#ተስፋችን ጥግ አናሳጣው።

 

#ተስፋችን ጥግ አናሳጣው።
 

 
አንድ ዕውነት ልነግራችሁ እፈልጋለሁ። ሰው ሆኖ ተፈጥሮ እኛ እንደ ቅዱስ አድርገን የምናዬውም ሰው ነው። ይህን ግድፈታችን መቀበል ግድ ይለናል።
በህይወታችሁ ውስጥ በተለዬ አጋጣሚ በተለዬ ሁኔታ የተለዬ ችሮታ የምትለግሱት// የምትለግሷትም ሰው ናት ብላችሁ ተቀበሉት።
መፀሐፈ ሄኖክ ደቂቃን የሚላቸው መላዕክታን መውደቃቸው የምድር ክፋት ምንጭ መሆናቸውን ያመሳጥራል። ይህ ስላልተሰጠኝ አልገባበትም።
የጋዜጠኛ መዓዛ መሐመድ ህይወት ብቻ ሳይሆን 100 እስረኞች በአንድ ክፍል ውስጥ አታሠር አሳስሮኝ በግል ሜሴጅ ሊስት ውስጥ ላሉ ላቀረቡኝ እህት እና ወንድሞቼ ስልክ ለዶር ሊያ ታደሰ ያቀርብኩትን አቤቱታ ብቻ እሷ ዶር ቴወድሮስ አድህኖም ማለት ናት። ተስፋ አታድርጊያት የሚል መልስ አግኝቻለሁ።
ይህ አደገኛ አካሄድ ነው። እኔ በወሮ ቀለብ ስዩም ዙሪያ ፅፌ አወንታዊ መልስ አግኝቻለሁ። በሥራቸው ትጉህ ሰው ናቸው። አፍ እላፊ ሲሄዱ አላዬሁም። ጭምት ናቸው። የተሻለ ሥርዓት ቢኖር እኒህ ሊቅ ጥሩ ህዝባዊነት ይኖራቸዋል ብዬ አስባለሁ።
ሁሉን አውግዘን መጠጊያችን ምን ሊሆን ነው? ሁሉን ጠልተን ከማን ጋር ልንኖር ነው። ፍፁም ሰው የለም። ተስፋችን ጥግ አናሳጣው።
ሹመታቸው ከቀጠሉት ውስጥ እኔ እንኳን ደስ አለወት ያልኩት ለሳቸው ብቻ ነው። እኔ በዶር ዳንኤል በቀለም ተስፋ ስላለኝ ነው አቤቱታ እማቀርበው።
የደነገለ፣ የፀዳ መንፈስ አለ በምለው ሰብዕናም እምታዘበው ዕውነት አለ። ሰው ሰው ነውና። ሰው ሲሳት ደስ ይለኛል። ካልተሳሳተ ያ ሰው ሰው አይደለምና። ደከም ሲልም እንዲሁ። ሰው ሊደክመው ይገባል። ሊያጠፋ ይገባል።
ፍፅምና መጠበቅ አይገባም። በተለይ የአማራ ፖለቲካ መሪም፣ ተቋምም ሁነኛም የለውም ይህም ሆኖ ሁሉን ጠል፣ ሁሉን አግላይ ከሆነ አወዳደቁ ይከፋል። መሞገት በአመክንዮ ይገባል። ግን ተስፋን ማጠውለግ፣ ማጠንዘል፣ ማድረግ ጅልነት ብልህነት የጎደለው ዝልኝነት ነው።
አጋጣሚው በዬእስርቤቱ በአንድ ክፍል ቤት ለታጨቁ እስረኞችም የፍትህ ቀዳዳ ይከፍታል።
"እግዚአብሔር በአንድም በሌላም ይናገራል፣ ሰው ግን አያስተውልም።" ሳቢያዋ እሷ ትሁን እንጂ እኔ ለዓለም ህብረተሰብ ሳሳውቅ በኮረና ዘመን ዬኢትዮጵያ መንግስት በእስረኞች ላይ ዲስክርምኔሽን መፈፀሙ ይጋለጣል። ይህ ለግልብ ፖለቲከኛ ምኑም ነው።
አይደለም በቁንጥንጡ የአብይ አስተዳደር ሥር በነፃነት አገር፣ በነፃነት ግንኙነት የግል ነፃነት አያያዝ እንደምን እዬተዳደረ እንደሆን እኔው እራሴን እንደ አንድ ኦብጀክት ወስጄ እያጠናሁት ነው። ሰው ሰው ነውና።
እንቅፋት አትሁኑ። ከቻላችሁ ሼር አድርጉ። ካልቻላችሁ ዝም በሉ። በቃ ዝምታ መልስ ነው። ቹቻ ለተንተራሰ ህዝብ አቃቂር አያስፈልግም። እኔን ባን ማድረግ ይቻላል። ካልተመቸኋችሁ። እኔ ሙቿል ጓደኛ ያደረኩት የለም። ፈቅደው ካደረጉኝ በስተቀር። ጥቂት ቅኖች ይበቁኛል። 20 - 50። አጀብ አልወድም። ግጥሜም አይደለም። ተስፋዬ ባለበት ሁሉ ጥረቴ ይቀጥላል።
እግዚአብሔር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
20/12/2021
ተስፋ አይገፋም።





  • Sergute Selassie shared a memory.

     
    Shared with Public

    አስተያየቶች

    ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

    ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

    እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

    አብይ ኬኛ መቅድም።