20.12.2019 የኦሩሙማ ፀረ አማራነት። የኦሮሙማ ፀረ ሴሜቲክነት።

 

የኦሩሙማ ፀረ አማራነት።
የኦሮሙማ ፀረ ሴሜቲክነት።
ኦሮሙማ ፀረ ሴሜቲክ ነው። እርግጥ ነው ፀረ ሴሜቲክነቱ እንዳይጋለጥ በፀረ አማራነት ብቻ ላይ ያተኮረ ይመስላል። ውስጡ ግን ለቄስ ነው። ኦሮሙማ ፀረ ሴሜቲክ ነው። እውነቱ ይህው ነው።
የኦሮሙማው ጠቅሚር አብይ አህመድ ድርብ፣ ንብርብር ተልዕኮ ነው ያላቸው። አረንዛዊ ጉዟቸው ብዙ ቅን ሰዎችን አፍዟል፣ አደንዝዟል ተከታይም አድርጓል።
በብዙ ወገኖች ማዘንም የተገባ አይደለም። ሲገባቸው፣ ሲረዱት ወደ መርኽ እና ወደ ዕውነት ይመጣሉ። ይልቅ ወንዝ እያሳሳቀ እንዲሉ በዚህ የዝለት ጉዞ እንደ ቅኑ ዶር አንባቸው መኮነን አይነቱን ወገን ማጣት ግድ ይሆናል። አቅም የነበረው ሁሉ በአንድም በሌላም ዘነዘናውን ቀርቷል። ይህ የመጀመሪያው የጦርነት ዓውድማቸው ነበር፣ ተሳክቶላቸዋልም።
የሚሊዮን ፍቅር ተንበርክከው ይዝቁ የነበሩትን ተፅዕኖ ፈጣሪዎች ሁሉ ወጥመድ ውስጥ ባላሰቡት አቅጣጫ እና ሁኔታ አስገብተው፣ ቦርቡረውም ሰርስረውም ዘነዘናቸውን አስቀርተውታል። አሁን እሳቸው ብቻ አማራጭ ተመላኪ ሆነው ጉብ ብለዋል።
በሁሉም ዘርፍ፣ በሁሉም ሁኔታ መለመላውን ያልቀረ ተፅዕኖ ፈጣሪ የለም። ቢያንስ በጠላት እንዲተያይ አድርገውታል። ከሞት የሚተርፋ ካሉ እግዚአብሄርን ያመስግኑ።
ጉዞው ገና አልተጀመረም። የባጁበት የመጀመሪያው ምንጠራ ላይ ነው። በሦስት እጥፍ ገና ይቀጥላል። ተበቅለውም አይረኩም። ምድማዱ መጥፋት አለበት። መልሶ እንዳይበቅል አድርገው ነው የሚነቅሉት። ቁዘማ ከበዛ "ማቅ አውልቀን ግምጃ እንልበስ " ቲያትር ገዝፎ ይወጣል።
አላዛሯ ኢትዮጵያ ዘርሽ ይምከን ሲላት እሳቸውን አበቀለባት። በቀላል ቀመር መተርጎም አይቻልም። መፀሐፈ ሄኖክ የደፈረው ቅኔ ነበር። መልካቸው እና ሰብዕናቸው ድርጊታቸው እና የአፈፃፀም ሂደቱን ሳስተውል አስፈሪው የመፃሐፈ ሄኖክ አፈንጋጭ መላዕክታን የምድር መከራ ዕድምታ ይመጣብኛል።
ብቻ እሱ በጥበቡ ይህን ዘመን ያሻግረን እንጂ ሁለመናው የክፋነት ስልትነት ድል እና ክብር የሆነበት ጊዜ ላይ ነን። በተለይ ብቅ ብቅ ያሉ ሞጋች አቅሞች እግዚአብሄር ይርዳቸው እንጂ ኢትዮጵያን ገጥሟት ከማያውቅ የመቃብር ሥፍራ ጋር ነው ተፋጠው ነው የሚገኙት። በተለይ ቅን ሴሜቲካውያን።
ከዚህ አንፃር ግልቢያን አቁሞ እርጋታን እና ስክነትን መላበስ ይገባል። ስልታዊነት ጅልነት ስላልሆነ እዩኝ እዩኝ ከማለት መታቀብም ይገባል። ጠንቃቃነት ማህንዲስ ሊሆን ይገባል። መቆጠብ። የጥቃቱ ዓይነት እና የኦፕሬሽኑ መንገድ ትብትብ ነው። ልብ ያለው ሸብ ይላሉ ጎንደሮች።
የአማራ ልጅ አብይዝም ዘመድ ይሆኑኛል ብሎ ማረግረጉን በልክ ቢያደርገው የተገባ ይሆናል። ለእርሻ የተሰናዳ ማሳ መሆኑን አማራ ለአፍታ ቸል ሊለው አይገባም።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
ትዕግሥት ሲያልቅ ፍቅር ይሰደዳል።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።