ያላለቀ መከራ ሰርካዊነት።

ማንዘርዘሪያ።
„ክፉ አድራጊዎችን ሁሉ ጠላሁ።“
መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፭ ቁጥር ፭
ከሥርጉተ©ሥላሴ
16.09.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ።

ትናንት እና ከትናንት በስትያ ሌሎች ተግባሮችን እዬተከታተልኩኝ የተሰጡ መግለጫዎችን አዳምጥ ነበር። በመጀመሪያ የአቶ ታከለ ኡማ የአዲስ አበባ መግለጫ ከውጭ ለሚመጡ እንግዶቻችን አዲስ አበባ አቀባባል ታደረግለች የሚል ዕድምታ ነበረው። 

ኦነግ እና ግንቦት 7 ብቻ ነው ወይ በስታዲዬም ደረጃ አቀባበል የሚደረግላቸውን ያሰኛል? የኦጋዴም፤ የአፋርም፤ የትግራይም፤ የአማራም፤ ኢትዮ መንፈስ ያለቸው የሲቢክስ ድርጅቶች መሪዎች እኮ ከዚህ ቀደም ገብተዋል። ምነው የዜግነት እሮብ እና ሲሶ ነበረውን ወይንስ አለውን? ሌሎቹ እኮ ከነመፈጠራቸውም አይታወቁም።

በአክቲቢስት ደረጃ የኢትዮ ሱማሊያ፤ የአፋር፤ የአማራ፤ የጋንቤላ /ኢትዮ/ ገብተዋል እነሱስ ዜግነታቸው የእንጀራ ልጅነት ያህል ነውን? ለነገሩ ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ሚሊዬነም አዳራሽ ንግግር ሲያደርጉ ሁለት የኦነግን ክንፍ ሲጠሩ፤ ሌሎችንም ሲዘረዝሩ አንድም የአማራ ድርጀት ሊሂቅ ሲጠሩ አልሳማሁኝም። አንድም የአማራ አክቲቢስት ሲያወሱ አልሰማሁም፤ ዶር አብይ አህመድ አብነት በሆኑበት በጎ አደራጎት ደግሞ አዲስ አባባ የከንቲባ ጽ/ቤት መልካም ተግባር ሲከውን ሰነባብቷል። 

ለነገሩ የብአዴን የካባ እና የጃኖ ልዩ ዝግጅትን እወክላለሁ ለሚለው አማራ አብራክ እና መህጸን ለተገኙ ሊሂቃኑን ሲቀበልም ሲያሰተናገድም ክብር ሲሰጥም አልታዬም። ይህ የአቶ ንጉሡ ጥላሁን ሌጋሲ መሆኑ ባይጠፋኝም ፊት የተነሱ ዜጎች መኖራቸውን ግን ግልጥ ሊሆን ይገባል። አማራም ይህን ከታሪክ እዬተጋፋ ስለመሆኑ ማወቅ ይኖርበታል። ባይታወርነቱ ቀጥሏል ለዛውም በተደራጀ ሁኔታ። 

በአማራ ስም ሥልጣን ይዘህ ተቀምጠህ ሳጅን በረከት ሰምዖን እዬወቀስክ ከዛ የከረፋ ተግባር ሲፈጸም እዬታዬ ዝምታ እስከመቼ ያሰኛል። አማራ የአንተ ነው ተብሎ ተቆርምጦ በተሰጠው ቀዩ እንኳን የሚታዬው የከረፋ ተዛነፍ ተግባር ድንቄም ለውጥ ያሰኛል።

ከሁሉ ያሳዘነኝ ያሰለቀሰኝ ግን የሞራል መምህር እላቸው የነበረው የኦቦ በቀለ ገርባ የሰሞኑ መግለጫ ነበር። ማዘን ሲባል የማዘነም ዓይነት አለው።  ቆሰልኩኝ። እጀ ሰባራ ስላደረጉኝ። ቃላቱ ራሱ አንድን አገር ብቻ ሳይሆን የሥነ - ምግባሩ አቅም ሉላዊነትን፤ ሰብዕዊነትን ይመራል ከሚበላ ክቡር ዜጋ የሚጠበቅ አልነበረም። „ወረበሎች‘ ዱርዮዎች“ ወዘተ … 

ከዚህ አልፎ ፎቶው አፈጻጸሙ ሪከርድ ይሁን ሲባልም እኛ ኢትዮጵያን የመግዛት አቅሙ ስላለን ፍርድ እንሰጥበታለን የሚል ቂም የቋጠረ ነገር ነበረው። ብቻ ከሳቸው በፍጹም ያልጠበቅኩት ብቻ ሳይሆን የማይመጥናቸው ውስጥ ነበር የተገለጠው። እኔ እንጃ እሳቸውን በዚህ ልክ ገምቻቸው አላውቅም ነበር።

ሌላው ያው የሚከበሩት አቶ ታዬ ደንዐም ችግር ፈጣሪውን ገፋ እያደረጉ ወደ ወያኔ ሃርነት ትግራይ የማሻገር ጉዳይ የተጉበት ጉዳይ ነው። ጥፋቱን ማሻገር አይገባም፤ በዬደቂቃው እኮ ፉከራ እዬተደመጠ ነው። ድምጥማጣችሁን እናጠፋለን እዬተባለ ነው። ለምን ወደ አሻጋሪ ይሄዳሉ?

ሰበር ዜና … .ከአዲስ አበባ ግጭቱ ጀርባታየ ደንደኣ
በዛው ሰሞን የኢንጂነር ስመኘው የተሰጠውን ኢ ፍትሃዊ የግለት ውሳኔ ያቀረቡበት ዘይቤ ከሳቸው የህግ እና የእውነት ደፋርነት የማይጠበቅ ሆኖ ሳለ አሁን ደግሞ ቅኝቱ ቅድስና አለን፤ በእኛ ዘመን እዬሆነ ያለው መልካሙ የእኛ ሲሆን ክፉው ግን ሌሎች ያደራጁት ነው ማለት ራስን ያሰገምታል። ይልቅ ዘመነኛ ነን እና እኛ ስናጠፋ የተጋባ ህጋዊ ነው ማለቱ ይበጃል።

በተመሳሳይ ሁኔ ኦቦ አዲሱ ረጋሳ ያቀረቡትም መሰሉን ነው። የሚገርመው ኦህዴድ ለዓርማው መታገሉን አቁሞ ለኦነግ ዓርማ እና ፍላጎት ቀጥ ብሎ ቆሟል። ኦፌኮንም የራሱን ድርጅት ዓርማ እና ፍላጎት ወደ ጎን ተወት አድርጎ ለኦነግ አርማ እና ፍላጎት ጥብቅና ቆሟል። እርግጥ ነው አብረው ሊሠሩ መስማማታቸው ይታወቃል። ይህ የቀደመ ስምነታዊ ነገር ነበርን?  

ሲደመር ሁሎችም የኦነጋውያን ዓላማ አራማጆች ስለመሆናቸው ቃለ ምልልሳቸው፤ ጹሑፋቸው፤ ቶኑ ራሱ ይመሰክራል። የጠ/ ሚር ጽ/ቤትም ከክብር ላይ ክብር፤ ከሊሻን ላይ ሊሻን ለቄሮ ከመሸለም ወዲያ ሃግ የማለት አቅም የለውም። እንዲያውም አሁን እኔ ሳስበው አዬሩ ኦነግ የነገሠበት ሆኖ ነው የሚሰማኝ። በመንፈስ የለውጥ አዬሩ ተለውጦ ኦነጋውያን እንዳሻቸው እንዲሆኑ ተፈቅዶላቸዋል።

እኔ በአቶ ጃዋር መሃመድ ምንም እማቀርበው ወቃሳ የለኝም፤ በሚዲያውም OMN  እንዲሁም። ለተፈጠሩበት ዓላማ ወለም ዘለም የለም። እንደ ሽንብራ ቂጣ አይገላበጡም። ተሸሽገው፤ አዩኝ አላዩኝ ብለው፤ ተደብቀው ተሰውረው ሳይሆን ፊት ለፊት ወጥተው የሚፈልጉትን በሚፊልጉበት መልክ እዬፈጸሙ ይገኛሉ። ያደረጃቱንም እንሱ ራሳቸው ያውቁታል። አብይን ከነመንፈሱ መፈንገል ወይ ማስፈለግል ... ይህ ተቀዳሚ ተግባራቸው ነው። 

አገር የገቡትም በሜዳው እንዳሻቸው እንዲሆኑ አይዟችሁ ተብለው ነው። ሁሉ ነገር በቅፅበት ነበር የተሰናዳላቸው። ፍጥነቱ እጅግ ያስተዛዝብ ነበር። ስለዚህ ከእነሱ የሚጠበቀውን ነው ያደረጉት። ለዛውም ደቡብ እና በአቶ ንጉሡ ጥላሁን መንፈስ የሚመራው ብአዴን ጉዝጓዝነት ተጠቅመው ራዕያቸውን ለማሳከት መታተር አገር የገቡበት መሠረታዊ ጉዳይ ነው። አይዟችሁ ተብለዋል። 

በዚህ ውስጥ ሴራ በረጅሙ የተጠነሰሰበት የአብይ ካቢኔ ሁለመናውን ክፍት አድርጎ ሆድ ዕቃውን ገልጦ፤ አማራን በስፋት አግልሎ ሌላውን አቅፎ  አክብሮ፤ አስከብሮ የጀመረው ጉዞ እንዲቀጥል ሳይሆን ተሰብሮ እንዲቀር የተባባሩት በፈለጉት መልክ እንዲሳጣ፤ ይነሳልን አብይ አሁኑኑ እንዲባል ተግተው እዬሠሩ ስላሉት የሴራ ባልደረቦች በቂ አክብሮት በቂ ዕውቅና ሰጥቶ እያሸሞነሞናቸው ነው።  ዝምድናውን ያዝልቅ ብለናል ... 

ቅኑ የአዲስ አባባ ህዝብ 5 ሚሊዮን ወጥቶ የደገፈው ለሴራውም ፖለቲከኛ፤ ለኦነጋውያን የማፈናቀል ዘመቻ ተጋልጦ ባለቤት አልቦሽ ሆኖ የህግ ጥበቃ እና ከለላ፤ የሚዲያም ጥግ ሳይኖረው ልክ በ97 የተደገመውን ሰቆቃ እዬከፈለ ይገኛል።

ሌላው ቀርቶ በዚህች ደቂቃ አንድም የመንግሥት እና የግል ሚዲያ እዬሆነ ስላለው ነገር ዘገባ የለውም። ሁሉንም ተዘዋውሪ አድማጭላሁኝ። 

አዲስ አባባ ላይ በግፍ በዚህች ቅጽበት ህይወት ያልፋል፤ ሴቶች ይደፈራሉ፤ ህፃናት ያለቅሳሉ፤ ነፍሰጡሮች ይንገላታሉ ለኦሮምያ ፓሊስ ደግሞ አስኮ ቡራዮ  ሊማሊሞ ሆኖብኛል እያለ ያሸፋል … ይስቃል፤ ይደልቃል … ለጤናችን እያለ ዋንጫውን ያነሳል።

ቀደም ባሉት ቀናት የፖለሲ ኮሞሸንሩ ጄ/ ዘይኑ ጀማል የኤርትራው መሪ ፕ/ ኢሳያስ አፈወርቂ ኢትዮጵያን ሲጎበኙ ህዝቡ የመንግሥት ዓርማ ብቻ ይዞ ይውጣ ባሉበት አንደበት፤ ኦነጋውያን የፈለጉትን ይዘው መውጣት አለባቸው ሲሉ ተደምጠዋል። ግንቦት 7 ዴሞክራሲ እያለ ያላጋጥል። እዚህ በነፃ አገር ያልሰጠውን ዴሞክራሲ … ሲያፍን፤ ሲያሳድድ፤ ብዕር ፈርቶ ማዕቀብ ሲያስጥል እንዳልኖረ ሁሉ፤

የሆነ ሆኖ አዲስ አበባ ባለቤት የሌላት ከተማ ናት። አዲስ አባባ ደጋግሜ እንደተናገርኩት ገና የምትከፍለው መከራ አለባት። ሌላው ቀርቶ ሁሉንም ክልል ጠ/ ሚር አብይ አህመድ ነዋሪውን፤ ሽማግሌዎችን፤ ወጣቶችን አወያይተዋል፤ አዲስ አባባን በመሰሉ ፕሮግራም ማወያዬት ሲገባቸው አላደረጉትም። ስለምን? ብልህ ስለሆኑ ያውቁታል እሳቸው ራሳቸው።

አሁን የአቶ ዳውድ ኢብሳ አቀባበል ከተለያዩ ከተሞች የመጡ የኦሮሞ ወንድሞች እህቶች አቀባበል እንዲያደርጉ የተደረገበት ከተማ አዲስ አባባ የኦሮምያ ስለሆነች ሸምተው እንዲሄዱ የተፈለገው የሥነ - ልቦና የባለቤትነት ጉዳይ ነበር። ይህ ፍሬ ነገር በልብ ጫካ ውስጥ መሽጎ በዬደቂቃው ልብን በማሸፈት፤ በቀጣይ ጊዚያት እዬፈነዳ ሰላም ያሳጣል።

ትናንት በልብ ውስጥ አዲስ ቦንብ ተቀብሯል። ከዚህ ቀደም ጥያቄው የሊሂቃኑ ነበር ሄሮድስ መሰል ዜናው ስለሸላሟቸው። አሁን በህዝቡ ውስጥ እንዲገባ ሆን ተብሎ በስልት ተቀነባብሮ የተከወነ የፖለቲካ ፖሊሲያዊ ተግባር ነው። እኛ አይደለነም ከጽንፍ እስከ ጽንፍ የኦሮሞ ጥያቄነው ለማለት አዲስ ካሪክለም ተነድፏል። 

ልክ ጣሊያን ኢትዮጵያን ሲለቅ ኢትዮጵያን በዬጊዜው እያፈነዳ የሚያምሳት ዛሬ የምናዬውን የክልል መከራ አሸክሞን እንደሄደው ሁሉ ያ ነው ትናንት ቅዳሜ 15.09.2018 የተፈጸመው።

ይህ ደግሞ ከሊቅ አስከ ደቂቅ ሁሉም የኦሮሞ ሊሂቃን የሚስማሙበት ነው። ከተማችሁ ይህች ብቻ ናት ነበር የትናንት ልዩ ሥጦታዊ ሽልማት። ሌላው መጤ ነው ቁም ነገሩ። ለዚህ እንግዲህ ሁሉችም የሰጡትን መግለጫ አዳምጣችሁታል፤ በአንድም በሌላም ተወራራሽ ነው። አህዳዊ ቶን ነው ያለው።

ሌላው እኔ ያልተመቸኝ የኦሮሞ ወገኖቻችን ተቋማት ጥቃት መድረስ የተገባ አልነበረም። የወገን ሃብት ማቃጠል፤ መንደድ ጀግንነት አይደለም። እንደዚህ ካለ ነገር መታቀብ በእጅጉ ያስፈልጋል። ከማቃጠል ምን ትርፍ ይገኛል። በዛ ድርጅት የሚሠሩ ምስኪኖችስ ምን ሰረተው ይደሩ? አለመተዛዘን። 

ቀጣዩ ነገር እንደዛ እግሩን እዬነቀነቀ በቁጭት እና በእልህ አቶ ጃዋር መሃመድ የተናገረው ነው ዛሬ እዬተከወነ ያለው። ተናግሬ ነበር ሽግግር ላይ ይህ እንደሚመጣ ሲል ነበርም።

በማግስቱ ነው ይህ የተከወነው መጪው ጊዜ መራራ ስለመሆኑ አዲስ ሥዕል ይሰጣል። በራሱ በኦህዴድ ውስጥ ያለው አዬር አስፈሪ ነው። በራሱ በብአዴን ውስጥ ያለው ሁኔታም አስፈሪ ነው። የታመቀ ያልፈነዳ ጉዳይ አለበት። የላዩ ቅቡን ሳይሆን ወደ ውስጥ ዘልቃችሁ ስታጠኑት ማንዘርዘሪያ ማጣሪያ የሚያስፈልጋቸው የታመሱ ነገሮች አሉ። የጊዜ ብክነቶች፤ የአቅም ብክነቶች፤ የትኩረት ብክነቶች ... ያደክማል ... 

ለአዲስ አባባ ግን በተናጠል ይህን የከፋ መከራ መሻገር ስለማይችል አዲስ አባባ ብሄር አልባ ስለሆነች በዚህ መንፈስ አንድ ጠንካራ ድርጅት ካልተፈጠረ ነገ ለሚወለዱት፤ በሃሳብ ላልተጸነሱት ብትን አፈር አያገኙም። ሁሉም ሲጀምረው በዚህ መልክ ነው።

የዛሬ የወልቃይት እና የጠገዴ መከራ ወላጆቼ እንደ ነገሩኝ ቀደም ባለው ጊዜ ሰቲት እዬመጡ ለሥራ ተቀጥረው የሚያገለግሉ የትግራይ ሰዎች ነበሩ፤ መሬት ላራሹ ሲታወጅ ተወልጄው ሱዳን ሲገባ እነ ተጋሩ ጫከ ሲገቡ ወላጆቻቸው ሲሰሩበት የነበረውን ታሪክ እና ምኞት አደረባቸው እና ለትግል ብለው እዛው መሸጉ፤ አገሬው እንደ እንግዳ ተቀበለ፤ ቀለበ፤ አብሮ ታገል ዛሬ የክርስቶችን መከራ ይቀበላሉ።

አዲስ አባባም መጪ ዕድሏ ዛሬ በምታደርገው ብሄራዊ፤ አህጉራዊ እና ዓለምአቀፋዊ ትግል ይወሰናል። ከተኛች ሬሳ ታቅፋ ትቀራለች፤ ለነፃነቷ ከተነሳች ግን እዬሞተች እራሷን አስከብራ ትዘልቃለች።

ከመደራጀት በላይ ሌላ መፍትሄ የለም። ቢያንስ በመንፈስ መደራጃት። ለአዲስ አባባ ዞጋዊ ሳይሆን ሉላዊ የሆነ አደረጃጀት ጠቀሚ ነው። አንዷ የሉላዊነት አብነታዊት ከተማ ስለሆነች። የሚያስከብር መደራጀት ብቻ ነው።

ሌላው ስለግለሰቦች ዝና ክብር ልዕልና ሳይሆን ስለ ሰው ልጅ ህልውና ማሰብ ይገባል። ይህ የጤዛ ጉዞ እንደ ኩርድሾቹ ብትን አፈር ለማኝ ከማድረግ አያድነንም።

በዚህ የሀዘን ቀን ዳንስ እና ጭፈራ፤ እልልታ እና ኩልልታ መቼም ያሳፍራል። ያሳዝናልም። ሌላው ኤንም ቢንም ሲኒም እንዳይከፋው የሚለው ነገር አያዋጣም። መልካም ሲሰራ ደፍሮ ማመስገን ሲጋባ፤ እንደዚህ ዝበት ሲታይ ደግሞ ዕውነቱን መናገር ሌላው ቢቀር ሰዋዊ ጠረን ያለው ስለመሆኑ ልብ ሊባል ይገባዋል።

ቄሮ „ኦነግ ለኢትዮጵያ ህዝብ ይታገላል“ እያለ ሲጨፍር አዳምጨዋለሁኝ። እንኳንስ አንደበቱ አጥንቱም ኢትዮጵያ የተጸዬፈ ድርጅት ነው ኦነግ ማለት።
አሁንም ለመሸጋገሪ እንጂ ኢትዮጵያን ወይ ቀጥቅጦ መግዛት ወይንም ደግሞ መፍለጥ ነው የሚፈልገው። "ኢትዮጵያ" ማለትን ቃሉን እንኳን አይደፍራትም። ነፍሴ ከ ኦነግ ነፃነት አይጠማትም። ደግሞም አያድርግብኝ።  

ሌላው የሚፈራው ደፍሮ መናገር የማይቻለው የሃይማኖት ጉዳይ ነው። ኦነጋውያን ምን እንደሚፈልጉ እነሱም ያወቁታል እኛም እናውቀዋለን። ይህም ለኢትዮጵያ እና ለኤርትራ እጅግ አስጊው ጉዳይ ነው። እነሱ ያበሰሉት የኛው ሰው ደግሞ ልብ ብሎ አስቦት የማያውቀው አሳሳቢ አመክንዮ ነው።

የኖረ ኑሮ አሁን ምን ስላሰበ ይሆን አቶ ጆዋር መሃመድ የሀጂ ጉዞ ያስፈለገው …? የነገን ጨለማ ዛሬ መታገል ካልተቻለ ትውፊትም - ታሪክም - እኛንም አልባ እንደምንሆን ማሰብ ያስፈልጋል። ይህ ዕሴታዊ እሳቤ መሬት ያዬዛ፤ በቅጡ የተደራጀ እና መሪም መረበም ያለው ነው። እራቅ አድርጎ ማሰብ ያስፈልጋል። „ልብ ያለው ሸብ“ ቅድስት ቤተክርስትያን ልዩ ጥበቃ እንዲረግላት ሁሉ ማስደረግ ይገባታል። አንዷ ዒላማ እሷው ናት እና።

ለወጡን ያመጣው በቄሮ ትግል ነው ይባላል፤ ጥፋት ሲመጣ ደግሞ በወያኔ ሃርነት ትግራይ ይላካለካል። ሚዛናዊ እንሁን። አሁን ያለው መንግሥት በኦህዴድ የበላይነት የሚመራ ነው። የልብ ልብ የሚሰጠውም ለዚህ ማህበረሰብም ይሄው ነው። ስለዚህ መጪው መከራ ምን ሊመስል እንደሚችል እዬታዬ ነው። 

ወገን፤ ዜጋ የሰው ልጅ ተገድሎ ተዝቅዝጎ ሲሰቀል፤ አንኳር የመንግሥትም የግልም ዜና አይደለም፤ በአደባባይ የተገደለ ኮከብ ዜጋ ዜና ደመ ከልብ ነው ይህም ፍትሃዊ ነው በኦህዲድ መሪነት ዘመን ሲሆን። በውነት ያማል።

ሌላው ውጪ አገር የነበሩትን የፖለቲካ ታታሪዎችን፤ ድርጅቶችን ሲቀበል የኢትዮጵያ መንግሥት ጥንቃቄ ሊያደርግ የሚጋባው ጉዳይ ነበር። አንድ ይህን ጉዳይ በባለቤትነት የሚከታታል ኮሚሽን ነገር እንኳን አላቋቋመም። ውጥንቅጡ የወጣ ጉዳይ ነው ያለው። 

ምክንያቱም የዲያስፖራ ፖለቲካ በአዳራሽ በመተቃቀፍ ብቻ የሚከላ አይደለም። የዲያስፖራ ፖለቲካ ራሱን የቻለ የሴራ፤ የሸር፤ የሥልጣን ሱስ፤ አንዱን ቀብሮ ራስን የማብቀል ትብትብ ሌጋሲ ነው። 

እኔ ስለ አቶ ጃዋር መሃመድ ብዙም ማለት አልሻም። ብቻ ጠ/ሚር አብይ ወደ ስልጣን ሲመጡ እዚህ ጄኔባ መጥቶ  በእንግሊዘኛ መግለጫ ሰጥቶ ነበር፤ ራሱ ከሰበሰባቸው ደጋፊዎቹ ጋር ሌላም ተናጋሪ ነበሩ። ጄኔባ ታላቅ የሆነ የፖለቲካ ትኩሳት ያለበት ከተማ ነው ኢሹ መሆን ይፍልጋል።

ከዛ በመቀጠል ደግሞ ኬኒያ ለኢትዮጵያ መንግሥት ያደረገችው አቀባበል እና ሚዲያው አስቀድሞ በነገረ አብይ ትጋቱ ያሳሰበው ነፍስ እዛ እንደነበር እና „ምሩን“ አሉን ሲል ከራሱ አንደበት አዳምጫለሁኝ አሁን ደግሞ ሃጂነት አሰኘው።

ወስጡ የሚንተከተከው ፍላሎት አገር በገቡት ሆነ የነፃነት አዬር መገኘቱ ችሮታውን በምን መልክ እንደሚያው በማስተዋል ሊታይ፤ ሊመረመር ይገባል። ግጭት መኖሩም የተገባ ነው ባይ ነው። ምክንያቱም የሚሻው ነገር አለ።
 … ግን ኦህዴድ እራሱ በዶር አብይ መንፈስ ውስጥ ነውን?ይብቃኝ …
  • ·       ያያዣ።

አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ በባንዲራ ጉዳይ ትናንትና ዛሬ ግጭት መፈጠሩን ነዋሪዎችና ፖሊስ አስታወቀ።

/ / ዐቢይ አህመድና የፌደራል ፖሊስ አዛዥ ዛሬ በወቅታዊ ጉዳይ የሰጡት መግለጫ

የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን፣ የአርበኞች ግንቦት ሰባት እና የኦሮሞ ነፃነት ግንባር አመራሮች በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ በጋራ የሰጡ

/ ታከለ ኡማ ሰለ ኦነግ አቀባበል የሰጡት መግለጫ

ጀዋር መሐመድ ዛሬ . ውስጥ ስለተፈጠረው ግጭት የሰጠው መግለጫ

ቄሮዎች ኢትዮጵያን እኖዳለን አማራን እኖዳለን

Ethiopia: ኦፌኮ ምክትል ልቀመንበር አቶ በቀለ ገርባ OMN ጋር ያደረጉት ቆይታ

ነፃነት፣ ወንድማማችነትና እኩልነት ካለፈዉ ታሪክም ሆነ ከባንዲራ በላይ ነዉ!!” – አዲሱ አረጋ

Ethiopia: የኦሮሚያ ክልል ኮሚሽነር አቶ አለማየሁ እጅጉ በክልሉ ስለተከሰተዉ ችግር ሁኔታ ተናገሩ!!



 ጌታ ሆይ እባክህን የሰጠህንን ተስፋ አትንጠቀን?
የኔዎቹ ኑሩልኝ።

መሸቢያ ጊዜ። 

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።