፍስ ፍልስፍናዎቿ፤ የአትኩሮት አቅጣጨዋቿ ከዓይን ያውጣት ነው እንጂ ሌላ የሚባለው ነገር የለም።
የክህሎት ልቅናው የተሰጣት ስለመሆኑ እሷም እራሷ ስጦታዋን አምናዋለች፤ ለዚህም ነው ብሩህ የሥልጣኔ አዋታር በአገሯ በኢትዮጵያም በአፍሪካም ለመዝርጋት ሁለገብ ትጋቷ ከብረት ቁርጥራጭ የተሰራ ብርቱ የሆነው። ሉላዊነቷን ስተቀበለው በመሆን ውስጥ ተግባራው ነው።
እኔ ለዚህ ነበር ወላጆች ልጆቻቸውን እንዴት ያሳድጋሉ የሚለውን የተስፋ በር መጸሐፍ የጻፍኩት። ህልመኛ ልጆች በህልማቸው ውስጥ ይኖሩ ዘንድ ለዛም ይታገዙ ዘንድ ነበር ያን መጸሐፍ የጻፍኩት።
አብሶ ትልቁ ቀውስ የትውልድ ክፍትተ በመሆኑ ይህን ለማቀራረብ አስቤ ነበር እጅግም ደክሜ የሠራሁት የተስፋ በር መጸሐፌን። ግን አገርም አጋቾች ከዚህም አጋቾች ተበራከቱ እና ከጥቂት ሰዎች አልፎ ለሁሉም ሊደርስ አልቻለም። መጽሐፉ ራሱ ትልቅ ፕሮጀክቴ ነበር በአዲሱ ትውልድ ቀረጻ ላይ። ግን ስቶር ያሞቃል።
እግዚአብሄርን አማመሰገንው የዚህች ልበ ብርሃን ወጣት ቤተልሄም ደሴ ህልም በልጆች ብሩህ የፈጠራ ሥራ ላይ ማተኮር ስለሆነ እኩሌታ ጭንቀቴን ተጋርታልኛለች ብዬ ስለማስብ እንኳን የእኔ ልዕልት ተፈጠርሽልኝ ልበላት በትህትና ከፈቀደችልኝ።
የማያልቀው ተቀድቶ፤ የማይደረቀው ፈልቆ፤ ዘወትር የሚያሽተው እዮራዊ ጸጋ እንዲህ ነው። ዘና ብላ ለሚቀርብላት ጥያቄ ሁሉ በሙሉ ዕድሜ እንዳለ አንድ ጎልማሳ ትመልሳለች። የእሷ ያልሆነውን የባለቤትነት ጉዳይ ላበለ ቤቱ ትሰጣለች። ውስጧ ፍጹም ሰላም አለው።
እራሷን አኮፍሳ አልቀረበችም። እንደ አልባሌ ወጣት፤ እንደ ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ወጣት ነው አለባባሷ እራሱ። መቼስ ምን ልበላት? ማንስ ብዬ ልጥራት? ትምህርተ ቤተልሄም ልባላትን ከቶ? ወይንስ ሥነ - ህይወት ቤተልሄም? ወይንስ ሥልጣኔ ተስከነት ልበላት?
እኔ እንደ ሥርጉተ የመሰጠኝ ሰብዕናዋ የተገነባበት ሁነት ነው። ሰብዕናዋ ተነባቢ ነው። ሰብዕናው አቅራቢ ነው። ሰብዕናዋ ተስፋ በቀጣዩ ትውልድ ላይ እንዲኖረን ያደርጋል። እኔ ውድድድድ አደረግኳት።
ጉልበተኞች ቢያጨናግፉብኝ ትልቁ ፕሮጀክቴ በልጆች ላይ መሥራት ነበር። እንዲህ ሆነው ልጆች ባልጠብቀኩት ሁኔታ በቅለው ጸደቀው ሰብለው ማዬት የአስችሉ መረጃዎችን ማግኘት ለማግሥት እረፍት ይሰጣል እንኳንስ ለሰው ልጅ።
ከሁሉ በላይ ወላጆቿ ያደረጉላት እንክብካቤ በላይ እኔ እማደንቀው ትልቁ ሥጦታ ወላጆቿ በጸጋዋ ውስጥ ሳያጨናንቋት እንድትኖር መፍቀዳቸው ብቻ ሳይሆን የጸጋዎቿ አባል ሆነው ለመመዝገብ መፈቀዳቸው ነው። ፍቅርንም ሰልመገቧት ነው።
ይህን ሁሉም ልጅ የማያገኘው ጥቂት ቤተሰቦች ብቻ የሚፈቅዱት ጉዳይ ነው።
አሁን ከዚህ ሲዊዝ አንድ ልጅ ትምህርቱን ሳይጨርስ በአንድ ሙያ ሳይመረቅ የጎንዮሽ ስጦታ ነገር ብሎ የለም። የሲዊዝ ልጅ የመጀመሪያ ተልዕኮው ተምሮ የሙያ ባለቤት መሆን ነው። ከትምህርት በኋዋላ ይደርሳል ባዮች ናቸው ሲዊዞች።
በሌላ በኩል መክሊት በሚባለውም ነገር ላይ ያላቸው አድናቆት ለሌላው ማናቸውም ማህበራዊ፤ ፓለቲካዊ ኢኮኖሚያዊ ድንገቴ ብልጽግናዎች አድናቆት በልክ የመያዝ ጸጋ ነው ያላቸው።
ዲታው ባለሃብት እና ዘበኛው፤ ዲታው እና ስደተኛው በአለባባስ ብዙም አይለዩም። ዲታዎች ከእኛ ጋር እዬተጋፉ በአውቶብስ በባቡር ይሄዳሉ።
ሲዊዞች ተፈጥሯቸው መጥኖ የመኖር ዓይነት ይመስለኛል። መቼም ሲዊዘርላንድ በተቋም ገብቶ ከሚገኘው ዕውቀት በላይ ህይወትን የተረጎሙበት መስመር ይመስጣል። ሳገኛቸው ውስጣቸው ምን እንደሚል ምርምራ እገባለሁኝ። ልዩ ተፈጥሮ ነው ያላቸው - መምህሮች።
አሁን ብዙ ጊዜ ልዩ ልዩ ስጦታ ያላቸው ልጆች ሄደው የሚወዳደሩት ጀርመን ነው። ጀርመንም ዕድሉን ሳይነፍግ ተወዳድረው አሸናፊ ለሚሆኑ ስጦታቸውን ያበለጽገዋል፤ ዕወቅናውን ያጎላዋል፤ የሲዊዝ ልጆች አቆርጠው ይህን ዕድል ሲያገኙ ወዲያውኑ ገንዘቡ፤ ዝናው ሳያታልላቸው መደበኛ ትምህርታቸውን እንዲቀጥሉ ቤተሰብ ጫና ያደርጋል።
ይህ እንግዲህ በሰለጠነው ዓለም ዕይታ ነው … ባላደጉ አገሮች ሲመዘን በውነቱ ቤትሻ ዕድለኛም ናት። እንደዚህ መሰል ዘመናይ ሥልጡን ወላጆች ያላት መሆኑ ብቻ እንደ ፈቃዷ ሊኖሩ የፈቀዱ ወላጆች ያላት በመሆኑ ብቻ አዶናይ ይመስገን። የሐረር ልጅ መሆና ደግሞ ህይወትን ቀለል አድርጋ እንድታይ አደርጓታል።
በሌላ በኩል በኢትዮጵያ መንግሥት በኩል ሆነ በአማራ ክልላዊ መንግሥት የተደረገላት እንክብካቤ እና የተሰጣት ዕወቅናም በውነቱ አንቱ ነው። እኔ ከጠበቅኩት በላይ ነው።
አንዲት የ10 ዓመት ልጅ አገራዊ ህልውናን ከሚወስን ኢንሳ ድርጅት በቅጥር መቀበል፤ በተለያዩ ሁኔታዎች በመምህርነት ዕድሉን እንድትጠቀም የተደረገላት ማበረታቻ፤ የተከፈተላት ቧ ፏ ያለ በር፤ የተሰጣት ዕውቅና፤ የተደረገላት ክትትል እና ልዩ አትኩሮት በውነቱ እጅግ ያስመሰግናል።
ምን አልባት ጠ/ሚር አብይ አህመድ ጋር አብራ በመስራቷም ይሆናል ጠ/ሚር አብይ አህመድ ወደ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚ/ር ሲዛወሩ ባገኙት ዕድል ይህን መሰል ፕሮጀክት የህሊናቸው ባለሟል የሆነው።
ዶር አብይ አህመድ በ10 ዓመቷ የሳቸው ባለደረባ የሆነችው ባለብሩህ አዕምሩ ባለጸጋ ልጅ በማዬታቸው ይህን አስፍተው እንደ ፕሮጀክት በሳይንስ እና በቴክኖሎጂ ሚ/ር በኽረ ትኩረት ለመስጠት ከቤትሻ ጋር መሥራታቸው አስተዋፆ አበርክቷል ብዬም አስባለሁኝ።
እሷም ዕድለኛ ናት በ10 አመቷ የወደፊት ጠ/ሚር ከሚሆን አንድ ብልህ እና ጥበበኛ ብልህ መሪ ጋር ለመስራት ልዑል እግዚአብሄር ስለ አመቻቸላት። ዛሬ ንጹሃን ቅኖች የት እናግኘው የሚለው ሙሴ ትናንት የእሷ የሥራ ባልደረባ አለቃም የሆነ ነው።
ለዶር አብይ አህመድ ቅናዊ ብሩህ በጎ ህልምም እንቡጧ ልዕልት የመንፈስ ማዳበሪያ ሆናለቸው ብዬ አስባለሁኝ።
አሁን ውዷ ቤተልሄም ደሴን ሳስብ ዶር አብይ አህመድ በዚህ ዕድሜያቸው ያላቸውን ልዩ ክህሎት አላዛሯ ኢትዮጵያ ለመጠቀም ጓጉታ ግን እክል ሲበዛባት ሳይ ተንከባካቢ አጥተው ደርቀው እንደቀሩት ኢትዮጵያዊ ፈላስፎች አያቸዋለሁኝ።
እሳቸውን ሳስብ ፈላስማ ዘረያዕቆብን አስታውሰዋለሁኝ። ካለዘመኑ የተፈጠረ ሰው ካለፈ በኋዋላ ነው አስተዋሽ ለዛውም ካገኜ።
ቤቲን ፍጹም ዕድለኛ የሚያደርጋት ግን ጸጋዋን፤ ክህሎቷን፤ ፈጠራዋን የምታውለበት ምቹ የአይዞሽ ባይ ሰፊ ማሳ አላት። እንግዲህ እያደገች ስትሄድ የቅናት አርበኞች ሌላ ሳንክ ካልፈጠሩባት በሙያዋ ለመቀጠል ባላት ህልም ብዙ ወጣቶችን ኮትኩታ 21ኛው ምዕተ ዓመት እና በሚገርም ፍጥንት በመብቀል ላይ ያለውን አዲሱን ቡቃዬ ታሰብላለች ብዬ አስባለሁኝ። ዕንቁ ናት። ቅኔ ናት። ድንጋጌም ናት። ዕድሜዋን ፈጣሪ ያርዝመው። ታሳሳለች።
በዚህ አጋጣሚ ፖለቲካ እና ኤልትሪክ በሩቁ ብሎ የሰነበተው አንድአፍታ ቱብ ዛሬ ይህን መረጃ ስላቀበልን እጅግ አድርጌ አመሰግነዋለሁኝ።
ቀደም ባሉት ወራት ፈጣን መረጃዎች በመመገብ የሚታወቀው አንድአፍታ አሁን ተቀላቢዎችን ረሳ አድርጎን በራህብ ቸነፈር አሰናባብቶን ነበር። እርግጥ ነው በጥበብ ዙሪያ አያለሁ የሚያወጣቸው ነገር ግን ከፖለቲካዊ ሁኔታዎች ራሱን ገለል ያደረገ ይመስላል።
የሆነ ሆኖ ዛሬ ባመጣው መረጃ ጥሩ ነው ለእኛ። እጅግ በጣም ተጉድተናል። ተስፋ ሲበቅል ሲከስል፤ ተስፋ ሲያቆጠቁጥ ሲያር፤ ደስታ መጣ ሲባል በቅጽበት ዶዝ ሙሉ ጭንቅ እና ዕንባ ስናስተናግድ ነው ያሳለፍነው፤ እና ይህን መሰል የህይወት ንጥረ ነገረም ያስፈልጋል ብሎ ለሰጠን ውብ ጊዜ አንድአፍታን አመስግናለሁኝ።
ይህችን ውብ የወለዷትን ወላጆቿን፤ ከዚህ እንድትደርስ ያገዟትን አካላት እና ኢትዮጵውያን ሆኑ የውጭ ዜጎች የሰጧት ብርታት እና ጥንካሬ እኔ በውስጤ ያለውን የምሻውን ስለሆነ የፈጸሙት ዝቅ ብዬ አመሰግናቸዋለሁኝ። ውጤቱ ተስፋው የሁላችንም ነው። ደስታውም እንዲሁ የጋራ ነው።
ልዑል እግዚአብሄር ከህልሟ፤ ከትልሟ በለለጠ ሁኔታ ያደርሳት ዘንድም ጤንቷን ይጠብቅላት ዘንድም ፈጣሪዬን እለምነዋለሁኝ። ድንግልዬም ትጠብቃት። አሜን!
እሷም ጠንቃቃ መሆንን መልመድ ይኖርበታል። አሁን በተሳከ መንገድ ነው እዬተጓዘች ያለው። ግን ከመጣችበት ጉዞ ይልቅ የፊተኛው ረጅም ስለሆነ ምንጊዜም ለህይወቷ ጠንቃቃ የመሆን መርህ ቢኖራትምለ ይህችን የአፍላ ዕድሜ እርከን እስክታልፍ ድረስ ከበፊተኛው የበለጠ ብልህነት እና ጥበብ ያስፈልጋታል እና መዝሙረ ዳዊትን ስንቅ ማድረግ ይገባታል ብዬ አስባለሁኝ።
በተረፈ ህልም እንጂ ዕውነት የማይመስል በታሪክ እንደምንሰማው ታሪክን ዛሬ ማድመጤ አዲስ የመተንፈሻ አዬር አግኝቻለሁኝ።
የልጆች ጉዳይ አጀንዳዬ ስለሆነ በሌሎች አገሮች የማዬው ጸጋ እና በረከት አገሬ ኢትዮጵያ ስለገኘች እንደ ዜጋ እኔም ደስ ብሎኛል። ተመስገንም ብያለሁኝ።
https://www.youtube.com/watch?v=A5gJTk92SvsEthiopi
አለምን እያነጋገረች ያለችው የአፍሪካዋ የሶፍትዌር ንግስት-ቤቴልሄም ደሴ!!
ሉዑል እግዚአብሄር ፈጣሪ በሰጠን ሥጦታ እንጠቀም ዘንድ ልብ ይስጠን። አሜን!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ