ፅናት ማሸነፍ ነው።

 ያጣኽውን በማጣትህ ከፀፀተህ በገደልከው በደል ውስ ለመኖር አትፍቀድለት።

 

አገርን
ፈጣሪ ከመረቃት
አይዞሽ ባይ እረኛ ይሰጣታል።
ይህ ካልሆነ አገር የህዳር ዝናብ እርግማን
እንደታዘዘባት ትረዳለህ። ሰብል አልባ ትውልድም
አደራም እራፊ መጠጊያ ዬልብ ዓይን የላቸውም እና። 
 
የክፋት ሽርሽር በደግነት ላይ ማፈናቀልን ለመተግበር ነው።
 
 ገዳዮች እርቃናቸውን ተወልደው፣ እርቃናቸውን ኖረው፣ እርቃናቸውን ከመሬት ጋር እርክክብ ይፈፅማሉ። ክትመት።
 
 ትዝታ ሲሄዱ ማደር ነው።
 
 ፅናት ማሸነፍ ነው።
 
 የህሊና ድንግልና የትውፊት ማህደር ነው።
 
 
ማድመጥ ሥጦታ ነው።
እራሱን የማድመጥ አቅም ያለው
ሌላውን ለማድመጥ ዳጥ አይሆንበትም።
አቅል ያለው ትውልድ የሚገነባውም ይህ መሰል
ሰብዕና ያላቸው መሪዎች ሲኖሩት ብቻ ነው። መታደል ከበለፀገ፣ ምርቃትም ከተበራከተ የተስፋ አዝመራ ይኖራል።
 
 ትውልዱን የምናባክነው እኛ ነን። ከትናንት የተሻለ ሥርዓት መፍጠር ስላልተቻለን። ለምን? በውዳሴ ሥካር አቅም ስለሚባክን።
 ትውልዱ ይረገማል። ረጋሚዎቹ ዘመኑን አባካኞች ናቸው። የእነሱን ዘመን አክስለው፣ የዛሬውን ቀምተው፣ የነገን ማሳረር የተፈጠሩበት ነው።
 ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
17.12.2019
 

 
 
 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።