7.2 ሚሊየን ቤቶችን እንገነባለን ወይስ እናፈርሳለን ?

7.2 ሚሊየን ቤቶችን እንገነባለን ወይስ እናፈርሳለን ?
መቼም << አብዛሀኛዎቹ የመንግሥት ሰዎች ቁርጥ ላይ እንጂ ቁጥር ላይ እስከዚህም ናቸው! >> የሚባለውኮ በምክንያት ነው!
የከተማ እና የመሠረተ ልማት ሚንስቴር ከአመት በፊት ይፋ ባደረገው "ዕቅዱ" 7,200,000 (ሰባት ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺህ) ቤቶችን በ 10 ዓመታት እገነባለሁ ብሎን ነበር ። ይህም ማለት፦
<< በዓመት 720,000 ቤቶች ፤ በወር 60,000 ቤቶች ፤ በቀን ደግሞ 2,000 ቤቶችን እገነባለሁ! >> ማለት ነው!
እንግዲህ ቁጥር የሚዳፈረው ተግባረ ዜሮው መንግስታችን ፤ በእስካሁኑ ልምዱ 400,000 ቤቶችን ለመገንባት 18 ዓመታት ፈጅቶበታል።
አይደለም በቀን 2 ሺህ ቤት ሊሰሩ (ሊያመርቱ) ይቅርና ለፕሮፓጋንዳ ''ሰራናቸው '' ያሏቸው ዳቦ ቤቶች እንኳ ፥ በቀን 2 ሺህ ዳቦ ማምረት አልቻሉምኮ!
ለመሆኑ ግን ሌላ ሌላውን ቁጥር ማግተልተሉን ተውትና ፥ ከታቀዱት 7 ሚሊዮን 2መቶ ሺህ ቤቶቹ ስንቶቹ ተመረቱ? ወይስ ደግሞ እቅዱ '' የ7.2 ሚሊየን ዜጎችን ቤቶች እናፈርሳለን!'' ነበር ወይ ?


 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።