የማህበረ አብይ ጉባኤ ... መሪ እና ፕሮቶኮል ሹም።

አንጄትን ቅቤ ያጠጣው የዲያቆን ዳንኤል ክብረት አገላለጽ ነው!


„ጥበብስ በቀደሙ ሰዎች ሁሉ ዘንድ ተመረመረች።“
(መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፵፱ ቁጥር ፩)
ከሥርጉተ ©ሥላሴ 31.07.2018
(ከገደማዋቷ ሲዊዘርላንድ)


በዲያቆን ዳንኤል ክብረት የሰሞናቱ የማህበረ አብይ ጉባኤ የመድረክ አመራር በርካታ ዕይታዎችን አነበብኩኝ። የፕሮተኮል ሹመነትም ተደማሪነትም አለበት። የሆነ ሆኖ ያው በእሱ ዙሪያ እጅግ በርካታ ውዝግቦችን ብራና አስተናግዳለች። እሱን በሚመለከት የተፈለገው ቢባል እኔ በራሴ ውስጥ ነበርኩኝ።  የወጣሁት ከእሱ ሰብዕና አልፎ ትዳሩ ላይ ወቀሳ ሲሰነዘር ግን በህግ አምላክ ብያለሁኝ። ጽፌማለሁኝ። በጣም መጠን አልፎ መሄድ አያስፈልግም። ትዳር ላይ የሚወሰድ ምንም ነገር የለም። 

ትዳር ከእግዚአብሄር እንጂ ከሰው አይደለም። የሰውም የእጅ ሥራ አይደለም የጣና ዘገሊላ ጉዳይ። እንዲያውም የሚስጢሩን ልቅናውን ብናወቀው ሌላ ዘሃ መጎተት ባላስለፈገን ነበር። አገርም በአህቲ መንፈስ ትጸድቅ ነበር። „ጋብቻ ቅዱስ መኝታውም ንጹህ“ ይላል አካል የሌለው የእግዚአብሄር አገልጋይ፤ ቢያንስ ይህ የህይወት ቃል አብሶ የተዋህዶ ልጆች ሊያከብሩት ይገባል። ወቃሽ ጸሐፊው የተዋህዶ ልጅ ስለነበሩ። 

ከዚህ በመለስ አሁን ትልቅ ቦታ ስለተሰጠውም ነው ሊያሰኝ አይችልም 7ኛ መጸሐፌ "ርግብ በር" ላይ መልካም ነገር ስላገኘሁ ሃሳቡን ለማስረጃነት ተጠቅሚያለሁኝ። እኔ ቅንነት ባለበት ቦታ ሁሉ ዳር ደንበር የለኝም።

ወደ ጉዳዬ እንብርት ስገባ መቼም ፈታኝ ነው፤ አደባባይ ላይ የተሳታፊን ጥያቄ ማስተናገድ። እኔ አይቼ አላወቅም በሰለጠነው ዓለም። አሁን የሆነው እንደዛ ነበር። ኢትዮጵያ ግን በዛ ሰሞን ዶር ገዱ አንዳርጋቸው የደሴን ከተማ ነዋሪ አዳራሽ መሰብሰቢያ ጠፍቶ ያው ሜዳ ላይ ስብሰባ ተካሂዶ ጥያቄ እና መልስ ሲስተናገድ አይቻለሁኝ። ደሴም ያው ዕጣዋ የኩሬ ውሃ ሆና ለ27 ዓመት መገደሟን እግረ መንግዴን አስተውያለሁኝ።  

እርግጥ ነው የገበሬ አደራጅ ስለሆንኩኝ ገበሬ መንደር ዋራካ፤ ሾላ፤ ባንባ ሥር አዳራሻችን ነበር። እዚህ የሥልጣኔ ጫፍ በደረሱ አውሮፓ እና አሜሪካ ግን ፈጽሞ አይቼ አላውቅም ነበር። ውይይት እንዲህ ሲካሄድ። ንግግር ብቻ ሳይሆን ጥያቄ እና መልስም ነበር።  በአዳራሽም ቢሆን ህዝቡ ብዙ ነበር። የ አንዲት ትንሽ ከተማ ህዝብ ይህል ነው የነበረው። አሜሪካ ይህን ያህል ሰው ስለ አገሩ ያገባኛል ማለቱ እራሱ አንዱ አዲስ የድል እርካብ ነበር።

ስለሆነም ይህን መሰል ሂደት መምራት መርግ ነው። እንዲያውም እኔ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ተሳክቶለታል ብዬ ነው እማስበው። እንኳንስ ሊያስወቅሰው። ዕደሉንም ለሁሉም በእኩልነት ለማስተናገድ ሞክሯል። ስለዚህ በእኔ እይታ የተሰጠውን ሃላፊነት ተወጥቷል ብዬ አስባለሁኝ። ግድፈት አላዬሁበትም። 

ይልቁንም አንጀቴን ቅቤ አጠጥቶኛል። ሰው ልብ አላለው ይሆናል። እኔ ግን የእኔ የልቤ አሰኝቶኛል። ያም ሚዲያ ያላቸሁ የሌሎችን ነፍሶች ዕድል አትሻሙ ያለው ነገር ነበር። አቤት እንዴት የልብ አደርስ ውሳኔያዊ ቃለ ምህዳን ነበር። ቃለ ህይወት ያሰማልኝ ብያለሁኝ።

ዛሬ የአቶ ጆዋር መሃመድ ቀን ነውና አሁንም በነካ እጄ እሱን ላንሳ ፈጣሪም አውጥቶታል በዚህ ዘመን ተከብሮ ለመቀጠል፤ ለፖለቲከኛው እና ለታታሪው ሁሉ የአብይን መንፈስ ሞገዱን ከመቀበል መራቅ ዋጋ ስለሚያስከፍል። ዋጋ ማስከፍል ማለት ደረጃቸው ከፍ ብለው የነበሩት  ሙጣጭ ሲሆኑ እንደገና አገግሞ ለመነሳት ፈተናው እጅግ ከባድ ነበር። ታች ለነበረው፤ ሚዲያ ለሌለው ግን ያው ነው። ተቀበለው አልተቀበለው ድሮም ድካም ያለው ነው አሁንም በዛው በታካች ህይወቱ ይቀጥላል።
  • መባጃው።

አቶ ጆዋር OMN ያህል ሚዲያ አለው። DW BBN VOA ህብር መደበኛው ደግሞ አቶ ጆዋር አህመድ ነው። አቶ ሁሴን ያሲን የመሰለ ሊሂቅ ያላት አገር፤ ሚዲያ የሌላቸው ሊቀ ሊቃውንታት ስንት እያሉ ጉሮሮ ያለው ተጨማሪ ጉሮሮ ተከፍቶለት ያው የተለመደ ድግግሞሽ ሲዘፍንብን ነው የተባጀው።  

ሌላውም ጋዜጠኛ ሳዲቅ ሚዲያ አለው፤ ለህብር ራዲዮን ደግሞ እሱ ተንታኙ ነው። ሌሎችም የግንቦት 7 ሰዎችም ቢሆንም እንዲሁ ነው። ኢሳት ራዲዮ እና ቴሌቪዥን፤ ትንሳዬ ራዲዮ፤ ፓልቶኮች፤ አባይ ሚደያ አሏቸው፤ በዛ ላይ ደግሞ ሌሎች በተደራቢነት ወዘተረፈ ናቸው።
  
እርግጥ ነው አንዳንድ ግድ የሚሉ ሁኔታዎች ይኖራሉ፤ ለምሳሌ የውጭ ሚደያዎች አቶ ልደቱ አያሌውን ስለማይፈቅዷቸው ከሳቸው ጋር የሚደረግ ዲቤት ሲኖር ይህን DW VOA ቢያደርጉ የተገባ ነው። ነገር ግን ግራ ቀኝ ሚዲያ ያላቸው እዛው በጋዜጠኝነት፤ በመሪነት፤ በተዋይይነት፤ በአወያይነት መጠነ ሰፊ ዕድል እያላቸው ኢትዮጵያ ሌላ ሊሂቅ፤ ሌላ ድምጽ የሌላት ይመስል በድግግሞሽ ታክተን ባጀን።

ብራናም እንዲሁ ነው፤ ያ መጠነ ሰፊ የድምጽ ጊዜ እያለ ብራና ላይም የትም ቦታ የእነሱ ትንፋሽ የክብር ክብር ነው ይለፉ ለዛውም በሽሚያ ነው። የፈለገ አፍራሽነት ይጻፉ ንጉሦች አይደሉ ለጥ ተብሎ ይወጣላቸዋል።

ሌሎች ሽምያው ቀርቶባቸው አንዲት ቆራጣ ነፍስ የሚያሰጠጋ ቢገኝ ያም አይፈቀደም። ስለምን የመኳንኖች ቃለ ምህዳን ብቻ ነው ለኢትዮጵያ ፖለቲካ የሚያስፈልጋት። 

ሞኳንንቶች፤ መኮነንኖች ሁሉጊዜም ማይክም ሰግዶ አድግድጎ ከእነሱ ጋር መባጀቱን የከረፋው ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በ43 ዓመት አንዲት ቀን በተገኝችው ጠበለ ጣዲቅ ደግሞ አብረው ጋዜጠኞች ሲጋፉ ነበር ደፈር ያለ ነገር የተናገረው። ወንዳታ! „ሚዲያ ያላቸሁ የሌሎችን ነፍሶች ዕድል አትሻሙ“ ተባረክ።
 
ያሳፍራል። የውነት ያሳፍራል። ምን ችግር አለው አቤቱታ ያለው በጹሑፍ ጽፎ ፌስ ቡኩ ላይ መለጠፍ። የፈለጉትን ይጻፉ ከልካይ አጋጅ የለባቸውም ለአሻቸው ድህረ ገጽ መላክ ነው። በቃ ከዛ በአንድም በሌላም ለጠ/ ሚር ዶር አብይ አህመድ ይደርሳቸዋል። 

የሚቀበሉትን ይቀበላሉ፤ የማይቀበሉትንም ደግሞ መንገዴ ይሄው ነው ብለው እንቅጩን ይነግራሉ። እኔ እጣ ነፍሴን ስደክምበት የባጀሁበትን የሽግግር መንግሥት በሚመለከት እንቅጩን ፍርጥ ተደርጎ "እኔው አሸጋግርላችሁ-አለሁኝ፤ የእኔ አልትሜት ግብ ይሄው ነው። እሱን ሲደርስ ታዩትአላችሁ።" ብለዋል።

 ይህን ቤንሻንጉል ጉምዝ ላይም ተናግረውታል ካልሰራንላችሁ በቀጣዩ ዙር ምርጫ አውርዱን ብለዋል። በመቀጠልም „ብቻ እኛ እዬተደራጀን ስለሆነ ተሸናፊ እንዳትሆኑ ሥራ አልጀመረችሁም ጊዜው እያለፋችሁ ነውም" ብለዋለ። ይህንንም እኔው ተናግሬ ነበር። „ቁርጥ ያጠግባል“ እንዲሉ ጎንደሬዎች ፍርጥ አድርገው ተናግረውታል። 

እግረ መንገዱንም የሰሞናቱ የዶር መራራ ጉዲና „የተጽዕኖ ፈጣሪዎች አንድነት መንግስት“ ህልም በዛው መቃብር ተልኳል። ውሳኔው ግን ምክንያታዊ ነው። አሳማኝም ነው። በፍርስራሽ ላይ መተከዝ የተለመደው ጨዋታ ዘመን በቃህ ብሎታል።

በእርሾ ላይ የበሰለ፤ የሰከነ ተግባር መከወን ኢትዮጵያ አጥታው የኖረችው መሠረታዊ ጉዳይ ነውና። ሌላውም ለአንድ ተልዕኮ ማስፈጸሚያ የሆኑ የሃሳብ ፍሰቶች ስብስብም ተፈጥሮ ካልተሳካ መፍርስ ስንቅና ትጥቅ መሆኑ ይታወቃል። ለዛውም የሰው ግብር ተከፍሎበት። ከሁሉ በላይ የቂም የቁርሾ መወጣጫ እና ማካካሻ ፖለቲካ አንድ ቦታ ላይ ማክትም ነበረብት። ይህም ብቻ አይደለም ከዚህ ሂደት በኋዋላ በኑሯችን ላይ የሚፈጥረው መከፍል። አጋ ለይቶ ያለው ዱላ ሁሉ አቤት ስንት ፍዳ ታለፈ? አሁን ከቅንጅት ክስመት ማግስት የሆነው እኮ እጅግ አሳዛኝ ልዩ የመከራ ቀንበር ነበር። ስንት ማህበራዊ ኑሮ ነው የተናደው። 

 ይህም ብቻ ሳይሆን ከ60 በላይ ፖለቲካዊ ድርጅት ተሸከመን በአንድ አጀንዳ መስማማት አይቻልም። ያሰብነው ንጹህ መንፈስ ሲመጣ እንኳን ምን ያህል ጋዳ ነበር ለመቀበል? ጮኽቱ እንኳን ችግር ተቃለለ ሳይሆን አጀንዳችን ተቀማን ነው። ብቻ በዚህም እኔ ቅቤዬን ጥጥት አድርጌያለሁኝ። ሁለት ጃንቦ ቅቤ ሲያጋጥም ... 

ወደ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት በትረ ሃሳብ ስመጣ የተገባ ውሳኔ ነበር። የፕሬስ ጉባኤ ከነበረ ትክክል ነው። የህዝብ ከሆነ ግን ዕድሉ ለህዝብ ነው መሰጠት የነበረበት። እኔ ብሆን እንዲያውም አልፈቅድም። እኔማ ሰብሳቢ ስሆን እጅግ ቆራጥ ነኝ። ደቂቃ ዝንፍ የለም።

ስለሆነም የዲያቆን ዳንኤል ክብረት ውሳኔ ትክክል ነበር። ለነገሩ ዕድሉን ከሰጠ በኋዋላ ነው ይህን የተናገረው። ምክንያቱም የሚዲያ ባለቤቶች ብዙ ዕድል አላቸው። የሌላቸው ነው ዕድል እንዲያገኙ የሚያስፈልገው። በዛ ላይ ሴቶች ደፍረው ከወጡ ቅድሚያ ለእነሱ የተገባ ነው።

ሌላው የገረመኝ አገር ቤት ሄደህ በክብር ቁጭ ብለህ ተነጋግረህ፤ ተወያይተህ መጥተህ አሁን ደግሞ ጥያቄ አቅራቢ መሆን በጣም የሚገርም ነገር ነው። አገር ከሄድክ፤ ሞጥረህ አደራጅተህ፤ መስኩንም ታውቀዋለህ፤ ማደረጀቱም ነበርክበት ስለዚህ ሃሳብን ለማሳካት መሬት ላይ መሥራት እንጂ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ የሚጠዬቁበት ምክንያት አልነበረም።

ሌላው ክብርን ማስከበርም ያስለፈልጋል። „ሁሉ ተፈቅዶልኛል፤ ግን ሁሉም አይጠቅመኝም“ በዝምታ ውስጥ ያለ ክብር ማንም አያገኘውም። ዝምታ ወርቅ ነው እያልኩ አይደለም። ደረጃን ማስጠበቅ። ሚዲያ አለህ። ድርጅት አለህ። አክቲቢስቶች አሉህ። ኢህዲግም እንዳተው አንድ ግንባር ነው። እቅሙ ካለህ ተደራጅ እና ግጠመኝ ብሏል። እና የምን እሰጣ ገባ ነው። የፖሊሲ ለውጥን በሚመለከት በመንግሥት ከተያዘው ውጪ አቅም ያለው ፖሊሲ የማመንጨት ሃሳብን፤ ቀርፆ ለህዝብ ካቀረበ ህዝቡ ይወስናል። ጠቃሚ ሃሳብ ያለው ደግሞ ባለው ሚዲያ ፍላጎቱን ምኞቱን መግለጽ ነው።
  • ድግግሞሽ።

ችግሩ ኢትዮጵያ ውስጥ አትኩሮታችን ተጣፍቷል። ሽርሽር በዛ በሚባልበት ቦታ ሁሉ ብዙ የነገ ቀኖች የሚአሳዩ ማይክሮስኮፖች ነበሩ። 

 የመክፈቻ ንግግሩ ጭብጥ፤ የሚሊዬነም አዳራሽ ድርብ ንግግር ፍሬ ነገር፤ የመቀሌ፤ የጎንደር፤ የባህርዳር፤ የጋንቤላ፤ የአዋሳ፤ የጉራጌ ዞን፤ የሲዳማ፤ የባሌ፤ የደንቢደሎ፤ የጅጅጋ፤ የአስመራ፤ የአፋር፤ የቤተመንግሥት፤ የጸጥታ አካላት ስብሰባ፤ የዲታዎች ጉባኤ፤ የመምህራን ኮንፍረንስ፤ የወርቅ ተሸላሚ ተማሪዎች ጉባኤ፤ የተፎካካሪ ፓርቲ አካላት፤ የዬክልሉ የሽማግሌዎች እና የተዋቂ ሰዎች የትውቅቅ ጉባኤ፤ ዶር ምህረት ደበደበ ያዘጋጁት ህዝባዊ ስብሰባ፤ 

የአረብ ኢምሬት፤ የግብጽ፤ የሱዳን፤ ሁለት ጊዜ ነበር ጁቡቲ፤ የሳውዲ፤ የኡጋንዳ፤ የኬንያ፤ የአማራር እና የአስተዳደር ጥበብ የተመክሮ ስብሰባ፤ የፓርላማ ንግግሮች እና ለተነሱ ጥያቄዎች የተሰጡ መልሶች፤ የጥበብ ሰዎች ጋር የነበረው ምክክር፤ አፍሪካ ነክ ጉባኤዎች፤ የመስቀል አደባባይ ንግግር እንዚህ ሁሉ የነገይቱን አፍሪካ፤ ኢትዮጵያ ራዕይ ያመላከቱ ነበሩ። በውነት ለውጥ ፈላጊ ከነበርን። ግን እኛ ለውጥ እምንሻ ለውጥን በጽኑ የመንፈራ ነን። 

ሥራዬ ብሎ ላዳመጠው ማስታወሻ ይዞ ለመረመረው ያለተደፈሩ ጥቂት አመክንዮዎች ብቻ ናቸው። ቴዲ ያነሳቸው፤ በተደጋጋሚ ዓለምዐቀፉ ጋዜጠኛ ዓለምነህ ዋሴ የሚያነሳው የፕሬስ ጉአባኤ እኔ አንኳን ይህን ሞግቼዋለሁኝ፤ ገፋ አድርገው ሰርተው ቢጠዬቁ ይሻላል፤ የአገር ውስጥም የጎረቤትም ያላላቀ ጉዳይ አለ ብዬ ማለት ነው። 

ብቻ እጅግ በርካታ በ20 ዓመት ወደፊት ገፋ አድርገን ልናስባቸው የማንችላቸው ቁምነገሮች፤ ውሃ ያልነካቸው እሸት አዳዲስ የፖሊሲ ሃሳቦች ብቻ ሳይሆን ለጉዳዮች፤ ባለቤት አካል እዬፈጠሩ በመሄድ ሥራ እና ሠረታኛን በማገናኝት እረገድ ከሚገመተው በላይ መጠነ ሰፊ የተግባር እርሾ እዬተዘረጋ ነው… ስለምን አፋር ላይ የበጀት፤ የፕርጀክት ጥምር ዝውውር ተደረገለት? 

ማንም መሪ ቢሆን ያደርገዋል ተብለው የማይታሰቡ የቀደሙ፤ የሰለጠኑ፤ ዘመናይ አማራሮች ነፍስ እዬዘራበት ነው… ፓርላማው። ለዛውም ባዶ ካዝና ተረክቦ፤ ማህበረ ደራጎን፤ የዲያስፖራው መታመስ፤ ሚዲያው ያውርደው የነበረ በረደ፤ የአገር ውስጥ እና የውጪ የፖለቲካ ድርጅቶች ሃያስያን „የጉልቻ ቢለዋወጥ ወጥ አያጣፍጥም“ አስናፊ ትጥቅ አስፈቺ እድምታ፤ 

ቢሮክራሲያዊ ሳቦታጅ፤ መፈናቀሉ፤ ሞቱ ወዘተ ይህን ሁሉ ተሸክሞ የህልም ያህል ተስፋን የሚያፋፉ እጅግ ድንቅ ክንውኖች ባለታወከ፤ በተረጋጋ፤ በሰከነ፤ በቅጡ በታቀደ ሁኔታ እዬተከወነ ነው። ዓለም ዐቀፉ የሰብዕዊ ድርጅቶች ሳይቀሩ ተመሰጥናል እያሉ ነው።
እስከ አሁን የተካሄዱትን ጥምር በፈተና ውስጥ ያለፉ ግን የሰማይ ስጦታዎችን እያዬዩ ምንም እንዳልተሰራ ተደርጎ ጥያቄ ቀርቧል። በ አንድ ንግግር ውስጥ እንኳን ነገን የሚያሳዩ መስተውታዊ ንድፎች ነበሩ። 

ከዚህ ቀደም በተለያዬ ሁኔታ የቀረቡ መልስ የተሰጣቸውም በድጋሚ ቀርበዋል። ይሄን ጉዳዬ አለማለት ካልሆነ በስተቀር የተለዬ ሃሳብ ቢኖርማ መቼ እስከዛሬ ድረስ የህዝብን ሙሉ መንፈስ ለማግኘት ይህን ያህል ዳገት ባልሆነ ነበር …  

ዕድሜ ልክ ዝግጅት የተደረገበት መሰናዶ እንደለ፤ አቅጣጫ ነዳፊ አቅም እንዳለ፤ እሰከ አፈጻጻሙ ድርስ መጠነ ሰፊ ሲናርዮና ቢጋር ተሰናድቶለታል ብዬ አስባለሁኝ። ይልቅ „ለምዶብህ“ ነው እንጂ ትክከለኛው አገላለጽ ነበር።

ያልተደገሙ፤ ያልተነሱ፤ በአገር ደረጃ በጠ/ ሚር ዙሪያ ያሉ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮችን ማንሳት ሲጋባ ሲደመጥ የተባጀውን መሆኑ የጊዜ ብክነት ነው። የማታገኘውን ሰው ስታገኝ ያችን ደቂቃ መጠቀም ልባምነት ነው። 

ለዚህ ነው እኔ ብጹዕን አባቶቼን አብራችሁ መሄድ አለባችሁ፤ አብረው እንዲሄዱም ጫና አድርጉ ያልኩት። መለዬት አቃተን። የማይገኘውን ዕድል ብክነት ተገቢ አልነበረም። አገር ቤት ያሉ ተፎካካሪዎች ሲዘመኑ ውጪ ያሉት ገልብጠው ባለ መንፈስ፤ ባለሟል ሆነው አረፉት። ከቶ ተመክሮ ብስለት - ብልህነት የሚባለው ለዚህ ቀን ካልሆነ ለመቼ ሊሆን ነው?

አሁን ግንቦት 7 አርበኛ አንዳርጋቸው ጽጌ ባስገኘው መንፈስ እንደሚንቀሳቀስ አሳምሮ ያውቀዋል። ነዳጁን የሞላው እሱው ነው። ያቺ ወርቃማ ጊዜ የግንቦት 7 ሙሉ ደምጽ ፕሮግራሙ በቤተ መንግሥት የተረጋጋጠችበት ቀን ነበረች። 

ስለዚህ አሁን የሌሎችን ጊዜ መሻማት አያስፈልገውም ነበር ራሱ ግንቦት 7። ሞረሽም እንዲሁ። ጠ/ ሚሩን ላያገኝ ይችላል ሞረሽ አገር ቤት ሄዶ በነበረበት ጊዜ። ግን ም/ ጠሚሩ ወይንም ዶር ገዱ አንዳርጋቸውን ያገኛል። ያ በቂ ነው። ምን ያጋፋል አሁን። 

ተሄደ እኮ ከተሄደ ሙግትህ እንዲሳካ የአንተን መንፈስ ማደራጀት ነው መሬት ላይ። ግንቦት 7 ለበጎ ሆኖለት አርበኛ አንዳርጋቸው ሲፈታ ዕድል አገኘ፤ የተሰካ ተግባር ተፈጸመ። እኔ እንዲያውም ዲሲ ላይ በነበረው አጠቃላይ መንፈስ ሳዬው የግንቦት 7 መንፈስ በጉልህ ነው የነበረው። ስለዚህ ቅጽልነት አያስፈልግም ነበር። ዋናውን መንፈስ ጭንቅላት ከሆነክ … አንድ ሰው ያገኘውን ክብር ማስጠበቅ ይኖርበታል።

መጠዬቅ ልማድ ከሆነ ደግሞ በአገር መሪ ደረጃ ሊፈታ የሚገባው፤ ያልተነካ አጭር፤ ግልጽ፤ ቁርጥ ያለ ጥያቄ። ለጥያቂ ካሊም፤  50 ክንድ ጋቢ አያስፈልግም። ሞናትነስ ነው የሚሆነው። የሆነ ሆኖ በሊሂቃን በሃሳብ ውስጥ መጽናት አላዬሁም። ህሊና ላለው ሰው ምን ያህሉ ድርጅት በተሾሙ ማግስት በነፍስ ወከፍ የ100 አመት ፍላጎቱን ጭኗቸዋል። ሰው ግን ይህን ሁሉ ይችላልን በሚያስበል ደረጃ። አሁን ደግሞ በዙር ተመለስ መጠዬቅ የተገባ ቢሆንም ደረጃውን የጠበቀ ቢሆን መልካም ነበር። 

ሌላው ጠ/ ሚሩ ሊሳሳቱ፤ ግድፈት ሊፈጽሙ አይችሉም ብሎ የማሰብ ነገር። በተጨማሪም ይደክማቸዋል፤ መንፈሳቸው ሲዝል መልሳቸው አቅም ያጣል ብሎ አዘኔታ እና ሃላፊነት አለመሰማትም ያዬሁት ግድፈት ነበር፤ ብቻ እኛ በመንፈስ አልተደራጀነም ስለሆነም በመንፈስ በአግባቡ ከተደራጀ ሞጋች መሪ ጋር በእኩል መጠን ለመቆም አልተቻለም።

ሌላው እኔ ይህን ቦታ ብይዘው ምን አደርጋለሁ ማለትም ይገባል። ምንስ ከዚህ ቀደም አድርጌያለሁ ብሎ ማሰብ ይገባል። ሁለት ፍሬ ሰው ሰብሰብህ በማወያዬት በቀጣይ ተጨማሪ አባል አፍርተህ ተጓጉተህ ለመገኘት በሌለበት አሁን ይህን ያህል ነገር … ውጪ ላለነው ይገርመናል። ለምንታዘበው ማለት ነው።

ያ ሁሉ ህዝብ እኮ በራሱ ጊዜ ነው እንደዛ የተመመው። በቃ። የተደረገለት ነገር የለውም። በልቡ፤ በመንፈሱ ያሰበውን ለማድረግ የቆረጠ፤ በወጉ የተሰናዳ ዝግጁ መንፈስ ሲያገኝ አብሮ ሰንበትን ፍንክንክ ብሎ አሳለፈ።

በዚህ ሂደት ግን እንደ ሰው እንጂ እንደ መላዕክም ማዬትም አይገባም።  ቤቱን፤ ትዳሩን ለመምራት የተሳነው፤ ወይንም ከአንድ ወዳጁ ጋር ለመዝለቅ ያልቻለ ነፍስ ግዴታን በሌላው ሲጭን ሰው መሆናቸውን አለመቀበልም ነው።

ሌላው ቁም ነገር ከኦህዴድ የመጡ መሆናቸውን ማወቅ። የግንባሩ ሥራ መሪ መሆናቸውን ማወቅ። ወቅቱ የሽግግር ስለመሆኑ መቀበል የተገባ ነው። በአጠቃላዩ ሁኔታ ከተጠበቀው በላይ ነው ዕድል የተገኘው። የትኛወም ፓርቲ ሥልጣን ቢይዝ የዚህችን 1/10 ኛውን ያህል የሃሰባብ ልቅና፤ የንድፍ ልቅና፤ የራይ ልቅና፤ የስኬት ልቅና፤ ሁሉን የማቀፍ አቀራረብ፤ የፍላጎት ቅደመ ተከተል ልቅና አይኖርም ነበር። አውነቱ ይሄው ነው። 

እምቅ ሃብት ያላቸው በሥርህ ሊኖር ይችላል። ግን ቁንጮው ካለወቀበት አይሆንም። ይህ ሁሉ የሆነው እኮ አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ሥልጣናቸውን ባሰረከቡ 3 ወራት ውስጥ ነው። መሪ ያስፈልጋል።  

የሰብሰባ አመራር ...

ሰው በዬዲቂቃው ሁሉንም ለማዳረስ እንዲህ በሚተጋበት ሌትና ቀን በሚሰራበት፤ በዛ ላይ የምኝታ ጊዜ የሰዓት ለውጥም አለ፤ ይህም ሆኖ በዚህ ዓይነት ብቁ መንፈስ ውስጥ ዲያቆን ዳንኤል ክብረት ጥሩ መርቷል። ጥሩ ኮኦርድኔት አድርጓል። ጥሩም አስተዳደሯል። 

መወሰንም ይጠይቃል ስብሰባ መምራት። ውሳኔው ከጊዜ ጋር ነው። ጊዜም ብቻም አይደለም መላሹ እዬተዳከመ ከሄደ መከወኛውን ያዝለዋል። ስለዚህ ቁርጠኝነት ያስፈልግ ነበር አርክቶኛል። ሰዓቱን በሚገባ ይቆጣጠር ነበር። እንደ ስብሰባ መሪም እንደ ፕሮተኮል ሹምም ነው የሠራው። ስብሰባ መምራት ራሱን የቻለ ሙያ ነው። ፕሮቶክልም እንዲሁ። ሁለቱንም አቀናጅቶ መርቶታል። የተሳካም ነበር። ውጤታማ ነበር። ፍቅርን በማሻገር፤ ፍቅርን በማስተላልፍ የሃላፊነት መንፈስን በመፍጠር ግዴታ እና መብትን በማሳወቅ ጥበባዊ ነበር።

አብዛኛው ሰው በአንድ መንፈስ ውስጥ ነው። ይህን ለማስቀጠል ኢንባሲዎችም ያን ጉርሽጣዊ አንባርጫቃ አስወግደው የተስተካከለ አቀራረብ እና አያያዝ ሊኖራቸው ይገባል።

 ውጪ የሚገኙ የፖለቲካ ድርጅቶችም ካድሬዎቻቸውን በሙሉ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት የማስተካከል፤ ፕሮዎቻቸውን የመሞረድ፤ ሚደያዎቻቸውን ኢትዮጵያዊ የማድርግ ግዴታ ይኖረባቸዋል። መቼም የኢትዮጵውያን የሁሉ ነበርን ብለው እንደማያስቁኝ ነው … 

የፖለቲካ ድርጅቶች ካድሬ ጋዜጠኞቻቸውን በፖለቲካ ተግባር ብቻ እንዲተጉ ሌሎች ጋዜጠኞች በነፃነት የሚሰሩበትን መንገድ የመክፈት ድርሻ አለባቸው። ተደባልቋል ጋዜጠኝነት እና ካድሬነት።
  • ልባም ነገር። 


ሌላው በዚህ ገለጣቸው በሚገርም ሁኔታ ምንም ዓይነት እንግሊዘኛ ቋንቋ ዶር አብይ አህመድ አልተጠቀሙም። እጅግ የገረመኝ ማድመጥ መቻላቸውንም ያመሰካርኩበት ነበር። አትርፈዋል፤ ተልዕኳቸውን አሳክተዋል። ፍቅር ቀንቶታል፤ ሴራ ደግሞ ጨልሞበታል። ምክንያቱም ሌላ መንፈስ ውስጥ ከፍ ዝቅ የሚያደርግ ጉዳይ ከእንግዲህ ስለማይኖር። አብሶ ባለቤት ያልበራቸው፤ በጸጥታ ውስጥ ለነበሩ ሰሞናተ ትንሳኤ ነበር ለያውም የመንፈስ። ተመስገን። ሥራችንም አቃለውልናል። 

ማስታረቅ የለመደባቸው። 

ሌላው በሰላም ፋውንዴሽን ላይ ስለ ዲያቆን ዳንኤል እና እስልምናን ለማገናኘት ባለቅኔው ጠ/ ሚር የሄዱበት መንገድ የሚገርም ነው። ይህንም ሰው አላስተዋለውም። ክፍተት ነበር። እና ዋሽቶም ማስታረቅም ያውቁበታል። ዶር/ ወርቅነህ ገበዬሁን ተቀበሉልኝም ሌላው ተደሞ ነበር። እኔ አይደለሁም ጠ/ ሚራችን ዶር ለማ መግርሳ ናቸው ሌላው ሚስጢር ነበር፤ ይህን እኔም በተደጋጋሚ ጊዜ ጽፌዋለሁኝ። ለዚህም ነው አቤቱታዬ ግልባጭ ለሳቸው ያደረኩት። 

ብቻ ተያያዥ የሆኑ አገራዊ ጉዳዮች ማዕካለዊ በሆነ ሁኔታ ተከውነውበታል። ሁሉ ረክቷል አይጠበቅም። የታቀውሞ ጉልህ ሃሳብ አለ። ከዚህ ጹሁፍ ቀጥሎ አቀርበዋለሁኝ። በዚህ መንፈስ ሥማቸው ጎልቶ ያለወጡ ነፍሶችም ቅሬታ ይቋጥሩ ይሆናል። ለእኔ ግን ሃይል፤ አቅም ሊፈጠር የሚችል መንፈስን ማብቀል ስለሆነ መሰረታዊው የተልዕኮው ድርሻ ይህን ስላሳካ መልካምነት ጎልብቶ ታይቷል። የቀሩትም ቢሆኑ በ አብይ ማህበረ ጉባኤ መንፈሱን መፎካካራቸው፤ መመጎታቸው ጥንካሬን ያመነጫል።

ከዚህ ላይ አንድ ምሳሌ ላንሳ መጀመሪያ ላይ ኮ/ መንግሥቱ ሃይለማርያምን አክብረው ነበር የተናገሩት። እስኪገርመን ድረስ። አሁን መንግስቱ ነበር ያሉት። ስለምን? እኛ የፈጠረንው ጫና ስለነበር። ከ እህቴ ጋርም ተዋይተንበታል። እሷም ደንግጫለሁኝ ብላኛለች። ምክንያቱም ሌላ ነገር ስለ አብይ መስማት አልፈለግም ስለቴ ደርሷል ባይ ናት። 

እኔ ግን በዛው ሰብዕናቸው እንዲቀጥሉ ቢተጉበት ክብራቸውን ያስጠብቅላቸዋል ብዬ አስባለሁኝ። አክብሮ መነሳት አሰከብሮ ያዘልቃል።  የኢትዮጵያ ሚደያዎች ኢሳትን ጨምሮ አንተ አንቺ እያሉ ነው የሚወያዩት፤ ልጆች ከዚህ ምን ይማለራሉ የለም፤ ትውልድን እዬናድ የትውልድ ተስፋዎች ነን መቼም ወጣ ገብነት ነውና። ይህንን እኔ ለልጆች ለጻፍኩት መጸሐፍ ላይ በሰፊው ሰርቸበታለሁኝ።

የመንግሥት ሚዲያም እንዲሁ ነበር። ሰው እኮ ሲፈጠር ተከብሮ ተፈጥሯል። በአምሳሉ ፈጣሪ ሲፈጠረው ቤተመቅደሱ አድርጎ ነው። የወደድነውን ሰብና ማስቀጠል ግዴታቸው ነው ዶር አብይ አህመድ ሆኖ ዶር ለማ መግርሳ። ልሳላሴያቸው፤ ትህትናቸው ነው የሚያምርባቸው። እራሱ አንበሳ የሚሆኑበት ጊዜ ሲመጣ ራሱ ያመርባቸዋል በተፈጥሯቸው ውስጥ ከሆኑ። ቀልዱም ፈገግታውም ውበቱም የሚኖረው እንዲሁ።

ሌላ ያስደሰተኝ የጠባቂዎቻቸው ወጣትትንት፤ ንቅት፤ ቅልጥፍና፤ የሃላፊነት ስሜት ዋው! ድንቅ ነው! 

 ለማንኛውም ፈሪዋ ሥርጉተ በሰላም ያግባልን! አሜን!

ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር ነው።

የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።