መማር ይታገዳል። መተካትም ይታገዳል። ኢትዮጵያ ወደ ማይምነት ጉዞ የቁልቁሊት እንዲህ ትነጉዳለች። 20.12.2020

 

ዕለተ - ትውልዱ።
 No photo description available.
 
መማር ይታገዳል። መተካትም ይታገዳል። ኢትዮጵያ ወደ ማይምነት ጉዞ የቁልቁሊት እንዲህ ትነጉዳለች።
ለስሙ የትምህርት ጉዳይን የሚከታተሉ፣ የወጣቶች፣ የሴቶች ጉዳይን የሚከታተሉ መ/ ቤቶች ተደራጅተዋል።
መማር የሚፈቀድላቸው መማር የማይፈቀድላቸው ደግሞ አሉ። የአማራ ልጆች መማር አይፈቀድላቸውም። ይህ #ስውሩ የዚህ #አውሬ ዘመን #ልዩ #መገለጫው ነው።
አመክንዮ ትንተናም፣ አመክንዮ ተጋድሎም ያልተደረገበት የነቀዘ መከራ ነው።
ለግዴታ ዘወትር በግንባር ሥጋነት የሚገኜው የአማራ ልጅ ማህይም ይሆን ዘንድ ተበይኖበታል። ይህ የውስጥ አይደለም።
ከዚህ የሚነሳ የተጋድሎ ዓይነትም አላዬሁም። ተመስጥሮ የተያዘውን ገመና ገልጦ ይህን ድውይ ዘመቻ የሚያመክን ቁምነገር አላዬሁም፣ አልሰማሁም።
የመንግሥት የትምህርት ተቋማቱ በምን ሸፍጥ ላይ እንደ ቆሙ መስታውቱ ዕውነቱ ነው። ዕውቀት የሚሳደድበት፣ የሚታገትበት አገር ኢትዮጵያ።
#ወጣቶቹ ሲታገቱ ወላጆች ፈርተው ልጆቻቸውን ትምህርት ቤት እንዳይልኩ መሰሪ ዕቅድ ነው።
ታናናሾች ትምህርትን #ሃራም ይሉ ዘንድ የተሠራ ሸፍጥ ነው። ትውልድ ቀድሞ የተማረ ይረሸናል፣ ወይ ይታሠራል፣ እጩው ሊቅ ይታገታል ይፈናቀላል።
ይህን መርምሮ የሚመጥን አመክንዮዊ አቅም ፈጥሮ ቁርጥ ያለ ውሳኔ ከመድረስ፣ ከግለሰብ ሰብዕና ግንባታ ጋር እሰጣ ገባ ነው አቅም ሲፈስ ውሎ የሚታደረው። ያሳዝናል።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
20/12/2020

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።