ዕውን የኢትዮጵያ የመንግሥት አደረጃጀት #ፌድራሊዝም ነውን?

 

May be an image of 1 person and text that says 'ዝም አንልም!! WE WILL NEVER BE SILENT Let's get together and stand against kidnapping!!'ዕውን የኢትዮጵያ የመንግሥት አደረጃጀት #ፌድራሊዝም ነውን? የት ቦታ ይሆን አማራ በቁጥሩ ልክ ውክልና ያለው። በራሱ በክልሉም ሆነ ከክልሉ ውጪ። ይህ የፋኖ #መቅድመ የመደራደሪያ አንኳር ነጥብ ሊሆን ይገባል። የፖለቲካ ውክልና #ይሉኝታ ሊገዛው አይገባም። ፈጽሞ።

"እግዚአብሄር በአንድም በሌላም ይናገራል ሰው ግን አያስተውለውም።"
የአማራ ህዝብ ደግነቱ፤ ችግርን ተሸክሞ መኖሩ መቀጫ እንጂ መመስገኛ፤ መከበሪያ አልሆነው። አሁን ያለው ሥርዓት ለዚህ የበቃው እኮ በአማራ ድምጽ ነው። ሌሎች የተከደኑ ጥረቶች ተዘሎ። ዕውነት ለመናገር አማራ እጁ አመድ አፋሽ ነው። ምንም ያልተደረገላቸው ጋዜጠኛ አቶ ታዲዮስ እና ወጣቱ ባለቅኔ በላይ በቀለ ለአብነት አሉ እንጂ።
 
ለእኔ ፌድራላዊት ኢትዮጵያ አይደለም። የፌዳሪዝልም ዕውነት ያለው አማራ ክልል ብቻ ነው። የቀደመው የመለሲዝም ክልሎች፤ የዛሬ የአብይዝም ተጨማሪ ክልሎች የፌድራሊዝም ጭላንጭል የለባቸውም። ድቅድቅ ጨለማ ናቸው። ገና ፊደል ያልቆጠሩ ልሙጥ። ልግጫ ነው። ደቡብ በጆግራፊ ነው የተደራጀው። ሌላው ደግሞ በተጫኝ #ዞጎች። ዕውነቱ ይህ ነው።
 
አማራ ክልል አርጎባ፤ አገው፤ ኦሮሞ፤ ቅማንት ልዩ ወረዳ፤ ልዩ ዞን አላቸው። በራሳቸው የእኔ በሚሉትም አካል ይተዳደራሉ። የሚገርመው የፖለቲካ ሥልጣን ውክልናው ዞጋቸው ሌላ ሆኖ ኮታው ግን እንደ #አማራ ይወሰዳል። የነበሩት የአገር መሪወች ሁሉ ውህድ ማንነት የነበራቸው፤ ወጥም የሆኑት አጤ የኋንስን ሳይቀር አማራ የሚከሰሰው እሳቸውም አማራ እንደሆኑ ነው።
 
ኮነሬል መንግሥቱ ኃይለማርያም ኦሮሞ ናቸው ነው የሚባለው። አጤ ኃይለሥላሴም ቅንጣቢ የላቸውም ከአማራ ነው የሚባለው፤ ግን የአማራ ገዢ መደብ ይባላል። አጤ ሚኒሊክም ውህድ ማንነት የነበራቸው ናቸው። አሁንም ሁሉም ክልል በጨቋኝ ብሄረሰብ ወድቆ #አህዳዊውም ሆኖ ተከሳሹ አማራ #አህዳዊነትን #ሊያመጣብን ይባላል።
 
ይህን ዕውነት ሊቃውንቱ የዲፕሎማሲውን ማህበረሰብ ሊሞግቱት ይገባል። ከ20 ሚሊዮን አማራ ከክልሉ ውጪ ይኖራል ይባላል። አንድም ክልል ላይ አማራ ውክልና የለውም። በክልሉም ፌክ ነው። እነ አቶ በረከት? እነ አቶ አዲሱ? ወዘተ …… አዲስ አበባ 50+ አማራ ነበረ። 32 ዓመት ሙሉ አማራ #የአዲስ አበባ፤ #የድሬም ከንቲባ ሆኖ አያውቅም። ደብረዘይት እና ናዝሬትም እንዲሁ በዚህ የዕውነት ማዕቀፍ ሊታይ ይገባል። ማሽሞንሞን፤ መሞሸርም አያስፈልግም። 
 
በሃይማኖት ውክልናም ኦርቶዶክስ ተዋህዶ በሰፊ ግለት ላይ ናት። የፖለቲካ ተሳትፎ እንዳይኖራት ተደርጋለች። ለዚህም ነው ጥቃቱ እዬበረታ የመጣው። እስኪ ኦሮምያ ክልል አንድ የተዋህዶ ልጅ ፕሬዚዳንት ሆኖ ያውቃልን? ሙሉ 33 ዓመት። አሁን መንበረ ፓትርያርክ እኛ እንሁን እያሉ ነው። እስኪ በሚችሉት ኦሮምያ ላይ፣ ደቡብ ላይ፣ ቤንሻንጉል ላይ፣ ሲዳማ ላይ ተዋህዶ ለክል ፕሬዚዳንት ልጆቿ ይታጩ???
 
በካፒቴኑ በህወሃት ክልል ከተጋሩ ውጭ ሌሎች ማህበረሰብ ነበሩ። አንዳቸውም የፖለቲካ ውክልና አልነበራቸውም። ለምሳሌ #አገው #አማራ ክልል ብቻ ነው የፖለቲካ ውክልና ዬነበረው። ልዩ ዞን፤ ልዩ ወረዳ ፈጽሞ አይታሰብም። እንደ ህዝብ ቁጥራቸው መጠን በትግራይ ክልልል እነኝህ ዞጎችም አሉ። ነበሩ። #አማራ#ኢሮብ#አፋር#አገው#ኩናማ። ባለፈው ጠሚር አብይ ሰብስበው ሲያወያዩ አንዲት የአገው እህቴ በአማራ ክልል የተሰጣት መብት እንዳላረካት ገልፃለች እንደ ቅልጣን እንደ ዘመናይነትም ነበር ያዬሁት። ትግራይ ላይስ ልሙጥ የሆነው?
 
ይህም ሆኖ አንድም የተጋሩ፤ የኦሮሞ፤ የሱማሌ ሊሂቅ ከዕውነቱ ጋር የታረቀ ሙግት ስለፌድራሊዝም ሲያነሳ አይሰማም። በውነቱ ስስታምነትም ነው። ዕውነት ሰብዕናን ካልመራ ፖለቲካ ምንድን ነው? ለነገሩ ይህን ያህል የአማራ ጭፍጨፋ እዬተካሄደ፤ መፈናቀሉ እስሩም እዬተከወነ ክልሎች ጁቢተር ላይ ተቀምጠዋል ማለት ይቻለኛል። አማራም ዜጋቸው ነውና። አማራም ኢትዮጵያዊ ነውና።
 
አሁን ፋኖ ሊያነሳው ከሚገባው በኽረ ጥያቄ አንዱ ከክልሉ ውጪ ስለሚኖሩ አማራወች #ያልተበጣጠሰ #ሙሉ #የፖለቲካ ውክልና #ልዩ ዞን፤ #ልዩ ወረዳ እንዲኖራቸው ማስደረግ ሊሆን ይገባል። አቶ ወንድም አቤ ቱኩቻቸው ቁጥር ሲነሳ ይገርመዋል። ቁጥር እኮ ፖለቲካ ነው። በአደጉ አገሮችም የድምጽ ሰጪው ቁጥር አይደል ምርጫውን የሚወስነው? አቤ እንግሊዝ አገር ተቀምጦ የጠራዋን ዴሞክራሲ እዬጨለጠ ነው ይህን ሃሳብ ሲያጣጥል እምትሰሙት። አቤ ልቅም አድርጌ ነው እምሰማህ። 
 
በዚህ ዘርፍ ወይ ልሙጥ ይሁን አማራ ክልል እንደ ሌሎቹ፤ የተሰጠው ልዩ ዞን፤ ልዩ ወረዳ #ይነሳ፤ ወይ ፌድራሊዝም በሁሉም ክልል #እኩል ይሥራ። ይህን ልጅ ሞገስ ዘውዱ የተጀመረን መልካም ነገር ማስቀጠል ሲገባ ለምን ልሙጥ ይሁን አማራ ክልል ጥያቄ ይነሳል ሲል ሰምቻለሁኝ። ሁልጊዜ ጅልነት ሊኖር አይገባም። ከጅልነትም ያለፈ #ጭድነትም ነው። ይበቃል እዬተጃጃሉ ተንቀራፎ መቀጥቀጥ። ሌላው ለፖለቲካ አመክንዮ ይሉኝታ አይሰራም። ፈጽሞ። 33 ዓመት ተቀለደ። መብት ተቀደደ። ግዴታ ተጫነ።
 
በበቀል ደማቸው ሲንተከተክ እምናያቸው ዶር ለገሰ ቱሉ በአማራ ውክልና ቁብ ብለው ነው በአማራ ላይ #ይፋዊ #ዲስክርምኔሽን ሲፈጽሙ የሚታዩት። ለአነጋገራቸው እንኳን መታረም የለበትም። በነገራችን ላይ ከሚሴ ያሉ አማራወች በቋንቋቸው አይማሩም። ልክ እንደ ወልቃይት ጠገዴ፤ እንደ ራያም፦ እንደ መተከል፤ እንደ ደራም፤ እንደ አርባምንጭም።
 
 አሁን ያሉት የአማራ ክልል መሪወችም የአማራነትን መንፈስ በጽኑ ያገለሉ ናቸው ሲባል አዳምጣለሁ። ለዚህ ነው መልከ ጥፋን በሥም ያደጉሱ ሆኖ ጠሚር አብይ አህመድ ትንታጉ ዶር አንባቸው፤ ጭምቱ አቶ ገዱ የመሩትን ክልል የስለት ልጅ አድርገው የአሁኑን አቶ አረጋ ከበደን ሲያንቆለባብሱ ያዳመጥኳቸው። ነገሩ የቤተዘመድ መሆኑ ተከድኖ ማለት ነው። ለነገሩ ክልሉ እራሱ ትርታው አለን????
 
#የሆነ ሆኖ።
 
የፖለቲካ ንግግሩ ሆነ ስምምነቱ ፋክትን ተንተርሶ፤ ፋክትን አቅርቦ መሞገት ይገባል። ተዋህዶን በሚመለከት አንድ ክልል ብቻ ተዋህዶ አንድ ፕሬዚዳንት አለው። አማራ ክልል። ለምክትል ፕሬዚዳንትነት እንድም ክልል ተዋህዶ ምንም ቦታ አልተሰጣትም። ወና ነው። እትጌ ትግራይን እለፈኝ ብዬዋለሁ ህዋህቶች ሶሻሊስቶች ነን ይሉ ስለነበር። ዶር አብይም ለ100 ቀናት ብቻ ነው ትግራይሻን የመሯት። 
 
#ሊሆን የሚገባው።
 
1) ፌድራሊዝም ይቀጥል ከተባለ ሁሉም ክልል ከተሞችን ጨምሮ የአማራ ክልልን ቀለም መምሰል ይኖርበታል።
 
2) ፌድራሊዝም አዬር ላይ ይንሳፈፍ፦ በሥሙ ጠግበን እንደር፤ በፍሬም አድርገን ለግድግዳ ጌጥ ይሁን ከሆነ አማራ ክልል ልዩ፤ ወረዳ እና ዞን የተሰጣቸው ተሰርዞ አማራ የፖለቲካ ውክልናውን ሙሉ ለሙሉ መውሰድ ይኖርበታል። መራራ ነው ግን ሊሆን የሚገባው ይህ ነው። የፋኖ ጉልበታም ቅድመ መደራደሪያ ነጥብም ይህ ሊሆን ይገባል። የቀልድ ቅልሞሽ መቆም አለበት። ፋኖ የአዲስ አበባ ከንቲባነትን መጠዬቅ ይኖርበታል። መረጃው ስለቀደመ አጠንክሮ መቀጠል ይገባል። እሺ።
 
አቅም አለኝ የሚሊ በዚህው በአጤ ፌቡ መንደር ይምጣ እና ይሞግተኝ። እኔ ሳመለክትም፤ እርዱን ስልም ልቅም አድርጌ ሙሉ 30 ቀን ፈጂቼ በተደራጄ ሃሳብ ነው። እንዲህ ለብ ለብ በእኔ ቤት የለም። "ከአነጋገር ይፈረዳል። ከአያያዝ ይቀደዳል እንዲሉ። " ሃሳብ ልኬ ጠንዝሎ አያውቅም። ውስጤን ነውና እምልከው።
 
ግልቢያ ተግ ይበል። ስክነት ይለምልም። ጥሞና ይሰነቅ ማስተዋል ይምራ።
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
21/05/2024
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።