የኢትዮጵያ መንግሥት ለስትራቴጂ ብቻ የሚፈለግ ከሆነ ...
ዓይን።
„የፈረደብህ በግፍ እንዳይደለ ትገልጥ ዘንድ
ስለ ሰው ሁሉ የሚያስብ ካንተ በቀር ሌላ
ፈጣሪ የለምና፤ ስለ በደለኞች፤ ሰዎች
ለመከራከር ወደ አንተ የሚደርስ ዳኛ ማነው።“
መጽሐፈ ጥብብ ምዕራፍ ፲፪ ቁጥር ፲፫
ከሥርጉተ©ሥላሴ
17.09.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።
- · መነሻ።
„በአሰላ ከተማ ነዋሪ የሆኑ የአማራ እና የሌላ ብሔር አባላት የሆኑ የክርስትና እምነት ተከታዬች
የመስቀል በዓል የደመራን ዝግጅት ተከትሎ ውጥረት እና ውክቢያ ውስጥ እንደሆኑ ኑዋሪዎቹ
ለልሣነ_ዐማራ ገልፀዋል።“
መስከረም
04/2011 ዓ.ም
https://www.facebook.com/AmharaPress/?__xts__[0]=68.
መነሻዬ የለጠፍኩት ጉዳይ ነው። ተያያዥ ጉዳዮችንም አክላለሁኝ። ኦቦ በቀለ ገርባ ስትራቲጂካዊ የ150 ዓመት ትግል ነፃነትን አሳዬን፤ የሞቱት ተነስተው ባዩልን ባይ ናቸው። ነገም ለስትራቲጂ ከሆነች ኢትዮጵያ የምትፈለገው ምን አስኪሆን ይሆን የሚጠበቃው የ ኢትዮጵያ መንግሥት የአብይስ ካቤኔ? ...
ወደ ቀደመው ስገባ ዛሬ ጥዋት አንድ መሰረታዊ ነገር
ከልሳነ አማራ ሚዲያ አዳመጥኩኝ። አሰላ ላይ መስቀልን ለማክበር ስጋት እንዳለ። አሰላ ላይ ብቻ ሳይሆን ቄሮ በተዳረጀባቸው አካባቢዎች፤
ጄኒራል አቶ ጃዋር መሃመድ በሚመራቸው ኔቶች ሁሉ መሰል ስጋቶች ይኖራሉ። ስጋቶች ካሉ ልዑል እግዚአብሄር የማያውቀው ስሌላ ቤት
መቀመጥ ነው።
በነገራችን ላይ አሰላን አየኋዋት ምንም ለውጥ የላትም። በዚህ አይነት ጢቾ፤ አምኛ፤ ዲክስስ፤ ሴሩ ምን ላይ ይሆኑ እል ለነበረው ግብረ
ምላሽ ሰጥቶኛል።
የሆነ ሆኖ እኔ ለአሰላዎች የምለው አንድ መሰቀል ባይከበር ሌላ ጊዜ ይከበራል። ልዑል እግዚያብሄር
የልብ እንጂ የታይታ አይደለም።
እግዚአብሄር ሁሉ ይቻለዋል። ትዕቢተኞችን የሚያበርደበት፤ የሚገስጽበት መንገድ አለው። ስለሆነም
ለእሱ መተው ነው። የታበዬ ባልተሰበ አደጋ ሲሰበር እንጂ ሲቃና አይቼ አላውቅም በህይወት ዘመኔ ሁሉ።፡
አሁን በማዬው ሁኔታ እጅግ የሚገርም መታበይ አያለሁ በኦነጋውያን ቤተሰቦች። እጅግ የሚያሳዝን
መጀቦንም አያለሁኝ መድረክ ላይ ጎርድድ አዬተባለ። መቼም ለእነሱ ለረጅም ጊዜ የሚዲያ ሽፋን ሲሰጡ የነበሩ አሁን ምን ይጠዋጠን
ማለት አለባቸው።
ድምጽ እያላቸው የእነሱ ድምጽ ሆነው መባጀታቸው ትርፉ ለዚህ ነበር። ውስጡ ጭካኔ እና አረመኔ
ለሆነ ሰብዕና ያን ያህል አዬር ጊዜ ሰጥቶ ማዘማነን ሰብዕዊነትን ማስረገጥ መሆኑን አሁን ላይ ያዩታል። ብቻ የተልዕኮው ጅረት ዠንጉርጉር
ነው ….
የፈለገ ቢሆን መታበይ መቀንጠሱ አይቀሬ ነው። ሁሉ ነገር ከአንድዬ በታች ነው። የአንድ ቀን
የመሬት መናድ፤ ወይንም የአንድ ቀን የሰማይ ማዕት ተባይ መፍስስ ሊሆን ይችላል፤ የተመረተው መሬት ላይ መቀረትም አለ። በጎርፍ መጠቅለቅ ሊሆን ይችላል፤ ሁሉንም ጭጭ
ረጭ ያደረገዋል በቅጽበት ቁታው። ችግሩ ለኃጣን የመጣ ለጻድቅን መሆን ካልሆነ በስተቀር የፈጣሪ ቅጣት በአንድም በሌላም ይገለጣል።
ለአሰላ የቅድሰት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ልጆች እኔ አምለው ከቤት ውስጥ በተደሞ ሆኖ ማሳለፍ ያስፍልጋል።
ለዛውም ቤታችሁ ካልመጡ ነው። ማን ጌታ አለባቸው። አሸባሪነት እንዳሻህ
ሁን የተባለበት፤ ጀግና ተብሎ በአደባባይ የሚሞገስበት፤ የሚቆለባበስበት
ወቅት ላይ ነን።
በሌላ ሁኔታ አዲስ አበባ መሰቀል አደባባይ ላይም ሊፈጠር የሚችለው ነገር አይታወቅም። ቢያንስ ህፃናት ያላቸው
ወላጆች እቤታቸው መቀመጥ ይኖርባቸዋል ለመስቀል ደመራ። ፖሊሱ ራሱ ምን እንደሆነ ምኑ ይታወቃል?
ሌላው አስጊው ነገር በህቡ የገዳይ ቡድኖችን አደራጅታቸው እንዳሻቸው እንዲፏልሉ ጸረ ሰላም ነፍሶች
እያሉ ነገ ት/ ቤት ሲከፈት ተማሪዎች እንደ አሶሳው እልቂት ተዘግቶባቸው ት/ ቤት ውስጥ ይነዱ ይሆን የሚል ስጋት ሁሉ አለብኝ።
እኔ ፈሪ ነኝ።
በይፋ አሸባሪነት ሚዲያ ተከፍቶ በሚሰብክበት በአላዛሯ ኢትዮጵያ በሚሊዮን ለሚፈናቀሉ፤ በሽህ ለሚቆጠሩ
አቅመ ደካሞች፤ በዬደቂቃው በሚደፈሩ ወላጆች፤ በአሰቃቂ ሁኔታ በሚታረዱ ወገኖች እና ለዕለት ጎሮሮ ያልበቁ ዜጎቿን የመንፈስ፤ የተስፋ መፈናቀል ሚዲያ ላይ
እዬተዋጀ የእኛ ከሆነ ማን ነክቶት ነው የተያዘው ጉድ።
"ቡድኖች ቡደኖች "ይባላል ምን ግልጡ ዕውነት ቄሮ ነው። የሚመራው ደግሞ በጄኒራል
ጃዋር መሃመድ ነው። ጸጥታ አስከበሪውም ያው ነው እሱ በእሱ። ጄናራላችን ብለው የሾሙት ዶር መራራ ጉዲና ናቸው። ንግሥና የቀቡት ደግሞ አቤቱ አቱ ንግዩሡ ጥላሁን ናቸው በአሪስኛ ዘይቤ ነው ታዲያ።
የሆነ ሆኖ ወደ ክ/ አገር የሚሄዱ የከፍተኛ ተማሪዎች ጉዳይም እጅግ አሳሳቢው ነገር ነው። ጦር
አዛዡ እኮ የክብር ሰው ነው። በከበረ ጥበቃ የሚጠበቅ። እኔ ሳስበው አንድ ኪኖ ማሰራት ይቻል ይመስለኛል። ትውናው ይገርማል።
የሆነ ሆነው ወላጆች ሊያስቡበት ይገባል። ትምህርቱ ነገ ይቀጥላል። ልጅ ግን መተኪያ የለውም።
አሁን ይህ ቦታ ያ ቦታ ይሻላል የሚባል የለውም። ምክንያቱም ኔት አለ የአብይን አመራር ሌጋሲ እንዳይቀጥል ተግቶ ሌት እና ቀን
የሚሠራ። ዋናው ሚስጢር ይህ ነው።
ይህን ደግሞ አገር ከመግባታቸው በፊት ተግተው ተጋርተውታል። አንዳንዶቹ እንደ እብደትም አድርጓቸው
ነበር። ስለሆነም ወላጆች የልጆቻቸው አዛዥ ስለሆኑ በተደሞ፤ በማስተዋል በመሆን ሁኔታውን ማዬት ይገባቸዋል።
የትም ቦታ የህግ ጥበቃ ይኖራል ብዬ አላሳብም።
በዬጓዳው ንጉስ ነው ያለው። ዘመነ መሳፍነት ነው። የሚገርመው ዘመነ መሳፍንቱስ
አሰተዳደራዊ ክልል ተሰጥቶት ነው አሁን እኮ የንጉሥ ዓይነት፤ የጠ/ ሚር ዓይነት፤ የጦር አዛዥ ዓይነት ሞገድ ላይ ነው የሚታዬው። አዲስ የመሳፍንታት፤
የነገሠታት ዘመን … በቢአይፒ ደረጃ እዬተከፈለለት ሆቴል ተይዞለት።
ሌላው የትኩረት ቀጣና የቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ የቤተ እግዚአብሄር ቅጽር ግቢ ዘበኞቿን ማጠናከር ያለባት ይመሰለኛል። ልዩ ሥርዓትም ቀርፃ ልዩ ጥበቃ ማድረግ
ይጠበቅባታል። ቁርሾው ከአራት አቅጣጫም ነው። የጠ/ ሚር አብይ አህመድ ቅንነት ለቅድስት ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ያሳዩት ፍቅር እና
አክብሮት በ የተወደደላቸው አይደለም።
ስለዚህም ከዚህ በመለስ ያሉ ጥበቃዎችን በአቅሟ ልክ ቤተክርስትያናችን ልታደርግ ይገባታል። ምዕመኑም
እንዲሁ ለቤተክርስትያኗ ዘበኛ መሆን አለበት። ቢያስፈልግ በፈረቃ አብሶ ማህብረ ቅዱሳን። በተጨማሪም ቤተክርስትያናችን ለምዕመኖቿም
የህግ ጥበቃ ጉዳይ አጀንዳዋ ሊሆን ይገባል።
ከዚህ በተረፈ ያው የተለመደው የሃይማኖት ግጭቱ ስለሚፈቀድ መስኪዶችንም ሼሔዎች ሃጂዎች ኡስታዞች
ሊያስቡበት ይገባል። እራሳቸው ሽፍቶቹ አቃጥለው ክርስትያኖች አቃጠሉ ማለታቸውም አይቀሬ ነው። ይህ ቀጣዩ ዒላማቸው ነው።
ምክንያቱም በአንድም በሌላም አብዩን መሳጣት አለበት። የመምራት አቅም የለውም እንዲባል ነው። ዋናው አጀንዳ የዚህ የለውጥ መሪ ቅስም
የሚሰብሩ ድርጊቶችን ማቀነባባር እና መምራት ነው። እነ አይነኬ እነ አቦይም ደግሞ አሉ … የእነሱ ጉዳይም ተመሪ ካለመሆን ይጀምራል።
ወደ ቀደመው ምልሰት ሲሆን ጃዋርውያን፤ "አራርሳውያን መንፈሱ"፤ ህዝቃያላውያን ጫን ተደል መከራን በማሸከም
የአብይን ሌጋሲ አደጋ ውስጥ መከተት በህግ ተፈቅዶላቸው። እንዳሻቸው እዬሆኑ ነው፤ ነገ ደግሞ ጫካ ያሰኛቸው እና ከቁጥጥርም ከአቅምም
በላይ መሆናቸው አይቀሬ ነው።
ዓለም እኮ እንዲህ ዓይነቱን አሸባሪነት እንዲህ በዝርግ ሳይሆን በሰፋ የደህንነት መዋቅር እና
ፋታ በማይሰጥ ሁኔታ ነው ልክ እምታስይዘው እንጂ እንዲህ በበዛ እንዝህላል በሆነ ሁኔታ „ፍቅር“ እያለች በሰው ህይወት ላይ፤ በዜጎች
ነፍስ ላይ የጭካኔ ሙከራ አታደርግም። ህግ ስለምን ኖረ። የዳኞች ቢሮስ ስለምን ተከፈተ። አለም በአሸባሪዎች ላይ ቆፍጣና እና ኮስተራ እርምጃ ነው የምትወሰድው። ግሎባሏ አለም
መረጃው ከኖራት በያለበት የነፈስ አሸባሪን ልኩን ለማስያዝ ፋታ አትጥሰጠም ግን ልበ ደፋር መንግሥት ከኖረ ብቻ።
ሌላው የጄ. ዘይኑ ጀማል ዘመናይነት ነው። እሳቸው ሸክም ናቸው ለአላዛሯ ኢትዮጵያ ራሱ። እሳቸው
ማን ምን እንደሆነ ሊነግሩን አይችሉም። ኦነግ ትጥቁን ጥሎ የገባው የኤርትራ መንግሥት ትጥቁን ስላስፈታቸው ብቻ እንጂ ሰላማዊ ትግል ፈልጎት አይደለም፤ ተራራ ላይ ተንጠልጥሎ ሰላም ማውክ ነው የተፈጠረበት።
OMN አገር
የገባው በጀቱ ስለቀነሰ ነው ወይንም ስለታጠፈ ነው። ወደው አይደለም። „ሲያጣ የጦመውን“ ነው የአሁኑ የሰላማዊ ትግል ጉዳይ ምርጫ
የሆነው። ቃለ ምልልሶች እኮ የመታበዩ ልክ ቋቅ ያሰኝ ነበር ከኦህዴድ ጋር በዶቼቬሌ በነበረው ቆይታ።
ይህም ሆኖ ዕድሉን በልክ መጠቀም የአባት ነው። "ፊኒፊኔ ዩንቨርስቲ" እያልክ፤ „በአልረባ የሰንደቅዓላማ
ጉዳይ አንጨቃጨቅ“ እዬተባለ፤ „መሬታችን የእኛ ነው አንተ መጤ ነህ ውጣ እዬተባለ፤ ሬሳህም አገር አይገባም ነበር እዬተባለ፤ አሳህይሃለሁ
እዬተባለ“ አንዲት ሰከንድ ካቴና የማያውቀው ነፍስ፤ በዬደቂቃው እዬተፎከረ መዘባነን አግባብ አይደለም። መንጠራራቱ ክልክ በላይ ነው። የመንግሥት ቸለልተኝነት ደግሞ ወጎቹን እያስፈጀ መቋደሻ እያደረገ ነው።
ኮንፊደንስ ጣሪያ ሲነካ አንባገንነት
እና አረመኔነት የሚጠበቅ ነው።
የኦሮሞ ወጣት የፖለቲካ ሊሂቃንን ተቀባይ ለማድረግ በስንት መከራ የተሰበሳበው የሥነ - ልቦና
አቅም ሁሉ አፈር ድሜ ነው ያስጋጠው ጃዋርውያን ሆኑ እሱን የሚደግፉ ኦህዴድ ውስጥ የመሸጉ ነፍሶች ሁሉ።
አብይ መንፈሱን ለማስጠቃት የታሰበው ማህበረሰቡ የሰጠውን ክብር ነጥቆ ድንጋይ እንዲወረወርበት
ነው የተሴረው። ክብርን ከልብ ሞልቅቆ የሚያወጣ ጉዳይ ነው በተደራጀ፤ በተቀነባበረ፤ በታቀደ ሁኔታ እዬተከወነ ያለው። „ጥቂት
ሰዎች ያላታወቁ ሰዎች“ ይባላል፤ ከትከት ... ከሜሪኩሪ ነውን የመጡት?የልዩነት ግድግዳው ከ አብይ ሌጋሲ ጋር መናዱን ሳይሆን ግድግዳው መጥበቁን ነው እያዬን ያለነው።
እኛ እኮ አሳምረን እናውቃቸዋልን፤ የእነሱ ልሳን የሆኑትን ሁሉ ስንሞግት ኖረናል። አዲስ ነው
የሚባለው የኦቦ በቀለ ገርባ ጉዳይ ብቻ ነው። ሳናውቃቸው እሳቸው አውቀውን በልባቸው ሲስቁብን ነው የኖሩት። በጅልነታችን ግን ፈጣሪን
እናመሰግነዋለን። ሌላውማ ይታወቃል …
ነገን አታገኛትም ፉከራው ቀረርቶው እፍኝ በማይሞሉ መንፈሶች። ዕውነት የኢትዮጵያ መንግሥት
ሊያፍር ይገባዋል። አንድ ጃዋር ከአፍንጫ ተቀምጦ … ?ያ ያነገሳችሁት፤ የቀሰሳችሁለትት፤ እነ አቶ ንጉሡ ጥላሁን ከባህርዳር
አስገስግሶ ለአቀባባል አዲስ አባባ ያስመጣ፤ ብድግ ቁጭ ብለው እነ ዶር ገዱ አንዳርጋቸው ያሰተናገዱት፤ የዩንቨርስቲ ሊቀነ ሊቃውንት
አድምጡ ሽብርን፤ ጭካኔን፤ ግልብ ስሜታዊነትን፤ ግራጫ ሰብዕናን ተብለው የተፈረደባቸው … ግፉ በዛ … ራስህ ከፍ አድርገህ ታወጣለህ
ራስህን ለማስመጥ?
… ምን አለ ድሃው ይለቅ … ከዛ "ይቅርታ ፍቅር መቻቻል" ምንትሶ ቅብጥርሶ በሰው ልጅ ነፍስ ህልውና ጢባ ጢቦ ጨዋታ … አሁን ደግሞ የሆነው ሁሉ ከ ከኦነጋውያን መንፈስ
የራቀ ነው … እመኑን። አሁን ያለው የኪጋሊ ዕጣ ፈንታ ፊት ለፊት ነገ ቀጣይ ነው … አፋጣኝ እርምጃ ካልተወሰደ።
ኢትዮጵያ እኮ በራሷ ላይ ፈረሺ ተብሎ ተፍርዶባታል። አቅም ካልኖረ የመቆጣጠሪያ ስልቱ ጥበብ ከሌላው ለምን በሩ ተበርግዶ ተቀላቀሉን ተባለ። ለህዝብ እልቂት። 2 ሚሊዮን ህዝብ በ አንድ ዓመት ብቻ ተፈናቅሎ? አልበዛንም? ይህ አይበቃንም? ያውም በሰው ሰራሽ ችግር። ተጠያቂ የለ? የሚፈረድበት የለ። በ አደባባይ በጥይት የተጨፈጨፈ ዜጋ አምላክስ ከዬት ይህድ?
ጀዋር መሐመድ ዛሬ አ.አ ውስጥ ስለተፈጠረው ግጭት የሰጠው መግለጫ
Ethiopia:
የኦፌኮ
ምክትል
ልቀመንበር
አቶ
በቀለ
ገርባ
ከOMN
ጋር
ያደረጉት
ቆይታ
አሁን ኦህዴድ ኦፌኮ ቢባል ማን ያዳምጣል። መታመን እኮ ከሜዳ አይታፈስም። ብዙ ተደክሞበት ነበር።
ድካሙንም ከንቱ አድርገውታል ከራሱ ከኦሮሞ የተፈጠሩ ልጆቹ። ሰው ከሚጠላው ጋር ልኑር፤ የሚጠላኝም ላክብር ብሎ እንኳን መኖር ካልቻለ ቀጣዩ
ምን ሊሆን ይችላል? ጆሮ መንፈግ። ልብ መንፈግ ነው። በልብ መሸፈት ነው። በመንፈስ መሸፈት ነው።
አሁን እኮ በታሪክ አይደለም እንደ አሶሳው ት/ ቤት ተዘግቶ ቃጠሎ ያለው እያዬው በዬጓዳው እዬገባ
ነው መከራው ቋያው። መሠልጠን፤ አባ ገዳነት፤ ጉድፊቻዊ
ትውፊት ሁሉም ነገር ዕድሉ ተሰጥቶ ታዬ፤ ተሰፈረ፤ ተለካ … የሚታዬው የሚደመጠው ሁሉ እንደ ሰው የሆኑ ነገሮች አይደለም። ማለከክም
ማመካኘትም አይገባም።
ጥሩ ሲሰራ የኦህዴድ የቄሮ ጀግንነት ፉከራ ነው፤ ቀረርቶ ነው። እነሰሳዊ ባርባሪዝም ሲከወን
ደግሞ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ነው ይባላል። ቧልት መቆም አለበት። አይደለም እራሱ እጁ ተነክሮበት ቢሆን እንኳን አገር እምራለሁ ካለ ኦህዴድ
ከማንኛው ድርጅት ሴራን ቀድሞ ማክሸፍ ግዴታው ነው እንደ ድርጅት እንደ ካቢኔ የአብይ ካቢኔ።
መምራት እኮ መቅደም እንጂ መቀደም
አይደለም። ማነው ጡጦ የሚጠባው? አናውቅውንም ኦነግን እኛ? መቼ ነው ኢትዮጵያን አገር አለኝ ብሎ የሚያውቀው?
መቼ? እኔ እንዲያውም ይገርመኝ ነበር እማከብረው ህብር ራዲዮ ለእነሱ ድምጽ ለአቶ ጃዋር መሃመድ እና ለፕ/ ህዝቃኤል ጋቢሳ ይሰጥ
የነበረውን ድካም ሳይ፤ በሌላ በኩል ግንቦት 7 እና ፕሮዎቹም አገራዊ ንቅናቄ እያሉ ሲወድቁ ሲነሱ ነበር። "ቁጭ ብለው የሰቀሉትን ቁሞ ማውረድ ይችግራል"
ጄ/ዘይኑ ጀማልም ዘመናይነቱን ቢያቆሙ መልካም ነው። ነፍሱ አንድ ነው። መነሻውም መድረሻውም አንድ ነው - ሴራ።
ፌርማታው አንድ ነው ቢቻል እስላማዊ ኢትዮጵያን ባይቻል ኦሮማዊ አንባገነናዊ መንግሥት በወረራ መመሥረት።
ያንገሸግሻቸዋል ኢትዮጵያ የሚለው ድምጸት። በሽታቸውን ያስነሳል ኢትዮጵያ ሚስጢር ናት ሲባል፤
በዚህ ሙግት እኮ ነው ፕሮፌሰር ህዝቃዬል የሚታወቁት እንዲሁም ፕ/ አባስ። ያንደፈድፋቸዋል የኢትዮጵያዊነት ጠረን ሆነ መንፈስ። ዕውነት ነው ይህ።
ዶር አብይ አህመድን እኮ መስማት አይፈልጉም ነበር። የተቃዋሚውን ሥራ ለእኛ ተውልን ሲሉ የነበሩ እኮ
ናቸው። ይህም መብት ነው፤ ነገር እንደ አገር ነፃነት ፈላጊ ማህበረተኛ አድርጎ ማዬት ግን ያቅለሸልሻል። ማመን እኮ የነፍስ ጉዳይ
ነው። ያልተፈጠሩበትን ከዬት ያመጡታል። ለእነሱ ኦሮምያ ናት የነፍስ ጉዳያቸው ኦቦ በቀለ ገርባ እንዲያ የሞራል መላክ ያደረግናቸው ሳይቀሩ ...
https://www.youtube.com/watch?v=SWzcsoc2twQ
„በስትራቴጂ ተምርቶ እዚህ እንዲደርስ ከ150 ዓመት በፊት የዛሬዋ ቀን እንድትታይ አንዴ
ተነስተው ይህን ባንዴራ እና ነፃነት ቢዩ ምን ይሉ ነበር።“
አማርኛ ዜና OBN 05 01
2011
በስተጀርባቸው ያሉት ፕ/ ህዝቃዬል ገቢሳ ናቸው፤ ፍካታቸውን እና ቁጭታቸውን ማዬት
ነው። ይህ አርማ ኢትዮጵያን ሳይሆን አገር አለችን ኦሮምያ የምትባል ነው። ቄሮ ደግሞ ኦነግ የታገለው ለኢትዮጵያ አንድነት ነው
እያለ ይጨፍራል።
ዓለም መስክሮልናል ለሚሉት ዕድሜ ለግንቦት 7 ይበሉ፤ የአማራ ተጋድሎን የህልውና አብዮት ያጫጫ መስሎት ግንቦት 7 እስከ ሚዲያው በግንባር ቀደምትነት እስከ አውሮፓ ህብረት ድረስ እሱ ሠርቶላቸዋል፤ ሰሞኑን ክብርት የፖለቲካ ሊሂቋ ክብርት አና ጉምዝ ጀግና ሲጠዬቁ "ቄሮ" ነበር ያሉት። የተሰጣቸውን። የተቀለቡትን መረጃ። ትግሉ እንዲህ ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ "ለአማራ መብት መታግል
አማራ መሆን አያስፈልግም" ዓመቱ የንግግር ጥበብን አስደምጠውናል ፕ/ ብርሃኑ ነጋ። ከዳር አስከ ደንበር የሠሩትን የሸፍጥ ተግባር አሳምረው እያወቁ
ህሊናቸውን ተዳፈረው … ይህም ብቻ አይደለም አማራ እና ትግሬ አይገዛነም የሚል መርህ እያራመዱ …
በሌላ በኩል ደግሞ እኛም የቄሮን ተጋድሎውን ሳንነጣጥል እኩል ከ አማራ የህልውና ተጋድሎ ጋር አክብረን ሚዛናዊ በሆነ ሁኔታ
ታትረንበታል። ሌላው "ስትራቴጂያዊ" የምትለው የኦቦ በቀለ ነገር የአሁኑ ጉዞም ቀጣዩ አብሮ መቆዬት ለእስትራቴጅ ብቻ ሰለመሆኑ
ሰፊ መረጃ ሰጥተዋል። ሰብበሰብ ማለት ያስፈልጋል። ሁሉም ቀበቶውን ማጠባበቅ። በርን ከፍቶ እንዳሻህ ማለትም ገደብ ሊበጀልት ይገባል። ቂልነት ከዚህ በኋላ መብቃት አለበት።
ጃዋርውያን ፊት ለፊት እሳቸውን ያመጡበት ምክንያት ግን ያቺው ለእስላማዊ መንግሥት ምኞት ሽፋንነት በሳቸው ሰብዕና ለመጠቀም ነው። ሌሎች ደግሞ
ኢብሳውያን የሠሯት ስትራቴጂ መሆኑን እግረ መንገዴን መጠቆም ግድ ይላል። ሌላው እስር ቤት አብረው የነበሩት የነፃነት አርበኞች
የሽግግር መንግሥት ሲሉ የነበሩትም ለስትራቴጂ ብቻ እንደተፈለጉ ዓዋጁ እሰከ ድንጋጌው ተገልጧል። አዬ የሞኞቹ ብዛታችን … ዲካ የለውም እኮ ታማኝነታችን ... "ስትራቴጂያዊ" ተጋድሎ የ ኦሮሞን አገራዊ ሰንደቅዓላማ ማዬት ነበር ... ግልፆቹ ቢሉ ምንም አይደለም። በኦቦ በቀለ ገርባ እና ግን አያምርም ...
ውዶቼ መድረክ ላይ የነበረውን ሙሉውን ሂደት ፈለጉት እና እንቅስቃሴያቸውን እና መንፈሱን
የምታውቋቸው እኒያ ፈርሃ እግዚያብሄር ያደረባቸው ኦቦ በቀለ ገርባ አይመስሉም። መታበይ ጎልቶ ታይቶባቸዋል። እንዲህ እኮ
አልነበሩም። ሊናገሩ እኮ አንደበታቸውን ለመክፈት የሚናፈቁ ሰው ነበሩ? ግን ምን ነካቸው?
በፍጹም ሰው እንዲህ ሆኑ ሁለት ገጽ ሲኖረው ማዬት መልካም ባይሆንም ከጣለብን ምን
እናድርገው፤ የሚገርመው ለነፃነት፤ ለኦሮሞ ሰብዕዊ መብት መከበር ታገዮቹ እነሱ ተወልጆቹ ብቻ ነበሩ ይሉናል። እኛ ደግሞ አለቅላቂዎች
… አንጣፊ እና ጎዝጓዦች። ኢሜላቸውን ባገኘው ደስ ይለኝ ነበር … ምን ያህል ግብር እንደተከፈለ አፋቸውን የሚያስዝ መረጃ
በእጄ ላይ ስለሚገኝ። ያፍራሉ ስለሚያድርጉት ሁሉ ነገር ያን ቢዩ …
የአሁኑስ መከራ ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ሰንደቁ ባለው ንቀት አይደለምን? አንድ የድርጅት የፖለቲካ
የዘውግ ድርጅት የአገር መለያ ይሁን እኮ ነው ጦርነቱ። ሁሉ የማይገልጸው፤ የማይደፈረው ደግሞ ይህ የበታችነት የሚበላው በሸታ ነው።
ኢትዮጵያ የተበጀችው በኢትዮጵውያነት ነው። የማርሻል ቲቶ ድል የማን
ነበር? ያን ጊዜ የአውሮፓ ሚዲያ አምድኛ ማን ነበር ለመሆኑ? በዬትኛው ሰንደቅስ ተዋድቆ? ሮምን ያንቀጠቀጠ የጀግኖች ቁንጮ ማን
ነበር?ኢትዮጵያ የቆዬችው ዛሬ አፋቸውን ሞልቶ የሚያናግራቸው ማናቸውም ነገር የሰንደቁ ገድል ነው።
የእነሱ በሽታ ግን ይህው ራሳቸውን አሹልከው ቅኝ ግዛት ምኞት ያሸከማቸውን መርግ ተሸክመው ዕድላቸውን
በዬዘመኑ ማሽሎክ ነው። ይህው አገር አይደለም አህጉር
ምሩ ተብሎ እኮ ተሰጠ …
መሆን የአባት ነበር … እንደ ተወቃሽ አጤዎቹ … ሜዳውም ፈረሱም ተብሎ ተሰጠ ማጣፊያው ያጠረው የእነሱ አቅም፤ ክህሎት ትእግስት አልቦሽነት ብቻ ነው።
አብይ „ፊቱ እንደ ለማ ኦሮሞ ባይመስልም፤ ንግግሩ እንደ አማራ ቢመስልም“ ተወደደ - ተፈቀረ
- ተቀባይነት አገኝ - ተሸለመ የሚወድቁበት የሚነሱበት ጉዳይ ይህው ቅናት እያብጠለጠላቸው ነው። በራሳቸው ወገን ላይ ይህን ያህል የሚያድሙ የሚያሴሩ ...
የአብይ
ልዕለና ግን የአሮሞ አቅም ማመሳከሪያ ጽላት ነበር ቢገባቸው ቢያውቁት። የአብይ አቅምም ቢሆን አፍ ሞልቶ
የሚናገሩለት እንጂ እንደ አሮጌ ጨርቅ፤ ብል እንደ በላው የሽንት ጨርቅ ለባጅ የሚፈልግ አልነበረም። ይበልጣቸዋል፤ አይገናኙምም።
ድንፋታ፤ መታበይ አይደለም የአብይ አቅም፤ ምንጩ መኖርን ለማድመጥ በትሁት መንፈስ መፈቀድ እንጂ። ቢያስወቀሰው
ወገገኔ ለሚላቸው ውስጡ አድርጎ ዕውቅና እንዲያገኙ የሄደበት ሩቅ መንገድ ነው። ይህ እኔ ስወደው ውደዱልኝ የማለት … ነገር …
በመቻል ውስጥ ሰላም አመጣለሁ ብሎ ራሱን ለሚያንዱት የራሱ ወገኖች ጊዜ መስጠቱ በአንድ መልኩ፤ በሌላ መልኩ ለተቆርቋሪዎቹ እና ለጀርባ
አጥንቱ ብጣቂ አትኩሮት አለመስጠቱ … ለሚገዘግዙት ከሰጣት ቅንጣት ለ አማራ ማህበረሰብ መሰጠት አይሻም።
ከአብይ ውጪ አቅም አለኝ የሚል ለዘመኑ ከኦሮሞ ቢመጣ ዶር ለማ መገርሳ፤ ኮ/ ጎሹ ወልዴ ብቻ ናቸው። ሌላውን
ለሌላው ሊሆን ይችላል ለሥርጉተ ግን መጀመሪያ ቢሮ ማደራጀት ይቻልበት … ትምክህቱ ከዛ ይጀመር …
የኔዎቹ ዕውነትን መድፈር ብቻ ትውልድን ከብክነት ያድናል። መድፈር አለብን ድክመቶችን፤ መገላላጥ
ያስፈልጋል ሽፍንፍን ብለው ያሉትን ገመናዎችን ሁሉ። ከአገር በላይ ማንም ምንም የለም። ከሰው ፍጥረት በላይም ማንም ምንም የለም።
ዘመን ጥሩ ነው ኦቦ በቀለ ገርባም ተለውጠው አሳዬን … ይገርማል። ብቻ ተመስገን። የሳቸውን ጉዳይ ለመልመድ ጊዜ ያስፈልገኛል ከመንፈሴ
ለማውጣትም እንዲሁ ተመስጦዬ ነበሩና።
ኢትዮጵያዊነት ከመፈጠሩ በፊት ፈተናን አሸንፎ የተፈጠረ ሚስጢር!
የኔዎቹ ውዶቹ ቅኖቹ ኑሩልኝ።
መሸቢያ ጊዜ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ