ዝርግነት የት ያደርስ ይሆን?
ክፍተት ጎዳና ላይ …
„ዳዊት በእግዚአብሄር አመነ፤ በእሱ አምኗል፤
መጠጊያ ሆነው። ከንጉሡ ከሳኦልም እጅ አዳነው።“
መጽሐፈ መቃብያ ቀዳማዊ ምዕራፍ ፳፩ ቁጥር ፩
ከሥርጉተ©ሥላሴ
17.09.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
- · ውዶቼ የዛሬ ጹሑፌ በመደዴ ነው የሚከድበት።
መቼም ይህን የመሰለ ያለተሳበ ሲሳይ ሲገኝ በጸሎት፤
በሰጊድ፤ በሱባኤ፤ በድዋ መቀበል ግድ ነው እያልኩኝ ብዙ ጊዜ ጽፌያለሁኝ፤ ምን ያህሉ ቅን ወገኔ በዚህ ጉዳይ ተመስጦ እንደነበረው
አላውቅም።
በሌላ በኩል ወንበሩ ባዶ ነው እያልኩ ስጽፍም ነበር።
ግማሽ ፊት አይቻለሁኝም ብዬ ነበር። ያ ንጊዜ ያ ባለ ግማሽ ፊተኛ ውጭ አገር ነበሩ። አሁን ገብተዋል።
በሌላ በኩል ዶር ለማ መገርሳ የት ናቸው እያልኩም
በዬጹሑፎቼ እጽፍ ነበር። አሁንም ደግሜ ይህን ጥያቄ ማንሳት እገደዳለሁኝ።
ዶር ለማ መገርሳ በፖለቲካ ሙሉ አቅማቸው እና ብልህነታቸው
እንዲሠሩ ተፈቅዷል ወይንስ ተገለዋል? ወይንስ ይታያል ጉዱ የቤተዘመዱ ላይ ናቸው? ኦህዴድ ወደ ሥልጣን ሲመጣ በበዛ ፍሰሃ እና ደስታ ሆኖው ቃለ ምልልስ አድርገው ነበር።
አሁን በቅርቡ የዓመቱ ምርጥ የበጎ ሰው ሽልማት ላይ
ባደረጉት ንግግር ደግሞ በዛ ውስጥ እንደሌሉ እንኳን ደስ አለዎት ልል በፃፍኩት ላይ አመላክቻለሁኝ።
አቶ ጃዋር መሃመድን በሚመለከት እግዚአብሄርን ባገኘው
የምጠዬቀው ስለምን እንደ ፈጠረው እጠይቀው ነበር ብዬ ሰብዕናው አስቂኝም አሳዛኝም ሳይሆን የሲቃ ነው። ቀለሙም ግራጫማ ነው ብዬ
ጽፌም ነበር። አሁን ባሉት ነገሮች ዙሪያ ለጊዜው ስርክክር ቢልም በጥራት መውጣቱ አይቀሬ ነው።
በዶር ለማ መገርሳ እና በዶር አብይ መሃከል ክፈትት
ከተፈጠረ ብቻ ለውጡ አደጋ ሊኖረው ይችላል ስልም ነበር፤ ምክንያቱም የሁለቱ ጥምረት ብቻ ነው አቅም አለን ብሎ ልብ ሊያስጥል የሚችለው
ቁም ነገር ያለው እንደ ፖለቲካ ፍልስፍና።
የሁለቱ ጥምረት ቄሮን ሆነ የ ኦሮሞ ሊሂቃኑን ባሰለፉት መስመር ልክ፤ በጥንካሪያቸው
እና በተስፋቸው ልክ ሁሉ ነገር እንደ ቀደመው አለ ወይንስ ሃይ ጃክ ተደርጓል ቢባል የሚታዬው ይመስክር።
ብቻ እኔ ከሰሜን አሜሪካ መልስ የሆነ አንዳች ነገር
እንዳለ በተደጋጋሚ ጽፌያለሁኝ። አሁን የምናዬው የዛያ ራዲዮሎጂ ህትምት ውጤት ነው። ቀድሞ ነገር የድጋፍ ሰልፉ የተጣደፈ ነበረ። ለሞላው
ጊዜ፤ ለሞላው ቅዳሜ ደቡብ በሺህ በሚቆጠር ወገኖቻችን በተፈናቀሉበት ፋታ በማይሰጥ ወቅት ነበር የታቀደው የተደራጃው።
ከዛ ቀጥሎ
ደግሞ የአካባቢዎች የድጋፍ ሰልፎችን ተመልክተናል።
ከዛም የስሜን አሜሪካ ጉዞ እና ዕድምታውን ተመልክተናል።
ሁሉም ለእኔ የተገቡ ናቸው ብዬ አላምንበትም። ምክንያቱም ሴረኛው የአላዛሯ ኢትዮጵያ ትንፋሽ ሰጪ ስለነበር። ቀስ ያለ ነገር ነው የምወደው። የተጣደፈ ነገር አልወደም። በስብዕናም ደረጃ።
የሆነ ሆኖ ዝርግ ነገር መልካም አይደለም። ቅናትንም አፋፍቶ ጠላት አምራች ስለሆነ። ተከድኖ
የተቀመጠ ሲሳይ ቀስ እያደረክ መጠቀም ነበር ብልህነቱ። የሚያስቸኩለው ነገር በቱቦ ውስጥ ስለሚያደር ወገን፤ ከ2 ሚሊዮን በላይ
ስለተፈናቀለው ወገን፤ ዘመን ከዘመን ስለማያባራው የድምጽ አልባዎቹ
የኢትዮጵያ እናቶች ዕንባ ነበር የጥድፊያ ትኩረት ይሻው የነበረው።
መወዳደሱም ቢሆን የልብ ሲሆን ነው። ቅብ ነገሮች
እኮ አይሰነብቱም። ጤዛ ናቸው፤ ፈጥነውም ይፋድሳሉ። ዕድሉ ከአያያዝ ጉድለት ከአማካሪዎች ቅን ካለመሆን ምክንያት እዬበለዘ ነው።
መስዋዕትነቱማ ኢትዮጵያዊ ሰው እኮ ሰው መሆነ መታዬት ከቀረበት 50 ዓመቱ ነው።
ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ወደፊት መጡ ሲባል ያበደ
መንፈስ ያን ሁሉ ድጋፍ እና ክብር ሲይ የፈለገውን እርምጃ ለመውሰድ ይገደዳል። በሌላ በኩል በዛ ፍቅር ልክ እንዳይንቀሳቀሱ የዶር
አብይ አህመድን ደግሞ አቅጣጫ ቀያሽ እና አማካሪዎች በማስገለል እና በመሳቀፍ ተጠምደው ነው የባጁት የተጠጓቸው የቅርቦቻቸው።
ሴራ ነው የኢትዮጵያ ፖለቲካ ሌጋሲ። ምቀኝነት ነው የኢትዮጵያ የፖለቲካ አማራጩ ግብ። ሴረኞች እንዳሻቸው እንደፈነጩ፤
ከህግ በላይ በሆነ ሁኔታ ሰለው ገብተው ቅጣትም ቁጣም እንዳይደርስባቸው ተደረጓል። በሌላ በኩል ኮለል አልድረገህ እልል ብለህ ያሰገባሕው
አካል ከአጠገብህ ሆኖ አንተን የሚያፈርስ መንፈስ ሲያደራጅ ሰሙንም ለመጠቅስ አቅም የለም።
ኦህዴድ የተሰጠውን ታሪካው ሃላፊነት በጽናት መታገል
ሲገባው፤ በራሱ ኢጓዊ ጉዳይ ተጠምዶ በፈጠረው ክፍተት አሁን እዬሆነ ያለውን እያዬን ነው። ሰው ሰው ነው እንጂ መላዕክ አይደለም። አንድ
ድርጅት በሙሉ አቅሙ ሊንቀሳቀስ የማያስችለው አሁን የወያኔ ሃርነት ትግራይ መዋቅራዊ ጥብቆ አይደለም። በኦህዴድ ውስጥ በተፈጠረው
ክፍተት እንጂ። ኦህዴድ ተብልጧል በሴሮኞችም ተቀድሟል። ዶር አብይ አህመድ ልባቸውን አትኮሮታቸውን የሸልሟቸው የቅርቦቹ እና የሩቆቹ በ ኢትዮጵያ ፓለቲካ ውስጥ አዟሪቱ እዬታዬ ነው፤፡
ኦህዴድ በጤናው ወስጥ፤ በጠበቅነው አቅሙ ልክ፤ በተሰጠው
ቃልኪዳን ልክ፤ በአፈሰው ፍቅር ልክ አይደለም። ለዶር አብይ አህመድ የተሰጠው ፍቅር እና ስኬት ኦህዴድ የራሱ አድርጎ የመቀበል
ችግር አለበት። ለኦህዴድ የተመቸው የኦነጋውያን ክብር እና ልዕልና ነው። ደግሞ ወቃሽም ነቃሽም እሱ ሆኖ ማረፉ ነው ገራሚው
ነገር። ችግርን እዬገፉ ከደሙ ንጹሁ ነኝም አያስኬድም። እዛው ውስጥ ለዚህ አፍራሽ ሃይል ድርጁ ደጋፊ አለ።
ቀውሱ የተፈጠረው እዚህ ላይ ነው። ስለዚህ ይህን
ዕድል ተጠቅሞ ኦነጋውያን፤ አራርሳውያን፤ ጃዋርውያን፤ ህዝቃኤላውያን እንዳሻቸው አደረጉት ቀለበሱት። እነሱ እኮ ለተሰለፉበት ዓላማ
ወለም ዘለም የማያውቁ ጽኑዎች ናቸው። ተሸሽገው አይደለም በግልጽ በአደባባይ ነው የሚናገሩት።
ለዚህ ትብብር ደግሞ እንደ ታቦት የሚታዩት ኦቦ በቀለ
ገርባ ፊት ለፊት ወጥተዋል። እሳቸውን ለመናጆ ስለመጠቀማቸው አልታያቸውም። የሳቸው ተፈላጊነት ወለጋ ከእጅ እስኪገባ ድረስ ሰለመሆኑ
አልታወቀም። ስለ እናት ታደሉ እንባ ጉዳይ አይደለም ለኦሮሞ ሊሂቃን ሰውኛ ጉዳዩ።
ሌላ የአንድነት ሃይል የሚባለው የለም። በሌለ ነገር
ላይ ጊዜ እንዲባክን ደግሞ የጠ/ሚር አብይ ካቢኔ ገፍቶ ሄዶ አማራን ወገቡን አስሮ፤ አልፈስፍሶ በቀደመው የ50 ዓመት የባርነት ዘመኑ
እንዲቀጥል በአቶ ንጉሡ ጥላሁን ሌጋሲ እዬተጣደፈ
ነው። አቶ ንጉሡ ጥላሁን የኢትዮጵያን ፖለቲካ መሪ ዘዋሪ አዳረጊ ፈጣሪ ናቸው። ግንኙነታቸው እጅግ የሰፋ ነው ለራሳችቸው ሌጋሲም እዬተጉ ነው።
የአርሲው የአቦ አባ ዱላ ሌጋሲን የማስፈጸም ተልኮን ባህርዳር ላይ ቁልጭ ብሎ
ዙፋን ደፍቶ ይገኛል። ስለምን ይህን ሰው ዝም እንዳለው አላውቅም። አሰላ ላይ የመስቀል ባዕል ለማክበር ስጋት እንዳለ ልሳነ አማራ
ዘግቦ አዳምጫለሁኝ።
አንደኛ ነገር ስጋት ካለ ቤት መቀመጥ ነው። ማንም
የህግ ከለላ አይሰጥም። ዛሬ ዶር ለማ መገርሳ ይት ነህ ማለት አይቻልም። ስለሆነም አሰላ ያሉ ምዕመናን ከጀብዱ ወጥተው በስክነት
አስበውበት፤ አላስፈለጊ መስዋዕትነት መክፈል አይገባቸውም። ቤታቸው ሆነው ያክብሩ። ጎንደር እኮ በ2016 ተስተጓጉሏል።
ሁለተኛ ባህርዳር ላይ ያለው ኦቦ አባ ዱላዊ መንፈስንም
ቢያንስ አውቀንብሃል የአባት ነበር አሁን መሪው መንፈስ ያለው አርሲያዊ ነው። ተንሳፋፊዎች ዶር ገዱ አንዳርጋቸው እና ዶር አንባቸው
መኮነን ናቸው። በዚህ በብአዴን ጉባኤ ላይ ለወገናቸው ንጹህ ተቆርቋሪ የሆኑ እንደ አቶ መላኩ ፈንታ ያሉ ሰዎች ካልመጡ ቢሮው የአማራ
መግደያ ማምረቻ መሆኑ አይቀሬ ነው።
ቢያንስ የሚሞግቱ መንፈሶችን ለማስቀመጥ ታች ያለው የአማራ ልጅ ሞግቶ ለድል መብቃት አለበት።
ድምጽ አለመስጠት። ፊት ለፊት ወጥቶም መታገል። አሁን ደግሞ ለኦሮሞ
በኢትዮጵያዊነት ሥም ተንብርክከህ ሰጥ ለጥ ብለህ ተገዛ 27 ዓመት ለወያኔ ተገዝተህ የለህንም ነው ጉዳዩ። የዚህ ፊታውራሪ ደግሞ አቶ
ንጉሱ ጥላሁን ናቸው።
በሌላ በኩል ደቡብ ሞት እና መርዶ ከማህል እስከ
ዳር ታዞለታል። አማራ የለመደው ነው። አንዲትም የትግሬ ልጅ ምንም ደረሰባት ተብሎ አይደመጥም። ወያኔ ሃርነት ትግራይ + ኦነጋውያን
+ ያፈነገጡ የብአዴን እና የኦህዴድ ሰዎች በአንድ ላይ ምሾ አሳውጀው „አብይ አሁኑኑ ይነሳልን“ ዋዜማ ላይ እንገኛለን። ይህ
ደግም አብዩ አልተገለጠለትም። „ፍቅር?“ እስተምን … ? ፍቅር ለማን? ፍቅር መቼ? ፍቅር የት? ፍቅር ወደዬት ለመሄድ?
ሌላው አብረን እንሠራለን ይሉ የነበሩ ድርጅቶች ከለውጡ
ማግስት ፍርክስክሳቸው ወጥቷል። ሸንጎ የት እንደ ደረሰ አይታወቀም፤ ዶር አረጋይ በርሄ ጥለውት አገር ገብተዋል። መድረክ ደቡብና
አረናን ጎልቶ ኦፌኮ ያው ኦነግ ጋር አብሬ እሰራለሁኝ ብሏል። አገራዊ ንቅናቄው ኦቦ ሌንጮ ባቲ የሚመራው የኦነግ ቅርንጫፍ፤ በዶር
ኮንቴ ሙሳ የሚመራው የአፋሩ ድርጅት ቀድመው አገር የገቡት ናቸው። ስለዚህም ፈርሷል። ኡጋዴ ነፃ አውጪ እና ግንቦት 7 ሲባልም አንዱ ክንፍ አገር እንደገባ ተደምጧል ... ህብረት ትብብር ይሄው ነው፤ የ አቅም ብክነት ሊጋሲ ...
ራሱ ከግንቦት 7 ጋር ነበረ ሲባል የነበረው የኢትዮጵያ
አርበኞች ግንባር ቅሪተ አካል ከስሟል። ተፎካካሪም ይባል ተደራዳሪ፤ ተቀናቃኝ ይባል ተቃዋሚ አዬር አውሎ ብቻ ነበር የሚመራው አሁንም አዬር ላይ መርዶው ሳይነገር ብን ብሎ ቀርቷል። ስለዚህም አቅም ብክነት በዙር ተመለስ በብቃት ማነስ ለሚጦዘው ኢትዮጵያዊ ፖለቲካ አይገባም። የከሰለ የጠቃጠለ ካርቦን ነው።
የወያኔ ሃርነት ትግራይ በአቶ ጌታቸው ረዳ እንዴት
የኦነግ አርማ ሚሊዬነም አዳራሽ ላይ ተውለበለበ ብሎ ያዙኝ ልቀቁኝ ሲል የነበረ ጀግና በቀዩ ሰፊ አቀባበል አድርጎል ለዓርማው።
በዚህ ዓርማ ሥም ወያኔ ሃርነት ትግራይ በቀን
600 ሰው ከመግደል እስከ በቀናት ውስጥ 700 ሺህ ህዝብ ስለመፈናቀል፤ ቢያነስ እስር ቤት የተገበረው አካል እና መከራው ጉዳዩ አይደለም ለኦነጋውያን … ዕለታዊ ስንቅ እዛው ዛለ አንበሳ እና መቀሌ መጸዳጃ ቤት በሚቀር ጉርሻ ዘላቂውን መስዋዕትነት ድል አድርጎ ጫማ ሶል ሆኖ ቁጭ ብሏል።
አሁን ግጥግጡ አማራ እና ደቡብን ደም በማፈሰስ ወደ
አስቸኳይ ጊዜ የሸግግር መንግሥት እንሂድ ዋና አቀንቃኝ አቅጣጫ ላይ እንገኛለን። ለዚህ ደግሞ ብአዴን ውስጥ ያሉ እና ኦህዴድ ውስጥም
ያሉ ፊት ለፊት ወጥተው የዚህ ጉዳይ አስፈጻሚ ይሆናሉ። ለዚህ ቀዳማይ ተዋናይ ማን ሊሆን እንደሚችል የሚታይ ይሆናል።
አማራ መሬት ላይ ፍሪዳ እስከማረድ የተደረሰበት ተውኔት
ሌላው የአብይ ሌጋሲ ፈቃድ እና ቸርነት አስቂኙ ጉዳይ ነው። በዚህ ውስጥ ቄሮ ቅዱስ አትንኩ የአሁን ሞቶ ነው። ቄሮ የተሰዋለትን፤ የደማለትን ድል ለአብይ እና ለመሰሎቹ አስረክቧል ነው ጉግሱ። የገዳ ዴሞክራሲ እና ሥልጣኔ ምጥቀት፤ የጉድፌቻ ሰዋዊነት እና አምካዊ ምርቃት ትውፊትም ሻሸመኔ ላይ፤ ቡራዩ አሽዋ ሜዳ
ላይ፤ አስኮ ላይ ነገ ማህል አዲስ አበባ ላይ ቀጣይ ነው። የውስጥ ለውስጥ ትእዛዙ ግን ትግሬን እንዳትነኩ ነው። የትግራይ እናትም
አለማንባቷ አንዱ ትርፍ ዕሴት ስለሆነ መልካም ነው እንደ እኔ ለድምጽ አልባዎቹ እናቶች ለሚታገል ፍጥረት።
ቄሮ የሰጠውን ድል መልሶ የመቀማት አቅም አለው በማለት
በቡድን የተደራጁ፤ "ያልታወቁ ብድኖች፡ እዬተባለ እንዲገለጽ መንግሥት እራሱ እራሱን ለሚያጠፋ መንፈስ እዬተገላት ነው። "ቄሮ በደለን፤ ቄሮ ገደለን፤ ቄሮ አሸበረን፤ ቄሮ ደፈረን" ማን ይናገራት... ዘመኑ ኦሮማዊ ነውና ... ኦሮማይ በዳግሚያ ትንሳኤ ላይ፤ ከዚህ ቀጥሎ የሚሰውሩ ይኖራሉ ... እዬታፈኑ ...
በጄኒራል ጃዋር
የሚመራው የቄሮ ቡድን ያሻውን በአሻው ሁኔታ ይፈጽም ዘንድ ኦህዴድ ራሱ ፈቃጅ ነው። ስለምን ኦህዴድ ከአብይ መንፈስ ጋር፤ ከጎን
የመቆም አቅሙ በማነሱ ምክንያት። ፌድራል ላይ የተሰጠውን የ አደራ እቅሙ ተኗል ወይንም የኩሬ በረዶ ግግር ሆኗል። ይህን ቢጋፋ አብይ ወክሎት የመጣውን ውክልና ያጣ እና ተንሳፋፊ ይሆናል። ከዚህ በመለስ አይነካም፤ ከዚህ በመለስ በተበለው ልክ ነው የጠ/ ሚር ጽ/ቤት እዬተንቀሳቀሰ ነው ያለው።
አማራው መጪውን የጨለማ ዘመኑን መቋቋም እንዳይችል
ደግሞ እነ ጥላሁን ግዛውን የተኩ ዘመነኞች ተፈጥረው እያመሱት ነው። የአማራ ተጋድሎ ገኖ ሲወጣ „የነጻነት ሃይል“ ሲሉ የነበሩት
ዛሬም አማራ በአቀባበል በካባ በጃኖ በእግረኛ በአጃቢነት ላይ ተጥመዶ ከፊቱ የደረሰውን እሳት ማዬት እንዳይችል ግርዶሽ ተሰርቶለት እዬተደናበረ
ይገኛል።
የገረመኝ ጎንደር በሬ ታረደለት ሲባል ሰማሁኝ። ወላጆቻችን ሠርግ ተጠርተው እንኳን እንዴት ብለው እንደሚሄዱ እናውቃልን። የሆድ ነገር ምናችንም አይደለም፤ አልነበረም። ቀድሞ
ነገር ሠርግ ሲጠራ እንኳን ያን ያህል ተከብሮ የነበረው መሬት የአባቶቹን ትውፊት እያስረገጠ ስለመሆኑ ልብ አላለውም። ጎንደሬ
እንደ ከብት በአሞሌ? ይህን ሳይሰሙም ሳያዩ የሞቶት በስንት ጣዕሙ።
ጀግና አስቀመጦ ጀሌነትን የሚመኝ ፍጥረትነት ያልነበረው
ህዝብ ዕድሜ¡ ለተተኪው የሳጅን በረከት
ስምዕኦን ለአቶ ንጉሡ ጥላሁን እና ለጥላሁን ግዛው ሌጋሲ አስፈጻሚ ሳጅኖች? የመደፈረም አለው ዓይነት? የጎጃም ደምም ከንቱ ሆኖ ባክኖ እንዲቀር፤ ታሪክ አልባ እንዲሆን ተተግቶ
እዬተሠራበት ነው። ታሪኩን የሚቆረጥም ትውልድ እንዲሆን፤ ታሪክ አልባ እንዲሆን እራሱን እንዲሰርዝ … የ አማራ የማንነት ይህልውና ተጋድሎ ዝጎ እንዲቀር በትብብር እዬተሠራ ነው።
አማራ መሪም አደራጅም እያለው ግን እግር ከወርች
በሚያስር የአቶ ንጉሡ ጥላሁን ግልብጥ በረከታዊ ጉዞ ላይ ተጠምዶ የራሱን አጀንዳ ገፍትሮ፤ ሲያረገርግ ይታያል። አሁን
ነው ኢትዮጵያ ሞቷ ቀርቦ የሚታዬው። ሁሉም እርብርቡ አማራ መደረጃት የለበትም ነው። አማራ ባለው አቅሙ ልክ ወጥቶ እንዲታይ አይፈለገም። ስለምን? ለቀጣዩ ዘመናት የ አማራ ሊሂቅ መታዬት የለበትም። የጋራ አጀንዳው ይህ ነው።
የአማራ
መንፈስ መቀበር አለበት ነው። ተገድሎው ሲነሳ በነበረው መልኩ እጅግ በረቀቅ መልኩ ከሊቅ አስከ ደቂቅ በአቶ ንጉሡ ጥላሁን ሌጋሲ
ፊታውራሪነት አማራ አንገቱን ደፍቶ ህልውናውን ለማስረገጥ እና ለማስጠቅጠቅ በትጋት ቀን ከሌት እዬተሠራ ነው። ግን አቶ ንጉሡ ጥላሁን ማን ናቸው? ፍሬ ነገሩ ያለው ከሳቸው ዘንድ ነው።
አማራዊ መንፈስ እንዲቀለበስ ተግተው እየሠሩ የሚገኙት እሳቸው
ናቸው። የአማራ የቄሮ ጄኒራል ማለት እሳቸው ናቸው። ሞጋች ናቸው፤ ኮስታራ ናቸው የሚሠሩት ግን ለራሳቸው ክብር እና ልዕልና ለተፈጠሩበት
ሰብዕና እትብት ገዢነት ነው። ቃልም ተገብቶሎቸዋል።
አባ ቅንዬ ዶር አብይ አህመድ የአማራን ጥያቄ ወደ
ጎን በመግፋት እንዲያውም የአፍሪካ ቀንድ ዜግነትህን ተቀብል በሚል የዋህ ፍልስፍና ሲባዝኑ፤ አቅማቸው እዬተሸረሸረ ስለመሆኑ ልብ
አላሉትም። የቆመ የሚመስለው ሁሉ እንዲሉ ...
ትእግስት ሲያልቅ ፍቅር እንደሚሰደድ ሳያውቁት ባይቀሩም አማካሪዎቻቸው ወደዬት እጃቸውን ይዘው እዬወሰዷቸው እንደሆን
አላወቁትም። ሰከንዶች፤ ደቂቃዎች ይብራሉ … በአደብ በአትኩሮት አጠገባቸው ያለውን ነገር ባሊህ ሊሉት ይገባል።
ሌላው ቀርቶ በግንቦት 7 አቀባባል ባነር ላይ አንድም
ቦታ ለውጥ አምጪ የሚባሉት ምስል አልታዬም ከዶር አብይ በስተቀር። ዶር ለማ መገርሳ ባይፈቅዱ አብይ ይገኝ ነበር ወይ? አቶ ደመቀ
ሞከነን እጩ ጠ/ ሚር ውድድር አባልነት አልፈልግም ባይሉ ከሲነሪቲ አንጻርም ዶር አብይ አህመድ ጠ/ ሚር መሆን ይችሉ ነበርን?
ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ባይቀበሉ ጠ/ሚር አብይ አህመድ ከዚህ ይደርሱ ነበር? ህልም ነበር። „አይቡን ሳያዩ በአጓቱ ጠገቡ፡ ሆነ እና
ትናንት እዬተረሳ ዛሬን ብቻ መኳኳል ዋጋ እንደሚያስከፍል ማወቅ ይገባ ነበር።
ከሁሉም ዶር ለማ መገርሳ ቀላል ሰው አይደሉም። ትህትናቸው
ቅንነታቸው እንጂ ቁጣቸው እና ሃዘናቸው ከባድ ነው። ወኔያቸውን እራሱ ሚኒያ ላይ አይቸዋለሁኝ። በዛ ላይ የደህንነት ሰው ናቸው።
በተጨማሪም ፖለቲካ በተለምዶ ሳይሆን ተምረዎት ሊሂቅ ሁነውበት ነው።
ተምረውት ብቻም ሳይሆን በህጋዊ መድረክ መሬት ላይ ሰርተውበት ነው። ቀድሞ
ነገር በዶር መራራ ጉዲና እና በዶር ለማ መገርሳ የተምክሮ ደረጃ ሰፊ ልዩነት አለው። ሙያውን መማር እና ማስተማር በንጽጽር ሲታይ
አንድ ቀበሌ ውስጥ ሊቀመንበር ሆኖ መሰሥራት ሰፊ ልዩነት አለው። እርግጥ ነው አሁን ዶር መራራ ጉዲና ጥሩ መንገድ ተከፍቶላቸዋል የብሮድ ካስት የቦርድ አባልነት የሚሰጠቸውን የልምድ አቅም የትም አያገኙትም።
ዶር ለማ መገርሳ የልባቸው ቅንነት እርግባዊ ቢሆንም
ብልህነታቸው እና እልሃቸው ደግሞ ለተፈጠሩበት ሰብዕና የማናውቀው ነው። ለነገሩ አናቸውቃቸውም እያልኩ ብዙ ጊዜም ጽፌያለሁኝ።
ልናጣቸው የማይገባ ግን መንፈሳቸው እዬራቀ ያለ፤
ወይንም በአያያዝ ግለት ምክንያት ወደ ሌላ አቅጣጫ እንዲመደቡ እዬተገፉ ያሉ ይመስለኛል። ብቻ ከ9 ወር በፊት የማውቃቸውን ዶር
ለማ መገርሳን ማዬት ካልቻልኩ ወራት አለፉኝ። ስብሰባ ላይም ማዕቀብ ተጥሎባቸው ይሁን ፈቅደው ይሁን አይሁን አላያቸውም።
ጠቃሚው ነገር የነበረው ኦህዴድን በማስቀጠል አገራዊ
አደራን በመወጣት እረገድ የዶር አብይ አህመድ እና የዶር
ለማ መገርሳ አንድ መሆን ከሁሉም በላይ ጭንቅላት መሆን የነበረበት፤ ትውስትም የሚያስኬድ አልነበረም። ለድርድርም የማይቀርብም ነበር።
ማንኛቸውም ሰው ናቸው እና ሊሳሳቱ እንደሰው
ተጽዕኖ ሊያሳድርባቸው የሚችሉ ተደራራቢ ገጠሞችኝ ነበሩ። ማዕበሉ እጅግ ፈጣን እና ሃይለኛም ገፊ ነበር። እና ፈንገጥ ብለው ሊታዩ የሚችሉ ባህሪያትን ቢያሳዩ እንኳን ከውስጣችን ከነበረ ክብሩ እና ፍቅሩ ማበላለጥ
አይገባም። ለእኔ አሁም የምዕት ቅኔ ናቸው ዶር ለማ መገርሳ።
ከዚህ ላይ የመርህ ጉዳይ ብቻ አይደለም። እንደዛ
ቢሆን አቶ ሙስጦፋ ሙሁመድ ወደ ኢትዮ ሱማሌ ሥልጣን ባልመጡ ነበር። በውስጣቸው የመፍቅድ የመሻት ብልህነት ስለነበረ ነው አብዛኞቻችን
የምንስማማበት እጩ ጠ/ ሚር ፊት ለፊት በማምጣት፤ በልተጠበቀ ፍጥነት እና አመራር ራሳቸውን ዝቅ አድርገው የሸለሙን። ይህ ከበቂ
በላይ ነው። ማተብ ላለው ትውልድ። ከዚህ በመለስ ያለው ነገር ቢኖር እንኳን መታገስ ያስፈልጋል። ሰው እንደ ሰው እንጂ እንደ መላክ ማዬት አይገባም።
አሁን ክፍተቱ የፈጠረው መከራ ግን ለውጡን አጋልጦ፤ አቅመ ቢስነቱን እያሳጣው ነው ያለው። ጥቂት ደቂቃ ያገኙ የሴራ አባ ወራዎች የፈጠሩት ሰቆቃ እና የመሰንጠቅ አደጋ ነው አሁን እንዲህ
ለጃዋርውያን በር ከፍቶ ይህን የመሰለ ጥቃት እዬተፈጸመ ያለው። ቀጣዩ ሲታስብ አስፈሪ ነው።
ቤንሻንጉል ላይ ብቻ ሳይሆን በጥቂት ቀናት ውስጥ
አፋር ላይም የሚታዩ ነገሮች ይኖራሉ ብዬ አስባለሁኝ። ከአዬር ላይ ፕሮፖጋንዲስቶቻችን ወደ ሆላ ዙር ዘጭ ዘጭ መልስ …
ሌላው ድራማ የአማራ እና የኤርትራ መንግሥት የጫጉላ
ሽርሽር ነው። ለፈግግታ ጊዜ ቢባል ይሻላል። በአንድ በኩል የሉዕላዊት ኢትዮጵያ አስፈጻሚ አካል የህብረ ብሄር ፓርቲ ቁንጮ ነኝ፤ የ አማራ ብሄርተኝነትን ምድማዱን አጣፋዋለሁ ብሎ አደግድጎ እዬሠራ ሉዑላዊነትን የመዳፈር ተግባር ደግሞ እንዲፈጽም ተፈቅዶለታል። ስንጥቅ ፖለቲካ። የዘበጠ ጉድ ነው።
ኤርትራ የነበሩት የትጥቅ ትግል አራማጆችን በካባ ሽልማት፤ በወረቅ እብነ በረድ
የሚያንቆጠቁጠው ብአዴን እሱ ደግሞ በተራው የተረባበትን ኤርትራ የምጽዋ
የአሰብ ፖለቲካዊ ጉብኝት እና ድርድር ላይ ነው ... ግንቦት 7 እስከ ፕሮዎቹ ባህርዳር ወሎ ጎንደር ብአዴን ኤርትራ እንዴት ያለ ግጥምጥሞሽ፤ ቅልቅሎሽ
ግጥግጦሽ ነው … አማረባቸው¡
ለዛውም ከጫፉ ከፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ የፖለቲካ አቅም
የማይደርሱ ሊሂቃንን ላከ ነው የሚለው ዘገባው … ከትክት። እሳቸውን የሚመጥነው የለማ፤ የአብይ፤ የዶር ካሳ ከበደ፤ የኮ/ ጎሹ ወልዴ መንፈስ ብቻ እና ብቻ ነው፤ ከዚህ በመለስ
ያለው የውርንጫ ድካም ነው፤
ቅጥ አንባሩ የጠፋበት አንድ ዓይና ይባል፤ ሸንጣራ
ይባል፤ ጓድጓዳ ይባል፤ ጠፍጣፋ ይባል፤ ሙልሙል ይባል ብቻ ውል የለሹ ጉዞ አቅጣጫው በማይታወቅ ጎዳና ላይ ይገኛል … ማለት አልችልም። የሳዖላዊ ጉዞ ጎዳና ላይ ነው፤ አማራን
በሚመለከት ያለውን ቧልት እመለስበታለሁኝ። ቀባሪዎቹ በህብረት በአንድነት እዬተረባረቡበት ነው እንደ እድገት በህብረት ዘማቻ። ዘመነ ኢህአፓ በህጋዊ መንገድ ታጋዮቹ ከእስር አልተለቀቁም በተግባር ግን ያ ነው የሚታዬው የጫጉላው ሽርሽር በጣና ነሽ መርከብ ...
ወዮ! ለዳግም እርድ አማራ መሰናዳት የለበትም። እትብቴ ላደረሰችው ተሸከማ፤
መንገድ መርታ፤ አብልታ አጠጥታ ለሸለመችው የትምህርት የሥልጣን ልቅና አልበቃ ብሎ በዬዘመኑ ለይሉንታ ቢስ ታራጅነት ማህበርተኝነት ዛሬ ደግሞ በግልብጥ ፈረስ ሎሌኔት መሰለፍ ያሳፍራል። ለነገሩ የሳሙና አረፋ ነው ጤዛ…
ማወቅ ማለት ዕውነትን መግለጥ ማለት ብቻ ነው።
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
ማላፊያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ