#ያልተደፈረው መከራ። ምፃዕተ አማራ የሴቶች በፋሽቱ ህወኃት መደፈር እና ባሊህ ባይ ማጣት።
አቋም የለሽ ሰብዕና ፖለቲከኛ ሊሆን አይችልም።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
20/12/2021
#ያልተደፈረው መከራ። ምፃዕተ አማራ የሴቶች በፋሽቱ ህወኃት መደፈር እና ባሊህ ባይ ማጣት።
1)በታቀደ የትግራይ ህዝባዊ ሠራዊት የጭካኔ የመደፈር አደጋ የደረሰባቸው እህቶቻችን የሥነ ልቦናም፣ የተደራጀ ህክምና አገልግሎት እንዳላገኙ ከሀበሻ ዩኒቲ ከተጣፈው ጦማር ተረዳሁኝ።
በውጫሌ፣ በመርሳ፣ በኡርጌሳ በቆቦ፣ በወልደያ፣ በቆቦ፣ በሃሙሲት፣ የሚገኙ እህቶቻችን የከፋ ግፍ ተፈፅሟባቸዋል። በ4 መሳሪያ የተደፈረች እንዳለችም ጋዜጠኛ ብሥራት መንግሥቱ ይገልፃል።
የሆነ ሆኖ ትልቅ ፕሮጀክት ይጠይቃል። የሙያተኛ። ጋዜጠኛው ስልክ ቁጥር ሰጥቷል ሌላ የጨመተ ተከታታይ ተግባር ያልጀመራችሁ እና የምትችሉ እባካችሁን እርዱ።
ስልክ 0919195135
የሚገርመኝ የአማራ ህዝብ እስከመቼ በውጭጭ መዋጮ እስከ መቼ ህልውናውን ሊያስቀጥል ይሆን?
2) በድጋሚ ጋሸና ሲያዝ ጋሸና እያንዳንዱ መኖሪያ በእሳት እና በመትረዬስ ነዷል ይላል የዛሬው የፈታ ደይሊ ኒውስ።
ከዚህ በተጨማሪ ተመልሰው ሲይዙት ህወኃት መራሹ የትግራይ ህዝባዊ ሠራዊት ሁለት ነፍሰ ጡር እናቶችን፣ አንዲት አዛውንት እናትን ሲደፍር ሁለት ህፃናትን በአደባባይ ረሽኗል ይላል የፈታ ደደይሊ ኒውስ። ሰሞኑን ዘጋቢወቹ ከዛው አካባቢ ነበሩ። ከዚህ ሲኦል ጋር ነው ድርድሩ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
20/12/2021
እንበርታ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ