ደስ ይበልህ ጐጃም።

        ደስ ይበልህ ጐጃም።
                                          ከሥርጉተ ‚ ሥላሴ 09.06.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
                                   „ብርና ወርቅ አገር ያጸናሉ፤ ከሁለቱ ምክር በ ምክር ደስ ታሰኛለች።“  
                                              (መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ ፵ ቁጥር ፳፭) 

የሁነኛ ማተብ የመሆን አብነት
የልብ አድርስ ኑሮ፤ የህሊና ባዕት
የቁርጥ ቀን ግማድ የመሠረት ጽናት፤
ደስ ይበልህ ጎጃም የኪዳን ጉልላት!

ትንግርተኛው የሰማይ ቅስቱ
የአማራ ምስባኩ የናፍቆት ስስቱ
ዕውቅናው ፈለቀ በገዱ በእትብቱ።

የደምመላሽ አንቱ የአድባራት ቅኝቱ፣
የበካፋ ህይወት የአድም ሰገድ ጥሪኙ
የጥንት የጥዋቱ የንግሥ ቱሩፋቱ፤
ዘመኑን አጎላው በውስጥ ሽልማቱ።

እስኪ ልጠይቅህ „ጣና ሆይ!“ ሚስጢርህ ምንድነው?
እስኪ ልጠይቅህ „ግዮን ሆይ!“ ሚስጢርህ የቱ ነው?
የተመሰጠርከው በህብሬ ደማሙ ፈቅደህ የሰጠኸው፤
በጨለመበት ለት፣ ሁሉ ፊት ሲነሳው፣ በደቦ ሲገፋው
ደረስክለት አንተ - ፊት ለፊት ተማግደህ - ሩቅ ራይ የሆንከው።

እስቲ ልጠይቅህ ጐጃም ሆይ! አንተኑ?
ፍቅረኛ የሆንከው፤ የደሙ ግብረኛ የሆንክልን ባይኑ።


ጐጃም ሆይ! ስለኛ ምን ያልሆነከው አለህ?
የደመር ዕድምተኛ
የስቃይ፣ የዕንባ፣ የአይዞህ ማበርተኛ!

ቀራንዮ ሆነህ  ….
…. ጎለጎታ ሆነህ
ዳንኤል ሆነህ ….
…  አናንያ ሆነህ
 አዛርያ ሆነህ …
….  ሚሳዬልን ሆነህ
 በዝምታኽ ሆነህ…
 አባታጣቅ ሆነህ …
... በበላይም ዘልቀህ
ገልሞን ተወዳጅተህ ...
ገብርዬንም ጠርተህ ... 
አብነን ቀደስከው በዮናስ ሆድ ሆነህ!

  • ·         ልዩ ምስጋና ጐንደር በከፋው ለት፤ ጐንደር ሆድ በባሰው ዕለት፤ ልጆቹን እንደ አብርሃም በግ ላቀረበው የዘመን እጬጌ ለልብ ፍቅረኛዬ ለቅኑ እና ለንጹሑ እንዲሁም ለሰማዕቱ ለጎጀም ህዝብ እና ታሪክ ይሁንልኝ። እግዚአብሄር ይስጥልን። ኑሩልን። ልዑል እግዚአብሄር እናንተን አያሳጣን። በደማችሁ የቀለመው ገናና ታሪካችሁ መኖራችነን ሰጥቶናል። ወደ ቀደመው ሚስጢራዊነታችን መልሶናል። 
  • ·         ተጣፈ 09.06.2018 ሉዘርን ሲዊዘርላንድ። ጐጃም የእኛ! ጐጃም ኬኛ!
  • ·         ፎቶ ምንጭ ፌስ ቡክ ላይ የተገኜ ስለሆነ በታሪኩ ስለተመስጥኵኝ  ዕርዕሰ ጉዳዬ አውራ አድርጌ ለጥፌዋለሁኝ። ከውጪ አገር ወደ ጐንደር ቤተሰብ ለማየት የምትሄዱ ጐንደሬዎች ጐጃምን ማዬት አንዱ የጉዞ መርሃ ግብር ሊሆን ስለሚገባው፤ መረጃውን ጨምሬ አቅርቤለሁኝ። ጐንደሬዎች ጐጃም አጀንዳችን ሊሆን ይገባል። 

  •        ዘመናት ፍች አጥቶለት የኖረው አምክንዮ በጥርስ የተያዝንበት፤ በዬደረስንበት በዓይነ ቁራኛ ክትትል የሚደረግብን፤ የምንሳደድበትን፤ በመኖራችን ውስጥ ነፃነታችን ተቀምተን የኖርን፤ ግን ለሰከንድ ለምንም እና ለምንም ማጎብደድን ያልሠራልን፤ ለዕውነት እና ለንጋት ጠፈፍ - ክውን - ልቅም ያልን ዘብ አደሮች ነን - ጎንደሬዎች። ዘመን ያልመለሰውን፤ ታምቆ የኖረውን፤ የመኖራችን የተሰወረ ግርዶሽ ገፎ ከራሱ በላይ እጅግ ከፍ ባለ ሞራላዊ መስዋዕትነት ውስጡ ላደረገን፤ ራሱን በፍጹም ሁኔታ ለሰጠን፤ መላ የጐጃም ህዝብ በሙሉ፤ ሁሉ የሚቻለው የሰማይ እና የምድር ልዑል ፈጣሪ አዶናይ የሻቱትን ሁሉ ይስጥልኝ። „አሜን!“ 

  •        ጐንደር ያሉ ባለልቦች የጐጃም የክብር ቀን በቋሚነት ቢኖራቸው ደስታውን አልችለውም። ዕድሜ ለአማራነት ፍቅርን ያህል ታላቅ ፈላስፋ ከነሙሉ ክብሩ እና ዝናሩ አስረክቦናል። ተመስገን! እርግጥ እኔ ሥርጉተ ሥላሴ አማራነቴን እወደዋለሁኝ! አዎን እኔ ሥርጉተ ሥላሴ አማራነቴም አከብረዋለሁኝ! 

          „ድንጋይ ደበሎ ማርያም አምሳለ ላሊበላ ጐጃም“

2. ድንጋይ ደበሎ ማርያም (አምሳለ ላሊበላ ዘጐጃም)
የዛሬ ትውውቃችን የሚሆነው በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናት መካከል ከሆነችው ድንጋይ ደበሎ ማርያምን ይሆናል ፡፡ መልካም ቆይታ!!

ቤተክርስቲያኗ ድንጋይ ደበሎ ማርያም ትባላለች፡፡ ይች ቤተክርስቲያን የቅዱስ ላሊበላ በረከት የፈሰሰባት፣ አሻራው ያረፈባት እንቁ ቦታ፣ የተቀደሰችና ታሪካዊ አሻራ የሚታይባት አምሳለ ላሊበላ ዘጎጃም ናት፡፡ ስያሜዋ ከድንጋይ የተፈለፈለች መሆኑን ለመግለጽድንጋይ ለብሶ (ድንጋይ ተጎናጽፎ) ማለት እንደሆነ አባቶች ይናገራሉ፡፡
የምትገኘው በምዕራብ ጎጃም ዞን በባሕርዳር ዙሪያ ወረዳ የመቃት ድንጋይ ደበሎ ቀበሌ ከጢስ አባይ ፏፏቴ በቅርብ ርቀት ከከተማዋ ደቡብ ምዕራብ አቅጣጫ ነው፡፡ 

የተሰራችው በንጉስ ላሊበላ 1131 .ም፤ ቅዱስ ላሊበላ ለትምህርት ወደ ጎጃም በመጡበት ወቅት እንደሆነና መቅደሷን ብቻ እንደሰሩ ወደቦታቸው ወደ ሮሃ እንደተመለሱ መዛግብት ያስረዳሉ፡፡ ቤተክርስቲያኗ 17ኛው መቶ ክፍለ ዘመን አፄ ፋሲል የጎጃሙን ግንብ ጊዮርጊስን (ባህርዳር ዙሪያ ወረዳ ግንብ ቀበሌ ከደብረመዊ ምእራብ አቅጣጫ የሚገኝ ) አሰርተው ወደ ጎንደር ሲመለሱ የቤተክርስቲያኗን ታሪክ ስለሰሙ ለመሳለምና ቦታዋን ለማየት ሲመጡ ታሪካዊነቱን በጠበቀ ሁኔታ አራት ማእዘን ቅርፅ ያለው ሕንፃ በድንጋይ በጭቃ ከአለቱ ጋር በማያያዝ ከእንጨትና በቆርቆሮ ጣሪያውን በማሳመር አሰርተውላታል፡፡ በቅርቡ ደግሞ በአማራ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ቤተክርስቲያኗን ከዝናብ እና መሰል ጉዳቶች ለመጠበቅ የመከላከያ ጣሪያ ተሰርቶላታል፡፡

ወደቦታው ለመሄድ ሁለት ዓማራጮች አሉ፡፡ ለሁለቱም አማራጮች በመጀመሪያ ከባህርዳር ከተማ በመነሳት ወደ ጢስ አባይ የሚወስደውን መነገድ መያዝ ያስፈልጋል፡፡ ከዚህ በኋላ ከሚከተሉት አማራጮች በአንዱ መሄድ ይቻላል፡፡
1
) አንዳሳ ከተማ እደደረሱ ከዚች ከተማ ላይ ከመኪና በመውረድ ወደ ደቡብ ምስራቅ አቅጣጫ ወደቀኝ በመታጠፍ በአካባቢው ልምላሜ መንፈስን በማደስ ለአንድ ሰዓት ያህል በእግር ወይም በበቅሎ መጓዝ፣
2
) እስከ ጢስ አባይ ከተማ በመጓዝ ከጢስ አባይ የደቡብ ምእራብ አቅጣጫ በመያዝ ወደ 12 . የሚደርስ ለአሸዋ መጫኛ በተዘጋጀው የመኪና መንገድ በመኪና ወይም በበቅሎ መሄድ ይቻላል፡፡

የመንገዶች አካባቢ ቆላማና ነፋሻማ የአየር ንብረት ያለው፣ በበጋም ሆነ በክረምት ልምላሜ የማይለየው ማራኪ ውበትን የተላበሰ በመሆኑ ለዓይን እይታ ማራኪ፣ የአየሩ ጠረን የሚያክም እና ልዩ ስሜትን የሚፈጥር ነው፡፡
የቤተክርስቲያኗ በተለያዩ ጊዜያት በስጦታ የገቡ የተለያዩ ተንቀሳቃሽ ቅርሶች የነገሥታት ደብዳቤዎችና ሌሎች ሰነዶችን የያዘች፣ የሰውን ልጅ ሥነ-ሕንፃ ጥበብ የምታሳይ ዳግማዊት ላሊበላ ናት፡፡ በተጨማሪም በጣልያን ወረራ ወቅት በአካባቢው ላሉ አብያተ-ክርስቲያናት ቃጠሎና ውድመት ሲደርስባቸው መጠጊያ ሆና እንዳገለገለች ምእመናን ያስረዳሉ፡፡

በአጠቃላይ ከቦታው ውበትና ታሪካዊነት ጋር ተዳምሮ ልዩ የሆነ ስሜትን የሚፈጥር ስለሆነ ወደቦው በማንኛውም ጊዜ በመሄድ መጎብኘት ይቻላል፡፡
ምንጭ፡- ሐመረ ተዋህዶ 3 ዓመት ቁጥር 5 መስከረም 2008 . ማህበረ ቅዱሳን
በሌላ ታሪክ እስክንገናኝ ቸር እንሰንብት!!!“
  • ምርኩዝ።


አማራነት አሞሌ ጨው አይደለም፤ አማራነት የከበረ የደም ቀለም ማንነት ነው!
አማራነት ለሟሟያነት የሚውል ቁሮ እንጨት ሳይሆን በደም የበቀለ ንጥር አንቱ ማንነት ነው።


„አማራነት ይከበር!“
የኔዎቼቹ መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።