እልል በል አማራ!
እልል በል አማራ!
ከሥርጉተ ሥላሴ 10.06.2010 (ከጭምቷ
ሲዊዘርላንድ።)
„እሱም ጥበብንና ምክርን ይገልጥለታል፣ የተሠወረውን
ይገልጥ ዘንድ ያሳስበዋል።“
(„መጽሐፈ ሲራክ ምዕራፍ
፴፱ ቁጥር ፯“)
አንተ እናት
ሆዱ እግዜሩን አማኙ፣
አንተ አንጀት አራሹ ትህትናን ተናኙ፣
አንተ ቅን ወተቱ ፍቅርነን ተመኙ፣
ስትሞላ የሰው ጓዳ ስትድር ጠጋኙ፣
አንተኑን እራስተህ ለሌሎች ሥንኙ።
እልል በል አማራ አንተ መከረኛ፣
እልል በል አማራ አንተ አሳረኛ፣
እልል በል አማራ እዬሞትክ ተረኛ፣
አንተ አናጋች በመሆን ለጋስ ተረብኝ፣
አልቀህ ባታልቅለት ለዘመን ወረተኛ፣
ቀንህ ጆሮ ገዛ የአብን ሁነኛ!
እኔስ እልሃለሁ ከልቤ ታድሜ፣
እኔስ እልህለሁ ከውስጤ አስቀምጬ፣
እኔስ እልሃለሁ ድምጼነን ሰጥቼ፣
ከእንግዲህ ጅልነት አውልቀህ ጣል ብዬ።
አንተ ገራገሩ የዘመናት ትንግርት፣
አንተ ብሩኽ ማዕልት የመቻል ትዕይንት፣
አንተ ግማደኛ የእንትዬ ትፍስህት፣
ስትጋፋ የኖርክ የደሙ ግብረኛ፣ ለባድማ ትውስት፣
ምን አትርፈህ ከቶ ከማገዶ ትርሲት?
መሸከም ብቻ እንጂ የዕንባን መፈለጥ።
አልል በል አማራ ደስ ይበልህ ከቶ፣
አቅምህን ብልሃትህ ሁሉነን አካቶ፣
የህልውና አብራክ መኖርህ ታክቶ፣
በብርሃና አገር ጨለማህ በርክቶ፣
የለህምም ተብለህ በእሬትም ተቦክቶ፣
ሃምሌ 5 መጣልህ የድል ብሥራት ተግቶ።
እልል በል አማራ አንተ የማዳን ቀኑ፣
እልል በል አማራ አንተ የቀደምት - ፊደሉ
እልል በል አማራ የባዕት ንጥር ጓሉ፣
እልል በል አማራ የመገፋት ድሉ።
አንተም ታውቀዋለህ እኔም አውቀዋለሁ፣
በጢስ ተሸፍነህ፤ በካሊም ታጅለህ፣ ብልህ እችላለሁ፣
ማተቤ አገር ክብሬ በማለትህ ተወርውረህ ኖረህ፣
በቃኝን ሸለሙህ አቡዬነን አመነህ።
ሰጊድ ለኪ! ልበል ሃምልዬን አክብሬ፣
ተመስገን አቡዬ ደመቀን ዝማሬ፣
ዘውዱን የዳፈለት ደምመልስ ለአገሬ!
ጎጃም አጋሳ ጎንደርን አስልቶ፣
ጎንደርም ተነሳ ጎጃምን አጉልቶ፣
የዘመናት ሊሂቅ ሰብሎን በጐ አፍርቶ!
ተጠቅልሎ ወድቆ አማራ ከክብሩ፣
ተጠቅልሎ ወድቆ አማራ ከክብሩ፣
ተረስቶ የኖረ አናጋች ሆኖ አዳሩ፣
ድልድይ እዬሰራ ሌላውን አሻግሮ፣
እሱ ትቢያ ለብሶ ሰኔል ተንተርሶ፣
ቹቻ ቅስት ሆኖት ዝናሩን አጉርሶ፣
አብነን ተጣራ ማዕዶት
አለስልሶ!
ይጩኹ ይንጫጩ እንደለመዳቸው …
አማራ አይመለስ ይሄው ነው ጎዳቸው …
ተሸኝቶ ማደር አይሆንም ስንቃቸው፤
እንደ ወንዶቹማ፤ እንደ ጀግናዎችማ መሆን ተስኗቸው
…
ቀበቶ ማውለቁን ማንስ ወስዶባቸው …
ሞገድ ይማጠኑ እሱ ይቀብጥራቸው …
እንደ ፍጥርጡሩ እሱ ይሁናቸው።
ምን እንዳለው ያውቃል አማራ በእጁ ላይ?
ምን እንደሚችል ያዋቅል አማራ ልቡ ላይ?
ምን መሆኑኑን ያውቃል አማራ ደሙ ላይ?
የቆረጠ ለታ፣ የሥርዬት ልዕልና፣ የመሆኑ ሲሳይ!
- · ሥጦታ ለአማራ ተጋድሎ አንበሶቼ ይሁንልኝ።
- የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄን መመሥረትን በተመለከተ የተገጠመ።
- · ተጣፈ 09.06.2019 - ሉዘርን ሲዊዘርላንድ።
- "አማራነት ይከበር"
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ