ግልብጥ ...

       ግልብጥ  የልብ  አፍርጥ ልጥ።
                                                ከሥርጉተ ሥላሴ 14.06.2010 
                                                       ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ።
                         „በዚያም ቀን ይህ ቅኔ በይሁዳ ምድር ይዘመራል። ፣---- የጸናች ከተማ አለችን፣ 
                          ለቅጥርና ለምሽግ መዳህኒት ያኖርባታል። ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፮ ቁጥር ፩“


ሲንጠባጠብ - ሽርክት፤ ሲሸረከት - ግርድፍ። ስከረከም - ታሬ። ስመትር - ቅርጥምጣሚ። ሲረግፍ - ጤዛ። ሀገር ምድሩን አካልሎ … ካለ ልኩ ተንቧልሎ ----- ሲሰጠስጥ በድንክ አልጋ - ግልብጥ ሳይናጥጥ ናጥ------! ላጥ …. እንጦርጦስ፤

ጢባ - ጢቦ፤ ጠራጠሮ --- ተንትርትሮ - ግርድ ሲሆን። ተያይዞ በሆድ ሰንሰለት ጅዋጅዊት ሲጫወት፤ በነፍሳት ቡድስ ….! እልልልልልልልልል …. ልል።

ያልሆነ - ተለጥፎ። ካለቦታው - ተኮፍሶ፤ ካለወርዱ - ተጀቡኖ፤ ካለቤቱ - ተጠምኖ፤ ሲቀረቀር - ከቀን፤ ሲተረተር - በዕብሪት … ፍርክስ---------! ስስስስስስስስስስስስ ….. ስስ፤

ቋጥ ለቋጥ - ሲያማትር፤ ቋጥኝ - ለቋጥኝ - ሲነፍስ፤ ሲል ክው፤ ድረቅ ብሎ ሲረግፍ … አያድርስ --------! ክው ብሎ ሹልክ ክክክክክክክክክክ …. የእንክርዳድ ክክ።

ድንበር አልባ ሲከምር፤ መሰረት አጥቶ - ሲንሳፈፍ፤ ድርቆሽ ሆኖ - ለሰንጋ መና ሲሆን፣ … ዋጠው ሙጃ - ጀንጅኖ ከሸጎሬ ሳይመለስ አስቀረው ሸንሽኖ - የጭድ ፍርሻ፤ ፉርሽካ የፊሽካ።

ማይኩን ቢያስተካክል - አልተሰማም - በቅርብ ቀን እያለ ሲንተባተብ - ጥቁር መጥቶ ሲያፋጥጠው፤ ማለቁን እያወቀ ሲትበሰበስ ዬእሳት ፍርንዱስ ድርስ …. ቡድስስስስስስስስ ፤ ካለቅርስስስስ። 

የት ይግባ! ምን ይዋጠው! ዓዋጅ አሳውጆ በሽልንግ ዕንባ ሲያዋጣ፤ በጢስ ልክ ሲመድብ - አራዊት፤ ሲያስደረድር ምሾ … በሌለበት በፉኮራ ሲያንኮራፋ … ያ … መሳቂያ - ድርምስ! ግርስስስስስስ

አሉ ነበር አሉ። ተጽፎ ያላለቀ … ያልተጠናቀቀ … ተንጥልጥሎ የነፈሰ፤ ተጎራርዶ የታረደ፤ ትወናው ከብትን አፈር ጋር ሲያወጋ ተጠፋ አሉ የጨለማው ድርሰት ዬቁጥር ዓመት ማላገጥ …. ሲማግጥ … ለመጋጋጥ - ወረደ እንጦርጦስ ለጋጥ - ተሾመ አሉ ለድንጋይ ልብስ - ለሰኔል ፍሩንዱስ፤ ለቹቻ በትሃ። ሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃሃ….

ተልጦ --- ተልጦ --- ተልጦ --- ተልጦ --- ተልጦ --- ተልጦ ሰንበሌጥ አድሞ። ተጋግጦ ተጎረባጦ ገመድ - ሞግዶ፤ ዓውጅ በዓዋጅ አስነግሮ ለእለት ቁርስ ስንቅ ቅርስ የለሹ ዕውነቱን - መሰከረ፤ እሱ - በእሱ ታቃርኖ፤ ተጠንዝሎ ረገፈ …. ክብር ዝናው ተገፈፈ …. ተራገፋ ---ተሞለፈፈ … ሄሮድስ እንደባከነ ሳይመለስ - ብራስልስ ላይ ተለሰነ።

                                                                    ለአሁን ብቻ ትራሱ
                         የጤዛ ነፍሱ
ነገማ ደሞ - ንፉሱ
ከፈሰሰበት አይታፈሱ
የምላስ ፈሱ!
የግምሱ
ፍረሰት - ምሱ።
ኢትዮጵያዊነት ቀለሙ የሚያበራ ዕንቁ ነው!

መሸቢያ ጊዜ።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።