ልጥፎች

የልጆች የውስጥ ቀለበትነት…እንደአብዩ ተደሞ!

ምስል
የአብዩ አፍቅሮተ - ልጆች ተደሞ። „የብልህ ሰው ጥበብ መንገዱን ያስተውል ዘንድ ነው“  ምሳሌ ፲፫ ቁጥር ፰ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie  22.12.2018 ከጭምቷ ሲወዘርላንድ። ·        የ ፍቅራዊነት መንገድ በመሪነት ሲቆምስ። በቅድሚያ በዶር ገዱ አንዳርጋቸው የተመራው ሉዑክ ተልኮውን አጣናቆ ኢትዮጵያ በሰላም መግባቱን አዳምጥኵኝ። ትልቅ ነገር ነው። በሰላም መግባት ትልቅ ዋጋ አለው - በእኔ ዘንድ። የሰው መኖር ነው አስፈላጊው ጉዳይ ሌላው ይደረስበታል። ተመስገን! እንዴት ናችሁ ቅኖቹ የኔዎቹ? ደህና ናችሁ ወይ? እስቲ ዛሬን በአዲስ አጀንዳ አብረን መጭ እንበል በሰላው መንገድ ... እንዲህ ... ዘንከትከት እንበልበት ...  ወላጆች ወይንም ኣሳዳጊዎች ልጆቻቸውን የሚያከብርላቸውን ይወዳሉ። ወላጆች ወይንም አሳዳጊዎች ልጆቻቸውን የሚወድላቸውን ይወዳሉ፤ ወላጆች ወይንም አሳዳጊዎች ልጆቻቸውን የሚቀርብላቸውን ይወዳሉ። ወላጆች ወይንም አሳዳጊዎች ልጆቻቸውን የሚፈቅርላቸውን ያፈቅራሉ። በዘመናት ሂደት አንድ ልዩ ክስተት ኢትዮጵያ ተከስቷል። ኢትዮጵያ ልጆችን የሚወድ፤ ልጆችን የሚያከብር፤ ልጆችን የሚያቀርብ፤ ልጆችን የሚያፈቅር መሪ  አላዛሯ ኢትዮጵያ አግኝታለች። ተመስገን! የኦሮሞ ጉዲፌቻ ባህል ትውፊት ነው ማለት የሚያስችል የኦሮሞ የፖለቲካ ሊቀ ሂቃን ቢኖሩ ዶር አብይ አህመድ ናቸው። በዚህ ታላቅ በሆነው የቀደምት የዕውነት ባህል ውስጥ  በአካልም፤ በመንፈስም ተገኝተዋል ጠ/ሚር አብይ አህመድ።  ዶር ለማ መገርሳም በልጆች ጉዳይ ላይ ባህርዳር ላይ ባደረጉት ንግግር አትኩሮት ሰጥተውት ነበር። እንዲያውም በፖለቲካ ሊቀ - ሊሂቃን ደረጃ እኔ ልጆች አጀን

የገቢዎች ቀን አዲስ ጥረት በኢትዮጵያ።

ምስል
የገቢዎች ቀን አዲስ ጥረት በኢትዮጵያ። „ሰው እግዚአብሔርን ይሰርቃልን ?   እናንተ ግን እኔን ሰርቃችኋል። እናንተም፦ የሰረቅንህ በምንድር ነው ? ብላችኋል። በአሥራትና በበኵራት ነው። ይህ ሕዝብ ሁሉ፥ እኔን ሰርቃችኋልና  በእርግማን ርጉሞች  ናችሁ።“ ትንቢተ ሚልክያስ ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፲፱ ከሥርጉተ©ሥላሴ Sergute©Selassie ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ዛሬ አንድ ዜና አዳምጥኩኝ የገቢዎች ሚ/ር የዘጋጀው ጉባኤ ነው። በጉባኤው ላይ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ተገኝተዋል። ጉባኤውን ያዘጋጀው የገቢዎች ሚ/ር ነው። ዛሬ በነበረው የጉባኤ ባህሬ ላይ አንድ ያስተዋልኩት ቁምነገር አለ።  ዶር አብይ አህመድ የሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ሚ/ በነበሩበት ጊዜ ከእርምጃ ወደ ሩጭ በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ የነበረው ሙሉ መንፈሳቸውን አይቻለሁኝ። ዘና ያለ ሁኔታ ብቻ ሳይሆን እርግጠኛ የመሆን አቅሙም ያን ያህል ጉልበታም ሆኖ ነው ያዬሁት፤ በግራ በቀኝ የሚወራጨውን የማህበረ ደራጎን የተስፋ ንጥቂያ ዘመቻ እና ትብትብ ሴራ ከመጤፍ አልቆጠሩትም። እንደ ዛን ጊዜው ሚ/ር እንደነበሩበት ወቅት ቅልል ብሏቸዋል። https://www.youtube.com/watch?v=vu-kkIUohRw&t=76s Ethiopia - Dr Abiy ኢትዮጵያን ማሸጋገር ይቻላል ! ከራዕያቸው ለመድርስ በሚያደርጉት ጉዞም አሸነፊ ሆኖ የመውጣት መንፈስ ልክ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ በነበረው አቅም ልክ ነው እኔ ያዬሁት -ዛሬ። ሁልጊዜም እኔ እንደምለው ንግግሩን ብቻ ሳይሆን የሰብዕን ውስጣዊ መንፈስ ለማግኘት ወደ ውስጥ ሰርስሬ ማዬትን ነው ምርጫዬ። ዛሬ የሰጠኝ ግብረ ምላሽ በጠ/ሚር አብይ አህመድ በኩል የመንፈስ ሙሉዑነት እና የለውጡ በሁለቱ እግሩ የመ

በተባረከ ማዕልት እልልታ ይድመቅ። ፍንድቅድቅ ፍልቅልቅም ይበል!

ምስል
በተባረከ ማዕልት እልልታ ይድመቅ። ፍንድቅድቅ ፍልቅልቅም ይበል! „ለቤቱ በዓይነ እርግብ የተዘጉ መስኮቶች አደረገ። በቤቱም ግንብ ዙሪያ በመቅደሱና በቅድስተ ቅዱሳኑ ግንብ  ዙሪያ  ደርብ ሠራ፤ በዙሪየውም ጓዳዎች አደረገ፤“ መጽሐፈ ነገሥት ቀዳማዊ ፮ ከቁጠር፭ እስከ ፮  ከሥርጉተ© ሥላሴ Sergute©Selassie  20.12.2018 ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ ·         የእልልታ ዕለት መነሻ … https://www.youtube.com/watch?v=lDymVE596Jc ዶ / ር አብይ ወልቃይትን የአማራ የሚያደርገውን አዋጅ አፀደቁ Ethiopia Abiy Ahmed     የህዝብ ተዋካዮች ምክር ቤት የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ረቂቅ ዓዋጅ በአብላጫ ድምጽ አጸደቀ / ዛሬ ። በ33 ተቃውሞ በ4 ድምጽ ተዕቅቦ። በጉባኤው ላይ የተገኙ 350 አባላትም ነበሩ። ረቂቅ ዓዋጁ የጸደቀው በ317 ድምጽ ነው። ተመስገን ከእልልታ ጋር ክብር ለእሱ ለአማኑኤል ይሁን። አሜን! ·        ዛሬ ለታላቋ ትግራይ ህልመኞች ሌላ የመርዶ ቀን ነው።  ለእኛ ግን የኢሰብአዊነት አወራሪሱ የማህበረ ደራጎን ዘመን ግብዕት ስለሆነ እንላልን እልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልልል። ሰው ገድሎ፤ አሰቃይቶም፤ ሰላምንም ነስቶም፤ ዘርፎም፤ ወሮም ለማይደከመው ብቻ ሳይሆን ደልቶት መኖርን ለተመኘው የህውሃት ህልም ዛሬ ደግሞ ሌላው የምሾ ቀኑ ነው። ለእኛ ደግሞ የሐሤት ቀናችን እልልታ ነው! እንግዲህ የወያኔ ሃርነት ትግራይ የማንፌሰቶ ማህበርተኞች የልሳናቸው መክፈቻ ህገ መንግሥት ተጣሰ ነውና ይህንንም በ317 ድምጽ ያጸደቀውን ፓርላማው የህግ ጥሰት ፈጸ