አዲስ አበቤ ሆይ ይቅናህ!
ለዘላቂ ህልውና አይ ተመራጭ መንገድ ነው።
„ጽኑ ፍለጋ ታሳያለህና ወደ መርከብም
በመውጣት ኖኅን አድነሃልና።“
መጽሐፈ ጥበብ ምዕራፍ ፲፬ ቁጥር ፬
ከሥርጉተ©ሥላሴ
17.09.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ
ቀጣዩ የአዲስ አባባ ዕጣ ምን ይሆን?
ከአልጎሼ አይጠራም። ብራቦ አዲስ አባባ! ህልውናህን
የሚጠበቀው በአቅምህ ልክ ነው። ክብርህ የሚጠበቀው በህሊናህ ልክ ነው። መኖርህ የሚረጋገጠው በጥበባዊ የአይ ተጋድሎህ ልክ ነው።
አዲስ አበቤ ሆይ!
የእኔ አዲስ አባባ ብለህ መነሳትህ የተገባ እና ፍትኃዊም ነው። አዲስ አባባ የእኔ፤ የአንተም፤ የእንቺም፤ የእርስዎም ናት
ብለህ መነሳትህ መልካም ነው። ተቋማዊ ካልሆነ ግን የወረት ነው የሚሆነው። ጤዛ!
አዲስ አበቤ ሆይ!
አቅምህ ዝምታህን ጥሶ መውጣቱ ጎሽ የሚያሰኝ ቢሆንም
ይህን አቅምህን ወደ ባለቤት ያለው ተቋም ማሰደግ
ግን ግድ ይለሃል። ተጋድሎው
በዚህ መልክ እንደ ሳሙና አረፋ ተኩረፍርፎ መቅረት ሳይሆን 50 ዓመት በትጋት እና በታታሪነት ተዶልቶ 27 ዓመት ተመስጥሮ የቆዬው
ለመደራደሪያነት የነበረው የአንተ የህልውና ክስመት ድንጋጌ ነበር። የአንተ የቁም የቀብር ሥርዓት ነበር። የአንተ የብትን አፈር
ለማኝነት ሌጋሲ ነበር የ50 ዓመቱ የታጋድሎ ዝክረ ድንኳን።
አዲስ አበቤ ሆይ!
ህልውናህን ከነገ ባሻገር ማዬት፤ ከማግስት ባሻገር
ማድመጥ፤ ከበስቲያ በላይ በርቅት ገና ላልተወለዱት፤ በጽንስም ላልታሰቡት ልጆች እና የልጅ ልጆችህ ስለሆኑ ዛሬ ብቻ ሳይሆን በተከታታይ
ሳትሰለች፤ ፈጽሞም ሳትደከም በጀመርከው መልክ ትግልህን አቀናጅተህ በትእግስት፤ በማስተዋል፤ በፍር ኃ እግዚአብሄር፤ በፈርኃ
አላህ ማድርግ ይኖርብሃል።
አዲስ አበቤ ሆይ!
ማናቸውም መደለያዎች ህልውናህን ለቀብር ቀጠሮ የሳጥን፤
የቹቻ፤ የሰኔል ጊዜ ቢያራዝመው እንጂ መፍትሄ ሊሆን ስለማይችል ቁልጭ ያለ፤ ጥራት ያለው ኢትዮጵያዊ ዜጋ መሆንህን የሚያረጋግጥ
ህጋዊ ዕውቅና በዓዋጅ ረቆ፤ ጸድቆ እስክታዳመጥ ድርስ ማቋረጥ የለብህም። ድል ሂደት ነው። ሂደት ደግሞ ሳይታክቱ መከራን መቀበል
ይጠይቃል።
አዲስ አበቤ ሆይ!
በግልጽ የተደራጁ ብቻ ሳይሆን በስውር የተደራጁ ገዳይ
እስኳዶቹም እንዳሉ ተረድተህ፤ ባዶ እጅህን መሆንህን አውቀህ፤ ህግ ስለ አንተ ያለውን ጥበቃ ልክ ለክትክተህ፤ አቅምህ በሚፈቅደው
ልክ ብቻ ሰላማዊ ታገድሎህን ግን መቀጠል ይኖርብሃል።
አዲስ አበቤ ሆይ!
ከጀብዱ ነገሮች፤ ከስሜታዊ ነገሮች፤ ከቁሩሾ ጉዳዮች
በእጅጉ መቆጠብ ይኖርብ ኃል። በማስተዋል በመከባበር፤ በመደማመጥ ቢያስፈልግም እዛው አደባባዩ ላይ ምንጣፍህን
ይዘህ፤ ምግብ እና መጠጥህን ይዘህ፤ በቋሚነት መባጀት ብቻ ህልውናህን ሊያስቀጥል የሚያስችል ጫና የመፍጠረ አቅም ይኖረዋል።
አዲስ አበቤ ሆይ!
የበዛው እና የገለማው መታበይ እና ውጤቱ ቀጣዩን
ጊዜ መራራ የመስዋዕትነት ወቅት እንደሚያደርገው ቢታወቅም፤ ጥንቃቄን መታጠቅ ግን ያስፈልጋል። ታገሽ መሆንን መርህ ማድርግ ይጠይቃል።
ሌላውን ለማጥቃት አለማሰብን ይጠይቃል።
መቻል ሲባል መከራን ተሸክሞ ግን ድምጽን መሰማት
ስለሆነ ከህግ በታች እንጂ ከህግ በላይ የሆነን መዳፈረን ታግስህ፤ በህግ ሥር - ሆነህ አንተን ማንነትህን ሊገልጽ በሚችለው በተፈጥሮዊ ሥልጣኔህ ልክ ትግልህን ተደራጅተህ ቀጥል!
አዲስ አበቤ ሆይ!
በርታ!
አዲስ አበቤ ሆይ አይዞህ!
አዲስ አበቤ ሆይ!
ቅኖች ቢያንስ በጸሎት ከአንተ ጋር በመሆናቸው ለህልውናህ
የምታደርገውን ታገድሎ አትፍራው! አትዘናጋ! አታፋግፍ!
አዲስ አበቤ ሆይ!
ትግልህን በተሟላ ኢትዮጵያዊ ጨዋነት እንደ ቀደሙት
አባት እናቶችህ ተምሳሌነት ቀጥል! ትውፊትህን መሬት ላይ የምትተረጉመበት ጊዜው አሁን ነው! አትሰልቺ! ከድካም ነው ውጤት የሚገኘው።
ድከምህ ለህልውናህ ለተስፋህ ለነፍስህም ጭምር ነው።
አዲስ አበቤ ሆይ!
ይቅናህ!ለተሰዉት በዚህ ደቂቃ
ጭንቅና ሰቆቃ ለበረታባቸው ወገኖቻችን መጽናነቱ አዶናይ ይስጥልኝ። እንበርታ!
- · ምርኩዝ።
Ethiopia:መሬት አንቀጥቅጥ
የተቃውሞ ሰልፍ በአሁኑ ሰዓት በመስቀል አደባባይ
ፈጣሪ ሆይ በቃችሁ በለን!
የኔዎቹ ኑሩልኝ።
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ