#ጤናችን።

 

ከአቶ ኃይሌ አሳምነው ገፅ የተወሰደ ለጤናችን።
"የሳምባ ምች/Pneumonia
የሳምባ ምች በአንዱ ወይም በሁለቱም ሳምባ ላይ የአየር ከረጢቶች ላይ ኢንፌክሽን በሚፈጠርበት ወቅት የሚከሰት ነዉ፡፡ የሳምባ ምች ከመጠነኛ ደረጃ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ሊያደርስ የሚችል ሲሆን በህፃናት፣ እድሜያቸዉ ከ65 ዓመታት በላይ ለሆኑ አዛዉንቶችና የበሽታ መከላከል አቅማቸዉ በተዳከመባቸዉ ሰዎች ላይ እስከ ህልፈተ ህይወት ሊያደርስ የሚችል ጉዳት ሊያመጣ ይችላል፡፡
የህመሙ ምልክቶች
የህመሙ ምልክቶች:- የህመሙ ምልክቶች ህመሙን እንዳመጣዉ የጀርም አይነት፣ የታማሚዉ እድሜና አጠቃላይ የጤንነት ሁኔታ ከመጠነኛ እስከ ከፍተኛ ደረጃ ሊደርስ ይችላል፡፡ መጠነኛ የሳምባ ምች ያላቸዉ ሰዎች የህመም ምልክቶቻቸዉ ከጉንፋን ጋር ተመሳሳይነት ቢኖራቸዉም ህመሙ ለረጅም ጊዜ ሊቆይ ይችላል፡፡
የህመም ምልክቶቹ የሚከተሉትንም ሊያጠቃልል ይችላል፡-
• ትኩሳት፣ማላብና ብርድ ብርድ ማለት
• ሳል
• በሚያስሉበትና በሚተነፍሱበት ወቅት የደረት ላይ ህመም
• የትንፋሽ ማጠር
• ማቅለሽለሽ፣ማስታወክ፣ተቅማጥ ናቸዉ፡፡
የህክምና ባለሙያዎን ማማከር የሚገባዎ መቼ ነዉ?
የአተነፋፈስ ችግር፣ የደረት ላይ ህመም፣ የማይቀንስና ከ39 ዲግሪ ሴንቲግሬድ በላይ የሆነ ትኩሳት፣ የማያቋርጥ ሳል በተለይ መግል የመሰለ አክታ ከገጠመዎ የህክምና ባለሙያዎን ያማክሩ፡፡
ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ ነገሮች
የሳምባ ምች ማንኛዉንም ሰዉ ሊያጠቃ ይችላል፡፡ነገር ግን በጣም ተጋላጭነትን ከሚጨምሩት ዉስጥ
• ከ2 አመትና ከዚያ በታች የሆኑ ህፃናት
• ከ65 አመትና በላይ የሆኑ አዛዉንቶች
ሌሎች ተጋላጭነትዎን የሚጨምሩ
• የበሽታ መከላከል አቅምዎ የተዳከመ ከሆነ፡- የኤች አይቪ ኤድስ፣ የአካል ንቅለ-ተከላ የተደረገላቸዉና የካንሰር ህክምና መድሃኒቶችን እየወሰዱ ያሉ
• ለረጅም ጊዜ የቆየ ህመም ካለ፡- እንደ አስምና የልብ ህመም ያሉ ህመሞች ካሉ
• ሲጋራ ማጨስ፡- ማጨስ በተፈጥሮ የሳምባ ምችን ከባክቴሪያና ቫይረስ ሊከላከሉ የሚችሉ የበሽታ መከላከያን ስለሚቀንስ
• ሆስፒታል መተኛት፡- ሆስፒታል የተኙ ህሙማን በተለይ የመተንፈሻ ማሽን ላይ የተደረጉ ከሆነ
ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች፡-
የሳምባ ምች ህክምና ከሚያጠቃልላቸዉ ነገሮች ዉስጥ እንፌክሽኑን ማዳንና ሊያመጣ የሚችለዉን ጉዳት መከላከል ናቸዉ፡፡ ሊደረጉ የሚችሉ ህክምናዎች ዉስጥ
• መድሃኒቶች/አንቲባዮቲክስ፡- በባክቴሪያ ምክንያት ለሚከሰት የሳምባ ምች አንቲባዮቲክስ ሊሰጥ ይችላል፡፡
• የትኩሳት መቀነሻ
• የሳል መድሃኒት፡- እረፍት ለማድረግ እንዲችሉ የሳል መቀነሻ መድሃኒት ሊሰጥዎ ይችላል፡፡
እንዴት መከላከል ይቻላል?
• ህፃናት እንዲከተቡ ማድረግ
• የግል ፅህናዎን በአግባቡ መጠበቅ፡- አንዳንዴ የሳምባ ምች ከሚያመጡ የመተንፈሻ ላይ እንፌክሽኖች እራስን ለመጠበቅ እጅዎን በመደበኛ ሁኔታ መታጠብ አሊያም አልኮሆል ያላቸዉ የእጅ ማፅጃ ሳኒታይዘሮችን መጠቀም
• ያለማጨስ፡- ማጨስ በተፈጥሮ የመተንፈሻ አካላትን ከእንፌክሽንን ሊከላከል የሚችለዉን አቅም ስለሚቀንስ ከማጨስ መቆጠብ
• የሰዉነትዎን የበሽታ መከላከል አቅም ማጎልበት፡- ጤናማ አመጋገብ፣መደበኛ የሆነ የአካል ብቃት እንቅስቃሴና በቂ እንቅልፍ ማግኘት የሰዉነት የበሽታ መከላከል አቅምዎን ለማጎልበት/ማጠንከር ይረዳል፡፡"
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
20/12/2021
እግዚአብሔር ይስጥልን።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።