ዶር ደብረጽዮን ምን እያሉን ነው? ስታውሱን ካሉ በጥቂቱ .. ገመናችሁ።

ዶር ደብርጽዮን  ምን አያሉን ነው?
„አቤቱ ዝናህን ሰምቼ ፈራሁ፤
በዓመታት መካከል ሥራህን ፈጽም“
ትንቢተ ዕንባቆም ምዕራፍ ፫ ቁጥር ፪
ከሥርጉት©ሥላሴ
18.09.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድንድ።




  • ·       መነሻ ምርኩዝ።

የትግራይ ክልል መንግስት ለዶ/ አብይ የፌዴራል አስተዳደር ማሳሰቢያ ላከ
ከትግራይ ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት የተሰጠ መግለጫ 17.09.2018

አንዳንድ ሰዎች „ወያኔ ይሻላል“ እያሉ ነው። ቃሉ አባባሉ እራሱ ያሳፍራል። ከጭካኔ ጭካኔ ምን ይመረጣል? ከሞትስ ሞት ምን ሌላ ሞት ይመረጣል፤ ከኢ- ሰባአዊነት ኢ - ሰብዐዊነትስ ምኑ ይመረጣል?

ከአረመኔነት ምኑ ሌላ አረመኔነት ይመረጣል፤ ሁሉም ጸረ ሰው፤ ሁሉም ጸረ ተፈጥሮ፤ ሁሉም ጸረ እግዚአብሄር ናቸው።  እስታውሱን ከሆነ ትንሽ እስኪ ከጭካኔያችሁ ምስል ጋር በምልሰት ዋንጫችሁን አንስታችሁ የተለመደውን ፈንድሻ ርጫ ርጫ ማድረግ ነው

 ..ለዛራችሁ፤ ለገዳዩ አውሌያችሁ፤ ለአረመኔው ቆሌያችሁ። ምን አለ ዝም ብትሉ ደግ መሪ ሰጥቷችኋዋል አትንኳቸው፤ አትድረሱባቸው፤ እንኳንስ የሰው የዶሮ ደምም አይደፍሩም ትብሎላችኋል፤ ታውጆላችኋዋል። ዘር አላጠፉም ተብሎ ተመስክሮላችኋዋል የሰማዩን ቁጣ መስቀረት ከታቻለ፤ ልጅም ካወጣ ...  


ወያኔ ሃርነት ትግራይ በእያንዳንዷ ቀን ሲገድል፤ ሲዘርፍ፤ ሲያሳድድ፤ ሲያሰድድ፤ ሲደፈር፤ ሲጨክን ነው የኖረው። ለመሆኑ ወያኔ ሃርነት ትግራይን እንደ ሰውስ፤ እንደ ድርጅትስ ማዬት ይቻላልን?


በተብዕት ዘር ማፍሪያ ሽቦ ሰዶ የሚአሰቃይ? ከእባብ ጋር ሰዎችን የሚያሥር፤ አንበሳ ጋር ሲያታግል የሚያድር? ሴቶች ዘቅዝቆ የሚደበደብም? የዘር ፍሬን እንደ እንደ እንሰሳ የሚሸልት? ለመሆኑ ወያኔ ሰው ነውን?

የወያኔ ሃርነት ትግራይ ከሰው ዘር ነውን የተፈጠረውን? የሚታዬው ነገር ትሻል ሰድጄ ነው የሆነው ይህ እርግጥ ነው። የሆነበትን ምክንያት ማጥናት ግን ይገባል።

ሰላም ፍቅር እና ምህረት የህሊና እጠባ ያስፈልገዋል ይህ ሳይሆን ለዚህ ተቋማዊ ሁኔታ ሳይመቻች ሁሉም በቀሉን፤ ቁርሾውን፤ አመሉን እንደያዘ ተቀላቀለ ተባለ፤ በቃ የችግሩ ምንጭ ይህ ነው።


ሰው በጭካኔ፤ በቂም፤ በቁርሾ እንደኖረ ና እና አንዳሻህ ሁን፤ በሃሳብ ተሟግተህ አሸንፈኝ ተባል። ያ ሲያቅት በብጥብጥ፤ በሁከት፤ በረብሻ በግርግር ፈጠራ ጫና አሳድሮ መፈንቅለ መንግሥት ለመያዝ ታሰበ። የሆነው ይሄው ነው። ብንፈልግ እዬተባለ ሲፎከር ወሸኔ ተብሎ ደህነንት ተመድቦ በክብር ደረጃ ወጩ ተችሎለት ቅብጥ እና ቅልጥ ተሆነ፤ ጎዳና ላይ ሚሊዮነች ፈሰው ለኔት አርበኛ ብድግ ቁጭ ... ምን ይሻልህ? ምን ይምጣልህ?


ሃሳብ አፍልቆ ፍቅርን መሸመት ሳይሆን የተገኘውን ፍቅር በሃይል በጡንቻ፤ በማስፈራራት፤ በስጋት ሰቅዞ ስልጣን መረከብ ተፈለገ። ይህ የዛሬ አይደለም የጥር ጀምሮ የተሞከረ ነው።


ያን ጊዜ ተግ ያደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ነው የነበረው። የዚያን ጊዜ ጫጫታ ነበር። መሬት ላይ ሥራ ለመሥራት ለመሰብሰብ፤ ለመደራጀት፤ መልካሙን ነገር ለማድረግ አልነበረም፤ ይህን መሰሉን ግርግር ፈጥሮ ሥልጣን መቀረመት ነበር የታሰበው። ቀድሞ ነገር የአሁኑ ጉዳይ እኮ ያን ጊዜ ያተቃደ፤ የታለመ ነው የነበረው። የገታው አስቸኳይ ጊዜው ነበር።
                                  ትግራይ ስታዲዮም።

ሁሉም ሰው አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ሲለቀቅ የሚያደራጀቸው የሚያስተምራቸው፤ የሚያንቀሳቅሰው ፋይዳ ያለ ሀገራዊ ሁነትን ጠብቆ ነበር።

ይህ ሲጠበቅ መንቀሳቀስ ይችላል ሲባል አገር የነበሩት ውጪ አገር፤ ውጪ አገር የነበሩት ወደ አገር ቤት ገቡ፤ ሆቴል እስከ ዘመድ አዝማዱ ይከፍልላቸዋል፤ ውጪም አይጠዬቅም፤ ሽርሽር በአገር ውስጥም፤ በውጪ አገርም ሽርሽር። የጫጉላ ጊዜ ያስረሽ ምቺው የጉሮ ወሸባዬ እና ዶር አብይን የመመስል አባዜ ነው የታዬው።


ልብሱም፤ ቋንቋም፤ ሚስትን አስከትሎ በዬስብሰባው መታደም፤ ያው ኮፒነት ነው የታዬው። ጠቃሚው ነገር ራስን ሆነ መገኘት፤ በራስ ውስጥ መጽናት ነበር። አጋጣሚውን ደግሞ በመጠቀም ድርጅትን ማጠናከር ይገባ ነበር። የሚታዬው ግን ግርግር ፈጥሮ መፍንቅለ መንግሥት ማድረግ ነው። በ አንድም በሌላም መንገድ። ተዚህ እና ተዚያ የሚፈለገው ይህው ነው። ሢሶ መንግሥት ሳይሆን ሙለው መንግሥት። 


መሬት ላይ ሥራ ሃባ ነው። ከዚህም ዲስኩረ አገር ቤትም ዲስኩር። መባጃውን መደስኮር። በቃ አስቸኳይ ጊዜው ሲለቀቅ የታዬው የተፎካካሪ ፓርቲዎች የጠ/ ሚሩን ጉዞ የሥራ እንቅስቃሴ ዘጋቢ፤ ልዩ ሪፓርተር አቅራቢ፤ ልዩ መግለጫ አውጪ ነው የሆኑት። ሰነፎች ናቸውና። ሥራ አይወዱም። በገብያ ግርግር የሽግግር መንግሥት ወይንም የተጽዕኖ ፈጣሪ፤ የምንትሶ የቅብጥርሶ መንግሥት መመሥረት ነው የሚሻው። አሁን የዚያ አካል ነው የሰሞናቱ የዕልቂት አዋጅ።


በቀኝም በግራም የተሰቀዘው የአብይ መንፈስ ልሁቅ ስለሆነ በሃሳብ ማሸነፍ እንደማይቻል ስለታወቀ ብቻ ነው ይህ ሁሉ የጦርነት የፉከራ የቀረርቶ ዳንኪራ ሲደመጥ የተባጀው።


ቀድሞ ነገር ትጥቅ ፈቶ የገባ ሹልክ ብሎ፤ አፍሮ፤ አዩኝ አላዩኝ ተብሎ እንጂ እንዲህ በአደባባይ እልል ጉሮ ወሸባዬ እዬተባለለት ወርቅ እዬተበረከተለት፤ ካባ እዬተደረበለት ሊሆንም ባልተገባ ነበር። በተስፋ እጦት ስለማቀቀው፤ ስላለቀው ወገን እንኳን አቋጣሪ አልነበረውም። አንዱ ሲገለል፤ ሌላው ሲታቀፍ ሰርግ እና መልስ ነው የተባጃው።


 ውድድሩ ፉክክሩ ከጠ/ ሚሩ ጋር ነው። ሁሉም ያን ለመምስል ሲጥር ነው የሚታዬው። ያልተሰጠውን፤ ያልተፈጠረለትን ሊሆን አልተቻለም።  እንዲያውም ገላመን። እጅም አለን። ብቻ ያው የሳሙና አረፋ ነው። ጤዛ።

 የሆነ ሆኖ ምንጩ የችግሩ ይታወቃል፤ ቅናት እና ምቀኝነት ኢጎ የፈጠረው ነው። በሁሉም ዘርፍ ያለው ፌክ የሆነው፤ ማስመሰል ሆነ፤ ቅብ ሁኔታ ብጥብጡን ወለደው። ይህን ደግሞ ዛሬ ከመሼ ሚዲያዎች እንደሚተርኩት ሳይሆን አስቀድሜ እኔ በዝርዝር ጽፌበታለሁኝ። የራስ ተሰማ ናደው አድማ ጠረን ይሸተኛል እያልኩኝ። 


  • ·      ነገረ ማህበረ ቀያፋ።

በሆነው ሁሉ ነገር በሚታዬው ነገር ሁሉ አብረን ስላረጀን እንተዋወቃልን።  በጣም የሚገርም መግለጫ ነው የወጣው የወያኔ ሃርነት ትግራይ የሸፍጥ መግለጫ። ለማን ደህነነት ነው የወጣው? ለማንስ ታስቦ ነው ይህ መግለጫ የተጻፈው? ለኢትዮጵያ ህዝብ ታስቦ? ማንንስ ለማሳጣት ነው? ከመቼ ወዲህስ ነው ለሰብዕዊ መብት ተሟጋች የተሆነው? ለመሆኑ ሰውኛ ጠረን ተቀርቦ ያውቃልን?

ኢትዮ ሱማሌ ከ700 ሺህ ባላይ ሲፈናቀል ስለምን መግለጫው አለወጣም፤ በደቡብስ መሰሉ ሲከውን ስለምን እንደ ሰው አልታዩም? መቼም አማራማ ከቤቱም መቀመጥ አይቻለውም እንኳንስ ሌላ ቦታ፤ በረት ግልብጦ መዳፈሩ ቢቀር እንኳን መኖር በታባለ። 
  
                    ቅዳሜ ገብያ።

ቤንዚን ክብሪት አሳይዞ የህዝብን ጉሮሮ ቅዳሜ ገበያን ያነደደ ጨካኝ ቡድን? ስለሰው ልጅ ህሊና ያልሰራለት የ27 ዓመት መርግ አሁን የሰብዕዊ መብት ረገጣ ቆርቁሮት፤ ስለወገን ገብቶት ስለሰው ልጅ ክብርነት፤ ታላቅነት ተመስጦ ነው ይህን መግለጫ ያወጣውን?

27 ዓመት ሙሉ ዶሮ ነበር ሲገድል፤ ዶሮ ነበር ሲያስር የኖረው የወያኔ ሃርነት ትግራይ? አሁንስ ከቁልፍ የሥልጣኑ ቦታ እንሱው አሉበት አይደለምን? አፈ ጉባኤዋ የፌድራል ምክር ቤቱ ማን ናቸው፤ የራሳቸው ጠረን አይደሉምን?

ነው የራሳቸው መንግሥት መስርተው ልክ እንደ ጎረቤት አገር ተሆኗለኝ? እሲኪ ሰብዕዊነት ካለ፤ ከኖረ ባዶ 6 ባዶ ሆኖ ይገኝ። ዛሬ የራያ ሰዎች ወንዶች ሳይቀሩ እያነቡ ነው እሱን እስኪ ባሊህ ይበሉት።

Ethiopia || የትግራይ ልዩ ሃይል አፍኖ እየውሰደ በደል እየፈጸመብን ነው ለመሆኑ ትግራይ ላይ ስለ ሰው ልጅ እልቂት ክብር ኖሮ፤ ተወግዞ ያውቃልን? ከሊቅ አስከ ደቂቅ የትም ይኑር የትም ተወጥቶ ተወግዞ ይታወቃልን?


 ቢያነስ በክልላቸው ስለ ሰው ልጅ ትንሽ ራፊ ግንዛቤ አለን? ረሱት አዲግራት፤ መቀሌ፤ አክሱም ዩንቨርስቲዎች፤ ታዳጊዎችን በፎቅ ሲፈጠፍጡ? ረሱት ወልዲያ ላያ ያደረጉትን በኤልኮፍተር የተደገፈ ጭፍጨፋ እና ሽንት በኮዳ ሞልቶ ያን ስቃይ እና መከራ።


ረሱት ወይ የባህርድርን፤ የአንባ ጊዮርጊስን፤ የሬቻን፤ የሙያሌን፤ የቤንሻንጉልን፤ የወተርን፤ የአርባጉጉን ሰቆቃ? ተረሳ ኳስ ሜዳ ላይ ፊፋን ተዳፍሮ ዳኛ በአደባባይ መሃል አዲስ አባባ ላይ ያን መታበይ እና ጥጋብ ሲደበደብ ያን ትዕቢት፤ መቀሌ ኳስ ሜዳ ላይስ የሆነው ተዘነጋን? ጨካኝ እኮ ሌላውን ጨካኝ የማውገዝ ሞራል አይፈቅድለትም። በዬትኛው የሰውነት አቅም?


ዶር ደብረጽዮን ገ/ ሚኬኤል እስኪ በወረራ የያዙትን የወልቃይት፤ ጠገዴ፤ የራያን ነፍስ ባሊህ ይበሉት? ቀን እና ሌት ሲገድሉት የኖሩትን የወልቃይት፤ የጠገዴ፤ የራያን ነፍስ ሰው ነህ ወገናችን ነህ ይበሉት እስኪ?

አሁን ወያኔ ሃርነት ትግራይ በምን ሞራሉ ነው አረመኔነትን ማውገዝስ፤ መወቀስስ፤ መክሰስ የሚችለው? ሰው በመግደል እና በማሰቀዬት አብሾ የሰከረ የምድር አራዊት አሁን እንደ ሰው ተሁኖ መግለጫ? ማለገጥ ነው። የውነት ማላገጥ ነው።


አለንለት ተብሎ ፎቶው ተይዞ አደባባይ ደረት የተማታለት  የኢንጂነር ስመኘው በቀለን ቤተሰብ በሚመለከት ቅዱስ ዮሖንስ ዋዜማው ዶር ደብረጽዮን አዲስ አበባ ነበሩ፤ ሚሊዬነም አዳራሽ እና ስለምን ሄደው አላዮዋቸውም ልጆችን? ስለምንስ ገዳዩ ጉዳዩ የእኛ ነው የፖሊስ መግለጫው አልተመቸነም ብሎ አቋም አላያዘም? ማለት ቁልቁለት መሆን አቀበት ነው።


በደም ጋን ተጸንሶ የሚፈላው የንጹሑን ደም ምን ጊዜም ይጮኻል። ጩኸቱን ታንክም፤ መትረዬሰም፤ ሞርታርም፤ መድፍም፤ ዙፋንም ምንም አያድነውም።

ሰማዩ ዳኛ በቃችሁ ሲል ሁሉንም ልኩን ያስይዛል። ኢትዮጵያ አምላክ አላት። ፍርድ እና ፍትህ ከሰው ሳይሆን ከፈጣሪ ዘንድ ነው አላዛሯ ኢትዮጵያ የምትጠብቀው።

ፓርላማ ጽ/ቤትም፤ ጠ/ ሚር ቢሮም፤ የፌድራል ምክር ቤትም፤  የኢህአዴግ ጽ/ቤትም፤ የዲሞክራሲ ግንባታም ምንትሶም ያው እናንተው ናቸሁ ከላይ እስከ ታች አገር ምድሩን ያያዛችሁት። ንክት ያለ ወንጀለኛ ዘራፊ የለም።
                                      መቀሌ ላይ።
የተወረረው መሬት ነኪ የላባችሁም። እናንተ ስትፈቅዱ ብቻ ነው ሁሉ የሚሆነው። ምናችሁ ተነካና ቀድሞ ነገር። በሰብዕዊ መብት ዙሪያ የአሜርካ መንግሥት የደረሰበት አቋም እንዲሰረዝ እኮ ተጠይቆላች - ኋዋል። ዕድለኞች ናችሁ። የሰማዩን ማስቀረት ከተቻለ የሚታይ ይሆናል። ምን አለ ዝም ብትሉ።

በደላችሁ፤ ጭካኔያችሁ ይቅር ይረሳ ሰማይ አይታረስ ንጉሥ አይከሰስ ተብሎም አልበቃነም እያላችሁ የምትሠሩትን ታውቃላችሁ። "ከባለቤቱ ያወቀ ቡዳ ነው" እንዲሉ ያው ከተዘፈቃችሁበት ሰውን ከማጥፋት ሴራ አንዲትም ደቂቃ ታቅባችሁ አታውቁም።

እኔ ብፁዕን አባቶችን አይተው ከተመለሱ ጭካኔው ይቀንሳል፤ ንሰሃም ይገባል ብዬ ነበር፤ ዛሬ ራያ ላይ ወንዶች ያለቅሳሉ፤ ከዛ መልስ ወልቃይት ላይ ያደረጋችሁት ታውቁታላችሁ።

እናንተ ስለነገ የትግራይ ህፃናት አጀንዳችሁ ሆኖ አያውቅም። ለነገሩ በዘር ጥፋት አትጠዬቁም፤ ዘርም አልጠፋም ተብሎላችኋዋል። ፈጣሪ የራሄልን እንባ ከረሳው?

ድሮ ከነበራችሁ የቀረባችሁ ነገር አለን? ምናችሁ ተደርሶበት? ተንደላቃችሁ ትኖራለችሁ። አልፋ እና ኦሜጋ ንጉሶች አይደላችሁ? ተፈርታችሁ ኖራችሁ፤ ዛሬም እንደተፈራችሁ አላችሁ። 

እስኪ ወንድነቱ ካለ ትግራይ ላይ የመሸጉትን እነ አቶ ጌታቸው አሰፋን፤ እነ አቦይን አሳልፋችሁ ስጡ። እኔ አቶ ጌታቸው አሰፋ ሱዳን ሄዱ የሚባለውን አላምንም። እዛው ትግራይ ውስጥ እንዳሉ ነው የሚሰማኝ። 

ህግ ይከብር! እኮ ከራስ ሲጀምር ነው አንደበት የሚኖረው። እኔ የሚገርመኝ እንደ ሰው ቁማችሁ መሄዳችሁ እና እንዴት ብሎም እንቅልፍ እንደሚወስዳችሁ ነው።

የዚህ ሁሉ መካራ ምንጩ እኮ የወያኔ ሃርነት ትግራይ ጸረ ሰው እና ጸረ ተፈጥሮ ማንፌስቶ፤ ህገ መንግሥት እና የፌድራል ሥርዓት ነው። እናንተ የፈጣራችሁት ትናንሽ ንጉሦስች ናቸው ይህው 27 ዓመት ሙሉ በዬዕለቱ ደም የሚፈሰው፤ ህዝብ ከቀዬው የሚፈናቀለው። በ አማራ ተለመደ አሁን ከሆነ ደግሞ በ ኦሮሞም በሌሎችም እንዲሁ ቀጥሏል። ማቆሚያም የለውም።

አንድ ቀን ይህ መከራ ወደ እናንተ የዞረ ዕለት እናንተን አያድርገኝ። ዕድሜ ለደጉ፤ ለዬዋሁ እና ለቻዩ ዶር አብይ አህመድ በሉ። እሱ ይህችን ቦታ የለቀቀ ዕለት መላ ኢትዮጵያ ያለው የተጋሩ ቤተስብ ምን እንደሚሆን ፈጣሪ ይወቀው።

እኔ „መቋሚያ" ብዬ በጻፍኩት ላይ አቶ ያሬድ ጥበቡ ከ አሜሪካ ድምጽ አማርኛው ዝግጅት ጋር ባደረጉት ንግግር "የብሄረስብ ግጭት አያሰጋኝም፤ የዘር ግጭትም" ሲሉ ዕድለኛ ነዎት እኔስ እንቅልፍ አጥጫለሁኝ ብያለሁኝ። ባጋጣሚ አሁን አገር ቤት ናቸው መሬት ላይ ያለውን እውነት ያዩታል። የዘራችሁት ጥላቻ እያፋራላችሁ ነው።  ይህ ማለት ግን እናንተ ጋ ወጮፎም አልደረሰም እንኳንስ ሙላቱ።

እስከ አሁን ምናችሁም አልተነካም የ27 ዓመቱ ሰቆቃ አንድ ቀን ግን ገደቡን ጥሶ ይመጣል። ይህን ጠብቁ። ህግ የሚሰራው ሰላም ሲሆን ብቻ ነው። ሲከር ይበጠሳል ሲሞላም ይፈሳል። የህዝብ ሞገድ ከተነሳ መከራውን አትችሉትም። ይልቅ ከሴራችሁ ታቀቡ። 

ዙሪያ ገባው የእናንተ ሴራ የጥፋት ማጣፈጫ ነው። አቶ ጃዋር እኮ  በእናንተው ዶክተሪን ተኮትኩቶ ያደገ፤ በ እናንተው ዘመን ለትምህርት የተላከ ወጣት ነው። ሁሉንም ነገር የተማረው ከከእናንተ ነው።

የሆነ ሆኖ እናንተ የተሳላችሁት ሁኖላችኋዋል። ጥብብ፤ ስልት የሌለው ኦህዴድ ደግሞ እንዲረታ ራሱን በራሱ እያፈረሰው ነው። አብይን ከመደገፍ አብይን የመፈንቀል መንፈስ ሥልጣን ላይ አወጣለሁ ብሎ ግብግብ ሲፈጥር ይህው „አሸባሪ፤ ገዳይ፤ ጨካኝ፤ እንሰሳ“ የሚል ታቤላን አከበረ። 

አብሶ ያን የሚሊዮን ፍቅር በቅጽበት ቀበረው። ያ ሁሉ ድካም ባክኖ ቀረ። ያ ሁሉ መስዋዕትነት በኖ ቀረ። እኔ እንኳን የደከምኩትን ራሴ ነው የማውቀው።

ዓላማው የታላቁን የኦሮሞ ህዝብ ታላቅነትን ሊቃናቱ በድምጽ ብልጫ ማስከበር እንዲችሉ ነበር ትጋቱ፤ ግን ንደት አመጣ … ራስን ቀማ። ትውፊትን፤ ታሪክን ተዳፈረ። ዕድልም ሾለከ። ዕድል ስል የታመኝነት ዕድል ማለቴ ነው። መታመን መታደል ነበር። ከ50 ዓመት በኋዋላ የታመነ ድርጀት ነበር ግዛን ንዳን የተባለ። ግን መንፈሱ ቁንጣኑ አላስችለው አለ። ትዕግስት ነሳው ጠረኑ አዬሩ። 

ከዚህም ከዚያ አዳዲስ አክቲብስቶች፤ ጸሐፍት እዬወጡ ነው በዚህን በዚያ እያሉ እንደ ቀደመው ሊያጃጅሉን ይሞክራሉ። ይባቃል የጣና ኬኛ ጅልነት፤ እኛ ለታገልነለት ዓላማ እና ታማኝነት ሳይሆን ለምሽጋቸው ክብርን አሳልፈው ሸጠውናል። ይሄው የሆነው ሆነ። ያሳፍራል።

ከእንግዲህ መድከም አያስፈልግም። ማመንም እንዲሁ። ወረቅ ከቀለጠ ይፈሳል። የወንድ እናቱ አንድ ናት ይባል የለ እንደዛ …
   
ድል በሌለበት ድል ሆነ ተብሎ ዘራፍ ሲባል፤ የሚኒለኪን ሰፋሪ ከባሌ እና ከአርሲ ንቀል ሲባል፤ በዘመነ ጣና ኬኛ አናምናቸውም እነሱ ጨካኞች ናቸው ሲባል በስንት ፍዳ የተሰበሰበ የመንፈስ ሃብት እንደ ቅጠል ረገፈ።

የኦሮሞ ሊቃናቱን ጉልላት አድረጌ አውጣለሁ ሲል ኦህዴድ አፍሶ ለቀመ ሆነበት። ራሱ መግለጫ የሚባለውን ነገር ለማድመጥ አቅም አጣሁኝ። ሰንደቄ እዬፈረስ አገር የለሽም እዬተባልኩኝ ምን አቅም ይኑረኝ? ህም!

እንደ ጫት ምርቃን አላስችል ተብሎ በሌለ ድል ጉሮ ወሻበዬ ሲባል የህዝብን ተስፋ ታሪክን አጠቆሮው። እናንተ አንደከሰሳችሁ ሆኖ ተገኘላችሁ። አይመጥንም አገር የመምራት አይደል የምትሉት፤ እንደተባለው ሆኖ ተገኜ። እናም ለህዳር ጽዮን ጃንጥላ አስገቡ። ውይ እቴ ይቅርታ ለካንስ ሃይማኖት የላችሁም …

መንገድ ዕውነት ብቻ ነው።
ውዶቼ የጹሁፌ ታዳሚዎች የኔዎቹ ኑሩልኝ።

በቃችሁ ይበለን አማኑኤል። አሜን።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።