መስዋዕትነትን ማመጣጠን፦ መቀነስ በትግል ዓለም ውስጥ ሊታቀድ የሚገባው በኽረ ጉዳይ ነው።

 

መስዋዕትነትን ማመጣጠን፦ 
መቀነስ በትግል ዓለም ውስጥ 
ሊታቀድ የሚገባው በኽረ ጉዳይ ነው።
 
እንዴት ናችሁ የአገሬ ልጆች።
 
ደህና ናችሁ ወይ። በለውጥ ጊዜ የሚሆን ነው እዬተባል የትውልድ አጨዳ እና ጉስቁልና፤፦የኢኮኖሚ ድቀት እና እንግልት እንደ ጀብዱ ባይታይ ጥሩ ነው። ትግል ላይ ያለውም ቢሆን ትርፍ እና ኪሳራውን መዝኖ አትራፊነት ሚዛን እንዲፋ ጥበብን ማከል ይገባል።
ሌላው አቅም የለሹም አቅም እንደሌለው አምኖ በፈቃዱ በሚችልበት መሳተፍ ብልህነት ነው። ምክንያቱም አዳዲስ ተቋም ተፈጥሮ ለስኬት ሳይበቃ ሲተን በዛ ውስጥ የፈሰው አቅምና የተገበረው ህይወት እውቅና ሊሰጠው ይገባል። በተጨማሪም ተደጋጋሚ ግድፈት እንዳይኖር ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል። አትራፊነት ከአመራራ አቅም ተመክሮ ይመነጫልና። የሆነ ሆኖ ለትግል፤ ለስኬት፤ ለሂደት እንደሚታሰበው ሁሉ ያ 50 ዓመት ሁሉ እንደ ጥንቸል ሙከራ የሚደረግበት ህዝብ መስዋዕትነቱ በቀነሰ መልኩ እንዲሆን ሊታሰብበት ይገባል። 
 
በዚህ የ50 ዓመት ተጋድሎ ድልን በመቋደስ ብቻ ተጠቃሚው ደቡብ ነው። መልካም ነው። ግን ይህም ሊጠና ይገባል። እንደ አንድ ፕሮጀክት ምርምር ሊካሄድበት ይገባል። የትውልድ ጉዳይ የሚያገባው ሁሉ ይሰብበት። የደቡብ ብልህነት ጠቀሜታው ይጠና። በጥሞና። ማገዶነትም እስከመቼ ሊሉ ይገባቸዋል የተማገደውን የሚማገደውን ማህበረሰብ እንመራለን የሚሉ ወገኖቻችን።
ለምሳሌ ኢዲዩ፤ ኢህአፓ፤ ሻብያ፤ ከፋኝ፤ ግንቦት 7 // እራሱ ኦህዴድ የትግል በዓቱ ስሜን ነው። ስሜነኞች ከትምህርት ተገልለው ሲታገሉ አቶ ኃይለማርያም ደስአለኝ ይማሩ ነበር። በኋላ የጠሚ ቦታ ለአቶ ገዱ፦ ወይንም ለዶር አንባቸው አልተሰጠም አቶ ደሳለኝ ኃይለማሪያም ጠሚር ሆኑ፤ በጦርነቱ ስንት ስማርት እንደወጣ ቀርቷል። የስሜን ህዝቡም ነበር የተማገደው። አሁንም ተማገዱልን የድል ቁንጮ በመሪት የሚል ዕድምታም አዳምጣለሁ። ፋኖ ዘገዬም ይባላል። ወዘተ ……
 
ዝም እምለው ትግል እንዳልጎዳ እንጂ አንድ ማዕከል ዕዝ በጥድፊያ ቢበጅ የዲሲ ፖለቲካ እንደ ጥርጥር ይሸበሽበዋል። ቅንጅን፤ አንድነት ሰማያዊን ያዬ። እራሱ ኦዲዮ አዘጋጅቼ በማዕቀብ ያስቀመጥኩት ተጽዕኖ እንዳያሳድር ነው። የሆነ ሆኖ የ120 ሚሊዮንን ኃላፊነት ፋኖ ይወጣ ጭነቱ በመሰዋት ልኬታ መታዬት አለበት። ጫካና ዱሩን ፋኖ አልያዘም ሁሉም በአካባቢው አልተመቸኝም ሲል ይሞግት። ቢያንስ ውጭ ያለው ኢትዮጵያዊ በፋይናንስ ሊረዳ ይገባል። አንተ ተጋፈጥ የድል ምክክር ገበርዲን እና ከርባት አዘጋጅተን እንጠብቃለን ፍትኃዊ አይደለም።
 
ሌላ የልጅ አስረስ ዳምጤን ፎቶ ያከልኩት ከእሱ ጋር የተመረቁ የደቡብ ልጆች ምን አልባት እስኮላር ላይ ሊሆኑ ይችላሉ። ፋኖ አስረስ ጫካ ባይገባ የከፋ የህይወት ገጠመግ ይኖረውም ነበር። የሆነ ሆኖ ከእሱ የፍትህ አገልግሎት የሚያገኙት ተጎድተዋል፤ ወላጆችም ጭንቅ ላይ ናቸው። ይህ የሆነው በሚሊዮኖች አማራወች ነው። ለአብነት ነው ያቀርብኩት። ተስፋ እማደርገውም እላፊ የማይሄድ የታረመ ወጣትም ነው። መሪነት እንዲህ ጥንቅ ያለ ሲሆን ህሊና ገብ ይሆናል።
 
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 
እግዚአብሄርም ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
22/05/2024
ለመማር በሁሉም መስክ መዘጋጀት ይገባ

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።