በተቋሰለ መንፈስ አዲስ ነፍስ አንዴት?

·                                                           መደራጀት በጠራ ህሊና 
                ቢሆን ይመረጥ ነበር።
               አዲስ መንፈስ በቅይጥ
               እና በተቋሰለ እዝል 
               ግን እጅግ ፈታኝ ነው።
                         ከሥርጉተ ሥላሴ 10.06.2018 (ከገዳማዊቷ ሲዊዘርላንድ)

              „ሁሉ ከምድር ተፈጠረ ሁሉም ወደ ምድር ይመለሳል የወንዙ ውሃ ወደ ውቅያኖስ ይመለሳል።“
                                     
                                           (መጸሐፈ ሲራክ ምዕራፍ 40 ቁጥር 11)

መዳረጀት የሃይል መሰረት ነው። መደራጀት የአቅም ልዕልና ነው። መደራጀት የህልውና መኖር ነው። መደራጀት የህሊና ብልህንት ነው። በመደራጀት ውስጥ ትርፍ እንጂ ኪሳራ የለውም። አማራ ባለመደራጀቱ የደረሰበትን ሶቆቃ እና መከራ ከእንግዲህ በተሻለ አቅም እና ብቃት ለመቋቋም የሚያስችለው የመጀመሪያውን ፈተና አልፎታል። ግን ከሌላ ድርጅት አባልን መቀበል በአዲስ ኮት ላይ ላይ የዘለበ ሱሪ የመታጠቅ ያህል ነው። አንድ ፖለቲካ ድርጅት ይሁን ስብስብ ፈርሶ አዲስ ሲደራጅ የመውደቂያው መለከት ይሄው ነው። ሰዉ ከእነጓዙ ነው የሚመጣው። ያን የትርምስ መንፈስ ተሸክሞ እንዳዘለው ነው ከአዲሱ ጋር የሚቀላለቀለው። ለዚህ ነው ከብርሃን ቀድሞ መረጃው በፍርሻ የሚፈተሸው። ፈተና የፈጠረው የስንት ምጥ አዲስ ድርጅት አህዱ ሲል ገና ፈተናን በራሱ በገንዘቡ መፍቀድ ወይንም ፈተናን መግዛት ብልህነት አይመስለኝም። አሁን ደግሞ አማራ ራሱን ችሎ መቆም ተስኖት ነው ጥዋራ ያሰኘው፤ ጥገኝነት የናፈቀው?

እርግጥ ነው ጉባኤው ከዬትኛውም የብሄራዊ ድርጅት ጉባኤ ሁሉ የደመቀ እና ደስ የሚል ድባብ የነበረው በመሆኑ በአዘጋጆች ሆነ በተሳታፊዎች እጅግ አድርጌ ኮርቻለሁኝ። አማራ ከእንግዲህ የአገኜ እራስ እራሱን የሚቀጠቅጥበት ዘመን የሚቋቋምበትን ታላቁን መሳሪያ ደሙን፤ ኑሮውን፤ ሰላሙን ሁለናውን ገብሮ ዛሬ አህዱን ጀምሮታል። ግን አሁን ከሰማያዊ ፓርቲ መንፈስ ጋር እራሱን እንዲህ እያንጨባረቀ መሆን አልነበረበትም። ለዛ የደም ግብር ከዛ ደም የፈለቀ ንጽህና ይጠይቅ ነበር።

በመከራ ውስጥ ያለፈ ድርጅት ከብረት የተሠራ ጠንካራ ይሆናል ብዬ አስቤ ነበር። ከሁሉም በላይ በወያኔ ሃርነት እስር ቤት ከሞት የተረፉት አረበኞቻችን በዚህ ታላቅ የምሥራችን ቀን ጉባኤ ላይ በመገኘታቸው እጅግ ደስታኛ ብሆንም የተሰዉለት ዓላማን በቅይጥ መስፈርት መጀመሩ ግን አደጋው እጅግ የከፋ ነው።
በዝግጅት እና በመሰናዶ ደረጃ ግን ደስታዬ የመጀመሪያ የመሆኑን ያህል በስብሰባባ ላይ የነበረው የተሳትፎ ደረጃ ከጠበኩት በላይ ጥሩ ነበር። እኔ በዚህ ደረጃ አላሰብኩትም ነበር። እጅግ የተሟላ እና በውስጡ አቅም ልክ የበቀለ ስለመሆኑ በጉባኤው ድባብ ግማሽ ተስፋን ሰንቄያለሁ። ግማሽ ያልኩበት መቀዬጡን አልተመቸኝም። በድርጅት ህይወትም ከመርህም ከምግባርም ከሞራልም አንጻር አያስኬድም። ከብሄራዊንት ወደ ጎሳ ድርጅት፤ ከጎሳ ድርጅት ወደ ብሄራዊነት? ? ? ውጥንቅጥ ነው።

በሌላ በኩል እኔ እንደማስበው ከአማራ መደራጀት ቀጥሎ በፌራል መንግሥቱ ይወሰዳል ብዬ እማስበው ይህ አስፈሪ አቅም ሌላም ዓዋጅ ያማጣል ብዬ እገምታለሁኝ። ከመታወቂያ ላይ ዜግነት የሚል አዲስ ውሳኔ ይመጣል ብዬ አስባለሁኝ። ስለምን ቢባል አንደኛው በዚህ ድርጅት ውስጥ በአባልነት በገፍ በመግባት ድርጅቱ ብሄራዊ የማድረግ ተልዕኮ ለማስያዝ እና በተለመደው መንገድ አማራ እራሱን ችሎ ውክልና እንዳያገኝ ግርዶሽ ለመሥራት ሲሆን፤ ሁለተኛው ደግሞ የድርጅቱን ዋንኛ ዒላማ ለማኮሰስ ብዬ አስባለሁኝ። ይህ የአማራ ሃይል በዚህ መልኩ አጀማመሩ የማያስፈራው እንደ ግልም እንደ ድርጅትም ማንም ሊኖር እንደማይችል እገምታለሁ። ስለዚህ ቀጣዩ እርምጃ እንደ ሥርጉተ ሥላሴ መታወቂያ ላይ ጎሳ ቀርቶ ዜግነት ሊሆን ይችላል።

ዋናው ፍሬ ነገር ግን እኛ ነው እማናውቀው እንጂ እዛው ያለው ማን ምን እንደሆኖ ስለሚታዋወቅ ብዙም አይከብድም። እኔም ደስ ይለኛል ጎሳ ሳይሆን ዜግነት በብሄራዊ ደረጃ መለያ ቢሆን እሻለሁኝ። ግን አማራን በሚመለከት ሁልጊዜም ለመናጆነት ነው እንጂ ለዋናነት ስለማይፈለግ ድርጅቱ በበቂ ሁኔታ ቢገጥም ብሎ ማሰብ ያስፈልገዋል።

ሌላው ምርጫ አመራር አካሉት ላይ በቀደመው ጹሑፌ ላይ የሰጋሁት ጉዳይ ተፈጽሟል። አቶ ጋሻው መርሻ-የድርጅት ጉዳይ ሀላፊ (የሰማያዊ ፓርቲ አመራር የነበረ)  ይሄ ቀይ መስምር ነው። ለዛውም የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ። አልተዋጠለኝም። ያማል፤ የቆስላልም። እውነት ብናገር እኔ የሰማዬዊ ፓርቲ አካሄድም በፍጹም ሁኔታ የማያምረኝ እና መሠረታዊ ዓላማውም ቅይጥ ሆኖ ነው የሚታዬኝ። ግራጫማ ቢባል ስያሜው የሚያስኬድ ነው። ሰውር ነገሮችን ሰንቆ የሚጎዝ ድርጅት ነው።

ይህን ታላቅ የድርጅቱን ጭንቅላታዊ ቦታ ሰማያዊ ፓርቲ ለነበር ሰው መስጠት አደጋው እጅግ የከፋ ነው የሚሆነው። ስለዚህ ተስፋዬ በግማሽ ነቅዟል ማለት እችላለሁኝ። ለተራ የሥ/ አስፈፃሚ አካልነት እንኳን እጅግ ከባድ ነው። ለአባልነት ራሱ ተመራጭ አይደለም። በቀደመው ጹሑፌም አበክሬ አስገንዜቤያለሁኝ። ጤነኛ መንፈስ እዛ ድርጅት ውስጥ አላይም። አሁን ከማህል አልታራስ ከደንበር አልመለስ ብሎ እያወከ ያለው እሱ አቤቱ ሰማያዊ ነው።

ጠረኑንም እኔ እንደ ፖለቲካ ድርጅት የህዝባዊ ድርጅቶች እና የሙያ ማህበራት አደራጅነቴ ውሰጡ ጤነኛ አይደለም የሚል የጸና አቋም ነው ያለኝ። የተጠቀለለበት ሌጋሲ በሸተኛ ስለሆነ። ስለሆነም ጽናቱን ይስጣችሁ።
ይህ የሚሊዮን ድምጽ በጸዳ እና በነጠረ ሁኔታ መጀመር ሲገባው የተቋሰለን ሃሳብ እዝሎ መነሳቱ ነገን ለማለም እጅግ ከበድ ነው። ለዛውም ከማህበረሰቡ ለተሰረዘ ማህበረሰብ የህልውና ግዙፍ ጥያቄ በቅይጥ ፍላጎት አህዱ ማለቱ ድርጅቱን ከጅምሩ በጥንቃቄ እንዲታይ ያደርገዋል። እንዲህ ዝንቅ መሆን አይገባውም ነበር። ዬድርጅቶች ፍርሻ በአንድ ሰው ምክንያት ሊሆን ይችላል። አንድ በጥባጭ ወይፈን ካለ በረቱ ሁሉ ሲታመስ ያድራል። አብን ካለፉት ስህተቶች ሁሉ ራሱን አርሞ እና አርቆ ሥራውን አህዱ ይላል የሚል ሙሉ እምነት ነበረኝ። ግን አልሆነም።  
„አማራነት ይከበር!“
መሸቢያ ጊዜ።


አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።