ይድረስ ለኢትዮጵያ ሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር ዶር ዳንኤል በቀለ፦ ይድረስ ለሰባዕዊ መብት ተሟጋች ክቡር አቶ ያሬድ ኃይለማርያም፦

 

ይድረስ ለኢትዮጵያ ሰባዕዊ መብት ኮሚሽን ኮሚሽነር ክቡር ዶር ዳንኤል በቀለ፦
አዲስ አበባ።
ይድረስ ለሰባዕዊ መብት ተሟጋች ክቡር አቶ ያሬድ ኃይለማርያም፦
ካሉበት።
"የቤትህ ቅናት በላኝ።"
 May be an image of 1 person and textMay be an image of 1 person and textMay be an image of 1 person, beard and text
 
ጉዳዩ፦ የሰማዕቱ ኢሳያስ በላይ ቤተሰቦችን እና አብረው እስረኛ ስለሆኑ ጓዶቻቸው #ቀጣይ #ሕይወት ይመለከታል።
አሁን በመረጃ አቀራረብ ጥራቱ እና ቅልጥፍናውም፦ በሚዛናዊነት አቅሙም ተስፋ ከማደርግበት ሚዲያ አንዱ ኢትዮ ኒዊስ ነው። ከደማችን ጋር እንዲዋህድ በተገደድነው #ዘወትራዊ "#ሰበር" #አስደንጋጭ ዜና እንደ ተለመደው በዛሬ ኢትዮ ኒዊስ ረፋድ ዜና ደነገጥኩኝ። ሰውነቴም #ተንዘፈዘፈ። መቀመጥ ተስኖኝ ጋደም ብዬ ነው የምጽፈው።
 
ሰማዕቱ ሟች አቶ እያሱ በላይ አሰቃቂ በሆነ ድብደባ እና ዘለፋ በታከለበት ሁኔታ ህይወታቸው ማለፋን የእሥር ቤት ጓዶቹ መሠከሩ ይላል ዘዬዘገባው ዕድምታ። #አስፈሪው ጉዳይ ተረኞች ሊኖሩ እንደሚችሉም #ዛቻ እንደሚደርስባቸው የእስር ጓዶቻቸው ገልፀዋል ይላል ኢትዮ ኒውስ በስደት ባለበት አገር አሁን በሰማሁት ዘገባ።
 
1) እነኝህ ዛቻ ስንቃቸው እንዲሆን የተገደዱት እስረኞች ለቀጣይ ህይወታቸው ማን ዋስትና ይስጥ? እንዴትስ ማፍትሄ ማግኜት ይቻል ይሆን?
2) ቁጥራቸው በውል ለማይታወቀው የአማራ ህዝብ ሊቃናት እና ሊሂቃን እስረኞች በቀጣይ እንደምን ጥበቃ ሊደርግላቸው ይችል ይሆን? ስጋቴ አይሏል።
3) በሻለቃ ናሆሰናይ ጉዳይ የታሰሩት ባለፈው አጭር ዘገባ በመንግሥት የተሠራባቸው ወገኖች እና እስሩም በዚህ ዙሪያ ከቀጠለ ልቁን ጭካኔ ማን ሊገድበው ይችል ይሆን?
 
4) የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ መጠናቀቁ ሆነ መቀጠሉ መቼ ነው ይፋዊ መግለጫ በጠሚር አብይ መንግሥት አገዛዝ የሚገለፀው?
4.1 አስቸኳይ ጊዜ ዓዋጁ ተጠናቋል ከተባለ ከአስቸኳይ ጊዜ ዓዋጁ ጋር ተያይዞ በአማራ ክልል የታገተው ኢንተርኔት ሙሉ ለሙሉ መቼ ሥራ ይጀምራል?
4.2 አስቸኳይ ጊዜ ዓዋጁን ተከትሎ በመላ ኢትዮጵያ ይመለከታቸዋል ተብሎ የታሠሩ የአማራ ልጆች፤ እና የአማራ ወዳጆች፤ የሰባዕዊ መብት ተሟጋቾች እና የህግ ባለሙያወች መቼ ይፈታሉ?
4.3 እይጨነቀኝ ያለው እስር ቤት በድብደባ፤ በመሰወር ለሚገደሉ ምንዱባን ማን ይሆን ተጠያቂው? እንደምንስ ተቋማችሁ ጥበቃ ሊደረግላቸው የሚችልበትን ሁኔታ አደራጅቶ ሩሄ እረፍት ሊያደርግ እንደሚችል አላውቅም። 
 
5) የአማራ ባንክ ተመሰረተ ድል በድል ሆነ ሲባል ከፈንጠዝያው ጋር አልነበርኩም። በየአንዳንዷ የስኬት መስመር ያዬለ ፈተና ከፊት ለፊቱ ሊገጥመው እንደሚችል፤ በማን ተማምኖ ይህን መሰል እርምጃ እንደወሰደ በወቅቱ ጽፌያለሁኝ።
5.1) ደስ ላላቸው ወገኖቼ ደስታችሁን በልክ አድርጉት፤ ምክንያቱም ደስታችሁን ከተቀማችሁ ተስፋ ቆራጭ እንዳትሆኑ።
5.2) ሌላ ደስታ ብታገኙ መደርደሪያ እንዳታጡ።
 
5.3) በበዛ ደስታ ምርቃት የሚያስነሳ ሁነት ከላይኛው እንዳይገጥም በሚል። ተመሳሳይ አቋሜ የጠሚር አብይ አህመድ መንግሥት መቀሌን ተቆጣጠረ ርችትም፤ ፈንጠዝያ ላይም እነኝህን ሰለስቱ አንኳራትን ጽፌያለሁ። ጦርነቱም ያልተገባ በማለት ቀድሜ ነበር የሞገትኩት። አሁንም ለጠቅላላ የአማራ ባንክ ሠራተኞችም፤ ለተቋሙም ማን ዋስትና ሊሰጥ ይሆን? ሊቃናቱ እንደሚታረድ የአብርኃም በግ አንድ ዕልፍኝ ላይ ስላሉ፤ ሥጋቴ ጥልቅ ነው። እጅግ ጥልቅ!
 
#ወደ ቀደመው አመክንዮዬ። 
 
የጠሚር አብይ መንግሥት የፀጥታ አካላት በአቶ እያሱ በላይ የግፍ ግፍ ግድያ ሊያዝን፦ሊፀፀት ሲገባ ጭራሽ እንደሚቀጥልበት ፍንጭ ነው ኢትዮ ኒዊስ ዘገባው ላይ ያዳምጥኩት። ለነገሩ ማጽናናት፤ ሐዘንን መጋራት፤ አይዟችሁ ባይነት የመከነበት፦ #ክው ብሎ የደረቀበት ብቻ ሳይሆን የመነበት ስለመሆኑ አውቃለሁ። ማንን ፈርቶ???
የሆነ ሆኖ ከዘገባው እንደተረዳሁትም የኢትዮጵያ የሰባዕዊ ኮሚሽን ባልደረባ ተገኝተው እንደነበርም አድምጫለሁ። ጊዜው ሳያመልጥ ግን በጥድፊያ ፈጣን እርምጃ የሚያስፈልገው ይመስለኛል።
 
ጉዳዩን ለሚመለከታቸው #ብሄራዊ#አህጉራዊ እና #ዓለምዓቀፋዊ ተቋማት ማሳወቁ እብሪተኛ ሰብዕናወችን ለማስታገስ የሚረዳ ይመስለኛል። እጅግ አሳስቦኛል። አውቃለሁ በሰባዕዊ መብት ድፍጠጣ ላይ ኢትዮጵያ #ሱናሜ ላይ ስላለች፤ የተቋማችሁ አቅም ማነስም ችግር ሊሆን እንደሚችል አስባለሁ።
 
#ግን ……
 
ቅድሚያ ለሚሰጠው ጉዳይ ቅድሚያ በመስጠት በአቶ እያሱ በላይ ቤተሰቦች፤ በእስር ባልደረቦቻቸው በጥርስ በተያዙ ፀሐፍት፤ ጋዜጠኞች እና የህግ ባለሙያወች፤ አርቲስቶች እና ጠበቃወች መሰል የበቀል እርምጃ እንዳይወሰድባቸው ትረዱን ዘንድ በትህትና፦ በአክብሮትም አሳስባለሁ።
ለምትሰጡኝ ጊዜ በቅድሚያ ትሁት አክብሮቴን እገልፃለሁ።
 
#ልዩ ማስታወሻ ለአቶ በለጠ ካሳ። 
 
ለትጉሁ ለኢትዮ ኒውስ ባለቤት ለጋዜጠኛ በለጠ ካሳም ያለኝን አክብሮት እና ምስጋና በትህትና እገልፃለሁኝ። የራስ ጥበቃውንም አጠንክሮ እንዲቀጥል በትሁት መንፈስ አሳስበዋለሁ። መሰደድ ብቻውን በቂ አለመሆኑን እኔው እዬኖርኩበት ስለሆነ። ጥንቃቄ ያተርፋል እንጂ አያከስርም። ሁሉ ተፈቅዶልኛል፥ ሁሉ ግን አይጠቅምም። 
 

·        https://www.youtube.com/watch?v=Hc5Ic6e-e2I

«ጄ/ አበባው ታደሠ ፍርድ ቤት እንዲቀርብ ታዘዘ!//ደምቢያ.! ወልዲያ.! ሰከላ.! አምባሰል.! 11 June 2024»

 
እህታችሁ፦
እግዚአብሄር ይስጥልኝ።
ሥርጉተ©ሥላሴ
Sergute©Selassie
11/06/2024
ሲዊዘርላንድ፦ ቪንተርቱር ከተማ።
ጊዜ ራዲዮሎጂ ነው።

አስተያየቶች

ከዚህ ጦማር ታዋቂ ልጥፎች

ዛሬ ያለው ነገር „ፈረቃም፤ ተረኝነትም“ አይደለም።

እህት አጊቱ ጉደታ አገር ነበረች።

አብይ ኬኛ መቅድም።