ግልብጥ ...
ግልብጥ የልብ አፍርጥ ልጥ። ከሥርጉተ ሥላሴ 14.06.2010 ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ። „በዚያም ቀን ይህ ቅኔ በይሁዳ ምድር ይዘመራል። ፣---- የጸናች ከተማ አለችን፣ ለቅጥርና ለምሽግ መዳህኒት ያኖርባታል። ትንቢተ ኢሳያስ ምዕራፍ ፳፮ ቁጥር ፩“ ሲንጠባጠብ - ሽርክት፤ ሲሸረከት - ግርድፍ። ስከረከም - ታሬ። ስመትር - ቅርጥምጣሚ። ሲረግፍ - ጤዛ። ሀገር ምድሩን አካልሎ … ካለ ልኩ ተንቧልሎ ----- ሲሰጠስጥ በድንክ አልጋ - ግልብጥ ሳይናጥጥ ናጥ------! ላጥ …. እንጦርጦስ፤ ጢባ - ጢቦ፤ ጠራጠሮ --- ተንትርትሮ - ግርድ ሲሆን። ተያይዞ በሆድ ሰንሰለት ጅዋጅዊት ሲጫወት፤ በነፍሳት ቡድስ ….! እልልልልልልልልል …. ልል። ያልሆነ - ተለጥፎ። ካለቦታው - ተኮፍሶ፤ ካለወርዱ - ተጀቡኖ፤ ካለቤቱ - ተጠምኖ፤ ሲቀረቀር - ከቀን፤ ሲተረተር - በዕብሪት … ፍርክስ---------! ስስስስስስስስስስስስ ….. ስስ፤ ቋጥ ለቋጥ - ሲያማትር፤ ቋጥኝ - ለቋጥኝ - ሲነፍስ፤ ቃ ሲል ክው፤ ድረቅ ብሎ ሲረግፍ … አያድርስ --------! ክው ብሎ ሹልክ ክክክክክክክክክክ …. የእንክርዳድ ክክ። ድንበር አልባ ሲከምር፤ መሰረት አጥቶ - ሲንሳፈፍ፤ ድርቆሽ ሆኖ - ለሰንጋ መና ሲሆን፣ … ዋጠው ሙጃ - ጀንጅኖ ከሸጎሬ ሳይመለስ አስቀረው ሸንሽኖ - የጭድ ፍርሻ፤ ፉርሽካ የፊሽካ። ማይኩን ቢያስተካክል - አልተሰማም - በቅርብ ቀን እያለ ሲን