መሻገር እና መሸጋገር የአምክንዮ ልዩነት አላቸው።

ስንፈጠር 
መቻልም መቻቻልም ተሰጥቶናል።


„በግዞትም ቤት አደባባይ ታሥሮ ሳለ የእግዚአብሄር ቃል እንዲህ ሲል  ወደ ኤርምያስ መጣ፣--- ሂድ ለኢትዮጵያዊው አበሜሌክ እንዲህ በለው፣-  የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፣--- እንሆ ለበጎነት ሳይሆን ለክፋት ቃሌን በዚህች ከተማ ላይ አመጣለሁ፤ በዚያን ቀን በፊትህ ይፈጸማል። በዚያ ቀን አድንሃለሁ ይላል፤ እግዚአብሄርም በምትፈራቸው ሰዎች እጅ አልሰጥህም። ፈጽሜ አድንሃለሁ፤ ነፍስህም እንደ ምርኮ ትሆንልሃለች አንጂ በሰይፍ አትወደቅም፣ በእኔ ታምነሃልና ፣ ይላል እግዚአብሄር። (ትንቢተ ኤርምያስ ምዕራፍ  ፴፱ ከቁጥር ፲፭ እስከ ፲፰)
ከሥርጉተ ሥላሴ 31.07.2018
(ከገዳማዊቷ የደም ገንቦዋ ሲዊዝሻ።)
  • ·       እፍታ።

አሁን ያለው ሁኔታ መሻገሪ እንጂ መሻገር አድርገው የሚመለከቱት ወገኖቼ አሉ። 

ውዶቼ እንዴት ናችሁ? ስለደከመኝ አሳደርኩትኝ። በፈለገ ሁኔታ ቢሆን የሚኒያፖሊስን የስብሰባ ድባብ ሳላዳምጥ አልተኛም ብዬ እሰከ እኩለ ሌሊት ቆዬሁኝ። ቅድመ መሰናዶው መስፍኔ ፈይሳ እንደ ዲሲዊ ሲያስቃኘኝ ቆዬ። ያዘንኩት ግን ለታታሪው የእርቅ ጌታ ለመስፍኔ ፈይሳ ቅድሚያ አለመሰጠቱ ነበር። የሚገርመው ትንሳኤዋን ልዕልት ልጁን ይዞ ነበር ሲንገላታ ያዬሁት። ልጅ የያዙ፤ ጤናቸው የጎደለ ደካሞች፤ ነፍሰጡሮችን በሚመለከት ቅድሚያ ሊሰጣቸው ይገባ ነበር፤ በዚህ ዘርፍ የዲሲውን አድንቄያለሁኝ።

አዛጋጆች ከOMN ጋር የቅድምያ ቃለ ምልልስ በኦሮምኛ እና በአማርኛ አድርገው ነበር። ምቾት የሚሰጥ አልነበርም። በበዛ ሁኔታ የመነጠል ተደሞ ነበረበት። በዚህ በመነጠል መንፈስ ዘመናት ተቆጠሩ የተረፈ የለም። ጀርመን የአውሮፓ ህሊና የሆነው የበርሊን ግንብ በማፈረሱ ምክንያት ነበር። ስለዚህ እያንዳንዱ የኦሮሞ ልጅ ወገኖቹን ይቅርታ የሚጠይቅበት ጊዜ አሁን ነበር። እንኳንስ በነበረው መንፈስ መጪ … የመርህ እና የሰውነት ነገር ተደባልቋል - ለእኔ።

ፆታ፤ ሃይማኖት፤ ዕድሜ፤ የዕውቀት ደረጃ ሳይለይ ነበር የለማ ቡድን በንጹህ ልቡ የኢትዮጵያ ህዝብ የተቀበለው፤ በንጹህናውም ደሙን የገበረው። አካሉን ያጣበት። ልጆቹን ያጣበት። ይሄ ዘመን የኦሮሞ ልጆች ያላስተማራቸው የትኛው ዘመን ሊያስተምራቸው እንደሚችል ይገርመኛል። ዬትኛውም የአፍሪካ ወገኖቻቸው ለእነሱ አይቀርቡም፤ በመከራም በሃዘንም ያለነው እኛው ኢትዮጰውያን ነበርን።

የዝግጅቱ መቅድም በነበረው ጊዜ የነበረው የእልህ እና የተነጠለ ራስን አንግሦ የመውጣት ንቅናቄ ነው የምለው ጤነኛ አልነበረም። እኔ የፖለቲካ አደራጅ ባለሙያ ባልሆን ኖሮ ለታዳሚ፤ በቅርብም በሩቅም ለሚከታተል ፈተኝ ነበር ማለት እችላለሁኝ። መቼም አብይ እና ለማ ሆኖበት እንጂ ከዛ የነበረው ህዝብ ጥሎ ይወጣም ነበር። „ቄሮ“ ብቻ  ነበር የሚያነግሰው፤ የሚወደሰው በቄሮ ብቻ ድል እንደተገኘ ነበር ሲዘከር የነበረው።

ብአዴን አንዲት ድምጽ ቢነፍግ እዚህ እንደማይደረስ አልገባቸውም። „የኦሮሞ ደም ደሜ ነው“ ብሎ በጎንደር፤ በባህርዳር፤ በአንባ ጊዮርጊስ፤ በደብረታቦት፤ በማርቆስ፤ በዳባት፤ በዳንግላ  የፈሰሰው የንጹሃን ደም፤ ከዚህም ባሻገር 20ሺህ ወጣት ብር ሸለቆ በርሃ ላይ አሳሩን ያዬው፤ ይህን ቀን ያመጣል ተብሎ ስለታሰበ ነበር ያን ፍዳ የተቀበለው። „ጣና ኬኛ፤ ግዮን ኬኛ“ አማራ ባይቀበልም ይህ ድል ምንም ነበር። የትም አይደርስም ነበር። የትግራይ ልጆች እኮ ጎንደር ሄደው ነበር።

ሌላው አማርኛም ጠላት አይደለም ዶር ለማ መገርሳ  አማርኛ ቋንቋ ባይናገሩ ይህ ሁሉ ሚሊዮን መንፈስ ከጎናቸው ባልቆመ ነበር፤ ዶር አብይ አህመድም ሆኖ ዶር. ለማ መገርሳ በኦሮምኛ የተናገሩትን አርኬቡ ላይ ግቡ እና እዩት ….  የታዳሚውን መጠን።

የኢትዮጵያም ህዝብ ጠላት አይደለም፤ አማራም ጠላት አይደለም። ዛሬ በብዙ ሺህ ስበሳባው ላይ ወጥቶ የተገኘው ህዝብ የኦሮሞ ልጅ ያን ጊዜ የለማን ቡድን አልደገፈም። የደግፈን ሌት እና ቀን እኛ ነበርን ፍዳችን የከፈልነው፤ ሳተናው ሌት እና ቀን  ነበር ጠጋው፤ የራዳን ሌላ ሚዲያ ከቶውንም አልነበረም።  የ ኦሮሞ ልጅ  ከነሚዲያው ከዚህ መንፈስ ጋር አልነበራችሁም። 

ማተብ ከኖራቸው የለማ መንፈስ እና የአብይ መንፈስ ይህን ቢመዝኑት መልካም ይመስለኛል። ይህ በታዬው ነው ባልታዬው መድረክ ላይ ደግሞ እጅግ ብዙ ተግባራት ተከውኗል። ለምሳሌ ውጩ ባለው ቅዱስ ሲኖዶስ መንፈሱን እንዲደግፍ፤ አድማጭ ለሆኑ ለውጭ መንግሥታት እገዛ እንዲያደርጉ የደከሙት አማራዎች ናቸው። ግልጥ ያልወጡ የሎቢ ሥራዎች ተሠርተዋል። 

እጅግ ብዙ መጠነ ሰፊ ሥራ ተሰርቷል። ኔት በመፍጠር፤ የቅኖች ጋላሪ በመዘርጋት። የ ኦሮሞ ወገኖቼ ከሊቅ አስከ ደቂቅ ኦህዴድን ጨምሮ ዘመን ሊያስተመራችሁ ካልቻለ ነገም ያው ነው። አብረህ ሞተህ በመዳን ቀን እንኳን ያን ገፍታችሁ በራሳችሁ ጎራ ባጅታችሁ አሁን ቅን ኢትዮጵውያን እንደግፋለን ብለው ሲነሱ የፉክክር ዝግጀት ነበር የሆነው ሁሉ። ህሊና ላለው ሚስጢሩ ይኸው ነው።
  • እንግዶች እና ንግግራቸው።

ንግግሩን ያዳመጥኩት የዶር ለማ መገርሳ በወኔ የተሞላ ነበር። ያን ዓይነት የንግግር መንፈስ አንቦ ላይም፤ ባሌ ላይም አይቼ አላውቅም። የዶር አብይ አህመድ ደግሞ ማዕከላዊ ለመሆን የጣረ ነበር። ላይፍ ላይ አስተያዬት ይሰጥ ነበር። ምድር ቀውጢ ነው የሆነችው። ነፍስ ከእሳት ተጥዳ በጠራራ ጸሐይ በርዕሰ ከተማዋ ላይ ደም እዬፈሰሰ፤ ነፍሱጡር እናት አደባባይ ላይ በባሩድ እዬነደደች፤ ስለነገ የምናውቀው ነገር የሌለን ምንዱባን ያን ያህል ሰይበር ላይ ጦርነት ማድረግ ሰው ስለመሆናችን ያጠያይቅ ነበር።

አውሮፕላኑ ሉዕካኑን ይዞ ወደ ኢትዮጵያ ሲጓዝ አዬር ላይም ምን ሊፈጠር እንደሚችል አላገናዘብነውም። በዚህች ቅጽበት ምን እንደሚፈጠር የማናውቅ የፈጣሪ ፍጡራን ኦሮምኛ ቋንቋ ተነገረ ተብሎ ያን ያህል ቀውጢ ሲሆን ሳይ እኛ ከምን እንደምንመደብ ይጨንቃኛል። እኔ ዝም ብዬ ነበር የማለቅሰው። እርግጥ ሳይበሩን ለማረጋጋት ሞክሬ ተሳክቶልኛ። እሺ የሚሉ ከሁለቱም ወገን ታዳሚዎች ነበሩ። 

እነኛን ፍቅሮች በዚህ አጋጣሚ አመሰግናቸዋለሁኝ። እንዲህ መንፈስን የሚገራ አረጋጊ ጠፍቶ ወይንም በሩ ተዘግቶበት እንጂ ከዚህ የሚያደርስ ምንም ነገር አልነበረም። አሁን እራሱ የተሸነፉ መንፈሶች አብረው ቀድመው ፕሮ ሆነው ለትዝበት ከሚዳረጉ መድረኩ ቢኖር ሚዛናዊ ማድረግ በተቻለ ነበር። ጭራሽም ከአብይ መንፈስ ጋር መንፈሳቸውን ማስጠጋት የማይሹ መንፈሶችን ሁሉ አይቻለሁኝ።
  • ·       ማማከል፤

ዛሬ ጥዋት የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ተሽሎት ከሁሉም የሚደያ ዓይነት ተሽሎ ከፕሮፖጋንዳ የጸዳ ንጹህ ዜና ያቀርብ ነበር። ዜናው የትናንት ነው። ራማ መረብ ላይ ያለች አዋሳኝ ከተማ ናት። ከመረብ ወዲያ እና ወዲህ ያሉ ህፃናት አብረው ያድጉና 18 ዓመት ሲሞላቸው እንዳይገናኙ ይደረግ ነበር አለን ጋዜጠኛ ሰመረ እንደ ዘገበው። እንባዬን መቆጠጠር አልቻልኩም። በእኛ ሃጢያት ልጆች ታመሱ። በሁሉቱም አዋሳኝ ያሉ ህዝቦች አቧራ የለበሱ ናቸው። እሚያስቀና ኑሮ የላቸውም። እጅግ ያሳዝናሉ፤ በድህነት እዬኖሩ ግን ፈቃዳቸው፤ ሳቃቸው፤ ደስታቸው ተነጥቆ በስጋት።

ለዚህች ለድንኳን ኑሮ፤ ከሦስት ቀን ህልፈት በኋዋላ ሥጋችን አያስቀርብም ይሸታል? ይህን ፈራሽ ሥጋ ተሸከምን ፈጣሪ በሰራው ፍጡር ላይ ለኩንትራት ዕድሜው ይህን ያህል የፈተና መረብ ዘርግተን ስናመሰው ኖርን።

ማጂ፤ በባቢሌ፤ በጉጂ፤ በገዲኦ በጠረፍ አካበባ የሚኖሩ ወገኖች አፍር ለብሰው ይህም ተቀንቶባቸው በፈረሰው ኑሯቸው እንኳን እንዲኖሩ አልተፈቀደላቸውም። ይህን የተሸከመ ህዝብ ኦሮምኛ ቋንቋ ተነገረ ብሎ ያብዳል ይጦፋል። ሌላው ደግሞ አሮምኛ ተነገረልኝ ብሎ እልልታውን ያቀልጣል፤ በለማ በአብይ ላይ ደግሞ ናዳ ይወርዳል። አሳፋሪነት።

ከኦሮሞ ጋር ያልተጋባ፤ የልተጎራበት፤ ጓደኝነት ያልገጠመ፤ በሥራ የማያገናኝ ማን አለና? አለን? ከአማራ ጋርስ ቢሆን? ኢትዮጵያ ግን የማን ናት? ኢትዮጵያ የአፋርኛው፤ የኢትዮ ሱማሌውኛው፤ የአደሬኛው፤ የሲዳማኛው፤ የወላይታኛው፤ የትግሬኛው፤ የአማርኛ የጉራጌኛው የከንባታኛው፤ የኮንሶኛው፤ የሃድያኛው፤ የኩናማኛ ወዘተ ቋንቋ አገር አይደለችንም? ማን ሰጪ ማን ነሺ አለና? ማነው ባለመብቱ? ማነው ባለድርሻው? ይህ የቋንቋ ሃብታት የሁላችን አይደለምን?

እስልምና ክርስትና ዋቄፈታ የእኛ አይደሉንም። ከዚህ ዕምነት ውጪ ያሉትስ ወገኖቻችን አይደሉንም። የፈለገውን ቋንቋ ይናገሩ … ቋንቋው፤ ቅርሱ፤ ትውፊቱ፤ ታሪኩ፤ ትሩፋቱ የሁላችን አይደለምን? አማርኛ ቋንቋ የ ኦሮሞ አንጡራ ሃብቱ አይደለምን? አዱኛው አይደለምን? ከቶ አይኮራበትንም በዚህ ቋንቋዊ ሉላዊነት? እናስተውል። ክብረታችን በመጣላችን እኮ ነው ፈጣሪ የቀጣን። 

እኔ ቁራን በግዕዝ ይቀራ እያልኩ እኮ ነው … የ እስልምና ሊቂሃቃን የቀረባቸው ጥልቅ የፍለስፍና ዓውድ አለ እአልኩ እኮ ነው እነ ወጣት ኡስታዝ አህመዲን ጀብልን። ጀርመንን የፈጠረው እኮ እጬጌው ግዕዝ ነው። ግዕዝ የኦሮሞ አይደለምን? ግዕዝ የ አፋር አይደለምን? ግዕዝ የወላይታ አይደለምን?  ስለምን ይሆን ክብረታችን ጉድጓድ ውስጥ አጣብቀን ለመጣበቅ እምንፈቅደው። ስለምን ሰፋ አድርገን ህሊናችን ለጥበብ አናዘጋጀውም።

 ስለምን በተለያዩ ቀኗንቀዎች ሙዚቃውን ስንሰማ ነፍሳችን ጥፍት ይላል? „ህዝብ ለህዝብ“ እኮ አሳብዶን አልነበረም ፍቅሩ? ደማችን ስለሆነ እኮ ነው። አሁን እኔ ወጥቼ ተወዛውዤ አላውቅም፤ ግን ለእኔ ጉራጌኛ፤ አርሲኛ፤ ትግርኛ፤ ወላይተኛ ብሞክረው የምችለው ይመስለኛል፤ ከአማርኛው እስክስታ ይልቅ። ለእኔ ሁሉም ሙዚቃ ከእኛም አልፎ የጎንደር ከተማ ልጅ ስለሆንኩኝ ሱዳንኛም ይታከልልኝ፤ የብስክሌት ውድድርም ይጨመርልኝ ነፍሴ ጥፍት እስክኪል ድርስ አውዳቸዋለሁኝ። ማለት እኔ የሙዚቃ ሰው አይደለሁም ግን በአጋጣሚ ከሰማሁ ሰናይ ነው የሚሰማኝ።

ስለምን? እግዚአብሄር አንድ ያደረገውን ህዝብ የሰው ሥራ ሊገደብው ስለማይችል። የ እኔን መንፈስ ውስጥ ያለውን መቀበል ማንም ሊገደበው፤ ሊያስረው አይችለም። በፍጹም። ዶር ለማ መግርሳ ሲናፍቁኝ ድምፃቸው ጥፍት ሲልብኝ OBN ገብቼ አዳምጣቸዋለሁኝ። ወ/ሮ አዳነች አበቤንም እንዲሁ። አልሰማውም ግን ቢያንስ ቃናው ልቤን ይገዛዋል። ይሄ እኮ ስጦታ ነው። 10 ዲቂቃ ለማይሞላ ንግግር ያን ያህል ህውከት። ዶር ለማ መግርሳ እኮ የተጋበዘቡት ጉባኤ ነው። የጋበዛቸው አካል ደስ በሚለው መንፈስ ማግባባት ይገባል። ደግሞስ የ ኦርሞያ ፕሬዚዳንት አይደሉምን? የሥራ ቋንቋው እኮ ኦሮምኛ ነው። ለምንድን ነው እምናከረው? ይልቅ አስተርጓሚ ቢኖረው መልካም በሆነ ነበር። ያው የቅንጅት ጉድለትን አይቸበታለሁኝ። መድረክ ላይ ወጣ ገብ የሆኑ መሪ አልቦሽ የሆኑ ተዛነፎች አይቻለሁኝ።

  • ·       ውሸታሞች ነን።

አሁን እኔ የኤርትራ የመጀመሪያው ቡደን ቦሌን ሲረግጥ ያ ሁሉ ዕንባ እኔን ሳያስፈቅድ ይወርዳል ብዬ አላስብኩትም ነበር። ፈጣሪ የሰጠን እኛ ያለወቅነው፤ ምርምር ያለደርግንበት፤ ግን የገፈናው ቅዱስ መንፈስ አለ። አሁን በሃሳብ ብንለያዬም፤ ቁርጥ ሆኖ እንልያይ ቢባል አንችለውም። ውሸታችን ነው፤ ውሸታሞችም ነን። 

እኔ እንጂነር ስመኘው የተገደሉ ቀን በቀጥታ ፕ/ ብርሃነ ነጋ ነው ትዝ ያሉኝ። ከዚህ ቀደምም ተናግሪያለሁኝ አይደለም አፍሪካ አገር ጣሊያን አገር እንኳን እንዳሄዱ። ይሄ በእኛ ፈቃድ የሚሆን አይደለም። እኛ የማንቆጣጠረው ግን በፈጣሪ የተወሰነልን እትብታዊነት ሃዲድ አለ። ያ ሚሰጢር ነው ያልገባን ግን በምንም ዳኛ የማናስቆመው ነው።  
ሌላው  ውጪ አገር እንግሊዘኛ፤ ጀርመንኛ፤ ስፓንኛ፤ ፈረንሳይኛ፤ ቻይንኛ ወዘተ… ለማጥናት እንጣጠር የለምን? ቋንቋ ጠላት ነው ወይንስ የዕውቀት ዘርፍ? ቋንቋ አኮ ሙያ ነው፤ ፍልስፍና ነው። መክሊት ነው። ጸጋ ነው። ጥበብ ነው። ቋንቋ ተፈጥሮም ነው። ምላስ፤ ጥርስ፤ ትናጋ፤ ጆሮ፤ ዓይን፤ እጅ የተፈጠሩት ለቋንቋም ነው።  አዘንኩኝ የእውነት፤ ይህ ገመና ተይዞ ነው መደመር? ይህ ገማና ተይዞ ነው መፈቀር? ሳይበር እኮ ጦር ሜዳ ይመስል ነበር ዶር ለማ መገርሳ በኦሮምኛ ሲናገሩ። 

ይህን ከጠላን እኮ የለማ መንፈስ ተጋሪዎች ልንሆን ከቶውንም አንችልም። ዶር ለማ መገርሳ እኮ ብሄሩ ኦሮሞ ነው፤ ኦህዴድ ድርጅቱ የኦሮሞ ነው መለያው የዘር ሐረጉ እኮ ኦሮሞ ነው። ቋንቋውም ኦሮምኛ ነው። አርበኛ ሊሊሳ ፈይሳ እኮ ኦሮሞ ነው፤ ኮ/ አብዲሳ አጋ ኦሮሞ ነው፤ አትሌቶቻችን  ኦሮሞዎች ናቸው ቋንቋቸው አሮምኛ ነው። እነሱን ስንፈቅድ እኮ ሁለመናቸውን መሆን አለበት። አካልህን አካሌ አይደለህም የማለት እኮ ነው። ዓይኔ የ እኔ አይደለህም የማለት ያህል ነው …

ስንት መከራ ላይ ያለ ህዝብ፤ ነፃነቱ ያልተረጋገጠለት ህዝብ፤ የራሱ የደሙ እና የአጥንቱ አካል ቋንቋ  ኦሮምኛ ተነገረ ብሎ ያን ያህል፤ በሌላ በኩል ደግሞ ኦሮሞ ወገኖቼ ደግሞ እልልታው የጉድ ነበር አማርኛ ቀረልን፤ ዕውቅናው ተነፈገ ብለው። ካለገዱ፤ ከለ አንባቸው፤ አብሶ አቶ ደመቀ መኮነን ከእጩነት ራሳቸውን ባያገሉ ይህ ዕድል ነበርን? አይገኝም ነበር። አሁነም ሥ/ አስፈጻሚ ላይ ያለው ኦህዴድ 9 ድምጽ ብቻ ነው። ፓርላማ ላይም እንዲሁ ነው …

ሌላው ኦሮምኛ ቋንቋ ቢነገር  ምን አዲስ ነገር አለው። አለመቻላችን ነው እንጂ ቋንቋው እኮ የመንፈሳችን፤ የደማችን፤ የነፍሳችን ክፋይ ነው። ደማችን ቀለማችን ነው። በሌላም አንጻር ኦሮምኛ ስለተነገር የገዛናችሁ የድል ነጋሪት መጎሰምም የተገባ አልነበረም። ኖርማል እኮ ነው። ሲዊዘርላንድ አኮ 4 ቋንቋ ነው የሚነገረው። ነገር ግን ወደ ጀርመንኛ ያደላ ዝንባሌ ነው ያለው።  ጀርመንኛ ሊንክ እና የተፈቀደም ነው። 

በማንኛውም ሁኔታ ውድድር ላይ ይህ ይገጥማል። ተወዳዳሪዎች ግን ምርጫቸው ጀርመንኛ እንዲሆን ነው። ምክንያቱም ጀርመንኛ መቻል ለሀገር ጀርመን፤ ለሀገረ ኦስትርያ ብሄራዊ ቋንቋ ስለሆነ የተሻለም ዕድል ስላላቸው ጀርመንኛውን ይፈቅዱታል። ፈርንሳይ ኢጣሊያንም ለሁለቱ ቋንቋም መሰሉ ዕድል አለ። ግን ሳይ ከፈረንሳይም፤ ከጣሊያንም፤ ከቀይ ሮማንኛም የሚወዳደሩት ወጣቶች ጀርመንኛውን የተሻለ ምርጫቸው ሆኖ ነው የማዬው ሁልጊዜ።
የሆነ ሆኖ በዚህ በሁለቱ ያለው የጎራ ልዩነት ለተመለከተው በስሜታቸን ላይ የተሠራ ምንም ነገር እንደሌላ ማሰተዋል ችያለሁኝ። ሳይበር ታወከ። የሚያስታግስ መንፈስ በመጥፋቱ እኔ ዘው ብዬ መግባት ግድ አለኝ እና አዬር ላይ ችክክቸካ ገባሁኝ። ተሳካልኝ እና በረድ አደረግኩት።

በእውነት ታመናል። አማርኛ የሚቀርበት ነገር እኮ የለም በዛ ጉባኤ ላይ ሳይነገር ቢቀር። አማርኛ የራሱ ማንነት ያለው ቋንቋ ነው። ያደገ የበለጸገ ሥልጡን ቋንቋ ነው። ይህን ያህል ዓለም የተደበላቀ ተደርጎ የሚታይበት ባልሆነ ነበር፤ አማርኛን መግደል ቢአችል ኖሮ 43 ዓመት የተደራጀ ተግባር ተከውኖበታል፤ ግን ሉላዊ ከመሆን አላገደውም፤ የራሱ የፊደል ገበታ ያለው ስለሆነ። ኦሮምኛ ደግሞ የራሳችን አዱኛችን ነው። 


አርሲ ጢቼ ሰርቼያለሁ እኔ አይደለም ገጠር ከተሞች ካለ አስተርጓሚ አይቻልም ነበር መግባባት። በደርግ ጊዜ ማለት ነው። አሁን 27 ዓመትማ የቁቤ ትውልዱ ድፍን ያለ ጉድ ነው። ይህም የሆነው ትውልድን በመነጠል የራስን የፖለቲካ ልዕልና ማስጠበቅ  የአክተሮቹ ተግባር ስለነበር ነው። ደቡብ ምን ተጎዳ? አሁን ብዙ ቁልፍ ቦታ ያላቸው እነሱው ናቸው። ከትግራይ ሰዎች ቀጥሎ የደቡብ ልጆች በመንግስታዊ ቁልፍ ቦታዎች ሰፊ ቦታ አላቸው። በመልማትም ከትግራይ ጋር ያልተናነሰ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።   
  • ·       ቅድመ መሰናዶ በሚኒ ዝግጅት ያዬሁት እና ውስጤ።

አሁንም አጠናክሬ እምገልጸው ይልቅ ፕሮግራሙ ከመጀመሩ በፊት የነበሩ ቅስቃሳዎች እጅግ የሚገርሙ ነበር። የሌላ አገር ነበር የሚመስለው። ድሉም የቄሮ ብቻ፤ የኦህዴድ ብቻ ተደርጎ ነበር ሲቀሰቀስ የነበረው። በቅድመ ዝግጅቱም ቃለ ምልልሱ መንፈሱ እንደዛ ነበር። እጅግ የሚነጥል እና የሚከፍል ጉድ ነበር። 

በዛ ላይ መሥራት የቲም ለማ ጉዳይ ይሆናል። በተረፈ በጉባኤው ላይ ኦሮምኛ መናገሩ ዝግጅቱም ለዚህ ስለነበረ ነውር የለበትም።  ቀድሞ ነገር የቲም ለማን የደገፈ አማራ እንጂ እነሱ ምናቸው አልነበረም። ከዚህ ቦታም ይደርሳል ብለው አላሰቡትም ነበር። ፎቷቸው እንኳን በዬሚዲያቸው አለነበረም። ጭራሽ ዶር አብይ አህመድ ወደ ፊት ሲመጡ ቀውጢ ነበር። ለዛውም ዶር ለማ መግርሳን ሰማቸውን መጥራት ተጠይፈው ኖረው ነው ኋላይ ደግሞ ስለምን አብይ መጣ የነበረው ጦርነት። የተጠቀለለ መርዛማ ጉድ፤ አቅጣጫው የማይታወቅ መንፈስ የነበረው። እኔም ሃራም ብዬ ከረሜ ሰሞኑን ነው OMN ላይ የታደምኩት። ጤና ማጣትን በገንዘብ መግዛት አስፈላጊ ስላልነበር።

አሁን አብዩ ጸሐይ ሲወጣለት ነው ጋባዥ የሆኑት እንጂ ምኞታቸው ሌላ ነው የነበረው። ያልታወቀ መንግሥታዊ ህልም ነበር ራዕያቸው። የአትላንታው ጉባኤ እኮ የቅርብ ጊዜ ነበር። የሆነ ሆኖ እግዚአብሄር ፈቅዶ ለዚህ ከተደረሰ ደግሞ የሚጠቅማቸውን የሚጎዳቸውን አይተውታል እነ ቲም ለማ ሆነ የድላቸው ሰሞናት ታዳሚያቸው አማራን በጥርሳቸው የያዙት ወገኖቻችን ማስተካከል ይገባቸዋል። እንኳንስ እንሱ ኤርትራም አይታዋለች።  ከኢትዮጵያዊነት መንፈስ ውስጥ ምንም ነገር ቅንጣትስ እንኳን ቋት መግፋት እንደማይቻል። ግንቦት 7 ራሱ አይቶታል። አንጣፊውን፤ ሎሌውን አገለለ አዬው …
  • ·       ከሁሉም በላይ … ግን

ደሃ አገር ከሁሉ በታች የሆነች አገር እያለችን ቋንቋ እና ብሄራዊ ሰንደቅዓላማ ልዩነት ተፈጥሮበት ተኖረበት። ያተረፈው ነገር የለም። ወደ ቀደመው ኢትዮጵያዊነት ምልሰት ስለሆነ ነው ይህ ሁሉ ክብር፤ ዝና እና ፍቅር የረበበው። ወደፊትም ቢሆን በዚህ መልክ ማስቀጠል ካልተቻለ ሁሉም ነገር ከንቱ ነው። የለማ ቡድን ክብርም ይፈርሳል፤ የእውነት ከልብ መለወጥ ካልሆነ ኩላሊትን የሚመረምረው  ፈጣሪ ስለሆነ ተስፋው ሁሉ የድቡሽት ቤት ነው የሚሆነው።  

በአማራ ማህበረሰብ ጥላቻ ውስጥ ሆነው ግን በቅብ ሲያረግዱ የነበሩት ህብረ ብሄር ፓርቲ ደጋፊያትም ቢሆኑ ሁሉ የዘሩትን እያጨዱት ነው። ነገም በዛው ይቀጥላል ፈጣሪ የሰጠንን የምርቃት የበረከት ጊዜ በወጉ እና በአግባቡ መያዝ ከተሳነን። መርዙን ከውስጣችን ማውጣት ካልተቻለ በርቀት እንኳንስ አፍሪካን ራስንም ማስቀጠል አይቻልም፤ በ2030 ከሚፈርሱት አገሮች ተርታ አኮ ነው ያለነው።

ይሄው እና ኦቦ ሌንጮ ለታ ከሄሮድስ መለስ ዜናዊ ጋር ሆነው በአማራ እና በአማርኛ ቋንቋ ላይ አደሙ፤ ዛሬ ዕድል አግኝቶ ኦሮሞ የሚመራት ኢትዮጵያ ተፈጠረች፤ መቀሌ ላይ የነበረው ሰላማዊ ሰልፍ ታይቷል። ድሮም ካልነበረ መንፈስ ጋር የነበረው ሦስት ጉልቻ ዘመን ጉዱን አሳዬው። ግንቦት 7 አገራዊ ንቅናቄው እና ፍርሰቱን አይቶታል። እኒያ እጅግም አማከብራቸው ለይችም እምወዳቸው፤ ላገኛቸውም እምፈቅደው ዶር ኮንቴ ሙሳ ለዶር አብይ አህመድ የሰላም ሽልማት ሎቢ ላይ ነኝ በማለት በአደባባይ ተናገሩ። ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ተሰዶ ነው ይህን እርምጃ ያስወሰደው …

አብሶ የመንፈስ አቅም ምንጩን አክብሮ መነሳት ብቻ ሳይሆን ተገቢ አክብሮት፤ ተገቢ አትኩሮት፤ ተገቢ ፍቅር ሊሰጠው ይገባል። ይህ ዘመን ከሊቅ እስከ ደቂቃ መንበር ላይ ላሉት መኳንነታት ያሰተማረው ቁምነገር ታላቅ ነው።

ዛሬ ዶር አብይ አህመድ የኢሳት እና የግንቦት 7 ፕሮ ናቸው። የግንቦት 7 ፕሮዎች ሚደያውን ኢሳትን ጨምሮ የአብይ መንፈስ ቀዳሚ ደጋፊ ፕሮፖጋንዲሰት ሆኗል። ዘመን እንዲህ ነው። ወጀብ የማይነቀንቀው በፋክት ላይ የቆመ ሰው፤ ወይንም ተቋም ግን የመጣ ቢመጣ፤ የሄደ ቢሄድ ፋክትን ይዞ ከቆመ ጸጸት የለበትም -- ቢያንስ። ጉዳዩ የግል ኢጎ አጀንዳነት የመሆን የሥም እና  የዕውቅና አይደለም እና። 

ነገም ፋክት ላይ ለዘለቀ ሰው አይጨነቀውም የተወዛወዘ ቢወዛወዝ … ጥጉ ችሎቱ ፋክት ነው … ፋክትን የሙጥኝ ማለት ባለዝና ላያደርግ ይችላል፤ ግን ህሊናዊ ትርፉ እዮራዊ ነው። ድፍረቱና በራስ የመተማመን መንፈሱም የአገር ጉልላት ነው። ለዚህ ነው እኔ የ ኢኮኖሚ ሊቀ ሊቃውነቱን ዶር ፈቃደ በቀለን ከምር የማከብራቸው። ጹሁፋቸው በሙሉ ፋክት ነው። ትንተናቸው ፋክት ነው። ድጋፋቸው ፋክት ነው። የህሊና ሃብት ናቸው።
  • ·       ሞት።

ኢንጂነር ስመኛው ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ። አንዲት ኦሮሞ መሬት ላይ የሆነች ኮሽታ አልተደመጠችም፤ ሀዘኑ የጎንደር፤ የጎጃም፤ የወሎ፤ አዲስ አበባ ላይ ብቻ ነው። የአዲስ አባባው የስንብት የሀዘን ቦታ ላይ የተገኘውም በያዘው ሰንደቅዓላማ ማዬት ይቻላል። ለዚህ ነው እኔ የአማራ ሊሂቃን በኢትዮጵያዊነት ላይ መራቀቁን ተግ አድርገው ወደራሳቸው አጀንዳ መመለስ አላባቸው አምለው።

ለሁሉም መሃል ላይ አገናኙ አማራ ብቻ ነው። የፈጣሪም ዝንባሌ አለበት። ስለምን? ቅን ህዝብ ሰለሆነ።  ግን ስለሱ መንፈሱን በዕውኑ ሊገብር የተነሳ ለማግኘት እንደ ማህበረሰብ እዬከበደ ነው፤ የመቱ ወርቃማ ተጋድሎ እንደተጠበቀ ሆኖ … ስመኛው የአማራ ብቻ አልነበረም የሁሉም ነበር፤ የሆነው ግን ሌላ ነው። ይልቅ መቀሌ ላይ በቁጭት ይናገሩ የነበሩ ንጹሃንን የትግራይ ተወላጆችን የዘራይ ደረስ አርበኞችን አይቻለሁኝ። በእነሱ ተጽናንቻለሁኝ።

እኔ የሬቻው ዕልቂት ጊዜ ያደረኩትን ደግሞ ሁነኛ ሰው ሳገኝ እናገረዋለሁኝ። እኔ ወገኖቼ ናችሁ፤ ለእኔ ደሞቼ ናችሁ እናንተ ጎንደሬ አማራ ብላችሁ ልትጸዬፉኝ ትችላላችሁ። ግን እኔ የእኔ ብዬ የተቀበልኳችሁ ዛሬ አይደለም መጸሐፍቶቼ፤ ጸጋዬ ድህረ ገጽ፤ ጸጋዬ ራዲዮ፤ ቀንበጥ ብሎግ፤ ቁጥር አንድ እና ቁጥር ሁለት Seregut Selassie ዩቱቤ ይመስከር። በማለት የኖርኩ ስለማለት የተፈጠርኩ ስለማለት የምተጋ አይደለሁም። ልዑል እግዚአብሄር ለ አንድ ነፍስ ብሎ ሌላውን ይምራል። እማዬው ግን ሚዛናዊነቱ ያነሰ ነገር ነው።
  • ·       ማት።

ሌላው የአቶ ጆዋር መሃመድ ጉዳይ ነበር ሳይበር ላይ ማት የነበረው።  ማዬት የማይፈልጉ ግን አበይ ላንተ ስንል ያሉም አይቻለሁኝ። ወጣት ጆዋር ከዚህ ቀደምም ተናግሬያለሁኝ፤ በእኛ የተለመደው መገፋት ደርሶበታል፤ በዛ ላይ ወጣት ነው፤ በዛ ላይ የሁላችንም ተፈጥሮ ተመሳሳይ አይደለም፤ በዛ ላይ አወጣጡ ከታች ተነስቶ አይደለም በአንድ ጊዜ ነው ንግሥና ነበር የተሰጠው ለፖለቲካ ትርፍ ሲባል፤ ያደገበት አካባቢም እና አሳዲጊዎችም ድርሻ አላቸው። በሌላ በኩል በኩል አብሯቸው የሚሠሩት የፖለቲካ ሊሂቃን የሚደግፉት፤ የሚያርሙት፤ የሚገስጹት አይደሉም። 

እኔ እኮ ገ/ መድህን በርጋ የመሰለ ነፍስን የሚያበጅ አባት ሰልነበረኝ ነው። ገብሬ ጉራጌ ነው። ግን ምድር እሱን የመሰለ የድርጅት ሰብዕና ያለው አልፈጠረችም። ተቀራረቢ ግን አንድ ሊሂቅ ብቻ ገጥሞኛል። እኔ ገብሬን ባይጥልልኝ ወንዱን ባይጥልልኝ የትም ቦታ ፓርቲዬ ኢሠፓ በመደበኝ ሁሉ ለፓርቲያችን የምታኮራ ባልተባልኩ ነበር። ማንም ሰው ለኮርስ፤ ለሰሚናር ሲሄድ ከጎንደር መጣሁ ሲል/ ስትል ጥያቄው የእኔ ደህንነት ነበር። ስለዚህ ወጣት ጆዋር መህመድም ወጣት ተመስገን ደሰላኝም አጋዥ የፖለቲካ ሊሂቅ  አላገኙም። ወጣትነት ራሱ ፈተና ነው።

የማዬው በዕድሜ የሚበልጡት የእሱን ስሜት የሚከተሉ እንጂ የሚያርሙት፤ የሚያርቁት ሰብዕናውን በወጥ አቋም የሚያንጹት አይደሉም። እሱ ታላቅ ወንድም እነሱ ታናሽ ነው የሆኑት። አሁን ያለው የአብይ መንፈስ ቅብብሎሽ ከዘለቀ መቼስ መልካም ነው። ቋሚ አቋም የቅርብ ክትትልን ይጠይቃል። ምን ለማለት ነው በፖለቲካ ሕይወቱ ወላጅ አልባ ነው አቶ ጆዋር መሃመድ። የማያቸው የእሱ ስሜት ተከታዮች ብቻ ናቸው።  የእሱ ሰረጋላ የሚመራቸው ናቸው። ለዚህ ነው እኔ ልጄ ቢሆንስ ብዬ በማሰብ ምንም ነገር በእርሱ ወጣ ገብ የፖለቲካ አቋም ጽፌ የማላውቀው። እንዲያውም አዝነለታለሁኝ። ፖቴንሻሉን የሚገራለት አላገኘም እንጂ ቢያገኝ ጠቃሚ ወጣት ነው።
  • ·       ተዚህ ላይ ..

አንድ የአልኮል ወዳጅ የሆነ ወጣት ነበር። እና ለክ/ የሠራተኛ ማህበር እጩነት ሲቀርብ ይጠጣል የሚል ሙግት ገጠመኝ። የቢሸፍቱ ልጅ ነበር። እኔ ሥ/ አስፈጻሚ አካላትን አንድ በአንድ ፕሮግራም እያዬስያዝኩኝ ሞገትኳቸው ዕድሉ ይሰጠኝ አሰተካከለዋለሁኝ ብዬ። ላጣው የማልፈልገው ወጣት ስለነበረ። እኔም ወጣት ነኝ የዛን ጊዜ ነገር ግን ያበቃኝ የሊቆች ሊቅ የገብሬ ልጅ ነኝ እና። ይህም ስለሆነ በፓርቲ አካልነት አዲስ ሰው ሲመደብ  እንኳን ነፍሳቸውን ይማረውና ጓድ ገዛህኝ ወርቄ ወደ ምድብ ቦታችሁ ከመሄዳችሁ በፊት እሷን አግኟት ይሉ ነበር፤ አዲስ ተመዳቢዎችን፤ አለቃዬም አጀንዳ ሲያስዝም አማክረሃታል ብለው ይጠይቁ ነበር።

ወደ ቀደመው ስመለስ ያ ወጣት ዕድሉ ተሰጠኝ እና ክ/ መኢሰማ ተመራጭ ሆነልኝ። ቁልፍ ቦታ ተሰጠው። ከዛማ ምኑን እንግራችሁአለሁኝ። ቡደን ሲንቀሳቀስ ከማህበራት ሲባል ተመራጩ እሱ ነበር። ማርከሻ ነው። አሁን ትልቅ ቦታ እንዳለው እሰማለሁኝ። የሚገረመው እናቴ በተለመደው ሁኔታ ይጠይቃታል። በነበረው ፍቅር። ለዛውም ያን ጊዜ እኔ እታገልት እንደነበር  ይሄን አያውቅም ነበር። ምን ለማለት ነው አቶ ጆዋር መሃመድ ጥሩ የፖለቲካ ሊሂቅ አባት ወይንም እናት ካገኜ ኢትዮጵያን ይጠቅማል። ኢትዮጵያ እኮ በውስጡ ባትኖር አማራ ተጋድሎን አይቀበልም ነበር። የሆነ ሆኖ የሚገራው ባለማግኘቱ በራሱ መንገድ ብቻ ይጓዝ ስለነበር፤ በስሜት በሚናገራቸው ጨለማዊ ቃላት የተነሳ  በዙ ሰው ቂም ቋጥሮበታል።

ወጣት ጆዋር ንጉሥ ነው፤ አንድ ሚሊዮን ደጋፊ አለው። የእሱ ሰብዕና  ደግሞ ግራጫማ ነው። ሲፈልጋው ደስታን ያርከፍክፋል፤ ሲያሰኘው ደግሞ ተስፋ ቆራጭነትን ያዘንባል። በሱ ጉዳይ ብዙ ሊሠሩ የሚገባቸው የቤት ሥራዎች አሉባቸው ዶር አብይ አህመድ። ኦህዴድ ውስጥ ያመጡትን የመንፈስ ለውጥ ይህንንም የማድርግ አቅም ይኖራቸዋል ብዬ አስባለሁኝ። ግን አቶ ጆዋር መሃመድን ከሥር ከሥራቸው እንዳይጠፋ በማድረግ በግል ህይወቱም፤ በማህበራዊ ህይወቱም ሊረዱት ይገባል። የማድርግ አቅም አለው።

እኔ እማደንቅለት ተሸናፊነትን አለመቀበሉ ሳይሆን ተሸናፊነቱ አሸናፊ አድርጎ መንበር ላይ ዕወቅና የማሰጠት አቅሙ አንቱ ነው። ጀግና ነው። እኔ ተሸንፈው አቅማቸውን ቀብረው የሚቀሩትን ሳይ ምነው የጆዋርን ቅንጣቢ ልብ ቢሰጣችሁ እላለሁኝ። እኔ ራሴ ተኝቼ በለኝ ባልልም የእሱን ያህል አቅም ቢኖረኝ ሥርጉተ ሥላሴ የማንም መጠቃጠቂያ አትሆንም ነበር። ማንም እንዳሻው አቅሜን የሚያግተው እና የሚያሰቆመው ባልሆነ ነበር። 

እሱ ቤተሰቦቹ፤ የአገሩ ልጆች አብሶ ኦሮሞዎች ሙሉ ጊዚያቸውን በእሱ ፕሮጀክት ላይ ያሳልፋሉ፤ እኔ ግን ከአንድዬ በስተቀር ማንም የለኝም። ያለተሳከለት ሁሉ … ሌላ ተግባር የለውም። ብቅ ብሎ ለመታዬት እንኳን ዕድሜ ለሳተናው ድህረ ገጽ። ለዛውም በኢሜል የሚመጡ መልዕክቶች፤ ያለማባራት የሚታወከው የቤተ ስልክ እንደ ተጠበቀ ሆኖ።
የሆነ ሆኑ ወጣት ጆዋር እና ዶር ጸጋዬ አራራሳን እኔ እኩል አላያቸውም። ወጣት ጆዋር ኦሮሞ ሆኖ ነው ያደገው። ዶር ጸጋዬ አራራሳ ግን ኦሮሞ ሆነው ሳአድጉ ነው ኦሮሞ ልሁን የሚሉን። ወላጅ አባታቸው ስለ ንጉሦሶቹ ንጉሥ አጤ ሚኒሊክ ክፉነት እዬዞሩ ቦታዎችን እያሳዩ ሲያስጠኗቸው፤ ኦሮምኛ ቋንቋ ግን አላስተማሯቸውም። 

ስለዚህ በዚህ ውስጥ የእሳቸውን የኦሮሞነት ተሟጋችነት ስመረምረው  ልሙጥ ነው። ተሟጋችነቱ እንደ ድንገቴ አድርጌ  ነው የምመለከተው። እልህ ቁጭት ያለበት እኮ ያን ያህል በዓለም አቀፉ የህግ ሙያ ሲጠበቡ ኦሮሞነት ዕውነት ከሆነ ኦርሞኛ ቋንቋን በመንፈስ ተገፍቶ ባልነበረ። ለነገሩ በወቅታዊ እንቅስቃሴዎች የሚመጣው የፖለቲካ መሪነት እና ከልቡ በስሎ የሚመጣው ልዩነቱ ይህ ዘመን አሳምሮ እያበጠረው ነው። ራሱ የተፎካካሪ ፓርቲዎች ከጠ/ ሚር አብይ አህመድ ጋር በነበራቸው ቆይታ ሞግቶ አሸነፎ እሺ ያሰኛቸው አንድም አቅም አላዬሁም።

ለዚህ ነው አትችሏችሁም፤ መሰናዶ የላችሁም እያልኩ የምሟገተው። ሌላው የተለመደው መጠይቅ ነበር ፤ ላዘው መሬት ላይ መልስ እዬተሰጠ ያለው ጥያቄ ነበር ሲጠዬቅ የነበረው ሰክኖ የ3ወራትን ክንዋኔ በንግሮች ውስጥ ያሉ የፖሊሲ መንፈሶችን ማገናዘብ የተሳናው መንፈስ የቀረበበት ሁኔታ ነው፤ አንድ ከልቤ የገባው የቴዲ ነበር፤ እሳቸውም አልደፈሯትም ከድነዋታል፡ መንገዱንም ወድጄዋለሁኝ። የአባይ ግድብን ጥያቄ እንዲህ አድርገው ክድን አድርገው ቢሆን ኖሮ የሀምሌ 19ኗ ዕለተ ሃሙስ ደም ባለበሰች ነበር። 

ጊዜያቸውን ያልጠበቁ ጥያቄዎች መልሶቻቸው ለይደር መቅጠር ግድ ነው። የማይነከውን መንካት የተገባ አይደለም። ለዛውም የትናንት ምሽት የሳይበር ነውጥ ላይ የጉድ ነበር … ገና መሠረት አለያዝነም። 

ፍላጎታችንም ከስሜታችን በላይ ለማድረግ  የአቅም ግንባታቸው እጭ ላይ ነው ያለው … ለዛም ከበቃ ዕድለኛነት ነው … በዚህ ላይ የትጋት ትትርና በ እጅጉ ያስለፈልጋል። መቃውም ብቻ ሳይሆነ የፍላጎታችን ድልድይ አገነባብ መንፈስ አቅም ቋት የማደራጀት የፊት ለፊት ተግባር ይመስለኛል። ለዚህም ነው እኔ ቀንበጥን የጀመርኩት። በፖሰተርም፤ በድምጽም እቀጥላለሁኝ። ሰፊ ራይ ላለው ሰው ይህን መንገድ ነቅፎ ሳይሆን ደግፎ፤ ስህተቶችን፤ ክፍተቶችን እዬገለጹ ግን ለዘላቂ ቋሚ የእኩልነት ሥርዓት ግንባት መትጋት ግድ ይላል። ሊነክ ነው፤ መሸጋጋሪያ ድልድይ ነው …

የሆነ ሆኑ ጭርሽ የ ኢትዮጵያዊነት መንፈስ በሌላቸው ላይ አቅም ማባክን አይገባም። እውነተኛ ሆኖ በመውጣቱ ረገድ የሚያዳግቱ ነገሮች ስለአሉ። ለዚህም ነው እኔ አጀንዳዬ ሆኖ የማያውቀው። መንፈሳቸው የሚገርመው አይረብሸኝም። አቶ ጆዋርን በሚመለከት ግን ኢትዮጵያዊነት ተቆርቋሪነቱም በተወሰነ ደረጃ ጠረን አለበት ስለዚህ በአቶ ጆዋር መንፈስ ውስጥ ኢትዮጵያዊነት ደንቡልቡል ነው ብዬ አላስብም።

ዝቅ ባላው እሳቤ አብረን እምንኖር ከሆነ እኛ እንምራ ነው። አጀንዳ ቅርብ የሚሆን ከተገኘም አቅም የመስጠት ዝንባሌ አያለሁኝ። ለምሳሌ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ያልደፈሩትን እንደ መሪ፤ ካቢናቸውም እንደ አገራዊ መንግሥትነትም የአማራ የህልውና የማንነት ተጋድሎን በሥሙ ደፍሮ የመጥራት ጉዳይ አቶ ጃዋር መንፈሱ ውስጥ አስቀምጦ ሞግቷል፤ ፖለቲካዊ ትንተናውም አቅም ነበረው። ተቃውሞ የባዘበት ሁኔታም ቁልጭ አድርጎ ተናግሯል። ይሄ የቃላት ጨዋታ አይደለም በቼ እና በሼ ማህል ያለ፤ የፖሊሲ ጉዳይ እንጂ። የታጋድሎው  የዓላማ እና የግቡ ጉዳይ እንጂ ... 

ሚደያውም OMN ዕድሉን ሰጥቶ፤ ሰፊ ጊዜ ሰጥቶ አትኩሮት ሰጥቶ፤ ህጋዊ ዕውቅና ሰጥተዋል። የምናደንቀው እና የምናከብረው OBN ግን ይህን አልደፈረም። ወደፊትም አይደፍረውም። ጥንቅሮችን ሲሳራ ሲዘግብ አያለሁኝና።

ዛሬ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ አማራ ተጋድሎ ነኝ ብሎ የወጣውን የህዝብ ድምጽ ለዚህ ቦታ እንዳበቃቸው ልባቸው እያወቀው ካቢኔያቸው የሚመራው ሚደያ በፍጹም ሁኔታ ማግለሉ ሲገርመኝ በአደባባይ በተደጋጋሚ ከሳቸው የዙፋን መዳረሻ ዋዜማ ላይ እና በማግስቱ ለአውቅናው በብጥበጣ በተተጋለት የትናንት ከታቱ ያልውጣ የወጣት ድርጅት ሲያድንቁ፤ ሲያወድሱ፤ ሲያከበሩ፤ ሲያልቁ የአማራ የህልውና ተጋድሎን ግን መድፈር አቅቷቸው፤ ግንቦት 7 የሸለመውን ስም ይዘው „ፋኖ“ ሲሉ ሳደምጠው ልቤ ተቀረረደድ። አዘንኩባቸውም። 

በሳቸው ላይ ያለኝ ዕምነት መርሃዊ ናቸው ብዬ አስብ ስለነበር ማዘኔም፤ መከፋቴም የተገባ ነው። ሊያደምጡኝ አለመፍቀዳቸውን ከልቤ አይቻለሁኝ። ዓይኔ ያለው ከልቤ ውስጥ ነው። 

ከሳቸው ካቢኔ ማግሥት ጎንደር በምን ሁኔታ በሚዲያ ሰፊ የሆነ የመንፈስ፤ የሥነ - ልቦና፤ የሚዲያ ግለት እንዳለበት እያሰተዋልኩኝ ነው። የሆነ ሆኖ ምንግዜም ጎንደር ለማገዶነት የተበጀች ናት እና  አንድ ዓይኑም በጠራራ ጸሐይ በሽጉጥ ተደብድቦ በአደባባይ ሙቷል። ማን ይግደለው ማን? ማን ያስገድለው ማን፤ የገደለው ለፍርድ ይቅረብ አይቅረብ ለጎንደር ምንም አይሰራለትም። የቀብር ሥርዓቱም ሴሪሞኒው ምንም አይሠራለትም። ፋሲል ፋሲል ያሰኘው ፍጻሜው እንጂ ጅምሩ አልነበረም።

በጣምራ ፍዳውን ለሚከፍል ቅን የዋህ ትእግስተኛ ህዝብ ግን ፍርዱን ከሰው ዘንድ ሳይሆን ከእዬር እጠብቃለሁኝ። ፍትህ እያሉ የሚጮኹ የአዲስአበባ ወገኖቼ አሁንም ሀምሌ 22 ቀን ቀብር ላይ እንዳይገኙ ሁሉ ተደርጓል፡ እሰቡት በአብዩ ካብኔ ነው ይህ የሆነው አቶ ደመቀ መኮነን በሚመሯት አገር ነው ይህ የሆነው።  

ለቀብር አብረን እንሄዳለን ሲሉም በአደባባይ ተደብድባዋል፤ ሞተዋልም። ሞትን በሞቱ ያሸነፈው ልዑል እግዚአብሄር ስለንጹሃን ጠበቃም ዳኛም እሱ ብቻ ነው። በ43 ዓመት የታዬው ነገር ነው በመዲናው በአዲስ አበባ የተደገመው። ይህ በድንቅነት ታሪኩ የተጀመረው አዲሱ የለውጥ ሰውኛ መንፈስ ጋር ነገን ለማስቀጠል ግራጫማ ቀኑ ነው። በዚህ ዙሪያ ለተጉ፤ ለወደፊቱም ለሚተጉ ሰዎች ደንቀራ ገጠመኝ ነው። የማዬው ሁሉ። የማደምጠው ሁሉ። በሌላ በኩል በፍጹም ሁኔታ አትቀበሉት የአብይን መንፈስ የሚሉ ነፍሶችም እዬደወሉ ነው። ቀን ከሌለ ጨለማ፤ ጨለማ ከሌለ ቀን አይታወቅም።
  • ·       እንደ ሥርጉተ።

ለገሃዱ ዓለም ግን ጥገናዊ ለውጥ መራራውንም ጣፋጩንም መቀበል በመቻል ውስጥ መስከን አለበት። ሰው ምን አለው? የሁሉም መንግሥታት ጀንበር ትናንት ጠልቃለች፤ ወደፊትም እንዲሁ፤ ምድር ድንኳን ናት። ይልቅ ሰውኛ እና ተፈጥሮኛ መንፈሱን የማይበክሉ አንዱን ያለገለለ፤ ሌላውን አብዝቶ ያለቀረበ ማዕከላዊ የሆነ ነገር ቢፈጠረ ቅብዕውም ምርቃቱም ይሰክናል።

በስተቀር ግን ብረት መዝጊያ፤ የጀርባ አጥንት የሆነ ህዝብ አማራዊ መንፈስ ተገሎ ከሆነ ግን ፍርዱ የእዮር ይሆናል … የተሰደደው ሲገባ እንደ ለመደበት አማራ ደግሞ በጅምላ ይሰዳደል …. ሞቱንም ለምዶታል፤ ስደቱንም እንዲሁ …

ብቻ ዳሩ ሲደፈር ማህሉ ዳር መሆኑ መረሳት ግን የተገባ አይደለም … ። ከሁሉ የሚከብደው የመንፈስ ሽፍትንትን ነው። ወግ ያለው አትኩሮት ሊኖር ይገባል። ተከታዩ ደግሞ የሚደግፍ ከሆነ በጽናት መሆን አለበት። እዬባዊነት ሲባል ሁሉንም ለመቻል ሆደ ሰፊ መሆን ማለት ነው። ችሎቱ ሲያልፍ ግን ግድቡን ጥሶ በራሱ ጊዜ ሂደት ይመሰክራል … ሲከር ይበጠሳል፤ ሲሞላም ይፈሳል ነውና። 

በፖሊሲ ደረጃ የተገለለ ህዝብ እና ሌላው በፖለቲካዊ ፍስፍናው አያያዙም ጥቃቱም እኩል ለማዬት ሎጂኩ አይፈቅድም። ኦህዴድ እያጣ ያለው መንፈስ እንዳይኖር መጠንቀቅ አለበት። በትንሹ በትንሹ ሲሆን አይታወቅም። በመደመር ውስጥ መቀነሰም አለና። ይህ ማዕረግ እና ዝና በማን እና በምን ብሎ ማሰብ አለበት ኦህዴድ እንደ ድርጅት። የአሁኑ የሁሉም መነጠፍ ሳይሆን በመከራ ጊዜ ማን ነበር ከእኔ ጋር  ብሎ ማስተዋልን ቢጣራ የሚበጀው ይሆናል - ቲም ለማ። 

ሲሞቅማ ማን አሞቀኝ ብሎ ሂደቱን መገምግም እና ሰፊውን አትኩሮት መሰጥት ይገባል። ዛሬ ያለው የአደባባይ ሰው፤ ሚደያው ሁሉ እንዲያውም ፕሮ እና ፕሮፖጋንዲስትም መሆኑ መጠኑን በላፈ መልክ እያስተዋልኩኝ ነው። በዛ በበረዶ ወቅት፤ በዛ ጨለማ እና ወከባ ወቅት የትኛው ነበር፤ ማን ነበር አብሮኛ የተፋለመ ብሎ ማሰብ ይበጃል። አሁምን እጅግ ሊቀራረቡ የማይችሉ መንገዶች በግራ በቀኙ በማስተዋል፤ ቢያንስ ከእጅ የገባ መንፈስ እንዳይታጣ መጠንቀቅ ይገባል። ትዕግስት ሲያልቅ ፍቅር ሰለሚሰደደ… በፍቀር ሁሉን ለማቅረብ ሲታሰብ ያለቀሱ ጥቁር ለባሾችም ቢያንስ ብትን አፈር ለማልበስ የዜግነት መብታቸው መደፈር አልነበረበትም።
  • ·       ትዝብት ና ሲቃ። 

 አሁን እማዬው የአሜሪካው ጉዳይ ግን ግርም እያለኝ በትዝብት ነበር የተከታተልኩት … አንዳንድ ጊዜ ውሽክ እያልኩኝ ነበር የተከታተልኩት፤ የተዋህዶ፤  እስልምና የሰላም ፋውንዴሽን እና የሎሳጅለሱ ለእኔ ተፈጥሯዊ መንፈስ ሆኖልኛል። ህውከትም አልነበረውም። የፖለቲካ ትርፍ እና ኪሳራ ንግዳዊ እሰጣ ገባም አልነበረውም። መንፈሱ ጤናማ ነበር … እንዲያውም አባቶቼ ለመስከረም 11 ሲቀጥሩት ቤተሰቦቼን ማግኘት ነበረብኝ፤  የእግዚአብሄር ቀን መከበር ስለነበረበት። 

ቅብዕውም መደፈር ስላልነበረብት ይሁንታ እንዲነረው አብረው ፈጣሪ ከሰማይ ከሰጣቸው ልጃቸው ጋር እንዲሄዱ ስለወሰንኩኝ በጋራ ነበር የተከታተለነው ማለት ይቻላል … ያው በሲቃ ማለት ነው።

ትናንትን ለመርሳት ዛሬ የሴራ ፖለቲካ መቆም ሲቻል ነው። አሁን እኔ በኤርትራ መንግሥት ላይ ሙሉ እምነት አልነበረኝም። ዛሬ ደግሞ ያን ሁሉ ረስቼ ብዙ መንፈሰችን ሞግቻለሁኝ። ትዝ የሚለኝ ነገር የለም። ነገር ግን ኤርትራ ደግሞ መንፈሷ ካገመገመ ማግስት  በዛ እኔ አስበው በነበረው መስመር ከመጣች ደግሞ እንደ ገና እማልሞግትበት መንገድ የለም። ሌላው ግን አንድ ሰው ውደዱልኝ ሰልለኝ አልወድም፤ ጥይልኝ ስላለ አልጠለም። 

ያ ቢሆንማ በዬዘመኑ ጀኬቴን አዬቀያዬርኩኝ የስንት ፓርቲ ካድሬ በሆንኩኝ ነበር። ከዛ በላይ ሥርጉተ ሥርጉተ እንጂ ሥርጉተ በቀለች ወይንም ጥሩነሽ ወይንም ትሩፋት አይደለችም።

የራሴ ማንነት፤ መንገድ እና መርህ አለኝ። ለመንፈሴ ቅን የሆኑ እርህርህና ያላቸው ነገሮች ቅርቦቼ ናቸው፤ አብሶ ከ እግዚአብሄር ነው ብዬ ካመንኩኝ እጅግ ጠንካራ አቋም ነው ያለኝ። በአንጻሩ ውስብስብ ያሉ የኢጎ መረቦች ደግሞ ጠረናቸውን መርምሬ አላስጠጋቸውም። አጋጣሚው ቢያገኛኝ እንኳን በዳግም ያ መንፈስ አያገኝም።

አንድ ጀግና ከቅርቡ ያለውን መንፈስ ሲያቀርብ እንጂ ባሻጋሪ ወዲያ ማዶ ሄዶ ጀግናዬ ቀን ስለሰጠው ብላ ሥርጉተ አትቀበለውም። አብይን ዛሬ አይደለም ሥርጉተ የእኔ ያለችው። ለማንም እንዲሁ። ስታስከፉኝ ደግሞ ለማም ይሁን አብይ አይቀርም እንደ ግንቦት 7 ሙግቴ ይቀጥላል ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል እና … ዋናው ነገር በእኔ ውስጥ እኔን የፈጠረኝ፤ ያኖረኝ ንጥረ ነገር እንዲከለስ ወይንም እንዲበረዝ ወይንም ትውሰት ቅልውጥ እንዲሄድ አልሻም። በራሴ ውስጥ ትናንትም ነበርኩኝ ወደፊትም እንዲሁ … ለማምንበት ነገር ደፋር ነኝ ይህን አውቃወለሁኝ።  ስልት አልባ ነኝ ለማገዶነት … ይህንም እገነዘባለሁኝ።

ጠበቃዬም፤ ደጋፊዬም መዳህኒ ዓለም እና ድንግልዬ ብቻ ናቸው። እምነቴ ጽሙ ነው።
ውዶቼ //// ቀጣዩ በዲያቆን ዳንኤል ክብረት የመድረክ አመራር እና ሂደት የቀረቡ ዕይታዎች ስለነበሩ ተከታዩ በዚህ ዙሪያ ይሆናል … ዛሬ ትንሽ ከሃዘኔ ተገስ ስላልኝ ስጽፍ እውላለሁ ብዬ አስቤአለሁኝ። ቀጠሮ ነበረኝ ዛሬ አራዝምኩት። 

ክብረቶቼ --- ሰሞናቱ ብዙ የፈተኑኝ ነገሮች ስለነበሩ … ዛሬ ብዕሬም መንፈሴም ከዳመናዊ ሁኔታ ተሽሏቸዋል። ተፈጥሯዊ የሆኑ ነገሮች ነው የምወደው። ፍቅርም ሲባል ንጹህ መሆን አለበት የክብር ቅርጥምጣሚ ሽልንግ የሌለበት …

ክብረቶቼ ስለቋንቋ የኢሳቱ ጋዜጠኛ ኤርምያስ ለገሰን የሞገትኩትበት ሊንክ ነው … ከቻላችሁት አክላችሁ ብታነቡት ይያዝላችኋዋል - በአክብሮት።

ቋንቋ ማወቅ ሊቀ ለቃውነትነት እንጂ መወቀሻ ሊሆን አይገባም።

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው።

የኔዎቹ ክብረቶቼ ኑሩልኝ።
ማለፊያ ጊዜ።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።