ዛሬ የምታዮዋቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ነገ የሉም ይፈርሳሉ ወይ ይዋጣሉ ወይ ይከስማሉ። በምኞት ያለውም "የኦሮሞ ብልፅግና" ያው ጠቅላዩ ነው ያሉት ጊዜው ሲደርስ ይረሸናል 20-12.2019

 

ዕለተ - ትውልዱ።
ዛሬ የምታዮዋቸው የፖለቲካ ድርጅቶች ነገ የሉም ይፈርሳሉ ወይ ይዋጣሉ ወይ ይከስማሉ። በምኞት ያለውም "የኦሮሞ ብልፅግና" ያው ጠቅላዩ ነው ያሉት ጊዜው ሲደርስ ይረሸናል።
ለምን? ትውልዱ ታስቦ ተጠንቶበት፣ ተመክሮበት፣ ህዝብ ተወያይቶበት ፓርቲ አይደራጅም። ለዚህ መሥፈርት የበቃው ባልደራስ ብቻ ነበር በአገር ውስጥም በውጭም ተመክሮበት። እርግጥ ገፊ ምክንያት ቢፈጥረውም።
እስካሁን ባለው ተመክሮ ገፊ ጊዜያዊ ነገር ይፈጠራል አንድ የፖለቲካ ድርጅት በግጥምጥሞሽ አህዱ ይባላል ሳይሰክን ይበተናል። ወይ መራራ ስንብት እንደ ቅንጅት ይገጥመዋል።
ይህ ክብር ሆኖ ይፎከርበታል። ይህ ማዕረግ ሆኖ ዳንኪራ ይመታበታል። ጉሮ ወሸባዬ ይባልለታል።
አሳዛኙ ነገር አማራ የሆኑ ሰብዕናዎች የሚፈጥሯቸው ድርጅቶች መሪዎቻቸው አቅማቸውን፣ ክህሎታቸውን ጥበባቸውን የሚያሰክኑበት ዕድል ማጣት እንደ እኔ ኢትዮጵያ መፍትሄ፣ መድህን እንዳታገኝ ትናንትም ዛሬም የጉሮሮ አጥንት ሆኗል ብዬ አምናለሁኝ።
የፖለቲካ ድርጅት መርኽዊ ነው። ከውስጥ የመነጨ ፈቃደኝነትን ይጠይቃል። በነገሮች አስገዳጅነት ሳይሆን በሰከነ ሩቅ ራዕይ ነው ሊፈጠር የሚገባው። ግን አልሆነም።
ነገም ሞት አለ፣ ነገም መታሠር አለ፣ ነገም መታገት አለ። ለምን? የንቃተ ህሊና ድርቀት ስላለ። መቻቸል ሲያልፍም አይነካው ለኢትዮጵያ የፖለቲካ ባህል።
ለምን?
ከመርኽ ጋር ትውውቁ ሳያውቁ ያወቀ መስሎ በመታዬት የህዝብ መንፈስ ንደት ስንቅ እና ትጥቅ ስለሚሆን።
ለሸፍጥ፣ ለሴራ፣ ለበቀል፣ ለቂም፣ ለግድያ ግን እርግጥ ነው ለግርዶሽ ግድግዳ ወዘተረፈ ፕሮፖጋንዲስት ያስፈልጋል።
ሰርክ በታንቡር፣ ሰርክ በጭብጨባ፣ ሠርክ በኦርኬስተር፣ ሠርክ በወዘተረፈ ማይክ ዳንኪራ። ቅንጣት መርህ፣ ቅንጣት ዕውነት፣ ቅንጣት አመክንዮ የለም። ገለባ ብቻ።
መርኽን፣ ዕውነትን፣ አመክንዮ ያመኑ ለዚያ የታመኑ ውገረው ነው። ቢያንስ ግልቢያው ወና ስለመሆኑ እንደምን አይታያቸውም? እነማን ከትናንት እስከ ዛሬ አሉ?
በሸፍጥ በሴራ እነማንስ አልፈዋል? ማለፋ ትግል ሲገባ የተገባ ነው ግን የትውልድ ብክነት መቀጠሉ ነው ሊመረመር፣ ሊፈተሽ የሚገባው። የእነዛ ቅኖች ተሰውተው መከራው ይቀጥላል። ለምን?
50 ዓመት ሙሉ ለውጥ መጣ ሲባል ከበው የሚነኩሩ አክተሮች ዛሬም አሉ በሰፋ ዕድል፣ እነ ዶር ዲማ ነግዖ፣ እነ አቶ ሌንጮ ለታ።
እነሱ ፈጠርን ባሉት ድርጅት ሺዎች አልቀዋል፣ ታሥረዋል፣ አካላቸውን አጥተዋል፣ ዛሬም አገር ምሩ ተብለው የጫካውን ትግልም ያካሂዱታል። ኢትዮጵያም ፍዳዋ ጠና እስከ መቼ?
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
20/12/2020

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።