ነገ አምጦ እንዲመጣ ሴረኞች ተግተዋል።
ከበደ ነገ እያማጠ ነው።
„እኔ ግን በምሕረትህ ብዛት ወደ ቤትህ እንተ እግባለሁኝ።
በመፍራት ወደ ቅድስናህ መቅደስ
እሰግዳለሁ።“
መዝሙር ፭ ቁጥር፯
ከሥርጉተ©ሥላሴ
18.09.2018
ከጭምቷ ሲዊዘርላንድ
በአንቦ ሌላ የከበደ ዜና ተደመጠ። እርግጥ ነው የተጎዳ ወገን እንደሌለ ዘገባው ቢጠቅሰም ቀጣዩ
ግን እጅግ አስፈሪ ነው። በምን ሁኔታ ይህ ዝርግ ፖለቲካ ሊገራ እንደሚችል ፈጣሪ ይውቀው። እዬጨነቀኝ ነው።
ከነሴራው የተቀላቀለው መንፈስ ከአገር ውስጥ ሽምቅ ተዋጊው ጋር ተቀይጦ የአጥቂነት ሥራውን
እዬሠራ ነው። ንፁሃን ምን አደረጉ? በተበከለ ምግም 2000 ወገኖች ጥቃት እንደተፈጸመ በአንቦ አካባቢ ተገልጧል። በዚህ ዓይነት ስንቱ
ነገር ቁጥጥር ተደርጎ ሊደረስበት ነው።
አለመደብንም እኛ ሰላማዊ፤ ምህረት፤ ይቅርታ ፍቅር ብሎ መልካምነት። ግድለው፤ እስራው፤ አፍነው፤
አፈናቅለው ነው የተኖረበት። የሆነ ሆኖ ይህ አስደንጋጭ ዜና ነገን እንዲያምጥ ያድርገዋል። ከበደኝ።
ይህ ምስኪን ፍጥረት ምን ያድርግ? ከስንት ይቆራረጥላቸው? ያ ሌት እና ቀን ተባክኖ በውጭም
በአገር ውስጥም መንፈስን ለማስተካከል የተደረገው ዘመቻ በአዲስ ቀውስ ፈጣሪ እና አምራች ሃይል እና ጉልበት እንዲናድ፤ እንዲቀዬጥ፤ አንድነቱ እንዲበጠበጥ
ተተግቶ እዬተሠራበት ነው። ለዚህ እኮ ነው አንድም ተፎካካሪ ፓርቲ ሥራ ሊጀምር ፈቃደኛ ያልሆነው። ውስጥ ለውስጥ አድማው አለ።
መፍንቅለ መንግሥት።
በሌላ በኩል ከኢትዮ ሱማሌ የተፈናቀሉ ምንዱባን ባህርዳር ላይ የክልሉ የጥበቃ ሃይል ሊያግዛቸው
ሲገባ ጥቃት እንዳደረሰባቸው ዘገባው ይጠቁማል። ይኸው ነው ሴራው። ሌላውን ወርቅ ትሸልማለህ፤ ካባ ትደርባለህ በሰላም አገር ሲዘባነን የነበረውን ተመችቶት ደልቶት የኖረውን፤ ተፈናቅሎ የመጣውን ደግሞ ወታደር ልከህ ታስደብድባለህ። ይህ ነው የእንቶኔ የ አቶ ጃዋር መረብተኛ ቀብልኛ ሌጋሲ ማለት ...
ይህ ደግሞ ባህርዳር ላይ ሰላማዊ ሰልፍ እንዲኖር የሚሹ ወገኖች ያሰተባበሩት ነው። ድራማው ቀጥሎሏ።
ልዑል እግዚአብሄር ማበረጃውን እና ማስታገሻውን ያምጣ። ይህ በሰው አቅም ሳይሆን በፈጠሪ ጥበብ ብቻ የሚፈታ ትብትብ ነው። የሁለቱም ሊንክ ከሥር ለጥፌያለሁኝ።
ጸሎት እናድርግ።
ዶር አብይ አህመድ ከሥልጣን እንዲወርዱ ነው ይህ ሁሉ ሴራ ተቀናብሮ እዬተከወነ ያለው። አማራው
እንዲሸፍት ራሱ ተግተው እዬሠሩበት ነው። አማራው በዝምታ እና በትእግስት መዋጡ አልተፈለገም።
አማራው በአመጽ እንዲናወጽ ለማድረግ የታሰበው አልሳካ
በማለቱ ነው በህጋዊ መንገድ ዛሬ ተፈናቃዮች እና ቤተ እግዚአብሄር ተደፍሮ ወገኖች እንዲደበደቡ ትእዛዝ የተሰጠው። ቅዱስ አባታችን ኤርትራ እንደሄዱ አድማጭለሁኝ፤
የመፈንቅለ መንግሥት አራማጆች
የአማራው ዝምታ አላስደሰታቸውም። ልክ ዶር አብይ አህመድ ወደ ሥልጣን ሊመጡ ሲሉ እና ከመጡ በኋዋላ የነበረው የአድማ የወልዮሽ
ሞገድ መከራ አሁን መሬት ላይ ሴረኞቹ በደቦ በተቀነባበረ ሴራ ቀጥለዋል። አብዩም እጅግ ዘገዬ።
በምንም ሁኔታ፤ በዬትኛውም መሥፈርት ለአላዛሯ ኢትዮጵያ ብቻ ሳይሆን ለመላ አፍሪካ ከአብይ
መንፈስ የተሻለ በ50 ዓመትም አይፈጠርም። ይህ ያቃጠላቸው፤ እረፍት የነሳቸው ወገኖች ናቸው በስውር መሬት ለመሬት እዬተጎተቱ ሴራን አደራጅተው የመንፈስ
መፈንቅል ለማድረግ እዬታተሩ ያሉት።
ይህ ዕድል ካመለጠ መቼውንም ኢትዮጵያ ዛግጣ እና ዝጋ ትቀራለች። አብይን የሚተካ ሊሂቅ በህልም የለም
እንኳንስ በውን። ከተደገፈ ብቻ ነው ዓላማን ማሳካት የሚቻለው። ካልተደገፈ በቃኝ ካለ አንድ ቢሮ እንኳን ማደራጀት የማይችለው ነፍስ
ሁሉ ነው አሁን ፉከራውን እናውቃዋለን። አንዲት ሳምንት ማስቀጠል አይችልም።
ገበርዲንም ከረባትም መሪ አያደርግም። ዙረያ ጥምጥሙን ሴራ በማን እና በምን ሁኔታ እንደሆነ
የጠ/ ሚር ቢሮም ሰፊ አትኩሮት ቢሰጠው መልካም ነው። ዝርግነቱ ልቅነቱ ጉዳቱ ለህዝብ እና ለአገር ነው። ቆፍጠን እና ኮስተር
ማለት የግድ ይገባል።
- · አንቦ።
„Ethiopia:
በአምቦ ከ2000 የሚበልጡ ሰዎች ተመረዙ“
- · ባህርዳር፤
„ከሶማሌ ክልል የተፈናቀሉ የአማራ ክልል ተወላጆች በባህርዳር ከተማ ቤተክርስቲያን ደጃፍ በልዩ ሃይል ተደበደቡ"
ከዛ
ፍዳቸውን አይተው መጥተው አሁን ደግሞ ባህርዳር ላይ የግፍ ድርብ ግፍ ተሠራ። ይህ የሆነበት ምክንያት ያ የመፈንቅለ መንግሥቱ
ዓላማ አራማጆች አማራ መሬት ላይ የጠበቁትን አመጽ ስላለገኙ ነው። አማራ የእስካሁኑ ስለሚበቃህ በተደሞ እና በእዮባዊነት የአሸባሪዎች
ተባባሪ ላለመሆን ራስን ገዝቶ ወገኖችህን መጠበቅ ግድ ይልሃል። ታሪክህን እንዳታጠቁረው።
ሰው
መሆን ይጠይቃል አሁን። ያ እንዳለፈው ይህም ያልፋል፤ እና ታግሰህ አሳልፈው። ክብሪትም፤ ቤንዚንም ላለመሆን መታገስን ጠብቀው።
እንድትቆጣ፤ እንድትበሳጭ ነው የሚፈለገው። ኮ/ደመቀ ዘውዱም የኖሩትን ኑረው ዛሬ ማገዶ ላለመሆን በተለመደው እርጋታቸው ሂደቱን መከታትል ይኖርባቸዋል።
መቆስቆሻ እንዲሆኑ የሚፈለገው አሳቸውን ነው። ስለምን ፈታችሁት አካሉን ሳታጎድሉት ፈታችሁት ትብሎ ተጽፎ እንደነበር ማስብ አለባቸው። መታገስ ያስፈልጋል። በአንድ ጀንበር የሚሆን ነገር የለም። ለ አማራ አንዲትም ቅንጣት ነፍስ ከጎኑ የለም ከፈጣሪ በስተቀር። ስለዚህ ጠንቃቀነት በአጅጉ ያስፈልጋል።
አማኢአ ሆይ! በግራም
በቀኝም አንተ መሻገሪያ ብቻ ነህ። ለጄሌነት እንጂ ነፍስ ላለው ዕውቅና አይደለም ሞትህ የሚታቀደው። አይተህው የለምን ብአዴን ራሱ እኮ የአማራ የማንነት የህልውና ተጋድሎ ብሎ መጥራቱን እንኳን አይደፈረውም። ማሟያ ነህ። ስለዚህ ነፍስህን ጠብቅ። አለስፈላጊ መስዋትነት ለመከፈልም አትትጋ።
ጸሎትህን፤ ሱባኤህን፤
ሰጊድህን፤ ድዋህን ብቻ አድርግ። አዳራ። አንተን ለሚጸዬፉ ሴረኞች ተባባሪ እንዳትሆን። „ሙያ በልብ ነው።“ ታገስ።
- · ራያ።
Ethiopia || የትግራይ ልዩ ሃይል አፍኖ እየውሰደ በደል እየፈጸመብን ነው።
ይህ ሁሉ የታወቀ፤ የታቀደ ነው ዘመቻው አብይን ፈንቅሎ ጊዜያዊ መንግሥት መመሥረት
ነው። በማህል ደግሞ ጉልበተኛ ካለ ይነጠቅ እና ከአንዱም
ሳይደርስ ሁሉም ክው ብሎ ይደርቃል።
ለነገሩ „ኢትዮጵያ ካልፈሰች ኦሮምያ ሰላም አታገኝም“ የኦቦ ሊበን ትንቢቱ ይፈጸም ይሆን?ሁሉም
አሰፍስፎ አራት ኪሎ ላይ ነው ያለው። ክብር ዝና በቃ። ከዛ የሚያልፍ ዓላማ እንደሌለማ ታይቷል። ተሸነፈህ አሸንፍኩ እያልክ ማዘመር፤
መፏለል። ትጥቅህን ፈተህ ገብተህ ጀግና ነኝ ብሎ ፉከራ።
በልክ
መያዝን የመሰለ ነገር አልነበረም። ጠ/ ሚር አብይ አህመድ እስከ አሁን ባለው ሁኔታ በተረጋጋ መንፈስ፤ ራስን ዝቅ ባደረገ ሁኔታ
መታበይን አላሳዩንም። መኩራራትን አላደመጥንም።
ጎደሎ
እንዲኖር ግን የራስ ተሰማ ሌጋሲ ቤተኞች እንደተጉ ዛሬ ሳይሆን ቀድሜም ተናግሬያለሁኝ። አብሶ አማራ እንዲያኮርፍ ሰረፍተውበታል።
የሆነ
ሆኖ እንጸልይ። አቅማችን አማኑኤል ብቻ ነው።
ያ
በህልሜ ያዬሁት ግምሽ ፊት አሁን እዬመጣ ያውከኛል። ወንበሩም ሰው ተቀምጦበት አላዬሁትም። ስጋቴ ሰፊ ነው። ህልሜን አከብረዋለሁኝ።
ግን ፈሪ ነኝ።
ለመሆኑ እትጌ ኤርትራ ከዬትኛው ወገን ናት? ይህም አንድ ድንቡልቡል ያለብኝ ጉድ ነው። ለዛውም የአቶ ሞላ አስገዶም ሰራዊት
አልገባም። እሱ ሲገባ ደግሞ ሌላው ጋዳ ነው።
አቤቱ
ሁሉ ይቻልሃል እና ሴረኞችን ተሸንፈው አሳዬን።
የኔዎቹ
ኑሩልኝ።
በቃችሁ
ይበለን። አሜን!
አስተያየቶች
አስተያየት ይለጥፉ